ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ኢየሱስ ስለራሱ አንዳችን ነገር አላቅም ሲል. ኢየሱስ ይህን አይችልም (አያቅም)ብል ችግር አለው

የዮሐንስ ወንጌል
5፥30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።


የማቴዎስ ወንጌል
24፥36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።

የማርቆስ ወንጌል
13፥32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።

የዮሐንስ ወንጌል
13፥16 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም................
Jun 17, 2012 መንፈሳዊ አደራ (200 ነጥቦች) የተጠየቀ

4 መልሶች

0 ድምጾች
    የዮሐንስ ወንጌል 21፡ 17 ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤
    ቆላ .1:15-16 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።
    (ዮሃ 14:9) እኔን ያየ አብን አየ።እንዴትስ አንተ አብን አሳየን ትላለህ?
    ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን»ሮሜ 9፡5
ቆላ3፡11 «ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፥ በሁሉም ነው ።»

እኔ በአ ብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን ? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሰራል። እኔ በአ ብ እንዳለሁ አ ብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።

በአጠቃላይ ሰዎች ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው ማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ መሻታቸው መልካም ነው፡፡ አይችልም፣ አያውቅም ብሎ ለመናገር ብቻ ሣይሆን አልቻልኩም ሲል ምን ማለቱ ነው …. የሚሉ ውስጠ ሚስጥሩ ድረስ የሚዘልቁ ፍተሻዎችን ለማድረግ ራሱ ባለቤቱ ሊያግዛቸው ሊገልጥላቸው ይገባል፡፡ እላለው ነገር ከስሩ ውሃ ከጥሩ ነውና፡፡
Oct 2, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን።

አንደኛ።
የዮሐንስ ወንጌል5፥
30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።

ስላሴ(ሦስትነት)
ይህ ቃል በግልጽ የሚያሳየን አብ እና ወልድ የተለያዩ ሁለት ስብዕናዎች መሆናቸውን ነው። አብ ወልድ አይደለም፤ ወልድ አብ አይደለም (የዮሐ. ወንጌል 5፡26)
አንዱ ሌላውን ይሰማል። (እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ)
ከሌላው ተልኮ መጥቶአል። (የላከኝን ፈቃድ)
የራሱን ሳይሆን የሌላውን ፈቃድ ይፈጽማል። (የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና)

quote
የማቴዎስ ወንጌል 26፡
39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን <<አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን>> አለ።
የዮሐንስ ወንጌል 6፡
37 አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤
38 <<ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።>>

እንግዲህ ኢየሱስ <<እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ>> ብሎ የተናገረው ሙሉ በሙሉ የአብን ፈቃድ ለመፈጸም መምጣቱን የሚያሳይ ቃል ነው።
ወልድ ግን ሁሉን ቻይ (ኤል ሻዳይ) እና ሁሉን አዋቂ አምላክ መሆኑ በሌሎች ጥቅሶች ተጽፎአል።
የዮሐንስ ወንጌል 8
56 ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።
አብርሃም ያየው ሁሉን ቻይ (ኤል ሻዳይ) የሆነውን እግዚአብሄር ወልድን (ክርስቶስን) ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 17፡
1 አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን አለው።
ይህ አብ ሳይሆን ወልድ ስለሆነ ኢየሱስ <<አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው>> ሲል እውነትን ተናገረ።
የዮሐንስ ወንጌል 6፡
46 አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ(ወልድ) አብን አይቶአል።

የዮሐንስ ወንጌል 21፡
17 ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ።
የዮሐንስ ወንጌል
16፥30 ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት።

ሁለተኛ።
የማቴዎስ ወንጌል24፥
36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።
የማርቆስ ወንጌል13፥
32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።

እነዚህ ጥቅሶች ደግሞ አብ እና ወልድ በስብዕናቸው ብቻ ሳይሆን በግብር (በተግባር ድርሻቸውም) እንደሚለያዩ የሚያስረዱ ምርጥ ቃላት ናቸው። ሁልጊዘም
አብ በተግባሩ ዲዛይነር (እቅድ አውጪ) ሲሆን ወልድ አድራጊ (የእግዚአብሄር ክንድ) ነው (ትንቢተ ኢሳይያስ 59፡16)። መንፈስ ቅዱስ ደግሞ REVEALER ገላጭ(ፈጻሚ) ነው።
ከላይ በተጠቀሱት ጥቅሶች መሰረት የመጨረሻዋን የፍርድ ቀን መች እንደሆነች የሚያቅደው (የሚቀጥራት) መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ወልድም ሳይሆን አብ ነው።
የሐዋርያት ሥራ 17፤
31 <<ቀን ቀጥሮአልና>>፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ(በአድራጊው አማካይነት) በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።

አብ በቀጠራት በዚያች ቀን ላይ፣ በታላቁ ነጭ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ባላመኑት ሁሉ ላይ የዘላለምን ፍርድ የሚፈርደው አድራጊው ወልድ ነው። እንጂ መንፈስ ቅዱስ ወይም አብ አይደለም።
የወልድን ፍርድ እውነተኛ እና ፍትሃዊ አድርጎ የሚገልጠው ደግሞ ገላጩ መንፈስ ቅዱስ ነው።

የዮሐንስ ወንጌል 5
22-23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።

የማቴዎስ ወንጌል 25
31 የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤
32 አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥
33 በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።

ሌላ ምሳሌ እንይ። ወደ መንግስተ ሰማያት (ገነት) የሚያስገባው በሩ ወይም መንገዱ ወይም እንድትገባ የሚፈቅድልህ አድራጊው ወልድ ነው። በመንግስተ ሰማያት ውስጥ ግን ማን በምን ስፍራ እና ደረጃ እንደሚቀመጥ እቅዱን የሚያዘጋጀው ዲዛይነሩ አብ ነው። መንግስተ ሰማያትን የመንፈሳዊ ውበት፣ የእረፍት እና የዘላለማዊ ደስታ ስፍራ የሚያደርገው ደግሞ የደስታ መንፈስ የሆነው ቅዱሱ መንፈስ ነው።

በሩ (ደጁ) ኢየሱስ ብቻ ነው። የማቴዎስ ወንጌል 7፤13
<<በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 10፡9 በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
መንገዱ ኢየሱስ ብቻ ነው። የዮሐንስ ወንጌል 14፡6 ኢየሱስም አለ ፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ወደ ዕብራውያን 7፡25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ <<በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን>> ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
የሐዋርያት ሥራ 4፡12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።

ወደ ገነት መግባትን የሚሰጠው (የሚፈቅደው) ኢየሱስ ነው።

የሉቃስ ወንጌል 23፡42 ኢየሱስን፦ ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።
43 ኢየሱስም፦ <<እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ >>አለው።
የማቴዎስ ወንጌል 25፡34 ንጉሡም (እግዚአብሄር ወልድ) በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡9 የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።
10 በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
11 እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
13 የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።

በመንግስተ ሰማያት ውስጥ የሚኖረንን የእያንዳንዳችንን ስፍራ የሚያዘጋጀው ወልድ ሳይሆን ዲዛይነሩ አብ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል 20፡20 በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች።
21 እርሱም፦ ምን ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም፦ እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ <<አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ>> አለችው።
22 ኢየሱስ ግን መልሶ፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አለ። እንችላለን አሉት።
23 እርሱም፦ ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ፤ <<በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው>> እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም አላቸው።

ሶስተኛ።
የዮሐንስ ወንጌል
13፥16 <<እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም>>
ይህ ጥቅስ ያለ ቦታው የተጠቀሰ እና ትርጉሙ ተዛብቶ የተነበበ ነው። ቦታው ላይ ሂድና አንብበው። ባርያ የተባሉት ደቀመዛሙርቱ ሲሆኑ ጌታ የተባለው ኢየሱስ ነው። ዮሓንስ 1፡1 ቃልም ራሱ እግዚአብሄር ነበረ ይላል። በርግጥ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር የነበረው ጌታ የባርያን መልክ ይዞ መጥቶ እኛን ማዳኑን እናምናለን (የማርቆስ ወንጌል10፥18 የሉቃስ ወንጌል18፥19
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡6-11)
ዮሃንስ 13፡16 ግን የሚናገረው ከላይ እንደተመለከትነው ነው።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን። (የዮሐንስ ራእይ 22፡21)
Oct 3, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 3, 2012 ታርሟል
ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው። ስለዚህ አይሁድ። ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ። የምን መቅደስ ነው የፈረሰው? ወይም በሌላ አባባል መቅደስ ውስጥ ምን ነበር? መቅደሱን የሚያስተዳድረው የሚመራው ……… ምንድን ነበር? መቅደሱ ውስጥ ያለው ለመቅደሱ ምንድነው? መቅደሱ በውጫዊ አካል ነው ወይስ በውስጣዊ አካል የሚመራው? ይህ ጥያቄ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ከላይ የተነሱትን ጥያቄዎች በሙሉ ማለት ባለበት ቦታ ያለበትን ምክንያት መልስ ይሰጣሉ፡፡ ዝም ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማሣነስ እንዲሁም ብቻውን ያለ አምላክ መሆኑን ለመካድ ጥቅሶችን እየሸቃቀጣችሁ ለክርክር አታቅርቡ፡፡ እሱ የነበረ ያለ ወደፊትም የሚኖር አምላክ ነው፡፡
0 ድምጾች
(1) አብ ዕቅድ አውጭ መሆኑ።

የሐዋርያት ሥራ 1
6 እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት።
7 እርሱም (ክርስቶስ) አላቸው፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም።


(2) የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ ምክኒያት የደስታ ስፍራ መሆኑ።

ወደ ሮሜ ሰዎች 14
17 የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅ እና ሰላም፣ በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት፤ እንጂ መብል እና መጠጥ አይደለችምና።
Dec 28, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Dec 28, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
ሰላም ተወያዮች

በመሰረቱ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አይደለም። ሥላሴ የሚለው ቃልም ሆነ እግዚአብሔርን ኢየሱስንና መንፈስ ቅዱስን አንድ ላይ አድርጎ የሚጠራ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

ብዙዎች ክርስትና ከተመሰረተ በኋላ በብዙ ዘመናት ክርክርና ድንጋጌዎች የጸደቀውን ይህን ጽንሰ ሐሳብ ይይዙና፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊያነቡት ይፈልጋሉ።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡6 "ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ። ከተጻፈው አትለፍ የሚለውን በእኛ ትማሩ ዘንድ፥ ይህን በእናንተ ምክንያት ስለ ራሴና ስለ አጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።"

ከተጻፈው ባናልፍ እንዴት መልካም ነበር!

እናም ጠያቂ ወንድሜ፣ ኢየሱስ የተናገረው ሊናገር የፈለገውን ነው። ሚስጥር አይደለም እየነገረን ያለው። እግዚአብሔር አስተምር ብሎ የላከውን ሐሳብ ነው የነገረን።

አንዱ መላሽ ቆላስይስ 3፡11 ላይ "ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፥ በሁሉም ነው።" የሚለውን ጥቅስ ለሥላሴ ማስረጃ አድርጎ አቅርቧል። ሙሉውን የቆላስይስ መልእክት አንብቦ ሐዋርያው ጳውሎስ ሊል የፈለገው ምን እንደሆነ ያውቅ ዘንድ ለመላሹ እጋብዛለሁ።

እንዲህ አይነቱ አካሄድ ሐዋርያው ጳውሎስ "ሁሉን ቻይ" ወይም ኤልሻዳይ ነበር ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ ነው። ምክንያቱም ጳውሎስ "ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" ብሎአልና። (ፊልጵስዩስ 4፡13) መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ ማንም ሰው እዚህ ጥቅስ ላይ ሲደርስ ጳውሎስ ኤልሻዳይ ነበር ከማለት ይልቅ "ስደክም ክርስቶስ ብርታት ይሆነኛል" ማለቱ እንደሆነ በቀላሉ ተረድቶ ያልፋል እንጂ ምንም ዓይነት የሐሳብ መደናቀፍ አይታይበትም። (ኢሳይያስ 12፡2፤ 40፡29፤ ዮሐንስ 15፡5፤ 2 ቆሮንቶስ 4፡7፤ 12፡9፤ 2 ጢሞቴዎስ 4፡17 ላይ ያሉ ተመሳሳይ ሐሳቦችንም አንብብ)

የሥላሴን እምነት ይዞ ሳይሆን ቃሉን በንጹህ ልቡ የሚያነብ ሰው የቆላስይስ 3፡11 ሐሳብ ከነዚህ ጥቅሶች ጋር ተስማምቶ ያገኘዋል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 28፡18 "ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።"
Quote:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡22 "ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።"
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡28 "ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።"
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡23 "ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።"

ይህ አተያይ በግሪካውያን ፍልስፍና መጽሐፍ ቅዱስን ለሚያነብ ሰው የሚጥም አይደለም። የግሪካውያን ፍልስፍና ማለት ቃላትን እየሰነጠቁ ከንግግሩ በስተጀርባ የተደበቀ ነገር እንዳለ መፈለግ ማለት ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡28 "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤"
Quote:
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፥8 "እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።"
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡13 "መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም።"


ሰላም
Sep 23, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
Sep 23, 2013 ኦፍቲ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...