ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አንድ እውነት አለወይ?

አንድ እውነት አለወይ?ማለቴ በአለም ላይ በማንኛው ጉዳይ ላይ ሁሉንም ሰው የሚያስማማ አንድ ነገር አለ?
Mar 11, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 17, 2011 ታርሟል
ጥያቄውን ዘርዘር አድርገህ ብታብራራው? በደንብ ግልጽ አይደለም። ምን ለማለት ፈልገህ ነው አንድ እውነት አለ ወይ ስትል? ብዙ የመዳን መንገድ አለ ማለትህ ነው? ወይስ ምንድነው?

1 መልስ

0 ድምጾች
ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እውነት ማለት ሰዎች ሁሉ የሚስማሙበት ነገር ማለት አይደለም። እውነት ማለት ሐሰትን ሁሉና እውነት የሚመስልን ነገር አልፎ፡ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር፤ በፈተናም የሚጸና የማይነቃነቅ ዓለት ነው።

እንደ አዲስ ኪዳን አገላለጽ ደግሞ ያ ዓለትና የዘላለም እውነት ራሱ ክርስቶስ ነው።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
14፥6 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

የኢየሱስ ተቃዋሚዎች ኢየሱስን ሲሰቅሉ እውነትን ስላልፈለጉና እውነትን ስላልወደዱ ነው። እንዲያውም በመጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ስንመለከት ብዙዎች ይስማሙበት የነበረው በተሳሳተው ነገር ላይ እንጂ በእውነት ላይ አይደለም። ብዙ ጊዜ እንዲያውም የሚስቱት ጥቂቶች ሳይሆኑ ብዙዎች ናቸው። ለምሳሌ በኤሊያስ ዘመን ከሰባት ሺህ ስዎች በስተቀር እስራኤል ሁሉ ለበኣል እንደሰገዱና እርሱ ትክክለኛው አምላክ ነው ብለው እንደተከተሉት ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረ።
Quote:
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 19
14 እርሱም፦ ለሠራዊት አምላክ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ አለ።
15 እግዚአብሔርም አለው፦ ሂድ፥ በመጣህበትም መንገድ በምድረ በዳ ወደ ደማስቆ ተመለስ ከዚያም በደረስህ ጊዜ በሶርያ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አዛሄልን ቅባው
16 በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የናሜሲን ልጅ ኢዩን ቅባው በፋንታህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአቤልምሖላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ።
17 ኢዩ ይገድለዋል ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
18 እኔም ከእስራኤል ጕልበታቸውን ለበኣል ያላንበረከኩትን ሁሉ፥ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ።

ከግብጽ ባርነት ከወጣው ከእስራኤል ህዝብ ውስጥ ሕዝቡ የተሳሳተ መንገድ በመምረጣቸው ምክንያት፤ ሁሉም ካለ ካሌብና ኢያሱ በስተቀር ወደ ተስፋዪቱ ምድር እንዳይገቡ ተደርገዋል።

ስለዚህ ቁምነገሩ ብዙዎች መስማማታቸው ላይ አይደለም። ጥያቄው ያለው ጥቂትም ይሁኑ ብዙ የሚስማሙት በእርግጥ በእግዚአብሔር እውነት ላይ ቆመው ነው ወይስ በሥጋ ጥበብ ላይ ነው? የሚለው ነው።

ኢየሱስም ወደ ምድር የመጣው ሰዎችን ለማስማምት አይደለም። ለእውነት ለመቆምና እውነትን ለመስከት እንጂ።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
10፥34 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።

የእግዚአሔር መንግስት በእውነትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጂ በመስማማትና በማመቻመች አተመጣምና። የብዙዎችም መስማማት የእግዚአብሔርን እውነት አይቀይርም።
Quote:
ትንቢተ ኢሳይያስ
40፥15 እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።
Mar 17, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...