ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አሁን ክርስትና ሀገርን ያስተዳድር ብንል ህግ አለው ? ካለው ቢብራራ

Jun 17, 2012 መንፈሳዊ አደራ (200 ነጥቦች) የተጠየቀ
Jun 17, 2012 አደራ ታርሟል

1 መልስ

0 ድምጾች
ወንጌልን ለመስበክ እንጂ ሃገርን ልናስተዳድር አሁን አልተጠራንም። መንግስታችንም የክርስቶስ መንግስት እንጂ የዚህ ዓለም መንግስት አይደለችም። ክርስቶስ በምድር ሲነግስ ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር እናስተዳድራለን። አሁን ግን የእግዚአብሔርን መንግስት እንድንሰብክና ብዙዎችንም ወደ መንግስቱ እንድንጠራ ተላክን እንጂ የራሳችን ባልሆኑ በዚህ ዓለም መንግስታት ውስጥ እየገባን እንድናስተዳደር አልተጠራንም።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 1
6 እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት።
7 እርሱም፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤
8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።
Jun 18, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
መልስ መንፈሳዊ ማስረጃ ቢኖረው ጥሩ ነው ፣ ከባያብል
ህግ ማለት የሰው ልጆችን የለት ተለት ሂወት እና ጥፋት የሰራን መቅታት ማለት ነው በለምሳሌ በሙሴ ዘመን ይደረግ እንደነበረው ፣ ከተሰጠኝ መልስ አንፃር ግን ክርስትና ለዘመናችን የሚሆን ህግ የለውም ለማለት ይሁን ወይም ማስተዳደር የለበትም ለማለት አልገባኝም ቢብራራልኝ ? አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ወይስ ሐዋርያቱ የትኛውን ሃገር ሲያስተዳድሩ ወይም እንዲያስተዳድሩ ሲታዘዙ አይተህ ነው፤ አሁን አንተ ስለ ሃገር ማስተዳደር የምትጠይቀው? ክርስትና የሚመጣውን የእግዚአብሔር የጽድቅ መንግስት በተስፋ የምንጠብቅበትና ብዙዎቹን ለሚመጣው መንግስት የምንጠራበት እንጂ የዘመኑን ፖለቲካና ሃገር ማስተዳደሪያ መሳሪያ አይደለም። ለዚህም ነው ሐዋርያቱ ሁሉ ሰዎችን ወደ ንስሃና ወደሚመጣው የክርስቶስ መንግስት ሲጠሩ በመጽሃፍ ቅዱስ የምታየው እንጂ አንድም ቦታ ሃገር ማስተዳደር የእነርሱ ስራ ሆኖ የማታየው። ይህ ብቻ አይደለም በአዲስ ኪዳንም ይሁን በብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ላይ የዘመኑ መንግስታት በአውሬ እንደሚመሰሉ አታውቅምን? ሁሉም ፍትህና ጽድቅ የጎደላቸው መንግስታት ናቸው። የሚመጣው የክርስቶስ መንግስት ብቻ ናት ፍጹም የፍትህና የጸድቅ መንግስት። ቢቻልህ አዲስ ኪዳንን ራስህ እንድታነብበው እመክርሃለሁ። ሃገር ማስተዳደር የሚባል ነገር ቢያንስ በአሁኑ ዘመን የክርስትና አጀንዳ አይደለም። አዲስ ኪዳንን አንብብ።

ሌላው ክርስትና እንደ ሙሴ ህግ አትብላ አትቅመስ አትንካ ወዘተ ተብሎ ተዘርዝቶ በተጻፈ ህግ አይደለም የሚሰረው። ክርስትና የሚሰራ በመንፈስ መመላለስ በሚባል ህግ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች በመንፈስ ይመራሉ እንጂ ሁሉ ነገር ተዘርዝሮ ስለተጻፈላቸው፤ ያንን ህግ ለማሟላት አይደለም የሚጥሩት። ክርስትና ሃይማኖት አይደለም፤ ከክርስቶስ ጋር በመንፈስ የሚኖር ህይወት እንጂ። ክርስትና እንደ ሌሎች ሃይማኖት መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል። የክርስትና ምስጢር በዝርዝር በተጻፉ ህግጋት ሳይሆኑ በመንፈስ ቅዱስ በመመራትና በመመላለስ ነው።
ይሄንን አስተያየት አልጠበቅኩም ነበር እንደኔ አስተያየት ክርስትና የማስተዳደሪያ ህግጋቶች አሉት በቅድስና ሊመራ የሚችለው ክርስትያን የሆነ ሰው ነው
ይሄ ክርስቲያን የፖለቲካ መሪ ካልሆነ መፍትሄ አናገኝም የሚል ሃሳብ በሐዋርያቱ ዘንድ ያልነበረ፣ በአሁኑ ዘመን እየተስፋፋ የሄደ፣ በተለይም ከአሜሪካ የመጣና በእኔ ግምት ፈጽሞ የተሳሳተ አመለካከት ነው። አንደኛ የዚህ ዓለም መንግስትን ክርስቲያን ስለመራው የእግዚአብሔር መንግስት ሊሆን አይችልም። ክርስቶስ ሞቶ የተነሳውና ወደፊትም የሚመጣው እኮና እንዲሁም የሰበከው እኮ ከሰው መንግስት ፈጽሞ ስለተለየችው ስለ እግዚአብሔር መንግስት እንጂ የነበሩትን የሰው መንግስታት ለማሻሻል አይደለም።

በሁለተኛ ደረጃ ይህንን ሃሳብ አራምደው ክርስቲያኖች በመሩዋቸው ሃገሮች ራሳቸው ክርስቲያን መሪዎቹ ብዙ የሰሯቸው ፍትህ የጎደላቸው ስራዎች በአፍሪካም ይሁን በአሜሪካ (ለምሳሌ ጆርጅ ቡሽ) በግልጽ ታይተዋል። ምንም ከሌሎች ዓለማውያን የተሻለ የጽድቅ መንግስት ሲመሰርቱ አልታዩም። እንዲያውም የጌታን ስም ሲያሰድቡ እንጂ።

የጽድቅ መንግስት የጽድቅና የሰላም ንጉስ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የምትገኝ እንጂ በዚህ ዓለም መንግስታት የምትመጣ አይደለችም። የቀደሙት ሃዋርያት ተስፋቸውን በክርስቶስና በሚመጣው በመንግስቱ እንጂ በዚህ ዓለም መንግስታት እንዳላደረጉ ሁሉ እኛም አይናችንን ወደ ክርስቶስና ወደ መንግስቱ ማድረግ አለብን። ዝም ብሎ ላይ ላዩ እውነት የሚመስል፤ ነገር ግን የሰው ጥበብ እንጂ ከመንፈስ ቅዱስ ያልሆነ ሰዋዊ ጥበብ ይዘን የሰለጠንን መስሎን ሃዋርያቱ ከሄዱበት መንገድ ስተን እንዳንሄድና ትልቁን የእግዚአብሔርን መንግስት ተስፋ በዚህ ዘመን መንግስታት እንዳንተካው እንጠንቀቅ (እንደ ኤሳው ብኩርናችንን እንዳንሸጥ ማለት ነው)። ሰይጣን እኮ ለኢየሱስ የዚህን ዓለምን መንግስትና ስልጣን ሁሉ እሰጥሃለሁ ብሎት ኢየሱስ እምቢ ብሏል፤ የክርስቶስ መንግስት ከዚህ ዓለም ስላይደለች። እኛ ታዲያ ምን እያልን ነው? እውነተኛ የፍትህና የጽድቅ መንግስት ክርስቶስ የሚገዛባት የእግዚአብሔር መንግስት ናትና።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
18፥36 ኢየሱስም መልሶ፦ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም አለው።

ትንቢተ ኢሳይያስ 11
1 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
2 የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም
4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል
በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...