ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በኢዮብ ምእራፍ 2 ላይ የአምላክ ልጆች የሚለው እነማንን ነው?፡ ግርማ ከሎነደን

Dec 3, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

5 መልሶች

+1 ድምጽ
ኦሪት ዘዳግም 14
1-2 እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3
1 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።
2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።

መላእክት የእግዚአብሔር ልጅ ለመባልም ሆነ በቀኙ ለመቀመጥ አልታደሉም።

ወደ ዕብራውያን 1
5 ከመላእክትስ "አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ"፥ ደግሞም "እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል" ያለው ከቶ ለማን ነው? (ለማንም አላለም።)
ወደ ዕብራውያን 1
13 ነገር ግን ከመላእክት "ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ከቶ ለማን ብሎአል?
14 ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው (ስለ እኛ) ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?

እኛ ግን ከክርስቶስ ጋር ይህ ክብር ተሰጥቶናል።

የዮሐንስ ወንጌል 17 (ታላቁ ሊቀ ካህናት እና ብቸኛው አማላጃችን ሲናገር)
22-23 እኛም (አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ) አንድ እንደ ሆንን፣ አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ፣ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ (እኔን) በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።
24 አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፣ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
25 ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ፤ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤
26 እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን፣ እኔም በእነርሱ (እንድሆን)፤ ስምህን አስታወቅኋቸው፤ አስታውቃቸውማለሁ።


ከክርስቶስ ስራ የተነሳ በአብ ተወድደናል። በቀኙ ተቀምጠናል።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2
5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፤
6-7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን

መዝሙረ ዳዊት
29፥1 የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።
2 የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ። (ጻድቃን /እግዚአብሔርን የሚከተሉ ሰዎች/ የእግዚአብሐር ልጆች ይባላሉ።)

እንዲሁም ደግሞ ሃጢአን /እንግዳ አምላክን (ጣኦትን) የሚከተሉ ሰዎች/ "የእንግዳ አምላክ ልጆች" ይባላሉ። ደግሞም "የሰው ልጆች" ተብለዋል።

ኦሪት ዘፍጥረት 6፡
1 እንዲህም ሆነ፤ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው።
2 የእግዚአብሔር ልጆችም (ጻድቃን) የሰውን ሴቶች ልጆች (ሃጢአንን) መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
3 እግዚአብሔርም፦ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ። (ጻድቃን ሃጢአንን ስላገቡ አዘነ)
4 በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፤ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ። (... ነገር ግን ሃጢአን ነበሩና)
5 እግዚአብሔርም የሰው ክፉት (የመላእክት አይልም) በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።
6 እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።
7 እግዚአብሔርም፦ የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና አለ። (መላው ታሪክ የሚመለከተው ሰዎችን ነው መላእክትን አይደለም። )

እግዚአብሔርን በሚገባ ያልተከተሉ ሰዎችም "ሰዎች ብቻ" ተብለዋል።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡
4 አንዱ "እኔ የጳውሎስ ነኝ"፥ ሁለተኛውም "እኔ የአጵሎስ ነኝ" ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?

ትንቢተ ሚልክያስ 2
10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን (የአምላክ ልጅን) ስለ ምን አታለልን?
11 እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል። (ጻድቃን ሰዎች ሃጢአንን ስላገቡ እግዚአብሔር አዘነ፤ ስለዚህ...)
12 ይህን ከሚያደርግ ሰው፥ እግዚአብሔር የሚጠራውንና የሚመልሰውን ለሠራዊትም ጌታ ለእግዚአብሔር ቍርባን የሚያቀርበውን ከያዕቆብ ድንኳን ያጠፋል።

ትንቢተ ሆሴዕ 2
1 የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል። እንዲህም ይሆናል፤ (ጣኦትን በተከተሉ ጊዜ) እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ (ወደ እግዚአብሔር በተመለሱ ጊዜ) የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።

አያችሁ? የእንግዳ አምላክ ልጆች አሉ። የህያው እግዚአብሔር ልጆችም አሉ። እነዚህ ሁለቱም ወገኖች ሰዎች ናቸው እንጂ መላእክት አይደሉም።
እናም በመጨረሻ በኢዮብ ምእራፍ 2 ላይ የአምላክ ልጆች የሚለው ሰዎችን ነው። እግዚአብሔር በሁሉ ስፍራ ስለሚገኝ ወይም ስፍራዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ስለሆኑ ሰዎች መስዋእት ሲያቀርቡ፣ ሲጸልዩ፣ ሲሰግዱ "በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ" ይባላል።
Dec 5, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Dec 6, 2012 ታርሟል
የመለሳችሁት መለስ አልተስማማኝም ምክንይቱም ኢዮብ መዕራፍ 2 የሚያወራው ስለመላዕክት ነው : :
"የመለሳችሁት መለስ አልተስማማኝም
ምክንይቱም ኢዮብ መዕራፍ 2 የሚያወራው ስለመላዕክት ነው : :"
ያሉ ወንድሜ/እህቴ ሆይ፣ ምን ማለትዎ ነው?

"የመለሳችሁት መለስ አልተስማማኝም ፦"
ዋናው ነገር እኮ ለእርስዎ ተስማማ ወይስ አልተስማማ የሚለው አይደለም። ነገሩ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው ትምህርት ነው የሚል መሆን አለበት ዋናው ጥያቄ። የአምላክ ቃል ከሆነ ባይስማማዎትም መዋጥ አለብዎት። እኔ የጻፍኩት በሙሉ የአምላክን ቃል/ጥቅሶችን ብቻ/ እንጂ የራሴን አሳብ አይደለም። ስለዚህ እርስዎ የአምላክን ቃል ለእኔ "አልተስማማኝም" እና የሚስማማኝ እንዲህ ቢባል ነው እያሉ ነውና በጣም ያሳዝናል።

ያለምንም ማስረጃ እና ማጠናከሪያ ጥቅስ የራስዎን ትምህርት " ኢዮብ መዕራፍ 2 የሚያወራው ስለመላዕክት ነው " ብለዋል።
በርግጥ ሰው ነኝና ተሳስቼ ወይም ጥቅሶችን ያለቦታቸው ጠቅሼ ከሆነ ለመታረም ዝግጁ ነኝ። ስለዚህ ጥቅሶችን በዝርዝር ጽፈው ማስረዳት ነበረብዎት። አለዚያ ግን ሌሎች አንባቢዎችን ላለማደናገር ዝም ብለው አርፈው ቢቀመጡ ይሻል ነበር። እንደ ገና ወደ መልሴ ተመልሰው በተለይ ደመቅ ባሉ ፊደሎች የተጻፉትን ቃላት ልብ ብለው እያስተዋሉ እንዲያነብቡ እጠይቅዎታለሁ። እርስዎም ቢሆኑ በመሲሁ ካመኑ፣ ቢያውቁም ባያውቁም የአምላክ ልጅ ነዎት። መላእክት ግን በመላው መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የአምላክ ልጆች ከቶ አልተባሉም፤ በቀኙም ለመቀመጥ አልታደሉም። የጌታ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።
+1 ድምጽ
የጌታ ጸጋ ለሁላችን ይሁን፤ አሜን።

ወደ ዕብራውያን 12
5-6 እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።
7 ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
8 ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና፤ ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?

ስጋችንን የወለዱት ሰዎች "የሥጋችን አባቶች" ተብለዋል። እነርሱ ስጋችንን (ማደሪያችንን) ወለዱ እንጂ መንፈሳችንን (ዋናውን ማንነታችንን) አልወለዱም ወይም አላስገኙም። የእነርሱ አባትነት በሞት ጊዜ ያበቃል።

ሌላ ግን የዘላለም አባት አለን (ትንቢተ ኢሳይያስ 9፡6)። እርሱም መንፈሳችንን (ዋናውን ማንነታችንን) የወለደው እግዚአብሔር ነው። ደግሞም መንፈሳችን በሃጢአት ምክንያት በሞተ ጊዜ በክርስቶስ ቤዛነት ዳግመኛ ልደትን ሰጠን። እግዚአብሔር መንፈሳችንን ስለ ወለደ "የመናፍስት አባት" ይባላል። መንፈሳችን የተወለደው ከእግዚአብሔር (ከመንፈስ ቅዱስ) ነው እንጂ እንደ ሰው ልማድ ከስጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አይደለም።

የዮሐንስ ወንጌል 1
12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

የዮሐንስ ወንጌል 3
6 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
7 ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ።
8 ነፋስ ወደ ሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ፣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።

የአዳም መንፈስ የተገኘው ከእግዚአብሔር ነበር (ኦሪት ዘፍጥረት 2፡7)። ስለዚህ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ እንደነበረ የሉቃስ ወንጌል 3፡38 ላይ ተጽፎአል። እንዲሁም በመጽሐፈ ኢዮብ ላይ።

መጽሐፈ ኢዮብ
38፥6-7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥
የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ (ለምሳሌ እነ አዳም፣ ሄዋን...) እልል ሲሉ፥ (የምድር) መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር?
የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ /አቁሞ የነበረ/ ማን ነው? (እግዚአብሔር ነው።)

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6
16 ... እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
17-18 ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል። ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ፤ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።

የማቴዎስ ወንጌል
5፥9 የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።

የሉቃስ ወንጌል
20፥36 (አማኞች ከትንሣኤ በኋላ) ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።

የዮሐንስ ወንጌል
11፥52 ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።

ወደ ሮሜ ሰዎች
8፥14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
8፥16 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ (መንፈስ ቅዱስ) ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
8፥19 የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።

ወደ ሮሜ ሰዎች
9፥6 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም።
7 ነገር ግን። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ።
8 ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው።

የእግዚአብሔር ልጅነትን ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው። የእግዚአብሔር ልጅነትን ማግኘት ታላቅ መታደል ነው።

ወደ ገላትያ ሰዎች
3፥26 በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና።
የዮሐንስ ወንጌል 1
12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
2፥14-15 በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ፣ የዋሆችም፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ፣ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ።

የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን እንቢ የሚሉ ሁሉ "የዲያብሎስ ልጆች" ናቸው።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
3፥10 የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግ እና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
5፥2 እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች (አማኞችን) እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።

እናም ያለ ጥርጥር በኢዮብ ምእራፍ 2 ላይ የአምላክ ልጆች የሚለው ሰዎችን ነው።
Dec 6, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Dec 6, 2012 ታርሟል
0 ድምጾች
እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ፤ ሰዎችን ግን ወለደና አሳደገ።

ትንቢተ ኢሳይያስ 1
2 እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፥ ምድርም አድምጪ ልጆችን ወለድሁ አሳደግሁም፥ እነርሱም አመጹብኝ።
3 በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም አላስተዋለም።

ወገኖች ሆይ እኛስ እንወቅ እናስተውል።
Dec 13, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
+1 ድምጽ
በመላው መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ መላዕክት “የእግዚአብሄር ልጆች” አልተባሉም፡፡ ሰዎች ግን “የእግዚአብሄር ልጆች” ተብለዋል፡፡

ዘዳ 32:5 ነገር ግን እስራኤል ባመፁ ጊዜ ለእግዚአብሄር “ልጆች አይደሉም” ተባሉ፡፡
ሮሜ 9:8
ዘዳ 32:6 እግዚአብሄር ለእስራኤል “የገዛ አባቱ” ነው ፡፡
ሮሜ 9:4
ዘዳ 32:8 የአዳም ልጆች ... እንደ እስራኤል ልጆች … የእግዚአብሄር ዕድል ፈንታ...( ናቸው፡፡)
ዘዳ 32:18 የወለደህን አምላክ … ያሳደገህን እግዚአብሄርን …
ኢሳ 1:2
ዘዳ 32:19 ወንዶች እና ሴቶች (የእግዚአብሄር) ልጆች … (ሰዎችን ያመለክታል)፡፡
ዘዳ 32:20 ያልታመኑም (የእግዚአብሄር) ልጆች… ዓመፀኞች ልጆች…
ኢሳ 30:1

ሆሴዕ 2:1 የእስራኤል ልጆች … የሕያው አምላክ ልጆች… የይሁዳ ልጆች እና የእስራኤል ልጆች… የሕያው እግዚአብሄር ልጆች ናቸው(ሮሜ 9:26)፡፡

የእስራኤል ልጆች እናት ራስዋ እስራኤል ስትሆን እርስዋም የያህዌ ሚስት ተብላለች፡፡ ባመፀች እና በያህዌ ላይ ባመነዘረች ጊዜ ግን እንዲህ ተባለች:- ”እናታችሁ ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባሏ አይደለሁምና፡፡” ሆሴዕ 2፡4 ኢሳ 50፡1

እስራኤል ከሌላ አማልክት ጋር ተባብራ የወለደቻቸው ልጆችም የእግዚአብሄር ልጆች ሳይሆኑ “የእንግዳ አምላክ ልጆች” ወይም “የግልሙትናዋ ልጆች” ተብለዋል፡፡ ሆሴዕ 2:6፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሄርን “የቀደመው ባሌ” ብላ በንስሃ ወደ እግዚአብሄር ትመለሳለች፡፡ ሆሴዕ 2፡9
የእስራኤል ባሏ ያህዌ ሲሆን እንግዳ አማልክት ግን "ውሽሞችዋ" ናቸው፡፡ ሆሴዕ 2 ፡ 12 ሆሴዕ 2፡13 ኤር 3፡1 ኢሳ 54:5-7

ሮሜ 9፡4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና (የእግዚአብሄር) ልጅነት እና ክብር ፣ ኪዳንም… ለእነርሱ ናቸውና፡፡
2ሳሙ 7፡14 እኔም አባት እሆነዋለሁ፡፡ እርሱም “ልጅ” ይሆነኛል… በሰው ልጆች… (ሰዎችን ያመለክታል)፡፡

ዘዳ 32:11 ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ (ንስር ልጆቹን እንደሚሸከም እግዚአብሄር ልጆቹን) በክንፎቹ አዘላቸው፡፡ (ማቴ 23:37) ልጆችሽን (ልጆቼን ማለቱም ነው)
ዘዳ 8:5 ምሳ 3:12 ዕብ 12:5-11 1ዜና 22:10

ሰሎሞን የእግዚአብሄር ልጅ ነበር፡፡ ምሣ 12:24 1ዜና 17:13
ዳዊትም ከእግዚአብሄር የተወለደ (ዘዳ 32:18) የእግዚአብሄር ልጅ (መዝ 2:7) ሲሆን መሲሁም (ክርስቶስ) እንዲሁ ነው፡፡
መዝ (89):26- 27

ኤር 3:19 አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፡፡ ሮሜ 9:4
ኤር 3:22 ከዳተኛ ልጆች ሆይ … (ዘዳ 32:20)
ኢሳ 63:16 አብርሃም ባያውቀን ያዕቆብ ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፡፡ አቤቱ አንተ አባታችን ነህ፡፡ (ሰዎች /አማኞች/ የእግዚአብሄር ልጆች ነበሩ ማለት ነው )፡፡

ኢሳ 64፡ 8 አሁን ግን አቤቱ አንተ አባታችን ነህ፡፡
ሚል 2:10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? ሚል 1:6

እግዚአብሄርን የሚከተሉት ሰዎች “የሕያው አምላክ ልጆች” እንደተባሉ ሁሉ እንግዳ አምላክን (ጣኦትን) የሚከተሉት ሰዎችም “የእንግዳ አምላክ ልጆች” ተብለዋል፡፡ ሚል 2:11 መዝ (89):6

በሚል 2:11 ላይ “የእንግዳ አምላክ ልጅ” የተባለችው ሴት ስትሆን እርስዋም ሰው ናት እንጂ ርኩስ መንፈስ አይደለችም፡፡ መላእክት በሰው ውስጥ በመግባት “possess” አድርገው ሴትን የሚገናኙ ከሆነ ርኩሳን መላዕክት ናቸውና “የእግዚአብሄር ልጆች” ከቶ አይባሉም፡፡

ነገር ግን በዘፍ 6:2 ላይ “መልካሞቹን የሰውን ሴቶች ልጆች” ምርጥ ምርጦቹን ሴቶች ያገቡት ቅዱሳን መላዕክት ወይም ርኩሳን መላዕክት ሳይሆኑ ያህዌን (እግዚአብሄርን) የሚከተሉ እንደ እኛ ያሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄር አዘነ (ቅዱሳን ሰዎች ኃጢአተኞችን ስላገቡ ማለት ነው)፡፡ እናም እንዲህ አለ:- “መንፈሴ በሰዎች ላይ ለዘላለም አይኖርም”።

“ስማቸው የታወቀ ሃያላን” እና ረጃጅም ልጆች (ኔፊሊም) የተወለዱበት ምክንያት ምንድር ነው? ከመልካሞች ሴቶች፣ ከምርጥ ምርጦቹ፣ ምናልባትም ከረጃጅም ሴቶች ስለተወለዱ ስለዚህ ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ህዝቦች “የእግዚአብሄር ልጆች” ሳይሆኑ እግዚአብሄርን የማይከተሉ “የሰው ልጆች” ነበሩ፡፡ 1ቆሮ 3:4 ስለዚህ እግዚአብሄር አለ፡- የፈጠርሁትን ሰው አጠፋለሁ፡፡ ዘፍ 6፡7

መላዕክት ፈጽሞ “የእግዚአብሄር ልጅ” አልተባሉም፡፡ ክርስቶስም በኋለኛው ዘመን ሰው ስለሆነ የእግዚአብሄር ልጅ ተባለ እንጂ መልአክ ቢሆን ኖሮ ከቶ የእግዚአብሄር ልጅ አይባልም ነበር፡፡ ዕብ 2፡17 ዮሐ 1፡50 ከመላዕክትስ፡- አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ (ያለው ከቶ ለማን ነው?) ደግሞም፡- እኔ አባት እሆነዋለሁ፣ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው? ዕብ 1፡5

እንግዳ አምላክን የሚከተሉ ወንዶች እና ሴቶች የእንግዳ አምላክ ልጆች ይባላሉ፡፡ ሚል 2፡11
እንዲሁም ህያው አምላክን የሚከተሉ ወንዶችና ሴቶች የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ፡፡ ሆሴዕ 2፡1 ሮሜ 9፡26 ዮሐ 1፡12
አዳምም የእግዚአብሄር ልጅ ነበር፡፡ ሉቃ 3፡38

መላዕክት የእግዚአብሄርን ባህርይ አልተካፈሉምና ልጅ አልተባሉም፡፡ ሰው ግን ይህን አግኝቷል፡፡ ራዕ 21፡7 ዕብ 12፡7

ለእናንተም አባት እሆናለሁ፡፡ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፡፡ ዘፀ 4፡22 2ቆሮ 6፡18 ኢሳ 43፡6-7 ሮሜ 8፡14 ኤር 31፡9፣20 ሆሴዕ 11፡1 የእግዚአብሄር ልጅ የተባሉት እስራኤላውያን ናቸው፡፡ በርግጥ ቃሉ በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ ነውና መሲሁንም ያመለክታል፡፡

ሙሴም ይህን በሚገባ ተረድቶ ነበር:: ዘፀ 4፡22 ዘዳ 14፡1::
በዘፀ 12፡12-13 ላይ የሚታየው የሰው ልጆች እና የእግዚአብሄር ልጆች ዕጣ ፈንታ ነበር፡፡ ዘሁ 8፡17
ዘማሪው አሳፍ የእስራኤል ልጆችን ትውልድ "የእግዚአብሔር ልጆች ትውልድ" ብሎ ተናግሯል። (መዝሙር 73፡15)

ኢዮ26፡7 ኢዮ1፡6 ፣ 2፡1 ፣ 38፡7 ለመሆኑ መላዕክት ከየት መጥተው ነው? ከዕለት ኑሮአቸው መጥተው ነው ከዕለታት አንድ ቀን በአምላክ ፊት የቆሙት? አይደለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡ መላእክትማ ከዕለታት አንድ ቀን ሳይሆን ሁልጊዜም ሳያርፉ ቀን እና ሌሊት በአምላክ ፊት ይቆማሉ ያመሰግኑታል። እነዚህ ግን ሰዎች ሲሆኑ እነርሱም እግዚአብሄርን የሚከተሉ እና በስሙ የተጠሩ የአምላክ ልጆች የነበሩ ናቸው - ለምሳሌ የራሱ የኢዮብ ልጆች፡፡ በአምላክ ፊት መቆም ማለት መፀለይ፣ ማምለክ… ወዘተ ነው፡፡

ሰይጣንም በእነርሱ (በሰዎች) መካከል መጣ፡፡ ማለት በመላዕክት መካከል መጣ ማለት አይደለም፡፡ አብን አየ ማለትም አይደለም፡፡ በእግዚአብሄር መገኘት ውስጥ (በዙፋኑ ፊት) ሰይጣን ይቆማል ማለት ከቶ የማይቻል ነው፡፡ እንኳን ሰይጣን፣ ቅዱሳን መላእክትም እኮ ሊቀርቡት በማይችሉበት ታላቅ ብርሃን ውስጥ እግዚአብሔር (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) ብቻውን ይኖራል። 1ጢሞ 6፡16። ቅዱሳን መላእክት ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያዩት ኢየሱስ ክርስቶስ በበቴልሄም ከተማ በተወለደ ጊዜ ነው። የሉቃስ ወንጌል 2፡11-15፡፡ 1ጢሞ 3፡16።

ነገር ግን ይህ ሰይጣን በሰዎች መካከል (በአምላክ ልጆች መካከል) ተገኘ- ምናልባትም በራሱ ሰው አድሮ፡፡ 1ዜና 21፡1 በስብሰባቸው ውስጥ እግዚአብሄርም ተገኝቷል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር የማይገኝበት ምንም ስፍራ የለምና፡፡ ይልቁንም ሰማይ እና ምድር ሁሉ በትልቁ በእግዚአብሄር ፊት ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁላችን አሁን እንኳ በእርሱ ፊት ነን፡፡

በርግጥ መላዕክትም ቢሆኑ በእግዚአብሄር ፊት ይቆማሉ፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ስፍራዎች በእርሱ አይኖች ፊት ስለሆኑ፣ መላዕክት የሚሰግዱበት ማንኛውም ስፍራ በትልቁ በእግዚአብሄር አይኖች ፊት ነው ማለት ነው፡፡ እንጂ ፊቱ ቆመው አብን ያዩታል ማለት አይደለም። ዮሓ 6፡46

ነገር ግን ኢዮ 1፡6 እና 2፡1 ላይ የተጠቀሱት የአምላክ ልጆች በእርግጠኝነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ለመፀለይ፣ መስዋዕት ለማቅረብ ቆሙ፡፡

የዕብራውያን መልዕክት ፀሐፊ ከእኛ የበለጠ እጅግ ጥልቅ የሆነ የብሉይ ኪዳን ዕውቀት እንዳለው ይታመናል፡፡ እናም እርሱ በብሉይ ኪዳን "የአምላክ ልጆች" የተባለውን ቃል በተመለከተ ምን እንዳለ ዕብ 1፡5 ፣ 14 ን ያንብቡ።

ኢዮ 38፡7 መላዕክት ከቶ እልልታን አያውቁም፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች ግን (እነ አዳም) ምድር ከተፈጠረች በኋላ በእርሷ ቆመው እልል ሲሉ የምድር መሠረቶች በምን ላይ ተተክለው ነበር ይላል ኢዮ 38፡7፡፡

መላዕክት በሞት ከቁጥር መጉደልን አያውቁም። ማግባትን፣ መውለድን ወይም በቁጥር መጨመርን አያውቁም፤ ዘር የሚተካ ዘርም የላቸውም፤ እርግጡን የሚያውቅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን። የማቴዎስ ወንጌል 22፡30። የሉቃስ ወንጌል 20፡35።
የእግዚአብሄር ልጆች ግን በዘፍጥረት 6፡2፣4 እንደ ምናየው ያገባሉ ይወልዳሉ- በሞት እስከሚለዩ ድረስ ወይም የትንሳኤ አካል እስከ ሚለብሱበት ቀን ድረስ ብቻ ነው የሚዋለዱት። የሉቃስ ወንጌል 20፡36።


እግዚአብሄር ሲፈጥር ማንም አማካሪ ከጎኑ አልነበረም፡፡ ኤር 23፡18 ኢሳ 44፡24 እና ኢዮ 38፡7 ስለ መላእክት ያወራል ማለት አንችልም።
የኢዮብ መጽሐፍ ተምሳሌታዊ የሆነ የቅኔ መጽሐፍ ነው (ለምሳሌ ኢዮ 38፡8)፡፡ “አጥቢያ ኮከቦች” ማለት “የመጀመሪያዎቹ ከዋክብት በተፈጠሩ ጊዜ” ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ኢሳ 44፡23 መዝ 148፡3 ዘፍ 1፡16፡፡

ደግሞም ኦርጂናሌው የዕብራይስጡ መጽሐፍ በኢዮብ 38፡7 ላይ “የእግዚአብሄር ልጆች” ስለ ሚል ዛሬ ይህን ቃል “መላዕክት” ብለው የተረጎሙ መጻህፍት ተቀባይነት ሊኖራቸው አይገባም፡፡ የጌታ ፀጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን። የቅጂ መብት ጌ/ጌ/አ/አ 2000
Dec 18, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Dec 18, 2012 ታርሟል
+1 ድምጽ
ብሉይ ኪዳን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተገልጦአል፤ ተብራርቶአል ወይም ይፋ ሆኗል። ታዲያ በመላው አዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ሰዎች ናቸው እንጂ መላእክት አይደሉም።

የማቴዎስ ወንጌል
5፥9 የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።

የሉቃስ ወንጌል
20፥36 (አማኞች ከትንሳኤ በኋላ) ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።

የዮሐንስ ወንጌል
1፥12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
11፥52 ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።

ወደ ሮሜ ሰዎች
8፥14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
8፥16 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
8፥19 የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
9፥6 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥
9፥8 ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው።

ወደ ገላትያ ሰዎች
3፥26 በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
2፥14-15 በመጥፎ እና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ፣ የዋሆችም፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
3፥1 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
3፥2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
5፥2 እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።

ክርስቶስን የማያምኑ ሰዎችም ቢሆኑ መነሻ ምንጫቸው፣ እውነተኛ ወላጃቸው እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ነበር። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች አባታቸውን የከዱ፣ የተው፣ አመጸኛ ልጆች፣ የማይታዘዙ ልጆች ተብለዋል። ይህ አመጻቸውም የዲያብሎስ ልጆች እንዲባሉ አድርጓል። እንጂ ዲያብሎስ የወለዳቸው ወይም የፈጠራቸው ሰዎች የሉም፤ አንድ ስንኳ። አስተዋላችሁ? የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉትም፣ የዲያብሎስ ልጆች የተባሉትም ሰዎች ናቸው እንጂ መላእክት አይደሉም።

ወደ ቆላስይስ ሰዎች
3፥6 በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
3፥10 የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።
ጌ/ጌ/አ/አ 2000
Dec 19, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...