ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 25 October 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ከ ፕሮተስታንት ክርስትና በምን ትለያላችሁ ታድያ?

አሜን ውድ ወንድሞቼ!

የምትሉትን እየተረዳሁ በድጋሚ የምጠይቃችሁ እናንተም ያልመለሳችሁት ጥያቄ "እናንተን ከፕሮቴስታንት እምነት የሚለያችሁ ወይንም የማያሰኛችሁ ምንድን ይሆን?"
ነበር።
አስቀድሜ ለመልሳችሁ አመስግናችሃለሁ
ሃይሉ
Oct 1, 2012 ስለ እኛ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ሰላም

እኛ የአማኞች የአንድነት መሰረት ዲኖሚኔሽን ሳይሆን ክርስቶስ ነው ብለን ነው የምናምነው። አላማችንም ዲኖሚኔሽን ስላነሰ ሌላ ዲኖሚኔሽን ለመፍጠር አይደለም። ፕሮቴስታንት ይሁን ኦርቶዶክስ ወይም ካቶሊክ ወይም ሌላ፤ የክርስቶስ የሆነ ሁሉ በጌታ የእኛ ወንድም እና የአንድ እምነት ተካፋይ ነው ብለን ነው የምናምነው፡፡ ስለዚህ አጥራችን ፕሮቴስታንት ወይም ኦርቶዶክስ ወዘተ የሚል ሳይሆን ክርስቶስ ነው። እንግዲህ እኛን ከፕሮቴስታንቶች የሚለየን ትልቁ ነገር፤ በዲኖሚኔሽን አለማመናችን ነው። ራሳችንን የክርስቶስ ብቻ እንደሆንንና የክርስቶስ የሆነም ሁሉ ፕሮቴስታንትም ይሁን ኦርቶዶክስ ወይም ሌላ በጌታ ወንድማችን እንደሆነ እናስባለን እንጂ፤ ራሳችንን የአንድ ዲኖሚኔሽን ወይም ሃይማኖት ተከታይ አድርገን አለማየታችን ነው እንግዲህ ምናልባት አንዱ የሚለየን ነገር።

ደጋግመን እንደገለጽነው፤ ወሳኝና ዋና የእምነት ጥያቄ ብለንም የምንወሰደው መዳን ወይም ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ በክርስቶስ ብቻ ነው የሚለው ጉዳይ ነው። በዚህም በወሳኙ ጥያቄ ከፕሮቴስታንቶች ጋር ምንም የሚለየን ነገር የለም። ስለዚህም በክርስቶስ የሆኑት ፕሮቴስታንቶች ሁሉ በጌታ ወንድሞቻችን ናቸው። የእምነት ዋና ያልሆኑ ነገሮችን በተመለከተ የተለያየ አመለካከት ሊኖረን ይችላል። ለምሳሌ አገልግሎትን በተመለከተ ወይም የቤተክርስቲያንን አሠራርና አስተዳደርን በተመለከተ ወዘተ። ይሄ አይነቱ ልዩነት ግን በፕሮቴስታንቶችም መካከል ያለና እንደ ዋና ነገር ተቆጥሮ የመለያያ ምክንያት የሚሆን አይደለም። የክርስቶስ የሆነ ሁሉ፤ በመንፈስ አንድ ነው፤ የክርስቶስ እስከሆንን ድረስ ፕሮቴስታንት ብንሆን ወይም ካቶሊክ ወይም ኦርቶዶክስ ሁላችን የአንድ አባት ልጆችና ቤተሰቦች ነን።

ለዚህም ነው ይህ ድረገጽ አንድን ዲኖሚኔሽን የሚያገለግልና ለአንድ ዲኖሚኔሽን ጥብቅና የሚቆም ሳይሆን ሰዎች ሁሉ ያለ ዲኖሚኔሽን አጥር እየተማማሩና ሃሳብ እየተለዋወጡ ክርስቶስን ወደ ማወቅ እንዲመጡ ለማድረግ ነው። ሰው የጌታ ከመሆን በስተቀር ሌላ እርግጠኛ የመዳኛ ዋስትና የለውም። ፕሮቴስታንት መሆን ወይም ኦርቶዶክስ መሆን ወዘተ በራሱ የመዳን ዋስታ አይደለም። የመዳን ዋስትና የሚገኘው በማይናወጠው ዓለት በክርስቶስ በመሆን ብቻ ነው።
Oct 3, 2012 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
ወንድሞቼ

ያላችሁትን ሁሉ በጥሞና ለመረዳት ሞክሬያልሁ በመሰረቱ "ክርስቲያን" ያሰኘንን የጋራ ስያሜያችንን ለእኔ ብቻ ይገባል እነሱ ግን.... ሳንል ሁላችንም የክርስቶስ መሆናችንን በማመን እሱ የተቃወመውን ጥላቻን አርቀን እሱ አድርጎ ያሳየንን የ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ፍቅርን አስተውለን ቢያንስ በፍቅሩ ዙርያ የጋራ ክርስትናችንም(የክርስቶስ መሆናችን) አከባብሮን ሊያስኖረን ይገባል እላልሁ።
ያላችሁት እውነት ነው ሰው በክርስቶስ ሲያምን አዲስፍጥረት ይሆናል ከዚያም ክርስቲያን ተብሎ ሊጠራ ግድ ነው ደግሞም የክርስቶስ ወዳጆች ልጆች ወንድሞችም ነን ደግሞም ግንዱ ክርስቶስ ቅርንጫፎች እኛ በርሱ የምናምን ስለዚህ መልሳችሁ ትክክል ነው
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...