ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 8 December 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ፕሮቴስታንት መባሉን ነው የማትፈልጉት ማለት ነው?

"በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈ የሁሉም አምላክ፤ የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስም አምላክና አባት በሆነ በአንድ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል...."

ውድ ወንድሞቼ
በዚህ አገላለጻችሁ እግዚያብሄር አብ የሁሉም አምላክ የጌታ የ እየሱስ ክርስቶስም አምላክ ነው። ጌታችን መደሃንያለም ክርስቶስን ታድያ አምላክ አይደለም ማለት አይሆንምን? የለም እሱማ አምላክ ነው ካላችሁ ሁለት አማልክት አልኖሩንምን? በዚህ አይነት የ እምነት ስረአት የሚጝዋዙ የ እምነት ድርጅቶች እንዳሉም ይታወቃል። እናንተ በየትኛውም የ እምነት ጥላ ስር ያልተጠለልን denomination የሌለን ነን ማለታችሁ የየትኛውም ቤ/ክ ያልሆንን ነን ማለታችሁ እንዴት ይታመናል? በክርስቶስ አማላጅነት እና በመካከል ስለመሆኑ የሚሰብኩ የ እምነት ድርጅቶች እንዳሉ እየታወቀ እናንትም ያንኑ እያላችሁ ነገር ግን እኛ none denominational ነን ማለታችሁ ልባችሁ እያወቀ የ እምነት ድርጅታችሁን ይፋ አለማድረጋችሁ ስውር አላማ ይኖረው ይሆን? ምናልባትም እኔ ተሳስቼ ክሆነ እናንተን ከፕሮቴስታንት እምነት የሚለያችሁ ወይንም የማያሰኛችሁ ምንድን ይሆን? ምናልባትም በ እምነት ድርጅትነት መታውቅ ሰለማትፈልጉ ይሆን?

በፍጹም መማማር መንፈስ የተጠየቁ ጥያቄወች እንደሆኑ እንደምትረዱ እምነቴ ነው።

ሃይሉ
Sep 28, 2012 ስለ እኛ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ሰላም ሃይሉ

በጥሩ መንፈስ እንደምትጠይቅ ይገባናል፤ ስለዚህም ጌታ ይባርክህ።

በመሰረቱ በዚህ ዘመን በጣም ነገሮችን አወሳሰብነው እንጂ የእኛ እምነት በጣም ቀላል ነው። መጽሃፍ ቅዱስ የሚለውን ሁሉ እናምናለን፤ መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ነገር ሁሉ ደግሞ አንቀበልም፤ የማንም ዲንኖሚኔሽን ቢቀበለውም ባይቀበለውም። በቃ አለቀ! ለምሳሌ እስቲ ሐዋርያው ጳውሎስን ውስደው፤ የየትኛው ዲኖሚኔሽን ተከታይ ነው? ወይስ የትኛው ዲኖሚኔሽን ውስጥ ልንመድበው እንችላለን? የትም። ምክንያቱም እርሱ የሰበከውም የሞተው ስለ ሃጢአታችን በመስቀል ደሙን ላፈሰሰው ጌታ ኢየሱስ እንጂ፤ ለሌላ ለማንም አይደለም። ለምንድነው በዚህ ዘመን ኢየሱስ ብቻውን እምነትና መንገድ የማይሆነው? ለምንድነው ኢየሱስ በራሱ ብቻውን ያለ ዲኖሚኔሽን በቂ የማይሆነው? ያለ ዲኖሚኔሽንና ያለ ድርጅት አባልነት በቃ ኢየሱስ ብቻውን በቂ ላይሆን ነው? የተሰቀለውና ስለ እኛ መከራ የተቀበለው እርሱ አይደለም እንዴ? ለምንድነው በዚህ ዘመን ያለ ሃይማኖት ድርጅትና ዲኖሚኔሽን የጌታ ደቀመዛሙርት ሆነን እንደ እነ ጳውሎስ ጌታን መከተል የሚከብደን? ልብ እንበል ዲኖሚኔሽኖች ከመፈጠራቸውም በፊት የክርስቶስ ተከታዮችና ሃዋርያት ነበሩ። የእኛም እምነት እንዲሁ ቀላል ነው። የሆነ የሃይማኖት ድርጅት ወይም ዲኖሚኔሽን በግድ ተከታይ ወይም አባል መሆን አለብን ብለን አናምንም። የክርስቶስ ተከታይ ከሆንንና በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቅን፤ መጽሃፍ ቅዱስ የሚለውን ሁሉ ደግሞ ካመንን ያ ይበቃል።

ከጀርባችን ምንም አይነት ድርጅት ወይም ዲኖሚኔሽን የለም ስንል እውነት እየተናገርን እንጂ ሐሰት እየተናገርን አይደለም። በሐሰት ወይም በማታላለ ደግሞ እግዚአብሔር አይከብርም፤ ሥራውም አይሠራም። የሆነ ድርጅት ወይም ዲኖሚኔሽን ከጀርባችን ቢኖር ኖሮና እኛም የሆነ የሃይማኖት ድርጅት ለማስፋፋት ፍላጎት ቢኖረን ኖሮ እስከ አሁን በሆነ መንገድ ሰዎች ያንን ድርጅት እንዲቀላቀሉ በገፋፋን ወይም የተወሰነ ፍንጭ በሰጠን ነበር። እስከዛሬም ምንም ድርጅትና ዲኖሚኔሽንን አልደገፍንም፤ ወደፊትም የማንንም ዲኖሚኔሽን ለመወከል ፍላጎቱ የለንም። ኢየሱስ ብቻውን በቂ ነው ብለን ስለምናምን። ሰዎችንም የትኛውንም ዲኖሚኔሽን እንዲከተሉ አልገፋፋንም ወደፊትም አናደርገውም። ሁሌም እያልን ያለነው እውነትና መንገድ የተሰቀለው ክርስቶስ ነው፤ ሰዎችም ይሄንን ክርስቶስ እንዲከተሉ እንጂ የሃይማኖት ተከታዮች እንዲሆኑ አይደለም ፍልጎታችን።

ስለ አብ አንድ አምላክ መሆን ያነሳኸው ነገር፤ ያንን ያልነው እኛ ሳንሆን አዲስ ኪዳን ነው። የአዲስ ኪዳን ጥቅስ ነው ያስቀመጥነው። እንዲሁም ደግሞ ኢየሱስም አምላክ መሆኑን የሚናገረውም ይሄው አዲስ ኪዳን ነው። እኛ ሁለቱንም እናምናለን። ሁለቱንም መጽሃፍ ቅዱስ ስለሚናገር። ገና ለገና ሁለት አምላክ ማለት ሊሆን ይችላል ብለን፤ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈውን አንዱን እውነት ለማፈንና አንደኛውን ብቻ ለማጉላት ስልጣኑ የለንም። የተጻፈው ሁለቱም ነው፤ ሁለቱንም እንቀበላለን። ለማጣጣምም ይሁን ለመቀየር ወይም አንዱን ለማዳፈን አንሞክርም። ይሄም ነው አንዱ የማንንም ዲኖሚኔሽን እንዳንከተል የሚያደርገን። ነጻ ሆነን መጻሃፍ ቅዱስ የሚለውን ሁሉ የማይስማማንን ጭምር ሳናዳፍን፤ ሁሉንም ለመቀበል ስለሚያስችለን ነው። ያለበለዚያ ከቃሉ ይልቅ በዲኖሚኔሽኖች የተጻፉትን የእምነት መግለጫዎች ልናስበልጥ ነው። ያንን ደግሞ ልናደርግ አንወድም።

አንዱም የዲኖሚኔሽን ችግር፤ ከቃሉ ውጪ የሆኑ በታሪክና በባህል የተወሰዱ ብዙ ብዙ ልምዶች፣ አሰራሮችና እምነቶችን ያቀፈ መሆኑ ነው። እኛ ደግሞ ከቃሉ ውጪ የሆነ ነገር የማንም ዲኖሚኔሽን ቢሆን ለመቀበል ወይም ለመደገፍ በፍጹም ፍላጎቱ የለንም። የምንደግፈውም ይሁን የምንከተለው፤ ስለ ሃጢአታችን የተሰቀለውን ክርስቶስን ነው። እርሱ ያለ ዲኖሚኔሽን በቂ ነውና። የጥንት ሃዋርያትም ያመኑትና የሰበኩት ይሄንኑ ነው።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1
22 መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥
23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
24 ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።

የጌታ ጸጋ ይብዛልህ!
Sep 29, 2012 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
Sep 29, 2012 iyesus ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...