ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጽዮን ማርያም ናት?

ጽዮን እና ማርያም ምን ያገናኛችዋል?ይብራራልኝ"ጽዮን ማርያም ነች እያሉ አደረቁኝ!!
Jul 26, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Nov 13, 2012 ተመልካች ታርሟል

6 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም መንፈሳዊ

ጽዮን ማርያም ናት የሚሉ ሰዎች እኔንም አጋጥመውኛል እናም ብቻህን አይደለህምና ብዙም አይግረምህ። ;)

ጽዮን ማርያም ናት የሚለው ሃሳብ፤ በመጽሃፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ጽዮን ተብሎ የተጻፉት ክፍሎች ማርያምን ነው የሚያመለክቱት በሚል ግምት ላይ የተመሰረተ ነው። የዚህ ሃሳብ ትልቁ ችግር ግን በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ጽዮን ተብሎ የተጻፈው ስለ ማርያም ነው የሚናገረው ብሎ የሚል አንድም ክፍል አለመኖሩ ነው።

ጽዮን ማርያም ናት ብሎ ከመጽሃፍ ቅዱስ አንድም ሰው አንድ ጥቅስ እንኳን ሊያሳይህ ስለማይችል፤ እንዲህ ለሚሉህ ሰዎች አጭር ጥያቄ ብቻ አቅርብላቸው። ጽዮን ማርያም ናት ወይም ስለ ጽዮን የተነገረው የብሉይ ኪዳን ትንቢት ማርያምን ነው የሚያመለክተው የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ክልፍ አሳዩኝ ብቻ በላቸው። ይህንን ሊያሳይህ የሚችል አንድም ሰው የለምና ነገሩ መላምትና ግምት ብቻ እንደሆነ ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱስ አንድም ቦታ የማይደግፈው ሃሳብ እንደሆነ በዚህ ጥያቄ ማሳየት ትችላለህ።

እኛ ደግሞ የትንቢትን መጽሃፍት እንደፈቃዳችን መተርጎም ስልጣኑ የለንም።
Quote:
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1
20 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤
21 ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

ስለዚህ ጽዮን ማርያም ናት ብለን ለመናገር፤ በብሉይ ኪዳን በነብያቱ ስለ ጽዮን የተጻፈው በእርግጥ ስለ ማርያም መሆኑን የሚያመለክት ቢያንስ ቢያንስ አንድ ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት አለብን። ይሄ ደግሞ አይቻልም። ምክንያቱም የትም ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ ጽዮን ማርያም እንደሆነች አይናገረምና።

ስለ ክርስቶስም ስንናገር እንደዚሁ መጠንቀቅ አለብን። የብሉይ ኪዳን ነብያት ክርስቶስን የሚያመላክቱ ብዙ የተናገሮዋቸውና የጻፎአቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህም አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ፦ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ አውጥቶ በምድረ በዳ ሲንከራተቱ ሳለ በእግዚአብሔር ላይ በማጉረምረማቸው እባቦች ሕዝቡን እንደነደፉና ሙሴም ስለ ሕዝቡ እንደ ጸለየ በዘኍልቍ 21 ላይ እናነብባለን። እግዚአብሔርም ሙሴ በናስ የተሠራ እባብ ሠርቶ ከፍ ያለ ቦታ ላይ እንዲሰቅልና ያንን የተሰቀለውን እባብ ያየ ሁሉ ከተነደፈው እባብ እንደሚድን ለሙሴ ነገሮት ይህም ተፈጽሞአል።

ይሄንን ታሪክ ወስደን የተሰቀለውና ሕዝብን የሚፈውሰው የእግዚአብሔር መፍትሔ የሚያመለክተው ሰውን ሁሉ ከኃጢያት ስለሚያድነውና በመስቀል ላይ ስለ ተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለን ስንናገር ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማቅረብ አለብን እንጂ እንዲያው ስለ ክርስቶስ ሳይሆን አቀርም ብለን ስለ መሰለን ብቻ ቃሉን እንደ ፈለግነው መተርጎም አልተፈቀደልንም። ይህ በናስ ተሠርቶ የተሰቀለው ሕዝብን የፈወሰ የእባብ ምልክት፤ የኢየሱስን የዓለም መድኃኒትነት እደሚያመለክት በአዲስ ኪዳን ስለተጻፈ ደፍረን ስለ ክርስቶስ ነው ብለን ማውራት እንችላለን።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
3፥14-15 ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተጠቀሱት ስለ ሌሎችም ነገሮች ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ነው ብሎ እስካላለ ድረስ፤ እኛ በግምት ወይም ስለመሰለን ከመተርጎም መቆጠብ አለብን።

ወደ ተነሳንበት ወደ ጽዮን ስንመለስ፤ በቅድሚያ የትም ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ጽዮን ማርያም ናት የሚል ስላልተጻፈ፤ ናት ብለን መደምደም አልተፈቀደልንም።

ጽዮን በኢየሩሳሌም የምትገኛ ከፍ ያለች ቦታ ናት። ከቦታዋም ከፍታዊ አቀማመጥ የተነሳ ነው አምባይቱ ጽዮን የምትባለው። በመጀመሪያ ከኢየቡሳውያን ይህቺን ቦታ የማረከው ንጉሥ ዳዊት ስለነበር "የዳዊት ከተማ" በመባልም ትታወቃለች።
Quote:
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 5
7 ነገር ግን ዳዊት አምባይቱን ጽዮንን ያዘ፥ እርስዋም የዳዊት ከተማ ናት።
9 ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ከተማ ብሎ ጠራት። ዳዊትም ዙሪያዋን ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ ቀጠራት።

ቆይቶ ሰለሞን ቤተመቅደሱን በኢየሩሳሌም ከሠራ በኋላ ጽዮን የሚለው ስም ቤተመቅደሱ ያረፈበትንም ከፍታ/አምባ ቦታ ሁሉ የሚያመለክት ሆነ። ስለዚህም ጽዮን የንጉሡን የዳዊትንም ከተማ እንዲሁም የእግዚአብሔር ማደሪያ የነበረውን ቤተመቅደሱንም የምታመለክት መሆን ጀመረች።
Quote:
መዝሙረ ዳዊት 2
6 እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።

መዝሙረ ዳዊት 132
13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።

እግዚአብሔር እንግዲህ ጽዮን ማደሪያው እንደሆነች የሚናገረው፤ በእርግጥም በዚያ የእርሱ ቤተመቅደስ ስለነበረ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጽዮን የሚለው ቃል የጽዮን ተራራ ላለባት ለጠቅላላዋ ለኢየሩሳሌም ከተማ እንዲሁም ለጠቅላላው ለአይሁድ ሃገርና ሕዝብ መጠሪያ ሲሆን እንመለከታለን።
Quote:
ትንቢተ ኢሳይያስ 40
9 የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ አንሺ፥ አትፍሪ ለይሁዳም ከተሞች። እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።

መዝሙረ ዳዊት
102፥21 የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ

መዝሙረ ዳዊት
51፥18 አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ

መዝሙረ ዳዊት
102፥13 አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና

48፥11 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለውየአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ

48፥12 ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቍጠሩ

69፥35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል።

ከዚህ የተነሳ እስራኤላውያን ወደ ባቢሎን ተማርከው በሄዱ ጊዜ ሃገራቸውን እንደማይረሱና እንደሚናፍቁ ይገልጹበት የነበረው በጽዮን መዝሙር ነበር።
Quote:
መዝሙረ ዳዊት
137፥1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።

እንግዲህ እነዚህና ሌሎችም ያልተጠቀሱ በብሉይ ኪዳን ስለ ጽዮን የተጻፉ ጥቅሶች የሚናገሩት የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ስለነበረባትና በኢየሩሳሌም ስለምተገኘው ስለ ኮረብታዋ ማለትም አምባይቱ ቦታ ጽዮን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ጽዮን የሚለውን ቃል፤ ያቺ የእግዚአብሔር መቅደስ ያለባትን አምባ እንዲሁም ለኢየሩሳሌም ከተማ ብሎም ለአይሁድ ሃገርና ባጠቃላይ ለእስራኤል ሕዝብ መጠሪያነት ሲጠቀመባት እንመለከታለን።

በፖለቲካው ዓለምም "ጽዮናዊነት" ወይም "Zionism“ ተብሎ የሚታወቀውም ንቅናቄ የእስራኤላውያንን ከተበተኑባቸው ሃገሮች ተሰብስበው ወደ ጽዮን ማለትም ወደ እስራኤል የመመለስን ሃሳብ የሚያራምድና የሚደግፍ ንቅናቄ ነው። ጽዮን የሚለው ቃል ለእስራኤል ሕዝብና አገር ሁሉ መጠሪያም ነውና።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ጽዮን የሚለው ቃል በተጠቀሰበት በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ውስጥ፤ ጽዮን የሚለውን ቃል ማርያም በሚለው ብንተካው ጨርሶ ትርጉም የሚሰጥም አይደለም። ለምሳሌ መዝሙረ ዳዊት 102፥13 ላይ "አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት" ብሎ ቃሉ የሚናገረው ማርያምን የሚመለከት ሳይሆን የእስራኤልን ሕዝብ ኃጢአት እግዚአብሔር ይቅር እንዲል የቀረበ ጸሎት ነው።

ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ትንቢተ ኢሳያስን እንውሰድ፦
Quote:
ትንቢተ ኢሳይያስ
3፥16 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና
3፥17 ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋቸውን ይገልጣል።

በዚህ ክፍል እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳያስ በኩል የጽዮን ቆነጃጅትን ኃጢአት ከዘረዘረ በኋላ እንደሚፈርድባቸውም ይናገራል። በዚህም ክፍል ጽዮን የሚለውን ቃል ማርያም በሚለው ብንተካው ጨርሶ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም። ነቢዩ የሚናገረው ግን በዚያን ዘመን በኢየሩሳሌም ስለነበሩ ቆነጃጅትና ስለሚገኙበትም የሞራል ውድቀትና የኃጢአት ኑሮ ነው።

ይህን የመሳሰሉ ማለትም ጽዮን በሚለው ፈንታ ማርያም ተብለው ቢተኩ ምንም ትርጉም የማይሰጡ በጣም ብዙ ምሳሌዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማውጣት ይቻላል።

ከሁሉም በላይ ግን ጽዮን ማርያም ነች ወይም ጽዮን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማርያምን ነው የሚል አንድም ክፍል በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሌለ እኛ ከተጻፈው አልፈን ለመጨመር ስልጣኑ እንደሌለን ማወቅ አለብን። "ከተጻፈው አትለፍ" ተብሎ ተጽፎአልና (1ኛ ቆሮንቶስ 4,6)
Jul 26, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Jul 26, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
ጽዮን በሴት ጾታ ብቻ ሳይሆን በወንድ ጾታም ተገልጾአል።

መዝሙረ ዳዊት 2፡
6 እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው (በተቀደሰችው አይልም) ተራራዬ በጽዮን ላይ። (ይሄውም በማርያም ላይ ማለት ሳይሆን በኢየሩሳለም ላይ ማለት ነው)
መዝሙረ ዳዊት48፥
11 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው (ይበላት አይልም)፥ የአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።
ጽዮን የተባለውን ተራራ (አምባ) የሚያመለክት ነው።
መዝሙረ ዳዊት
78፥68 የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ። ("የወደደውን ጽዮንን" ይላል "የወደዳትን ጽዮንን" አይልም። ጽዮን በወንድ ጾታ ተገልጾአል። እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ መረጠ፤ ቅዱሱን ተራራ ጽዮንንም ወደደው (ወደዳት አይልም))

መዝሙረ ዳዊት
102፥13 አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና።
ጽዮን ኃጢአተኛ ናት። ጽዮን ኢየሩሳለምን እና ህዝቦችዋን ያመለክታል። እንጂ ማርያምን አያመለክትም።

በምንም ሁኔታ ጽዮን ማርያም አይደለችም። ጽዮን ኢየሩሳሌም ናት።
ትንቢተ ሚክያስ 3
10 <<ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ>>።
11 አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ። ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም፤ እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
12 ስለዚህ በእናንተ ምክንያት <<ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች>>፥ ኢየሩሳሌምም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።

ትንቢተ ኤርምያስ 26፡
18 ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነቢይ ነበረ። ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ <<ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች>>፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል፤ ብሎ ተናገረ።

ትንቢተ ኢሳይያስ 49፡
14 ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች።
ይህም ማርያምን አይመለክትም።

ትንቢተ ኢሳይያስ 49፡
20 የወላድ መካን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱልሽ ልጆችሽ (ማርያምን አያመለክትም) በጆሮሽ፦ ስፍራ ጠብቦኛልና እቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልኝ ይላሉ።
21 አንቺም በልብሽ፥ የወላድ መካን ሆኛለሁና (ማርያምን አያመለክትም ከወለድኩ በሁዋላ ሞተውብኛል ማለት ነውና)፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁና ተቅበዝበዤአለሁምና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር እነዚህስ ወዴት ነበሩ? ትያለሽ።
22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓለማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ ወንዶች ልጆችሽንም (ማርያምን አያመለክትም) በብብታቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም (ማርያምን አያመለክትም) በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።
23 ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ (ማርያምን አያመለክትም)፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ (ማርያምን አያመለክትም) ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው <<ይሰግዱልሻል>> (ማርያምን አያመለክትም)፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፥(ማርያምን አያመለክትም) እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።

የዮሐንስ ራእይ 3፡
7 በፊልድልፍያም ወዳለው <<ወደ ቤተ ክርስቲያን>> መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ (ማርያምን አያመለክትም)። የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ እርሱ የከፈተውን የሚዘጋ የሌለ፤ እርሱ የዘጋውንም የሚከፍት የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል።
8 ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ። ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና።
9 እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት <<ይሰግዱ ዘንድ>> እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ። (ማርያምን አያመለክትም)
10 የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
11 እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
12 ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና <<የአምላኬን ከተማ>> ስም፥ ማለት <<ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን>> አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
13 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። (ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ነው)

ጽዮን <<የአምላክን ከተማ>> ኢየሩሳሌምን ያመለክታል እንጂ በፍጹም ማርያምን አያመለከትም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 60፡
4 ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ ወንዶች ልጆችሽ (ማርያምን አይመለከትም) ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችሽንም (ማርያምን አይመለከትም) በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
5 በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽ ይደነቃል ይሰፋማል።
6 የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል። (ማርያምን አይመለከትም)። ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።
7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ። የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል። እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
8 ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፥ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?
9 እርሱ አክብሮሻልና (ማርያምን አይመለከትም) ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስም እና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን (ማርያምን አይመለከትም) ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች፣ የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።
10 በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና (ማርያምን አይመለከትም) መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል (ማርያምን አይመለከትም)
11 በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ። ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።
12 ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ (ማርያምን አይመለከትም)
13 የመቅደሴንም ስፍራ (ኢየሩሳሌምን ማለት ነው) ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፥ ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።(ማርያምን አይመለከትም)
14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች (የኢየሩሳለም ጠላቶች ማለት ነው) አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ <<የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን>> ይሉሻል። (ማርያምን አይመለከትም)
15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽ እና የተጠላሽ ነበርሽ (ማርያምን አይመለከትም) ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።
16 የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ (ማርያምን አይመለከትም) እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
17 በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። <<አለቆችሽንም>> ሰላም፥ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ (ማርያምን አይመለከትም)
18 ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልና እና ቅጥቃጤ አይሰማም። (ኢየሩሳለምን ያመለክታል)። ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።
19 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።
20 እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና (ማርያምን አይመለከትም ኢየሩሳለምን ያመለክታል)። ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም።
21 ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ (ኢየሩሳለምን ያመለክታል)። እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ።
Oct 4, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 15, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
tsion mariam nat? ክፍል አንድ።
"ጽዮን ማርያም ነች" ማለት ምን ማለት ነው? ጽዮን ማርያም ናትን?
ጽዮን እና ማርያም ይገናኛሉ? በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ "ጽዮን" የተባለው ቃል ማርያምን ወክሎ ይገኛልን? የቱ ጋር? ጽዮን እና ማርያም ምን ያገናኛቸዋል? ስለ ጽዮን የተጻፉ ቃላት፣ ስለ ማርያም የተጻፉ ትንቢቶች ናቸውን? ለሚሉ ጥያቄዎች ምላሹን መጽሓፍ ቅዱስን ብቻ መሠረት አድርገን እንመለከታለን። "ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" /2ኛ የጴጥሮስ መልእክት1፡ 20-21/ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ የታወቀችው በንጉሱ በዳዊት ዘመን ነበር። ከንጉሱ ከዳዊት ዘመን በፊት ጨርሶ አትታወቅም ነበር። እስቲ ስለ ጽዮን የተጻፉትን ቃላት በዝርዝር እንያቸው።

(1) መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
5፥7 ነገር ግን ዳዊት አምባይቱን (ተራራይቱን) ጽዮንን ያዘ፥ እርስዋም <<የዳዊት ከተማ>> ናት። (ማርያምን አይመለከትም። ጽዮን ማለት የዳዊት ከተማ /ኢየሩሳለም/ ናት)

(2) መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
8፥1 ሰሎሞንም (የዳዊት ልጅ) የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት <<ከዳዊት ከተማ ከጽዮን>> (ከኢየሩሳለም ማለት ነው) ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎች እና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት፥ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው። (ማርያምን አይመለከትም)

(3) መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
19፥20 የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኽውን ሰምቻለሁ።
21 እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው። ድንግሊቱ <<የጽዮን ልጅ>> ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች <<የኢየሩሳሌም ልጅ>> በላይህ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
(ጽዮን ሴት ልጅ አላት። እንግዲህ ጽዮን ማርያም ነች ማለት ምን ማለት ነው? የአሦር ንጉስ ሰናክረም በጽዮን /በኢየሩሳለም/ ላይ ጦርነትን ባወጀ ጊዜ፣ የእስራኤል ቅዱስ /እግዚአብሔር/ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ነበር። በዚህ ስፍራ ጽዮን ኢየሩሳሌምን ያመለክታል እንጂ ማርያምን አይመለከትም። ቃሉም ራሱ ራሱን ይፈታል። "ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ" ማለት "የኢየሩሳሌም ልጅ" ማለት ነው፤ ጽዮን ማለት ኢየሩሳለም ማለት ነው።
"የጽዮን ልጅ" በእግዚአቢሔር ተደግፈው ተዘልለው በቅምጥል ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልን ልጆች የሚወክል ቃል ነው። ዛሬም ቢሆን የእግዚአብሔር ልጆች (የዮሓንስ ወንጌል 1፡12) በሰይጣን ላይ እንዲሁ ናቸው፤ በሰዎች ላይ አይደለም(የሉቃስ ወንጌል 10፡18-19)። "ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፥ የኢየሩሳሌም ልጅ በላይህ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።")

(4) መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
19፥31 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል። (ከተማይቱን ዙሪያ ከሚገኙት ተራራዎች ትልቁን ጽዮን የተባለውን ተራራ ያመለክታል)

(5) መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
11፥5 በኢያቡስም የተቀመጡ ዳዊትን፦ ወደዚህ አትገባም አሉት። ዳዊት ግን አምባይቱን <<ጽዮንን>> ያዘ፤ እርሷም <<የዳዊት ከተማ>> ናት።
(ጽዮን የዳዊት ከተማ /ኢየሩሳለም/ ናት እንጂ ማርያምን አይመለከትም)

(6) መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
5፥2 በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት <<ከዳዊት ከተማ ከጽዮን>> (ከኢየሩሳለም ማለት ነው) ያወጡ ዘንድ(ከማደሪያው ድንኳን ወደ ጽዮን ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ያዛውሩ ዘንድ) የእስራኤልን ሽማግሌዎች እና የነገድ አለቆችን ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

(7) መዝሙረ ዳዊት
2፥6 እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ። (ጽዮን በወንድ ጾታ ተገልጾአል፡-በተቀደሰው ይላል በተቀደሰችው አይልም። የተቀደሰው ተራራዬ የተባለው ጽዮን ነው፤ እንግዲህ ጽዮን ማርያም ነች ብሎ መናገር ማርያም ወንድ ናት/ነው ማለት ይሆናል፤ ይህም ውሸት ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው።)

(8) መዝሙረ ዳዊት
9፥11 በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ። (ቤተ መቅደሱ ያለበትን የጽዮን /ኢየሩሳለም/ ከተማን ያመለክታል)

(9) መዝሙረ ዳዊት
9፥14 ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ <<በጽዮን ልጅ በደጆችዋ>> በማዳንህ ደስ ይለኛል። (ጽዮን ሴት ልጅ አላት። ማርያምስ ሴት ልጅ አላት እንዴ? በዚህ ስፍራ ጽዮን ኢየሩሳለምን የሚያመለክት ሲሆን፣ "በጽዮን ልጅ በደጆችዋ" ማለት በኢየሩሳለም ልጆች አደባባይ፣ በቤተ መቅደሱ በሮች... ማለት ነው)

(10) መዝሙረ ዳዊት
14፥10 ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል። (ኢይሩሳለምን ወይም አይሁድን ያመለክታል። በዮሓንስ ወንጌል 4፡22 እንደተጻፈው መድኃኒት የሚመጣው ከአይሁድ ነውና። በርግጥም የአለም መዳን ከአረብ ወይም ከህንዱ ሳይሆን ከአይሁድ /ከጽዮን/ መጥቶአል)

(11) መዝሙረ ዳዊት
20፥2 ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።
(መቅደሱ ያለበትን ጽዮንን /ኢየሩሳለምን/ ያመለክታል።
መዳን ከአይሁድ ወይም ከእስራኤል ነውና። /የዮሓንስ ወንጌል 4፡22/
ስለዚህ ክርስቶስ ከእስራኤል መጣ። /ወደ ሮሜ ሰዎች 9፡ 4-5/)

(12) መዝሙረ ዳዊት
48፥1 እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ "በተቀደሰ" ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው (በተቀደሰች አይልም)
2 በሰሜን ወገን በመልካም ስፍራ "የቆመ" የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ "ነው"። "እርሱም" የትልቁ ንጉሥ ከተማ "ነው"።
(ጽዮን በወንድ ጾታ ተገልጾአል፦ "በተቀደሰ፣ የቆመ፣ ነው፣ እርሱም፣ ነው"... የሚሉ ቃላት ወንድ ጾታን ያሳያሉ። እርሱም <<የትልቁ ንጉሥ ከተማ>> ነው፦ ይህም ቀደም ሲል የዳዊት ከተማ የተባለው ጽዮን /ኢየሩሳለም/ ነው። በተጨማሪም ቤተመቅደሱ ስላለበት የእግዚአብሔር "የአምላካችን ከተማ" ተብሎአል። /መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 11፥5 በኢያቡስም የተቀመጡት ዳዊትን፦ ወደዚህ አትገባም አሉት፤ ዳዊት ግን አምባይቱን <<ጽዮንን>> ያዘ፤ እርሷም <<የዳዊት ከተማ>> ናት። አምባይቱን=ተራራይቱን ማለት ነው/።

(13) መዝሙረ ዳዊት
48፥11 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው(ይበላት አይልም)፥ የአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።
(ጽዮን በወንድ ጾታ ተገልጾአል። በዚህ ክፍል ጽዮን የኢየሩሳለምን ከተማ እና ህዝቦችዋን /የአይሁድን ልጆች/ ያመለክታል።)

(14) መዝሙረ ዳዊት
48፥12 ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም (ቅጥርዋን) ቍጠሩ። (የኢየሩሳለምን ከተማ ያመለክታል። የከተማይቱ /የጽዮን/ ጠባቂዎች የዙሪያዋን ቅጥር እና ግንብ በመቃኘት ከወራሪ ጠላት በንቃት እንዲጠብቁ የቀረበ ጥሪ ነው። አንዳንድ የተሳሳቱ ወንድሞች ይህ ጥቅስ ስለማርያም ነው ለማለት ቢዳዳቸውም እውነቱ ግን ይሄው ነው። ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም /2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡ 20/።)

(15) መዝሙረ ዳዊት
50፥2 ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።
(ከጽዮን /ከእስራኤል/ ማለት ነው። የማይታይ የነበረው አምላክ የሚታይ ሆኖ፣ ግልጥ ሆኖ፣ ሥጋ ለብሶ ከእስራኤል መጣ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 9፡
4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነት እና ክብር፣ ኪዳንም፣ የሕግም መሰጠት፣ የመቅደስም ሥርዓት፣ የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤
5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ <<ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ>> (ግልጥ ሆኖ መጣ)፥ እርሱም "ከሁሉ በላይ" ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ (እግዚአብሔር) ነው፤ አሜን።
Romans 9:5

NET © To them belong the patriarchs, and "from them," by human descent, came the Christ, who is God over all, blessed forever! Amen.

NIV © Theirs are the patriarchs, and "from them" is traced the human ancestry of Christ, who is God over all, for ever praised! Amen.

NASB © whose are the fathers, and "from whom" is the Christ according to the flesh, who is over all, God blessed forever. Amen.

NLT © Their ancestors were great people of God, and Christ himself was "a Jew" as far as his human nature is concerned. And he is God, who rules over everything and is worthy of eternal praise! Amen.

(16) መዝሙረ ዳዊት
51፥18 አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ። (ጽዮንን /ኢየሩሳለምን/ አሰማምራት፤ ገንባት፤ ቅጥሮችዋንም ሥራ፤ ህዝቦችዋንም አበርታ ማለት ነው።)

(17) መዝሙረ ዳዊት
53፥6 መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፤ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል። (ነቢዩ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ዘመናትን አሻግሮ ይመለከታል። በዚህም የዓለም ሁሉ መድኃኒት ሆኖ ገና ወደፊት ከጽዮን /ከአይሁድ/ የሚመጣውን ጌታውንና አምላኩን ከወዲሁ ይናፍቃል።
የዳዊት ጌታ።
የማቴዎስ ወንጌል 22:
41-42 ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት።
43-44 እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ "ጌታ ጌታዬን (አብ ወልድን)፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው" ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?
45 ዳዊትስ (ክርስቶስን) ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።
46 አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።

(18) መዝሙረ ዳዊት
65፥1 አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል።
(በጽዮን /በኢየሩሳለም/ ከተማ ባለው ቤተ መቅደስ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ወደ እርሱም ይጸልዩ ነበር። አቤቱ፥ በኢየሩሳለም ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል የሚል ነው)

(19) መዝሙረ ዳዊት
69፥35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና በዚያም ይቀመጣሉ፤ ይወርሱአትማል። (ከይሁዳ ከተሞች አንዷ ጽዮን /ኢየሩሳለም/ ናት። እግዚአብሔር ጽዮንን፣ የጽዮን ህዝቦችን ያድናል፤ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራል፤ ህዝቦችዋም በዚያ ይቀመጣሉ፤ ይወርሱአታል የሚል ነው። እንጂ ማርያምን የሚያመለክት አይደለም)

(20) መዝሙረ ዳዊት
73፥28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው፤ በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ። (ማርያምን የሚያመለክት ሳይሆን፤ በኢየሩሳለም ልጆች አደባባይ ወይም በአይሁድ ልጆች ደጆች የሚል ነው። አማኙ ነቢይ ለሎች ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ሲታመኑ አይቶ "ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው" አለ። ዛሬም አማኞች ነን ባዮች እናንተ ሆይ፣ በርግጥ አማኞች ከሆናችሁ ሌሎች በፍጡራን ሬድኤት እና አማላጅነት ሲታመኑ ብታዩአቸውም "ለእናንተ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻላችኋል፤ መታመኛችሁም እግዚአብሔር ይሁን"። በዚህ ከነቢዩ ወገን ትሰለፋላችሁና።
ራሷ ሥጋ ለባሽና የእግዚአብሔር ፍጡር ነችና በማርያም አትታመኑ። ነገር ግን ፈጣሪም አምላክም፣ ወዳጅም ወንድምም፣ ጌታም እመቤትም፣ እናትም አባትም፣ ዘመድም መመኪያም በሆነ ሊገድልም ሊያድን ቻይ በሚሆን በአንዱ በእግዚአብሔር ታመኑ። ወደ እርሱ መቅረብ ይሻላችኋልና። ወደ እርሱ በቀረባችሁ ጊዜ በዚያ ቅዱሳንን ሁሉ (ማርያምንም ጨምሮ) ታገኛላችሁና። “በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል“(መዝሙረ ዳዊት 118:8)
ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሟች ነው። መጽሐፈ ኢዮብ 34፥15 ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል። ትንቢተ ኢሳይያስ
40፥6 ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።
መጽሐፈ መክብብ 9፡4 "ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው። 5 ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም። 6 ፍቅራቸው እና ጥላቸው፣ ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፥ "ከፀሐይ በታችም" በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።"
ሥጋ ለባሽ ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል። ትንቢተ ኢሳይያስ
66፥23 እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻው እና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ ነው። ትንቢተ ኤርምያስ
32፥27 እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።
Oct 4, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 15, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
tsion mariam nat? ክፍል ሁለት (የቀጠለ)። ገና የሚታረም።

...በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር በጥቂት መሪዎችና ቄሶች ላይ ብቻ ሳይሆን በአማኞች ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስን አፍስሷል። ትንቢተ ኢዩኤል 2፥28 ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን "በሥጋ ለባሽ ሁሉ" ላይ አፈስሳለሁ፤ "ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችሁም" ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ። (ይህን ያላመኑ ግን አማኞች አይደሉምና ተጠቃሚ ሳይሆኑ ይቀራሉ።) የዮሐንስ ወንጌል 1፡16 እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና።
ወደ ገላትያ ሰዎች 3፡26 በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ 3፡27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። 3፡28 አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።

ማርያም ማለት እኮ ከበዓል ጥጋብ በኋላ ውድ ልጇን ረስታ የሄደች ሴት ናት። /የሉቃስ ወንጌል 2፡ 41-50/ የሚገርማችሁ ግን የሚታፈቅረውን ባሏን ዮሰፍን ረስታ አልሄደችም። ዮሴፍም ቢሆን በጥንቃቄ እንዲያሳድገው የተሰጠውን አደራ ዘንግቶ ብላቴናውን ኢየሱስን ረስቶ ሄደ፤ ሚስቱን ግን ረስቶ አልሄደም። ያኔ ውድ ልጅዋን የረሳች፣ ዝንጉ የሆነች፣ ማስተዋል ያልቻለች አንዲት ደካማ ሴት፣ ዛሬ የአለም ክርስቲያኖችን ሁሉ ታስታውሳለች ብሎ ማሰብ እኔ ከመጽሓፍ ቅዱስ በላይ አዋቂ ነኝ እንደ ማለት ነው። ሰው ቢረሳንም ሰው ባያውቀንም ግን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቶ አይረሳንም።

የተረገመ (ከእግዚአብሔር ለዘላለም የተለየ) እንዳትሆኑ በሰው አትታመኑ። በእግዚአብሔር ብቻ ታመኑ። ትንቢተ ኤርምያስ 17፥5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። የማቴዎስ ወንጌል 25፡41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
ይልቅ ለሎች ደባሎችን ትተን ክርስቶስን ብቻ አብዝተን እንድናፈቅረው መጻሕፍት ይመክሩናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16፥22 ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ ና።

ሓዋርያት የሰበኩት ክርስቶስን ብቻ ነበር እንጂ ማርያምን እና ሌሎች ፍጡራንን አዳብለው ከቶ አልሰበኩም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡2 በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው። 1፡24 ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
ሓዋርያት ያልሰበኩትን የሚሰብክ ማንም ቢሆን የተረገመ ነው።
ወደ ገላትያ ሰዎች 1፥8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ (እንኳን ቢሆን)፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። 1፥9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
አንዳንድ ሰዎች እስከአሁን ድረስ ልቡናቸው ጣኦት ማምለክን ስለ ለመደ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ የሆነውን ያህል ወልድ እና ማርያምም እንዲሁ አንድ የሆኑ ይመስላቸዋል። ስለዚህም "አባታችን ሆይ" ብለው ከጸለዩ በኋላ "እመቤታችን ሆይ" በማለት እግዚአብሔርን እና ማርያምን አከታትለው ያመሰግኑአቸዋል። ይህ ግን ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው። በግዕዙ ጌታችን፣ እግዚእነ ማለት ለወንድ አንቀጽ ሲሆን፤ እመቤታችን፣ እግዚእትነ ማለት ደግሞ ለሴት አንቀጽ /ለሴት ጌታ/ የሚጠቀሙት ነው። ቅዱስ መጽሓፍ ግን ሁለት ጌታ የለም አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው ይለናል። ይህም እውነት ለሰው ሁሉ የተገለጠ ነው፤ ሰው ግን በእልህ ተይዞ ራሱን ወደ ሞት ይነዳል። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፥12 በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው (በእኛ በአህዛብ) መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፥13 አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።

የክርስቶስ ባሪያዎች ሁኑ እንጂ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። የሰው ባሪያዎች እንዳንሆን ክርስቶስ ውድ ዋጋ ከፍሎ ነጻ አውጥቶናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፥23 በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 6፥24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ኦሪት ዘሌዋውያን 26፥13 ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡1 በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።

ክርስቲያን ሳይሆኑ ክርስቲያን ነን ብለው ተመሳስለው ወደ ጉባኤ ገብተው መድረኩን ከተቆጣጠሩ ሰርጎ ገቦች፣ ሓዋርያት ያልሰበኩትን ከሚሰብኩ ሰዎች ተጠበቁ። የይሁዳ መልእክት 1፡3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት" እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። 1፡4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። የማቴዎስ ወንጌል 7፡15 የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። 7፡16 ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?

(21) መዝሙረ ዳዊት
74፥2 አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ። (በዚህ ክፍል ጽዮን፡ (1) እግዚአብሔር የፈጠራት ማህበር/ሕዝብ ነች። (2) እግዚአብሔር የተቤዣት ርስት ነች። (3) ተራራ ነች። ቤተ መቅደሱ /የእግዚአብሔር ማደሪያ/ ያለው ጽዮን በሚባል ተራራ ላይ ነበር።

(22) መዝሙረ ዳዊት
76፥2 ስፍራው በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው። (ቤተ መቅደሱ /የእግዚአብሔር ማደሪያ/ በኢየሩ ሳሌም ማለትም በጽዮን ነው የሚል ነው)

(23) መዝሙረ ዳዊት
78፥68 የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ። ("የወደደውን ጽዮንን" ይላል "የወደዳትን ጽዮንን" አይልም። ጽዮን በወንድ ጾታ ተገልጾአል። እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ መረጠ፤ ቅዱሱን ተራራ ጽዮንንም ወደደው (ወደዳት አይልም))

(24) መዝሙረ ዳዊት
84፥7 ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል። (በኢየሩሳሌም ማለት ነው። አማኝ ሕዝቡ ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ አምላካቸውም በጽዮን/በኢየሩሳሌም/ ክብሩን ይገልጣል የሚል ነው)

(25) መዝሙረ ዳዊት
87፥1 መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው።
2 ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።
3 የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል። (ጽዮን/ኢየሩሳሌም በተራሮች ላይ የተመሰረተ ከተማ ነው። ከተራሮቹም ትልቁ ጽዮን ይባላል። እግዚአብሔር ከያዕቆባውያኑ የመኖሪያ ድንኳኖች ይልቅ፥ የኢየሩሳሌምን ደጆች ይወድዳቸዋል። ምክንያቱም ኢየሩሳሌም /ጽዮን/ "የእግዚአብሔር ከተማ" ነበረና፤ ብቸኛው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም የሚገኘው በጽዮን ከተማ ነበረና።)

(26) መዝሙረ ዳዊት
87፥4 የሚያውቁኝን ረዓብን እና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ ፍልስጥኤማውያን፣ ጢሮስም፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
5 ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት። 6 እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል። 7 በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።
(የተሳሳቱ ሰዎች በዚህ ክፍል ጽዮን በቀጥታ ማርያምን ትወክላለች ይላሉ። ነገር ግን ቀረብ ብለው በማስተዋል ቢያጠኑት ማርያምን እያከበሯት ሳይሆን እየበደሏት መሆኑን ይረዱ ነበር። ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው፡ (1) ብዙ ሕዝቦች በጽዮን ከተማ ተወለዱ። አስተውል ከእርሷ ተወለዱ አይልም፤ በዚያ ተወለዱ ይላል። (2)

(27) መዝሙረ ዳዊት
97፥8 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው

(28) መዝሙረ ዳዊት
99፥2 እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

(29) መዝሙረ ዳዊት
102፥13 አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና

(30) መዝሙረ ዳዊት
102፥16 እግዚአብሔር ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።

(31) መዝሙረ ዳዊት
102፥21 የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ

(32) መዝሙረ ዳዊት
110፥2 እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ።

(33) መዝሙረ ዳዊት
125፥1 በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።

(34) መዝሙረ ዳዊት
126፥1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።

(35) መዝሙረ ዳዊት
128፥5 እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።

(36) መዝሙረ ዳዊት
129፥5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።

(37) መዝሙረ ዳዊት
132፥13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።

(38) መዝሙረ ዳዊት
133፥3 በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።

(39) መዝሙረ ዳዊት
134፥3 ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።

(40) መዝሙረ ዳዊት
135፥21 በኢየሩሳሌም የሚያድር እግዚአብሔር ከጽዮን የተባረከ ነው። ሃሌ ሉያ።

(41) መዝሙረ ዳዊት
137፥1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።

(42) መዝሙረ ዳዊት
137፥3 የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም። የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።

(43) መዝሙረ ዳዊት
146፥10 እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ።

(44) መዝሙረ ዳዊት
147፥13 ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።

(45) መዝሙረ ዳዊት
149፥2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ።

(46) መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
3፥11 እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ እናቱ በሠርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።

(47) ትንቢተ ኢሳይያስ
1፥8 የጽዮንም ሴት ልጅ በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ፥ በዱባ አትክልትም እንዳለ ጎጆ፥ እንደተከበበችም ከተማ ሆና ቀረች።

(48) ትንቢተ ኢሳይያስ
1፥27 ጽዮን በፍርድ ከእርሷም የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ።

(49) ትንቢተ ኢሳይያስ
2፥3 ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው። ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።

(50) ትንቢተ ኢሳይያስ
3፥16 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና

(51) ትንቢተ ኢሳይያስ
3፥17 ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋቸውን ይገልጣል።

(52) ትንቢተ ኢሳይያስ
4፥3-4 ጌታም የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፥ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፥ በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፥ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፥ ቅዱስ ይባላል።

(53) ትንቢተ ኢሳይያስ
4፥5 እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤአቸውም ላይ በቀን ዳመናንና ጢስን በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።

(54) ትንቢተ ኢሳይያስ
8፥18 እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።

(55) ትንቢተ ኢሳይያስ
9፥11 ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ ተቋቋሚ ያስነሣበታል፥

(56) ትንቢተ ኢሳይያስ
10፥12 ስለዚህ እንዲህ ይሆናል ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኩሩ ልብ ፍሬን የዓይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይጐበኛል።

(57) ትንቢተ ኢሳይያስ
10፥24 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ አሦር በበትር ቢመታህ፥ ግብጽም እንዳደረገ ዘንጉን ቢያነሣብህ አትፍራው።

(58) ትንቢተ ኢሳይያስ
10፥32 ዛሬ በኖብ ይቆማል በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን ያንቀሳቅሳል።

(59) ትንቢተ ኢሳይያስ
12፥6 አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።

(60) ትንቢተ ኢሳይያስ
14፥32 ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፥ የሕዝቡም ችግረኞች በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።
Oct 4, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 31, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
ክፍል ሶስት (የቀጠለ) ገና የሚታረም።

(55) ትንቢተ ኢሳይያስ
9፥11 ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ ተቋቋሚ ያስነሣበታል፥

(56) ትንቢተ ኢሳይያስ
10፥12 ስለዚህ እንዲህ ይሆናል ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኩሩ ልብ ፍሬን የዓይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይጐበኛል።

(57) ትንቢተ ኢሳይያስ
10፥24 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ አሦር በበትር ቢመታህ፥ ግብጽም እንዳደረገ ዘንጉን ቢያነሣብህ አትፍራው።

(58) ትንቢተ ኢሳይያስ
10፥32 ዛሬ በኖብ ይቆማል በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን ያንቀሳቅሳል።

(59) ትንቢተ ኢሳይያስ
12፥6 አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።

(60) ትንቢተ ኢሳይያስ
14፥32 ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፥ የሕዝቡም ችግረኞች በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።

(61) ትንቢተ ኢሳይያስ
16፥1 በምድርም ላይ ለሠለጠነው አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ።

(62) ትንቢተ ኢሳይያስ
18፥7 በዚያን ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ከሆነ ወገን፥ ከሚሰፍርና ከሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ እጅ መንሻ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም ወደሚገኝበት ስፍራ ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል።

(63) ትንቢተ ኢሳይያስ
24፥23 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፥ በሽማግሌዎቹም ፊት ክብር ይሆናልና ጨረቃ ይታወካል ፀሐይም ያፍራል።

(64) ትንቢተ ኢሳይያስ
28፥16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም።

(65) ትንቢተ ኢሳይያስ
29፥8 ተርቦም እንደሚያልም ሰው ይሆናል በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይበላል፥ ነገር ግን ይነቃል ሰውነቱም ባዶ ነው ተጠምቶም እንደሚያልም ሰው ይሆናል በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይጠጣል፥ ነገር ግን ይነቃል፥ እነሆም፥ ይዝላል ሰውነቱም አምሮት አለው እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።

(66) ትንቢተ ኢሳይያስ
30፥19 በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።

(67) ትንቢተ ኢሳይያስ
31፥4 እግዚአብሔርም እንዲህ ይለኛልና። አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሳ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።

(68) ትንቢተ ኢሳይያስ
31፥9 አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፥ ይላል እሳቱ በጽዮን እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር፦

(69) ትንቢተ ኢሳይያስ
33፥5 እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ሞላት።

(70) ትንቢተ ኢሳይያስ
33፥14 በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?

(71) ትንቢተ ኢሳይያስ
33፥20 የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፥ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።

(72) ትንቢተ ኢሳይያስ
34፥8 የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፥ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።

(73) ትንቢተ ኢሳይያስ
35፥10 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ። እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ። የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል። ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

(74) ትንቢተ ኢሳይያስ
37፥22 እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው። ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።

(75) ትንቢተ ኢሳይያስ
37፥32 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

(76) ትንቢተ ኢሳይያስ
40፥9 የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ አንሺ፥ አትፍሪ ለይሁዳም ከተሞች። እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።

(77) ትንቢተ ኢሳይያስ
41፥27 በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነኋቸው እላለሁ ለኢየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።

(78) ትንቢተ ኢሳይያስ
46፥13 ጽድቄን አቀርባለሁ፥ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።

(79) ትንቢተ ኢሳይያስ
49፥14 ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች።

(80) ትንቢተ ኢሳይያስ
51፥3 እግዚአብሔርም ጽዮንን ያጽናናል በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፥ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔደን በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።

(81) ትንቢተ ኢሳይያስ
51፥11 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ የዘላለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።

(82) ትንቢተ ኢሳይያስ
51፥16 ሰማያትን እዘረጋ ዘንድ ምድርንም እመሠርት ዘንድ፥ ጽዮንንም። አንቺ ሕዝቤ ነሽ እል ዘንድ ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።

(83) ትንቢተ ኢሳይያስ
52፥1 ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።

(84) ትንቢተ ኢሳይያስ
52፥2 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ ተነሺ፥ ተቀመጪ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።

(85) ትንቢተ ኢሳይያስ
52፥7 የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም። አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።

(86) ትንቢተ ኢሳይያስ
52፥8 እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ።

(87) ትንቢተ ኢሳይያስ
59፥20 ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፥ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦

(88) ትንቢተ ኢሳይያስ
60፥14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።

(89) ትንቢተ ኢሳይያስ
61፥3 እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።

(90) ትንቢተ ኢሳይያስ
62፥1 ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።

(91) ትንቢተ ኢሳይያስ
62፥11 እነሆ፥ እግዚአብሔር ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል። ለጽዮን ልጅ። እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ በሉአት።

(92) ትንቢተ ኢሳይያስ
64፥10 የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል ጽዮን ምድረ በዳ ኢየሩሳሌምም ውድማ ሆናለች።

(93) ትንቢተ ኢሳይያስ
66፥8 ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።

(94) ትንቢተ ኤርምያስ
3፥14 ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ እኔ ባላችሁ ነኝና ተመለሱ ይላል እግዚአብሔር አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፥ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ

(95) ትንቢተ ኤርምያስ
4፥6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ ሽሹ፥ አትዘግዩ።

(96) ትንቢተ ኤርምያስ
4፥31 እንደምታምጥ የበኵርዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና። ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።

(97) ትንቢተ ኤርምያስ
6፥2 የተዋበችውንና የተሰባቀለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሰቍላለሁ።

(98) ትንቢተ ኤርምያስ
6፥23 ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።

(99) ትንቢተ ኤርምያስ
8፥19 እነሆ። እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ አገር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው?

(100) ትንቢተ ኤርምያስ
9፥19 በጽዮን፦ እንዴት ተበዘበዝን! ምድርንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አፈርን! የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።

(101) ትንቢተ ኤርምያስ
14፥19 በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።

(102) ትንቢተ ኤርምያስ
26፥18 ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነቢይ ነበረ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።

(103) ትንቢተ ኤርምያስ
30፥17 እኔ ጤናህን እመልስልሃለሁ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።

(104) ትንቢተ ኤርምያስ
31፥6 በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ጠባቆች። ተነሡ፥ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።

(105) ትንቢተ ኤርምያስ
31፥12 ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ እልል ይላሉ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።

(106) ትንቢተ ኤርምያስ
50፥5 ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው። ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘላለም ቃል ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ተጠጉ ብለው ስለ ጽዮን መንገድ ይጠይቃሉ።

(107) ትንቢተ ኤርምያስ
50፥28 የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል የመቅደሱንም በቀል በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን አገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።

(108) ትንቢተ ኤርምያስ
51፥10 እግዚአብሔር ጽድቃችንን አውጥቶአል ኑ፥ በጽዮን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር።

(109) ትንቢተ ኤርምያስ
51፥24 በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦

(110) ትንቢተ ኤርምያስ
51፥35 በጽዮን የምትቀመጥ። በእኔና በሥጋዬ የተደረገ ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን ትላለች ኢየሩሳሌምም። ደሜ በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን ትላለች።

(111) ሰቆቃወ ኤርምያስ
1፥4 ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ ደናግሎችዋም ተጨነቁ እርስዋም በምሬት አለች።

(112) ሰቆቃወ ኤርምያስ
1፥6 ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበትዋ ሁሉ ወጥቶአል አለቆችዋ ማሰማርያ እንደማያገኙ ዋላዎች ሆኑ ከሚያባርሩአቸው ፊት ተዳክመው ሄዱ።

(113) ሰቆቃወ ኤርምያስ
1፥17 ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች የሚያጽናናት የለም እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።

(114) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥1 አሌፍ። ጌታ በቍጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደ ምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቍጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።

(115) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥4 ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።

(116) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥6 ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቍጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ።

(117) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥8 ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ አሰበ የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ እጁን ከማጥፋት አልመለሰም ምሽጉና ቅጥሩ እንዲያለቅሱ አደረገ በአንድነት ደከሙ።

(118) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥10 ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።

(119) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥13 ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና የሚፈውስሽ ማን ነው?

(120) ሰቆቃወ ኤርምያስ
2፥18 ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ። የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ የዓይንሽ ብሌን አታቋርጥ።
Oct 4, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 31, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
ክፍል አራት (የቀጠለ)። ገና የሚታረም።
(121) ሰቆቃወ ኤርምያስ
4፥2 ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ!

(122) ሰቆቃወ ኤርምያስ
4፥11 ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፥ ጽኑ ቍጣውን አፍስሶአል እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፥ መሠረትዋንም በላች።

(123) ሰቆቃወ ኤርምያስ
4፥22 ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል ኃጢአትሽን ይገልጣል።

(124) ሰቆቃወ ኤርምያስ
5፥11 በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳም ከተሞች ደናግልን አጐሰቈሉ።

(125) ሰቆቃወ ኤርምያስ
5፥18 ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና።

(126) ትንቢተ አሞጽ
1፥2 እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል የእረኞችም ማሰማርያዎች ያለቅሳሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።

(127) ትንቢተ አሞጽ
6፥1 በጽዮን ላሉ ዓለመኞች፥ በሰማርያም ተራራ ላይ ተዘልለው ለተቀመጡ፥ የእስራኤልም ቤት ወደ እነርሱ ለመጡባቸው ለአሕዛብ አለቆች ወዮላቸው!

(128) ትንቢተ ሚክያስ
1፥13 በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጅ የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።

(129) ትንቢተ ሚክያስ
3፥10 ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ።

(130) ትንቢተ ሚክያስ
3፥12 ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌምም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።

(131) ትንቢተ ሚክያስ
4፥2 ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው። ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።

(132) ትንቢተ ሚክያስ
4፥7 አንካሳይቱንም ለቅሬታ፥ ወደ ሩቅም የተጣለችውን ለብርቱ ሕዝብ አደርጋታለሁ ከዚያም ወዲያ እስከ ዘላለም ድረስ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።
8 አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።
9
10 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።
11 አሁንም። ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።
12
13 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።

(133) ትንቢተ ኢዩኤል
2፥1 የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና

(134) ትንቢተ ኢዩኤል
2፥15 በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥

(135) ትንቢተ ኢዩኤል
2፥23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።

(136) ትንቢተ ኢዩኤል
2፥32 እንዲህም ይሆናል የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ።

(137) ትንቢተ ኢዩኤል
3፥16 እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።

(138) ትንቢተ ኢዩኤል
3፥17 እኔም በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ የዚያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።

(139) ትንቢተ ኢዩኤል
3፥21 እኔም ንጹሕ ያላደረግሁትን ደማቸውን ንጹሕ አደርገዋለሁ፥ እግዚአብሔርም በጽዮን ያድራል።

(140) ትንቢተ አብድዩ
1፥17 ነገር ግን በጽዮን ተራራ ላይ የሚያመልጡ ይሆናሉ፥ እርሱም ቅዱስ ይሆናል የያዕቆብም ቤት ሰዎች ርስታቸውን ይወርሳሉ።

(141) ትንቢተ ኢዩኤል
1፥21 በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ አዳኞች ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ መንግሥቱም ለእግዚአብሔር ይሆናል።

(142) ትንቢተ ሶፎንያስ
3፥14 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ እስራኤል ሆይ፥ እልል በል የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ።
15
16 በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም። ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።


(143) ትንቢተ ዘካርያስ
1፥14 ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ። ስበክ እንዲህም በል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።

(144) ትንቢተ ዘካርያስ
1፥17 ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል።

(145) ትንቢተ ዘካርያስ
2፥7 አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ፥ ኰብልዪ።

(146) ትንቢተ ዘካርያስ
2፥10 የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ ደስም ይበልሽ፥ ይላል እግዚአብሔር፦

(147) ትንቢተ ዘካርያስ
8፥2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ጽዮን ታላቅ ቅንዓት ቀንቻለሁ፥ በታላቅም ቍጣ ስለ እርስዋ ቀንቻለሁ።

(148) ትንቢተ ዘካርያስ
8፥3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።

(149) ትንቢተ ዘካርያስ
9፥9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

(150) ትንቢተ ዘካርያስ
9፥13 ይሁዳን ለእኔ ገትሬአለሁ ቀስቱን በኤፍሬም ሞልቼአለሁ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ አንቺንም እንደ ኃያል ሰው ሰይፍ አደርግሻለሁ።
(151) የማቴዎስ ወንጌል
21፥4-5 ለጽዮን ልጅ። እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።

(152) የዮሐንስ ወንጌል
12፥14-15 አንቺ የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አግኝቶ በእርሱ ተቀመጠ።

(153) ወደ ሮሜ ሰዎች
9፥32-33 ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ።

(154) ወደ ሮሜ ሰዎች
11፥26 እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ። መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል።

(155) ወደ ዕብራውያን
12፥22 ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥

(156) 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
2፥6 በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።

(157) የዮሐንስ ራእይ
14፥1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
Oct 13, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Oct 15, 2012 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...