ወንጌልን ለመስበክ እንጂ ሃገርን ልናስተዳድር አሁን አልተጠራንም። መንግስታችንም የክርስቶስ መንግስት እንጂ የዚህ ዓለም መንግስት አይደለችም። ክርስቶስ በምድር ሲነግስ ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር እናስተዳድራለን። አሁን ግን የእግዚአብሔርን መንግስት እንድንሰብክና ብዙዎችንም ወደ መንግስቱ እንድንጠራ ተላክን እንጂ የራሳችን ባልሆኑ በዚህ ዓለም መንግስታት ውስጥ እየገባን እንድናስተዳደር አልተጠራንም።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 1
6 እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት።
7 እርሱም፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤
8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።