ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ማርያም በስጋ የወለደችው ልጅ አላት? መጽሐም ቅዱስ ላይ ካለ ጥቅሱን ቢቻል፡፡

ማርያም በስጋ የወለደችው ልጅ አላት? መጽሐም ቅዱስ ላይ ካለ ጥቅሱን ቢቻል፡፡መ
Mar 11, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ማርያም በስጋ የወለደችው ልጅ የላትም፡፡ በድንግልና እንደወለደችው ነው ያሰተምረነናል እንዲሁም አየሱስ ወንድሞቼ የሚላቸው በወቅቱ የነበሩትን ሰዎች ወይም ሀዋርያት ወድሞቼ እህቶቼ በማለት ነው
ምስራቅ

እንዴት ነው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀስን እንጂ። እንዲያው በራሳችን ስልጣን ብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ያላላውን መናገር ሰው ያስታል። ከታች መልስ የሰጠው ሰው ማርያም በሥጋ ልጅ እንዳላት ከመጽሐፍ ቅዱስ ከተለያየ ቦታዎች አውጥቶ ጠቅሶ ነው ያስረዳው። አንቺ ደግሞ አይ ተሳስቶአል ማርያም ልጅ የለታም ካልሽ ይሄንን ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተሽ ማስረዳት ይኖርብሻል እንጂ እንደው ከራስሽ አይደለም። ሰው የሚፈልገው የእኛን አስተያየት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል ለማወቅ ነው።

"እኔ ራሴ መጽሐፍ ቅዱስ ነኝ" ወይም "እኔ ራሴ የእግዚአብሔር ቃል ነኝ" ካላልሽ በስተቀር ከቃሉ የአምላካችን ቃል በመጥቀስ መልስሽን መስጠት ይኖርብሻል። ያለዚያ የሰው አስተያየት ብቻውን ዋጋ የለውም፤ ያስታል።
እሺ ማርያም ሌላ በስጋ የወለደቻቸው እነማን ናቸው?
ቱቱ ከታች የተሰጠውን መልስ ብታነብቢ ስማቸው ተዘርዝሮ ታገኚአለሽ። ያንን ማንበብ ካልፈለግሽ ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል 13፡55-56 አንብቢ
በዚህ አይነትማ እህቶችም አሉት እነማን ናቸው? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
58 በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም ነው የሚለው ማቴ.12 ቁ 46. ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። 47 አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ
ስለዚህ እናስተውል ዮሴፍ ማርያምን አወቃት ወለደችም አላለም መጽሐፍ ቅዱስ
አመሰግናለሁ።
የላትም ነው መልሱ በድጋሚ ከኛ የሚጠበቀው ማስተዋል ብቻ ነው
እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። 47 አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ
ኦሪት ዘፍጥረት 4
1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች። 2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች እንዳለው ሁሉ ዮሴፍም ሚስቱን አወቃተት ልጆችንም ወለደች ብሎ ስማቸውን ይዘረዝር ነበረ
ስለዚህ እናስተውል ዮሴፍ ማርያምን አወቃት ወለደችም አላለም መጽሐፍ ቅዱስ
አየሱስ ወንድሞቼ የሚላቸው በወቅቱ የነበሩትን ሰዎች ወይም ሀዋርያት ወድሞቼ እህቶቼ በማለት ነው
ወገኔ የአንተ ሎጂክ የሚያስኬድ አይደለም

አንደኛ ማቴዎስም፣ ማርቆስም ሉቃም ሶስቱም የወንጌላቱ ጸሃፊዎች ኢየሱስን ሊያነጋግሩ የመጡትን ሰዎች "እናቱና ወንድሞቹ" እንደሆኑ ነው የሚጽፉት፤ እናቱና ወንድሞቹ እያሉም ነው የሚጠሯቸው። እነዚህ ሰዎች እናቱና ወንድሞቹ ካልሆኑ ለምንድነው የወንጌላቱ ጽሃፊዎቹ ራሳቸው እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት እንደፈለጉ የሚነግሩን?
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
12፥46 ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር

የማርቆስ ወንጌል
3፥31 እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት

የሉቃስ ወንጌል
8፥19 እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፥ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልተቻላቸውም

ይህ ብቻ አይደለም፡ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ደግሞ ሶስቱንም ለያይቶ ሲጠራቸው እንመለከታለን። ማለትም እናቱን፣ ወንድሞቹንና ደቀመዛሙርቱን። ይህም ሶስቱ የተለያዩ እንጂ አንተ እንዳልከው አንድ እንዳልሆኑ በማስረጃ ያሳየናል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
2፥12 ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።

አንተ ያልከው ፈጽሞ እንዳልሆነ የሚያስረዱ ሌሎችም ማስረጃዎች መጨመር ይቻላል። ሆኖም በዚሁ አምድ ላይ ብዙ መልስ ስለተሰጠባቸው እነርሱን አንብብ። እኔ እንደገና መድገም አልፈልግም።

4 መልሶች

+2 ድምጾች
ማርያም ኢየሱስን በጸነሰች ጊዜ ዮሴፍ እጮኛዋ እንደነበርና ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ግን አብረው በትዳር ኖረው ሌሎችን ልጆችም እንደወለዱ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 11
24 ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤
25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው የማርያም እጮኛ ዮሴፍ ማርያም "የበኩር ልጅዋን እስትወልድ ድረስ አላወቃትም" ነው የሚለው። ማለትም በሌላ አገላለጽ የበኩር ልጇን ከውለደች በኋላ ግን አውቆአታል። ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ ዮሴፍና ማርያም እንደማንኛውም ሰው በትዳር እንደኖሩና ወንድና ሴቶች ልጆችም እንደወለዱ መጽሐፍ ቅዱስ ይናራል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 13
53 ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ።
54 ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።

ከላይ እንደምናየው በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ወዳደገበት ወደገዛ አገሩ በሄደበት ጊዜ እርሱንና ቤተሰቦቹን በሚገባ የሚያውቁት ሰዎች የተናገሩት ተጽፎአል። ምንድነው ያሉት? ይሄ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? ጸራቢ ማለት አናጺ ማለት ነው። ዮሴፍ አናጺ ስለነበር፡ የአናጺው የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮስ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? ብለው ነበር የተናገሩት። ይህ ክፍል ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ብዙ አመታት አብረው እንደኖሩ ወንዶችንና ሴቶሽንም ልጆች እንደወለዱ ግልጽ ያደርጋል። በዚህ ክፍል የተጠቀሱት ያዕቆብና ይሁዳ የሚባሉት የኢየሱስ ወንድሞች ደግሞ በመጽሐፍ ቅድስ ውስጥ የሚገኙትን የያዕቆብንና የይሁዳን መልእክት የጻፉት እነርሱ እንድሆኑ የመጽሐፍ ቅድስ አዋቂዎች ይናገራሉ። ምንም እንኳን በመጀመሪያዎቹ የአገልግሎት ዘመኖቹ ወንድሞቹ በኢየሱስ ባያምኑም በተለይ ከሙታን ከተነሳ በኋላ የኢየሱስ ተከታዮች ሆነው አገልግለዋል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 7
1 ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበርና በገሊላ ይመላለስ ነበር። 2 የአይሁድም የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር። 3 እንግዲህ ወንድሞቹ፦ ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤ 4 ራሱ ሊገለጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ብታደርግ ራስህን ለዓለም ግለጥ አሉት። 5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና

ወደ ገላትያ ሰዎች 1
18 ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ፤ 19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።

የይሁዳ መልእክት 1
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ 2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።

መጽሐፍ ቅዱስ እንግዲህ በግልጽና በማያሻማ ቃላት የሚነግረን፤ ማርያም ኢየሱስን እስከምትወልድ ድረስ ዮሴፍ እንዳላወቃት፤ ከዚያ በኋላ ግን እንደ ማንም ሰው መደበኛ ትዳር ለብዙ አመታት እንደመሩና ልጆችን እንደወለዱ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ደግሞ ከልጆቻቸው ውስጥ በተለይ ያዕቆብና ይሁዳ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ በአገልጋይነት የሚታወቁና የያዕቆብና የይሁዳ መልእክት ተብለው በመጽሐፍ ቅዱስ የሚታወቁትን መልእክቶች የጻፉት እነርሱ እንደሆኑ ይናገራሉ።

ከዚህ ተጨባጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ውጪ ግን፡ ማርያም ልጅ ከወለደችም በኋላ ድንግልም ናት የሚል አስተሳሰብና እምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጭርሶ ባእድ የሆነ አስተሳሰብ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱትም ሐዋርያቱና ነብያቱ ጨርሰው እንዲህ ያለ ሃሳብ አልተናገሩም አላስተማሩምም።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 12
46 ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር
47 አንዱም፦ እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
48 እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፦ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።
Mar 11, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 11, 2011 ታርሟል
እስካሁን ስል ከቆየሁት አንጻር አሁንም አስረግጬ ጥቂት እላለሁ። ስለፍንጮች የሰጠኸውን እቀበላለሁ። ፍንጮቹ ከምናነባቸው የወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ የተመሰረቱ ስለሆነ ጥሩ ፍንጮች ናቸው። ፍንጭ ግን የምንፈልገውን ነገር ለማጠናከር የሚያገለግል የመረጃ ደርዝ እንጂ በራሱ ውጤት አይደለም። የምናገኛቸው ፍንጮች ወደእውነታው ሊመራን ይችላል። ፍንጮቻችን የቱንም ያህል እውነታውን ሊመስሉ ቢችሉ እውነታው እነዚህ ናቸው የሚል አስረጋጭ ነገር እስካልተቀመጠ ድረስ ያገኘናቸውን ፍንጮች እውነታውን ይወክላሉ ልንል ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። ማርያምና ዮሴፍ አብረው መኖራቸው አይካድም። ከዚህም የተነሳ እብራውያን ክርስቶስ ከዮሴፍ እንደተወለደ ለማመን ተገደዋል። ግምታቸው ሴትና ወንድ አብረው እስካሉ ሊታሰብ የሚችል ነገር ነው። ይህ ግን ሴትና ወንድ በአንድ ቤት ጥላ እስካሉ ሊሆን ከሚችል ከዓለሙ የኑሮ ጭብጥ በመነሳት የሚታሰብ እንጂ ከዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ዓላማ አንጻር አስተሳሰባቸው ውድቅ ነው። በኢሳ7፤14 ላይ ድንግል እንደምትወልድ ተቀምጧልና ነው። ዮሴፍ ማርያምን ወደ ቤቱ መውሰዱ እርግጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ነግሮናልና። ማርያም እጮኛው ነበረች? አዎ! ነበረች ሲል ይህንን አረጋግጧል። እጮኛውን ወደቤቱ መውሰድና አብረው መኖር ሊመጣው የሚችል ነባራዊ ሁኔታዎች ሊኖሩ አይችሉም? ሊኖሩ ይችላሉ፤ ግን በግልጽ የተቀመጠ ነገር ስለሌለ የኑሮ ውጤቶችን ተነስተን በራሳችን መናገር እንገደዳለን ። ያ ማለት ግን መጽሐፍ ቅዱስ ማርያም ከዮሴፍ ተጨማሪ ልጆችን ስለመውለዷ እስካልተናገረ ድረስ እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን በዝርዝር ሊናገር አይችልም ከሚል ደካማ አስተሳሰብ የተነሳ እኛ የተሟላ ለማድረግ ፍንጮቹን ወደ ተለጠጠ የነባራዊ ዓለም ህይወት ጎትተን ልናመጣቸው መብቱ የለንም። እያልኩ ያለሁት መጽሐፍ ቅዱስ ሙላት የጎደለው አድርገን እንዲህ ያለው እንዲህ ለማለት ነው፤ ይህ ደግሞ እንዲህ ቢሆን ነው አንበል ነው።እግዚአብሔር ነገሩን በግልጽ በቃሉ መጽሐፍ መናገር ያልፈለገው የኋላ ትውልድ (እኛ) የተሟላና ስሜት የሚሰጥ አድርገን እንድንጠቀምበት ወይም በግልጽ አብራርቶ ማስቀመጥ የሚገባው ሆኖ ሳለ አሁን እኛ ይሄን ነው፤ያ ነው እያልን እንድንፋጭበት ፈልጎ እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል።
የሙሴ መቃብር እንዳይታወቅ ያደረገበትን ምስጢር የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው። እንደዚሁ ሁሉ በግልጽ ማርያምን በድንግልና ኖረች ወይም ብዙ ልጆችን ወለደች ያላለበትን ምክንያት የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው። ግምቶቻችን የእግዚአብሔር ሃሳብ ምትኮች ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም።
ሌላው ወገን «በድንጋሌ ኅሊና፤በድንጋሌ ሥጋ የጸናች ክብርት እመቤታችን»የሚለው ክፍልም ቢሆን እንደዚያ የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ይዞ ሳይሆን ልቡ ያፈለቀውንና ኅሊናው ቢሆን ሲል የሚመኘውን ብቻ ይዞ ነው። ብዙ ጊዜ እጮኛ ማለት ጠባቂ ማለት ነው የሚል የጅል ክርክር ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ እጮኛን እብራይስጡ የሚናገረው(ארוס)ኧሮስ-ማለትም እጮኛ እንጂ ጠባቂ የሚለውን(שומר)ሾሜር ባለመሆኑ ይህንን ከየት እንዳመጡት አይታወቅም። እንዲሁም እብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ(אשתי)ኢሽቲ-ማለትም «ሚስቱን» ሲል በግልጽ አስቀምጦት ይገኛል።γυναίκα ግሪኩም ጊኔይካ ይለዋል። ከዚህ የተነሳ በኛ የሚሳልና የሚጻፍ ዘላለማዊ የሚባል ድንግል ወይም በኛ የሚሟላ የልጆች እናትነት የመጽሐፍ ቅዱስ እርማት ሊኖር አይችልም።
ፍንጮችን ወደ ተጨባጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ለውጠንና የጎደለውን አሟልተን የኛው ከዚያኛው የተሻለ ድጋፍ የሚሰጡ ጥቅሶች ስላለን በዚያ መነሻ የዘላለማዊ ድንግልና ሙግት ባለቤቶችን እንሽራለን ማለት ከከንቱነት አያልፍም። ለየትኛውም ወገን መልሱን በቀጥታ መስጠት ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንጂ እኛ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውን እኛ መጽሐፍ ቅዱስን አንተካምና ለምንናገረውና ለምናምንበት ነገር ጥንቃቄ ልናደርግበት ይገባል። ማስተዋልን ወደ ረቺነት መንፈስና የጥቅስ ፍንጭ ፍለጋ ከቀየርነው ጭንቁር ሃሳብ አራማጆች የመሆን ፍርሃት ይኖረኛል።
ወገኔ ማርያምማ ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና እንዳልቆየች በቂ ማስረጃዎች አሉ። ቃሉ የሚያወራው አንተ እንዳልከው ሴትና ወንድ በአንድ ቤት ስለ መኖር ብቻ አይደለም። ቃሉ በቀጥታ የሚያወራው ባልና ሚስት ሆኖ ስለመኖር ነው። ይሄንን ከዚህ በታች በማስረጃ አብራራለሁ፤ ሆኖም በቅድሚያ ግን የዮሴፍንና የማርያምን ግንኙነት በተመለከተ አንድ መሰረታዎ ነገር መረዳት ያለብን ይመስለኛል።

በማርያምና በዮሴፍ እጮኝነትና ትዳር ሕይወት እኮ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ነገር ብቻ ነው በዘመኑ ከነበረው ከሌሎች እጮኝነትና ትዳር የተለየ እንደሆነ የሚናገረው። ይሄውም በእጮኝነታቸው ጊዜ ማርያም አርግዛ መገኘቷ ነው። ይህንን ነው ማቴዎስም ይሁን ሉቃስ የተለየ ነገር እንደሆነ የሚናገሩትና ምክንያቱን የሚያብራሩት። ይህ በእጮንነት ጊዜዋ ማርያም ማርገዟ ባይኖር እኮ የዮሴፍና የማርያም የእጮኝነትና የትዳር ታሪክ ምንም የተለየ ነገር የለውም። ማርያምና ዮሴፍ የተጫጩትም እኮ አብረው ተጋብተው በትዳር ሊኖሩ ነው እንጂ ለሌላ አይደለም። ማርያም በመሃል አረገዘች ብሎ ይሄንን የመጀመሪያ እቅዳቸውን ዮሴፍ እንዳይተው እኮ ነው መልአኩ ለዮሴፍ የተገለጠለት። መጀመሪያም ሊጋቡና ትዳር ሊመሰርቱ ነው የተጫጩት፤ ማርያም ስታረግዝ ግን ዮሴፍ ጋብቻውን ሁሉ ሊተው ፈለገ፤ መልአክም ተገለጠለትና እንዳይተዋት አስረዳው፤ ከዚያም ዮሴፍ ልክ መጀመሪያ እንዳቀዱት ሁሉ ሚስት አድርጎ ወሰዳት። የተለየውን ነገር ብቻ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያብራርልን እንጂ ማንም የሚያደርገውንና የሚያውቀውን መደበኛውን አይደለም። ለዛ ማብራሪያ አያስፈልግም።

አሁን የሁለቱን የባልና ሚስት ግንኙነት ወደሚያረጋግጥልን ክፍል ልምጣ።
Quote:
Matthew 1:24-25

NASB
And Joseph awoke from his sleep and did as the angel of the Lord commanded him, and took Mary as his wife, but kept her a virgin until she gave birth to a Son; and he called His name Jesus.

NRSV
When Joseph awoke from sleep, he did as the angel of the Lord commanded him; he took her as his wife, but had no marital relations with her until she had borne a son; and he named him Jesus.

NIV
When Joseph woke up, he did what the angel of the Lord had commanded him and took Mary home as his wife. But he had no union with her until she gave birth to a son. And he gave him the name Jesus.

እስቲ ከላይ ያስቀመጥኩትን ማቴዎስ 1፡124-25 ያለውን ታሪክ ተመልከት። ዮሴፍ እጮኛውን ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ይላል በቁጥር 24። ይሄንን ሲጽፍ ማንም ይህንን የሚያነብብ ሰው ሌላ ማብራሪያ ካልተጨመረለት በስተቀር መደበኛ የትዳር ኑሮ እንደኖሩ ነው የሚረዳው። ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ብሎ ጽፎ፤ አንባቢዎች ግን ግብረ ስጋ የሌለው ትዳር ብለው እንዲያነብቡለት አይጠብቅም። ማንም የዛ ዘመንም ይሁን የአሁን ዘመን አንባቢ፤ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ካለ፤ ትዳር እንደመሆኑ የግብረ ስጋ ግንኙነትንም ትዳራቸው ያጠቃልላል ብሎ ነው የሚገነዘበው። ጸሃፊው ሌላ ማብራሪያ ካልሰጠ በስተቀር። ከመደበኛ ትዳር የተለየ ነገር ካለ ጸሃፊው ሊጽፈው ይገባል። ለዚህ ነው ማቴዎስ ወዲያው በቁጥር 25 "የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም" ብሎ ለየት ያለውን ነገር የሚጽፍልን።

ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት። ይሄ ማንም እንደሚያነብብው ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ነው። ሆኖም በማርያምና በዮሴፍ ትዳር ውስጥ ግን አንድ ለየት ያለ ነገር (exception) ነበር። ይሄውም ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ በትዳራቸው ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነት አልመኖሩ ነው። በትዳር ውስጥ ግብረ ስጋ ግንኙነት አለመኖሩ ነው ልዩ የሆነው ነገር እንጂ የግብረ ስጋ ግንኙነት መኖሩ በጣም ግልጽና ማንም ሊጽፍው የሚያስፈልገው ነገር አይደለም። አንድ ጸሃፊ "በትዳር ኖሩ" ወይም "ሚስት አድርጎ አገባት" ወዘተ ካለ፤ አንባቢዎች ግብረ ስጋ ግንኙነትን አብረው እንደሚያስቡ በጣም ግልጽ ነገር ነው። "የግብረ ስጋ ግንኙነት እያደረጉ በትዳር ኖሩ" ወይም "ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ትዳር ነበራቸው" ወዘተ ብሎ የሚጽፍ ጸሃፊ በዚያን ዘመንም ይሁን አሁን የለም። እንዲህ አይነት አጻጻፍ ጨርሶ የለም። ምክንያቱም ትዳር በውስጡ የግብረ ስጋ ግንኙነትን እንደሚያቅፍ ለማንም ግልጽ ነውና። ከሌሎችም የሰዎች ግንኙነቶች ለየት የሚያደርገውም አንዱ ነገር እኮ የግብረ ስጋ ግንኙነቱ ነው።

ስለዚህ ማቴዎስ ሲጽፍ፤ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ሆኖም የበኩል ልጇን እስክትወልድ ድረስ ግብረ ስጋ ግንኙነት አላደረጉም ካለ ይሄ ለማንም አንባቢ ግልጽ ነገር ነው። ከሌሎች ትዳሮች ልዩ የሚያደርገው ወይም exception የሆነው ነገር ተገልጿል፤ እርሱም ኢየሱስ እስኪወለድ ግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረጋቸው። ከዚያ ውጪ ግን ትዳራቸው ከሌሎች ትዳሮች የሚለይበት ተብሎ የተጠቀሰ ነገር የለም። ስለዚህ ጸሃፊው በትዳር እንደኖሩ ከነገረን ግብረ ስጋ ግንኙነት እንደነበረ ያለምንም ልዩ ማብራሪያ ማወቅ እንችላለን። "ግብረ ስጋ ግንኙነት ያለው ትዳር ኖሩ" ብሎ የሚጽፍ ጸሃፊ የለምና። ይልቁኑ ትዳር እየኖሩ ግብረ ስጋ ግንኙነት ባያደርጉ ኖሮ ነው መጻፍ ያለበት። ይህ በትዳር ውስጥ የተለየ ነገር ነውና መጻፍ አለበት። ያለዚያ ግን ጸሃፊው ያላለውን በግድ እንዲል ማድረግ ነው። ማቴዎስ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ እንደወሰዳት ሲናገር፤ ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ትዳር እንደኖሩ አንባቢያን እንደሚረዱ ለማቴዎስ ግልጽ ነበር። ለዚህም ነው አንድ ነገር ጸሃፊው ማሳሰብ የፈለገው። ይሄውም ምን እንኳን በትዳር ቢኖሩም ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ ግን ግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረጋቸውን ነው። ይሄንንም ዓረፍተ ነገር ማቴዎስ የጨመረው እኮ፤ ዮሴፍ ማርያምን ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት ብሎ ሲጽፍ በትዳራቸው ውስጥ አንባብያን ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ እንደሚረዱ ስለተገነዘበ ነው።

ስለዚህ ሁለት ሰዎች በትዳር ኖሩ ወይም አንድ ሰው አንድን ሴት ሚስት አድርጎ ወሰዳት ወዘተ ብሎ አንድ ጸሃፊ ከጻፈ፤ ሌላ ማብራሪያ ካልጨመረለት በስተቀር፤ ይህ ትዳራቸው ግብረ ስጋ ግንኙነትን ያጠቃልላል ብለው አንባባያን እንደሚረዱ ለጸሃፊው ግልጽ ነው። ማንም ጸሃፊ "ግብረ ስጋ ግንኙነት ያለበት ትዳር" ብሎ የሚጽፍ የለምና።

ማርያም ለዘላለም ድንግል ናት ብለው የሚያምኑ ሰዎች እኮ እያሉ ያሉት፤ ዮሴፍና ማርያም የመሩት ትዳር "ግብረ ስጋ ግንኙነት ያለበት ትዳር" ነበር ብሎ እንዲጻፍላቸው ነው የሚፈልጉት። ይህ ካልሆነ፤ ዮሴፍና ማርያም ምንም እንኳን ባልና ሚስት ቢሆኑም፤ በቃ ቃሉ በግልጽ አልተነጋረም ወይም በቃ ድንግል ናት ማለት ነው የሚል ፈጽሞ እኮ የማያስኬድ ሎጂክ ነው የሚሉት ያለው። ቃሉማ ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ኖሩ ወይም ባልና ሚስት ናቸው ብሎ ተናግሯል፤ ከዚህ በላይ አንድ ሴት ድንግል ሆና አለመኖሯ ሌላ ምን ማስረጃ አለ? ቃሉ ባልና ሚስት ናቸው ከማለት ሌላ ምን ይናገር? ኦ በነገራችን ላይ የዮሴፍና የማርያም ትዳር "ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ትዳር ነው" እንዲል ነው የፈለግነው?

ይሄ ለእኔ ልክ ኢየሱስ ተገረፈ ይላል እንጂ ቃሉ "ጅራፉ በጀርባው ላይ አረፈበት" አይልምና ጅራፉ በእርግጥ ጀርባው ላይ ማረፉን እርግጠኛ አይደለንም የሚል አይነት የልጆች ክርክር እንደሆነ አድርጌ ነው የማየው።
" ቃሉማ ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ኖሩ ወይም ባልና ሚስት ናቸው ብሎ ተናግሯል" ብለው የጻፉት፡ ኸረ እባክዎትን እንዲህ አልተሳፈም። የርስሆ አስተሳሰብ ማራመድ ይችላሉ ቃሉማ እያሉ የርስሆትን አስተሳሰብ ለካሉ አይስጡ
"he took her as his wife" ማለት ሚስት አድርጎ ወሰዳት ማለት ነው። በሙሉ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች እንደዛ ነው የሚሉት። እኔ የፈጠርኩት ነገር አይደለም። መጀመሪያም ሊያገባት ነው ያጫት ለሌላ አይደለም። በኋላም ሊተዋት ሲል መልአክ አትተዋት አለው ስለዚህ ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት ይላል ቃሉ እኔ ሳልሆን።

እዚህ በመጫን ወደ 8 የሚሆኑ የእንግሊዝኛ ትርጉሞችን ያንብቡ።
በጣም ያሳዝናል አለማወቅ ነው
–1 ድምጽ
ሰላም

ዮሴፍ ማርያም የበኩር ልጇን ከውለደች በኋላ ግን አውቆአታል የምለው አነጋገር በመጽሃፍ ቅዱስ በፍጹም አይደግፈውም። ምክንያቱም መጽሃፍ ቅዱስ የሚለው የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ነው እንጂ ከወለደች በዋላ አወቃት የሚል በጭራሽ አልተጻፈም።

የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ማለት ሰዎች ጌታ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ነው አንዳይሉ ነው። አንድም ቦታ በቅዱስ ቃሉ ዮሴፍ አውቃት የሚል የለም። ቢያውቃት ሓጥያት ነው እያልኩ አይደለም፤ አወቃት የሚል ሳይጽፍ እንደተጻፈ አድርጌ ሃሰት ግን አልናገርም።

ማቴ 13-55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም። መጽሃፍ ቅዱስ የሚለው ኢየሱስን የጸራቢ ልጅ ነው የጸራቢውም ልጆች (የስጋ)ወንድሞቹ ናቸው የሚሉ ሁሉ አሁንም እንደቀደሞ ዘመን እየተሰናከሉበት እንደውነ ነው።

በዚህም ዘመን ጌታን በስጋ(ከእናት፤ አባት) ወንድም አለው የሚል ይህንን ቃል ቢያስተውል መልካም ነው ፦ ማቴ12-47" እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው። እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፦ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።"
መድሃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ ፤ የንጉሶችም ንጉስ ነው።
Sep 7, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 29, 2011 ታርሟል
ሰላም ወንድሜ የአንተ ሎጂክ ትንሽ ችግር አለው።

አንደኛ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ማለት፤ ያላወቃት የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ብቻ ነው ማለት ነው። ይሄ ማለት ምን ማለት ነው? ከዚያ በኋላም ምንም እንዳላወቃት መናገር ቢፈልግ ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ አላወቃትም ወዘተ ይል ነበር። ስለዚህ በዮሴፍና በማርያም መካከል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያልተደረገው የበኩር ልጇን እስክትወልድ ደረስ ነው። ከዚያ በኋላስ? ለሚለው ጥያቄኮ መጽሐፍ ቅዱስ መልስ ሰጥቶአል። ይሄውም ዮሴፍና ማርያም እኮ እጮኛሞች ነበሩ ማለትም ለትዳር የሚተሳሰቡ ማለት ነው። ከዚያ ደግሞ ዮሴፍ ሊተዋት ሲል መልአኩ እጮንነቱን እንዳያቋርጥና እንዲወስዳት ነግሮት ወስዷታል። ሚስት እንድትሆነው ነው እንጂ እህት ወዘተ እንድትሆነው አይደለም የወሰዳት። ስለዚህ ሚስት እንድትሆነው ከወሰዳትና ካገባት ደግሞ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ ምንም የሚያጠያይቅና የሚያወያይ ጉዳይ አይደለም።

የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ከዚያ በኋላ ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት! ይህ ግልጽ አባባል ነው።
Quote:
Matthew 1:24

NET ©
When Joseph awoke from sleep he did what the angel of the Lord 1 told him. He took his wife,
NIV ©
When Joseph woke up, he did what the angel of the Lord had commanded him and took Mary home as his wife.
NASB ©
And Joseph awoke from his sleep and did as the angel of the Lord commanded him, and took Mary as his wife,
NLT ©
When Joseph woke up, he did what the angel of the Lord commanded. He brought Mary home to be his wife,
MSG ©
Then Joseph woke up. He did exactly what God's angel commanded in the dream: He married Mary.
BBE ©
And Joseph did as the angel of the Lord had said to him, and took her as his wife;
NRSV ©
When Joseph awoke from sleep, he did as the angel of the Lord commanded him; he took her as his wife,
NKJV ©
Then Joseph, being aroused from sleep, did as the angel of the Lord commanded him and took to him his wife,

ሁለተኛ ደግሞ ስለ ወንድሞቹ ያልከው ነገር ብዙም የሚያስኬድ አይደለም። ምክንያቱም ወረድ ብለህ ብታነብበው ኢየሱስ ራሱ የመሰናከያ ምክንያታቸውን የተናገረው ስለሚያውቁት እንደ ነብይ አለማክበራቸውን ነው እንጂ በስጋ ወንድም እንዳለው በመናገራቸው አይደለም።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 13
54 ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
58 በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።

ኢየሱስንና ቤተሰቡን ከልጅነት ጀምሮ በሚያውቋቸው በናዝሬት ሲመጣ የተሰናከሉበት የስጋ ወንድሞች እንዳሉት በመናገራቸው አይደለም። ኢየሱስም ያንን አይደለም ያለው። ነገር ግን ይሄ እዚህ የምናወቀው የእነከሌ ልጅ እንዴት ነብይ ነኝ ይላል? አናውቀውም እንዴ ብለው "አወኩሽ ናኩሽ" አይነት ነገር ነው የተሰናከሉበት እንጂ ወንድሞች እንዳሉት በመናገራቸው አይደለም።

ስለዚህ የመሰናከላቸው ምክንያት የስጋ ወንድሞች አሉት በማለታቸው ሳይሆን እርሱን፣ ወንድሞቹንና እህቶቹን እንዲሁም ቤተሰቦቹን ሁሉ ስለሚያውቁ ሊያከብሩትና ሊያምኑበት ስለከበዳቸው ነው። ኢየሱስም የመሰናከላቸውን ምክንያት ያብራራው እንደዚህ ነው።

የስጋ ወንድሞቹ ናቸው የሚሉ ሁሉ ይሰናከላሉ ትላለህ ነገር ግን ማርቆስ፣ ሉቃስና ማቴዎስ ራሳቸው ሲጽፉ እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት እንደፈለጉ ጽፈዋል። ዮሐንስ ደግሞ "7፥5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።" ብሏል። እንግዲህ እነዚህ ጸሐፊዎች ወንድሞቹ ብለው በስጋ ወንድሞች እንዳሉት በመጻፋቸው ተሰናከሉበት ማለት ነው። ዮሐንስ ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ሲልና የስጋ ወንድሞች እንዳሉት ሲናገር ተሰናከለበት ማለት ነው?

ሐዋርያው ጳውሎስም በገላትያ መልእክት ያዕቆብ የጌታ ወንድም እንደሆነ ጽፎአል፤ ታዲያ ጳውሎስ በኢየሱስ ተሰናከለ ማለት ነው? ይህ ሎጂክህ ጨርሶ የሚያስኬድ አይደለም።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች
1፥19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።
ወንድሜ ሆይ፡
የሉቃስ ወንጌል 1፥80 "ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡" ጌታ ለእስራኤል ከታየ በሃላ በምድረበዳ አልኖርምን እንዴ? "እስከ" የሚለው ቃል በእንተ ትርጉም ከወሰድነው፤ ጌታ ለእስራኤል ከታየ በሃላ ፈጽሞ በምድረበዳ አልኖረም እንደማለት ነው።

ለምን ያለተጻፈ እናነባለን? ወንድሜ "ስለዚህ ሚስት እንድትሆነው ከወሰዳትና ካገባት ደግሞ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ ምንም የሚያጠያይቅና የሚያወያይ ጉዳይ አይደለም" በጠቀስካቸው የእንግሊዘኛ ጥቅሶች ለሚስትነት ጌታን ገና ሳትወልድ እንደወሳዳት ይሰረዳሉ፤ " ካገባት ደግሞ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ ምንም የሚያጠያይቅና የሚያወያይ ጉዳይ አይደለም" ምን ማለትህ ነው? ወይስ ጌታ በድንግልና መወልዱን አታምንም? "መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ አላወቃትም ወዘተ ይል ነበር።" እንዲህ አንዲያ ይል ነበር ማለትና ፤ የአላለውን ብሎአል ብሎ ማወጅ፤ በፍጹም ትክክለኛ አካሄድ አይደለም ።

ቃሉ የሚለው አላወቃተም ነው፤ እንጅ አውቆአታል የሚል በፍጽም አልተጻፈም፤ በተጨማሪም ደግሞ የጌታ እናት አንዳንዶች እንደሚሉት ልጆች ቢኖራት ኖሮ ፤ ለምን በመስቀል ላይ ዩሃንስን ልጅ አድርጎ ለእርሱም እናት አድርጎ ሰጣት?
የማቴዎስ ወንጌል 13- 54 "ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው? 55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? 56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም። "
"እንዴት ነብይ ነኝ ይላል"ሳይሆን ያሉት ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው? ቤተሰቹንስ የምናወቃቸው አይደሉምን ? የሚል ሃሳብ ነው ይለው። የእግዚሃብሄር ልጅነቱን ስላልተረዱ ነው የተሰናከሉብት። አሁንም የተሰናከሉበትን ሰዎች ምስክርነት ይዘው የሚሞግቱ ወገኖች አሉ። የተሰናከሉበት ሰዎች እኮ ወንድሞቹ ናቸው ያሉዋቸውን ከመዘርዘራቸው በፊት አባቱን ጸራቢ(ዬሴፍን) ነው ያደረጉት።

እኔስ የጌታ አባቱ አብ ነው ብዬ ስለማምን የተሰናከሉበትን ሰዎች ምስክርነት አልቀበልም።

ወንዴሜ እንዳንተ አባባል ወንድሞቹ ካላመኑበት ያዕቆብ ደግሞ የጌታ ወንድም ከወነ ። ያልመነበትን ጌታን ነበር ይሰብክ የነበረው ማለት ነው? እንዳንተ አባባል ያዕቆብ ጌታን ያምን ነበር ለማለት መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ ከያቆብ በስተቀር ወንድሞቹ አላመኑበትም ማለት አለበትን? ካልወነ እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ አላወቃትም ትብሎ እንዲጽፍልህ ለምን ትጠብቃለ? በነገርችን ላይ የዬሴፍ ልጆች የሉትም አላልኩም። ዬሴፍ ልጆች የጌታ ወንድሞች ሊባሉ አይገባምም አልላኩም እኛ እንዃን ወንድሞቹ ተብለናልና።
ሰላም ወገኔ

በቅድሚያ አንተ የጠከስከው ሉቃስ 1፡80 የሚያወራው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንጂ ስለ ጌታ ኢየሱስ አይደለም። ከላይ ጅምረህ አንብበው።
Quote:
የሉቃስ ወንጌል 1
57 የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች
58 ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።
59 በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ
60 እናቱ ግን መልሳ። አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።
61 እነርሱም፦ ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት።
62 አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት።
63 ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።
64 ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።
65 ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤
66 የሰሙትም ሁሉ። እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት፤ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና።
67 አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ፦
68 የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤
69-70 ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፥ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፤
71 ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው፤
72-73 እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፤
74-75 በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን።
76 ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና
77 እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤
78 ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤
79 ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።
80 ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።

ኢየሱስ ወንድምና እህት አልነበረውም የሚለው ሃሳብ በመጀመሪያዎቹ አማኞች ዘንድ የማይታወቅ ጉዳይ ነበር። ለዚህም ጳውሎስና ወንጌላቱ ይመሰክራሉ። ኢየሱስ ወንድም አልነበረውም ማርያምም ለዘላለም ድንግል ናት የሚለው ሃሳብ በመጀመሪያ የመጣው ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ400 ዓመታት በኋላ Jerome በሚባል ሰው ነው።

ኢየሱስ ከድንግል እንደተወለደ እኮ ምንም አጠያያቂ አይደለም። ይህ በቀጥታ በቃሉ የሚገኝ ነገር ነው። እንደዚህም ደግሞ ኢየሱስ ወንድሞች እንደነበሩት የናዝሬት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ወንጌል ጸሃፊዎችና ጳውሎስም ጭምር ይመሰክራሉ። አንተ ግን ይሄንን ምስክር ልትቀበል አልወደድክም።

ዮሴፍማ እንደ አባቱ መታየቱ ምንም የእምነት ችግር አያመጣም ወንጌላቱንም ብታነብብ ኢየሱስ እግዚአብሔር የእኔ አባት ብቻ ነው አልነበረም የሚለው። ነገር ግን ደቀመዛሙርቱንም ቢሆን በሰማይ ያለ አባታችሁ ነበር የሚላቸው። ምንም እንኳን እነርሱ በስጋ አባት ቢኖራቸውም። ስለዚህ ከስጋም የተወለደ ሰውን አባቱ እግዚአብሔር ነው ማለት ይቻላል። ጉዳዩ እርሱ ላይ አይደለም። ኢየሱስም የትም ቦታ እኔ ከስጋ ያልተወልድኩ የአብ ልጅ ነኝ እያለ አይደለም የሰበከው። ነገር ግን መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ነበር የሚለው። ስለዚህ ብዙዎችም ያመኑት እርሱ የስጋ አባት የለውም ብለው አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር የላከው መሲህ ነው ብለው ነበር የተቀበሉት።

ኢየሱስም ስለ ናዝሬት ሰዎች ችግር የተናገረው "የእግዚአሔር ልጅ እንደሆንክ አላመኑም" አይደለም ያለው። ነገር ግን "ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም" ነበር ያላቸው። ማለትም እንደ ነብይ ወይም እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ አልተቀበሉኝም ነው ያለው።

እንደ ዮሴፍ ልጅ ሰዎች ኢየሱስን ማየታቸው ብቻውን ችግር የለውም። እንዲያውም የማቴዎስ ወንጌልን ብታነብብ የኢየሱስ የዘር ሃረጉን ማቴዎስ የሚዘረዝረው በዮሴፍ በኩል ነው። ታዲያ ማቴዎስ ተሰናከለ ማለት ነው?
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 1
1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ
2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤
...
15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
16 ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ

ይህ ብቻ አይደለም ማርያም ራሷ የ12 ዓመት በሆነው ጊዜ በኢየሩሳሌም ጠፍቶባቸው ሲፈልጉትና ሲያገኙት የተናገረችው ምን ብላ ነው? "አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበር" አይደለም ያለቸው? (ሉቃ 2፡48) እና ማርያም ዮሴፍ አባቱ እንደሆነ አድርጋ መናገሯ ተሰናከለች ማለት ነው? አይደለም።

ስለ ያዕቆብ ያልከው ነገር ደግሞ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያደርገዋል። ወንድሞቹ ከማርያም በስተቀር ያዕቆብን ጨምሮ ወንጌላቱ ላይ በእርሱ እንዳመኑ ሳይሆን ይልቅስ ወንድሞቹና ዘመዶቹ በኢየሱስ እንዳላመኑ ነው የሚናገረው። ሆኖም ከትንሳኤ በኋላ ግን ኢየሱስ ከታያቸው ሰዎች አንዱ ያዕቆብ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። ከዚያ በኋላ ነው ያዕቆብን እንደ አማኝና አንደ አገልጋይ በመጽሐፍ ቅዱስ የምንመለከተው። ስለዚህም ነው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ያዕቆብ በኢየሱስ ያመነው ከትንሳኤ በኋላ ነው ብለው የሚያምኑት።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
7፥5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።

የማርቆስ ወንጌል
3፥21 ዘመዶቹም ሰምተው፦ አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
3 እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥
4 መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥
5 ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤
6 ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤
7 ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤

ወደ ገላትያ ሰዎች
1፥19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።

ሌላው በናዝሬት ቤተሰቦቹን የሚያውቁት የአገሩ ሰዎች ከጠቀሷቸው የኢየሱስ ወንድሞች ውስጥ ያዕቆብና ይሁዳ ይገኙበታል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
13፥55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?

የይሁዳን መልእክት ስታነብብ ደግሞ ይሄንኑ ነው የሚያረጋግጠው።
Quote:
የይሁዳ መልእክት
1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤

ስለዚህ እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን የመረጣቸውና የተጠቀመባቸው ሰዎች በአብዛኞቹ በገዳምና ሰው በማይደርስበት ስፍራ ራሳቸውን ለይተው በፍጹም ጽድቅና ልዩ ቅድስና የኖሩ ሰዎች አልነበሩም። ይልቁኑ እንደ እኔና እንዳንተ ያሉ ዓሳ አጥማጆች፣ እንደ ማርያም ያሉ የ15 እና የ16 ዓመት የሚሆኑ ደናግል ህጻናት የመሳሰሉትን ነው (በዚያን ጊዜ የሚታጩት በዚህ ዓመት ስለነበር)። እንደ ፈሪሳውያንማ ሃጢአት እንዳይነካቸው ራሳቸውን የለዩትን ጭራሽ ሲገስጻቸው ነበር። ስለዚህ እንደ እኔና እንደ አንተ ያሉትን ኖርማል ሰዎችን እንደ ማርያምና እንደ ጴጥሮስ ያሉትን ልዩ ፍጥረታት ወይም ልዩ ከሰማይ የወረዱ ጻድቃን ባናረጋቸው መልካም ነው። ማርያም አግብታ በትዳር እንደማንም ሰው የሆኖረች ባለ ትዳር ሴት ናት። ገና የ15 እና የ16 ዓመት በሆናት ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን በድንግልናዋ እንድትወልድ ተጠቀመባት ማለት እንዲያው ከዚያ በኋላ ልዩ መላእክት ሆና ትዳርዋን ችላ ብላ መነነች ማለት አይደለም። ቢያንስ ቢያንስ ኢየሱስ የ12 ዓመት እስኪሆነው ድረስ ከዮሴፍ ጋር በትዳር አብራ ነበረች። አዲስ ኪዳን እኮ ሊያስተላልፍ የሚፈልገው መልእክት እግዚአብሔር ልዩ የገዳምና የቤተመቅደስ ጻድቃንን ሳይሆን በእንደ እኛ ባሉ ሃጢአተኞች፣ ቀራጮች፣ አሳ አጥማጆችና፣ ደናግል ህጻናት ወዘተ ይሰራል ይጠቀማል የሚል ነው። ስለዚህ እነዚህ እግዚአብሔር የተጠቀመባቸውን ሰዎች ልዩ መላእክት ባናደርጋቸውና ክንፍ ባናበቅልባቸው መልካም ነው።
እይ አንተ ጴንጤ ነህ ስለዚህ በ ምንም መንገድ ከ ኦርቶዶክስ ጋር መነጋገራ አትችልም እናንተ የ ትንቢቱ መፈጸሚያ ናችሁ ለምን ብትል በሁአለኛው ዘመን በ ጌታ ስም የሚመጡ አሉ ብሉአልና ሌላው ደሞ የ100 አመት ታሪክ ይዘህ ይማታውቀዉን አታውራ ስሜታዊ አትሁን ካቶሊክ እና ተዋህዶ(ቀደምቶቹ)የሚአስተምሩት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና የኖረች ብጺት መሆኑአን ነው እንጂ እንደ እናንት አይደለም እባካችሁ ክብሩአ የሚቀነስ መስሉአችሁ የማይገባ ቃል አትናገሩ ለ ተጨማሪ ማብራሪያ አምደ ሃይማኖት የሚል ምእጽሃፍ አንብቡ ስለ ሁሉ ታገኛላችሁ ደሞ እኛና እናንተ ያለን ልዩነት በ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ አይደለም በጣም በሚያስገርም እና በ ሚያስደንቅ ብዙ ነገር ነው እንጂ ብቻ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም ይባላል እግዚአብሄር ማስተዋሉን ይስጣችሁ አሜን!!!
0 ድምጾች
የተሰጡት መልሶች ሳነብ አንድ ነገር አስታወሰኝ።

A couple of years ago in Dallas, I met an African American young boy.

He said to me "What's up brother..."
I said to him "My mom never been in America."
He said. " .. to be your brother, do you think we have to have the same mother ..?" ... he said to me at last ".. are you ignorant or illiterate ?

( ትርጉም፦ ከጥቂት አመታት በፊት አንድ ጥቁር አሜሪካዊ በዳላስ ከተማ አግኝቶኝ እንዲህ አንለኝ - ሰላም ወንድሜ ፤ እኔ ደግሞ እናቴ አሜሪካ መጥታ ስለማታውቅ ወንድምህ ልወን አልችለም አልኩት፤ ጥቁር አሜርካዊውም ..ወንድምህ ለመባል አንድ እናት ሊኖረን ያስፈልጋልን? ...በመጨርሻም ወይ ማስተዋል አትፈልግም ወይም ምንም የማታውቅ ነህ አለኝ።

አሁን ግን ወንድምና ፤ እህት ለመሆን ከአንድ ማህጸን መውጣት አለበት ቤዬ የማስበውን ያላዋቂ አስተሳሰቤ አውጥቼ ጥያለው።

መጽሃፍ ቅዱስ የጌታን እናት ከጌታ ሌላ ወልዳለች፤- ዮሴፍ አወቃት፤ጸነሰች፤ ወለደች ሳይል የጌታ ወንድሞች የሚለውን ብቻ በመያዝ ከጌታ እናት የተወለዱ ናቸው የሚሉትን። ጥቁር አሜርካዊው ቢሰማ ምናልባትም እንዲ ይል ይሆናል "...to be his(Jesus') brother, do you think they have to have the same mother? ... He may say to them at last ".. are you ignorant or illiterate ?

stay blessed
Oct 29, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 29, 2011 ታርሟል
Now you show your self how ignorant you are of the word of God. If you live in Dallas then I am sure of you can read so open the word of God read it for your self stop "_" others. It is a challenge to you personally you don't even need to buy the book it is on iyesus.com download Iota and read, read, and read some more. The beauty of Iota is it has አማርኛ, KJV and it has Strong which you can read in the language it is originated to do word study so you have no excuse to stay in darkness about the true word of God.
stay blessed my prayer is you read the word of God ከ አሉ ወጥተ እኔም አወቅሁት ቃሉ ያለውን እውነቱን እድትል ነው። May the God open your eyes and heart to see HIM face to face, may the secret of the cross of Christ Jesus be revile to you. So you may know the truth.
How are you to judge on my faith?

My eyes are opened and they can see clear enough the light & the love of the Lord who is Son of God. I can't argue with a person start by insulting others.

My heart is full of the light of Jesus Christ the True Lord of Lords. I don't have any darkness and I don't have any shame to satisfy about the true Word of God. እኔስ የተሰቀለውን ብቻ እሰብካለሁ።የጌታ ኢየሱስን የስጋ ወንድሞችና እህቶች አላውቅም፤ የማውቀው ወንድሞቹና እህቶቹ በሰማይ ያሉ የአባቱን ፈቃድና ትእዛዝ የሚያደርጉትን ብቻ ነው። (ማቴ12፤50). You have the right to believe what ever you think, but I assure you the Word of God doesn't support your claim. Because it never said the Mother of Jesus Christ has other children. I assure you one thing if you are a believer of Jesus Christ the True One, you can be her son too.

Jesus Christ Lords of Lord, Kings of King.
I am sure if you read vs. 50 you can as well read the whole chapter. It was not me who said it that he has sibling, But the bible it self so if you have to pick and chose what you believe that is on you. But don't compare the word with a brother who called you thinking you are from the mother land you share his straggle. I did not insulted you if you feel that way I am sorry but it is as if you ignore the Holy word of God and put as if it is the same as "brother" that you are call by. IF you are try to say Christ has no brothers or sisters while he was on earth. That is dead wrong. He did and the proof is in Mathew ch12 but that does not take away for HIS divinity. If you think may be that will lower Him down no it does not as HIS birth in manger and death on the cross did not this will not and never has lower WHO HE IS.
መጽሃፍ ቅዱስ ላይ፡ - የጌታ እናት ሌላ ልጅ ወልዳለች የሚል አልተሳፈም።

የጌታ እናት ሌላ ልጅ ወልዳለች የሚል በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ አልተሳፈም!!!
0 ድምጾች
መጽሃፍ ቅዱስ ላይ፡ - የጌታ እናት ሌላ ልጅ ወልዳለች የሚል አልተጻፈም።
Mar 15, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...