ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ፔንቴ ምን ማለት ነው(ትርጉሙ)?

Jun 10, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ምናልባት የስሙን ትርጉም ፈልገህ ከሆነ፤ ጴንጤ ማለት በግሪክ ሃምሳ (50) ማለት ነው። ይህ ጴንጤ ወይም ሃምሳ የሚባለው ነገር የመጣው በበዓለ ሃምሳ ማለትም ፋሲካ ከተከበረ በኋላ በሃምሳኛ ቀኑ በሚከበረው በዓል ቀን በሃዋርያት ስራ 2 ላይ ከሆነው ነገር ጋ ተያይዞ ነው። በዚህ በዓለ ሃምሳ ቀን ወይም በዓለ ጴንጤ ቀን ወይም በpentecost ቀን ማለትም ከክርስቶስ ሞት በኋላ በሃምሳኛ ቀኑ (ክርስቶስ በፋሲካ ስለሞተ ማለት ነው) መንፈስ ቅዱስ በደቀመዛሙርቱ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወረደበትና በልሳን የተናገሩበት ቀን ነው።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 2
1 በዓለ ኀምሳ (Pentecost) የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
2 ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር

አማኞች እንግዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉበትና በልሳን የተናገሩበት ቀን በPentecost ወይም በዓለ ሃምሳ ቀን ነው። ለዚህ ነው እንግዲህ በዚህም ዘመን በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በልሳን መናገር የሚያምኑና የሚቀበሉ አማኞች ጴንጤዎች ወይም pentecostal ተብለው የሚጠሩት።
Jun 12, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...