ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 25 October 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እናንተ ስትሞቱ ከየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትቀበሩት?

Oct 31, 2012 ስለ እኛ ስም-አልባ የተጠየቀ
Oct 31, 2012 ታርሟል

2 መልሶች

0 ድምጾች
እነ አብርሃም የት ተቀበሩ
Oct 31, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ሰላም ስለ ጥያቄህ እናመሰግናለን።

በቅድሚያ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል በመጽሃፍ ቅዱስ አንድ ጊዜም ቢሆን በእጅ ለተሰራ ግንብ ቤት ወይም ቤት መጠሪያነት ሲውል አናይም። አንድም ቦታ ቤተ ክርስቲያን የሚባል ቤት በአዲስ ኪዳን የለም። ቤተ ክርስቲያን ብሎ በአዲስ ኪዳን የሚጠራው ሁል ጊዜም በክርስቶስ የሚያምኑ የአማኞችን ህብረት ነው። አማኞች ናቸው ቤተ ክርስቲያን ተብለው የሚጠሩት።

በሁለተኛ ደረጃ የክርስቶስ ተከታዮች በመጽሃፍ ቅዱስ አንድም ቦታ የመሰብሰቢያ ወይም የማምለኪያ የተለየ ቤት ሲሰሩና ሲመርቁ ወይም እዚያ ሲቀበሩ አንመለከትም። ቤተ ክርስቲያን የሚባል ቤት መስራት የተጀመረው ክክርስቶስ ልደት በኋላ ከ250 ዓመታት በኋላ ነው። ስለዚህ መጽሃፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የሚባል ቤት መስራትና እዚያ መቀበር የሚባል ነገር አያውቀውም።

አዲስ ኪዳን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ከሞትን በኋላ ይልቁንም ለዘላለሙ የት እንደምንኖር እንጂ ስጋችን የት እንደሚቀበር አይደለም። የትም ሊቀበር ይችላል፤ ይሄ ምንም ችግር የለውም፤ እኛ ግን ከጌታ ጋር ሁል ጊዜም ህያው ሆነን እንኖራለን። ክርስቶስንም የተከተሉ ቅዱሳን ለእምነታቸው በሰይፍ እየተገደሉ ስጋቸው የትም ሲወረወር ነው የኖረው፤ እነርሱ ግን በጌታ ዘንድ ህያው ናቸው። ለዘላለም ህያው ሆኖ ከጌታ ጋር መኖር እንጂ ለሞተ ሬሳ የተሸለመ ሃውልት መስራት አይደለም ዋናው ቁም ነገሩ።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
11፥25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤

የጌታ ጸጋ ይብዛልህ።
Oct 31, 2012 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...