ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ማርያሞች ስንት ናቸው?

ሃና ማርያም፤ ፃድቃኔ ማርያም፤ ኩክ የለሽ ማርያም፤ ጽጌ ማርያም፤ምስለ ፍቁር፤ ኪዳነ ምህረት ወዘተ…. በየቦታው ሲጠሩ እሰማለሁ፡፡ ታድያ እነዚህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አሉ? ካሉ ብትጠቁሙኝ ደስ ይለኛል፡፡
ተባረኩ!
Dec 6, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ኡ… ኡ ኡ ኡ!!! ኧረ የመልስ ያለህ!!!!
ሃና ማርያም=የኢያቄም እና የሃና ልጅ፣የኢየሱስ እናት ማርያም፤//// ፃድቃኔ ማርያም=ፃድቃኔ በሚባል ቦታ ላይ የምትመሰገን እና የምተወደድ የኢያቄምና የሃና ልጅ፣ የኢየሱስ እናት ማርያም፤////ኩክ የለሽም እንዲሁ፤////ጽጌ ማርያም= አበባ ማርያም፣ ፍሬ ኢየሱስን ያስገኘች/ የወለደች የሃና እና የኢያቄም ልጅ ብፅዕት የምትሆን ማርያም፤///////// ለወንጌላዊው ዮሐንስ እናት ትሆነው ዘንድ የተሰጠች ማርያም፣ በስጋ በመውለድ እናቱ አይደለችምና፣ ለእኛም እናት ትሆነን ዘንድ ታስፈልገናለችና....
ሃና ማርያም=የኢያቄም እና የሃና ልጅ፣የኢየሱስ እናት ማርያም፤//// ፃድቃኔ ማርያም=ፃድቃኔ በሚባል ቦታ ላይ የምትመሰገን እና የምተወደድ የኢያቄምና የሃና ልጅ፣ የኢየሱስ እናት ማርያም፤////ኩክ የለሽም እንዲሁ፤////ጽጌ ማርያም= አበባ ማርያም፣ ፍሬ ኢየሱስን ያስገኘች/ የወለደች የሃና እና የኢያቄም ልጅ ብፅዕት የምትሆን ማርያም፤///////// ለወንጌላዊው ዮሐንስ እናት ትሆነው ዘንድ የተሰጠች ማርያም፣ በስጋ በመውለድ እናቱ አይደለችምና፣ ለእኛም እናት ትሆነን ዘንድ ታስፈልገናለችና፤////ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ=ግእዝ ነው፣ ትርጉሙም ማርያም ከተወደድ ልጅዋ(ኢየሱስ ክርስቶስ) ጋር ማለት ነው። ኪዳነ ምህረት=የማርያም ልጅ አምላካችን፣ ጌታችንና መድህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገባላት የምህረት ቃል ኪዳን ነው (ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም)

3 መልሶች

+2 ድምጾች
 
ምርጥ መልስ
በጌታ ፍቅር የማፈቅርህ ውዱ ወንድሜ ሆይ መልስ ሳታገኝ በመቆየትህ አዝናለሁ። የጌታችን እና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ለሁላችን ይሁን፤ አሜን።

አንተ ከጠቀስካቸው ስሞች ሁሉ አንድስ እንኳ በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም። ከእንግዳና ባዕድ ነገሮች፣ ወይም በአምላክ ቃል ላይ ሰዎች ከለጠፉት ጭማሪ ነገር ሁሉ መጠንቀቅ ይገባናል።

በአጭሩ፦ በብሉይ ኪዳን ማርያም (በዕብራይስጥ ምርያም) የተባሉ ሁለት ሴቶች አሉ። በአዲስ ኪዳን 5 ማርያም እና 1 ማርያ (6ቱም በግሪክ ሜሪ) የተባሉ 6 ሴቶች አሉ። በጠቅላላው በመጽሓፍ ቅዱስ 8 ሴቶች በዚህ ስም ተጠርተዋል ማለት ይቻላል። ዝርዝሩን አንተው ራስህ እንድትመረምር በቅዱስ መጽሓፍ ያሉትን ማርያሞች በሙሉ ቀጥዬ አቀርብልሃለሁ።

ከብሉይ ኪዳን።

(1) የሙሴ እና የአሮን ታላቅ እህት ማርያም።
ኦሪት ዘጸአት
15፥21 ማርያምም እየዘመረች መለሰችላቸው፦ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

ኦሪት ዘኍልቍ
12፥1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።

ኦሪት ዘኍልቍ 12፥4 እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም፦ ሦስታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ።

ኦሪት ዘኍልቍ 12፥5 እግዚአብሔርም በደመና ዓምድ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወጡ።

ኦሪት ዘኍልቍ 12፥10 ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም ለምጻም ሆና ነበር።

ኦሪት ዘኍልቍ 12፥15 ማርያምም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተዘግታ ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም።

ኦሪት ዘኍልቍ 20፥1 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ። ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ። ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች።

ኦሪት ዘኍልቍ 26፥59 የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንን እና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

ኦሪት ዘዳግም
24፥9 አምላክህ እግዚአብሔር ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ በመንገድ ሳላችሁ በማርያም ላይ ያደረገውን አስብ።

መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 6፥3 የእንበረምም ልጆች አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ናቸው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዮድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ናቸው።

ትንቢተ ሚክያስ
6፥4 ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፤ በፊትህም ሙሴን እና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።
(2) የዕዝራ ልጅ የሆነው የዬቴር ልጅት ማርያም።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
4፥17 የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ። ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ።
ከአዲስ ኪዳን።

(3) የኢየሱስ እናት ናዝራዊቷ ማርያም።
የማቴዎስ ወንጌል
1፥16 ያዕቆብም (የዮሴፍ አባት) ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።

የማቴዎስ ወንጌል 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።

የማቴዎስ ወንጌል 1፥20 እርሱ (ዮሴፍ) ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

የማቴዎስ ወንጌል 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም (ለኢያሱስ) ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ እና ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።

የማቴዎስ ወንጌል 13፥55 ይህ (ኢየሱስ) የጸራቢ (የዮሴፍ) ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ እና ዮሳ፣ ስምዖንም፣ ይሁዳም አይደሉምን? (አስተውል፤ የያዕቆብ እና ዮሳ እናት ማርያም ራሷ የኢየሱስ እናት ማርያም ናት። ያዕቆብ እና ዮሳ የኢየሱስ ወንድሞች ማለትም የማርያም ልጆች ናቸው።)

የማቴዎስ ወንጌል 27፥56 ከእነርሱም መግደላዊት ማርያም እና የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም ፣ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ።
(ወንጌላዊው ማቴዎስ ማርያምን የያዕቆብና የዮሳ እናት ብሎ ገልጾአል። ማቴዎስ ከኢየሱስ ህጻንነት ጊዜ በቀር ማርያምን "የኢየሱስ እናት" ብሎ ጠርቶ አያውቅም። ጭራሽ እንዲህ ማለት አይፈልግም። ስለዚህ "የያዕቆብና የዮሳ እናት" ብሎ ይገልጻታል። )

የዮሐንስ ወንጌል 19፥25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ። ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ (ማርያም)፥ የእናቱም እኅት (የማርያም እህት)፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።

የማርቆስ ወንጌል
6፥3 ይህስ (ኢየሱስ) ጸራቢው፣ የማርያም ልጅ፣ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።

የሉቃስ ወንጌል
1፥27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።

የሉቃስ ወንጌል 1፥30 መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።

የሉቃስ ወንጌል 1፥34 ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለ ማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።

የሉቃስ ወንጌል 1፥38 ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ (ነኝና) እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።

የሉቃስ ወንጌል 1፥39 ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥

የሉቃስ ወንጌል 1፥41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥

የሉቃስ ወንጌል 1፥46 ማርያምም እንዲህ አለች።
1፥56 ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች። ወደ ቤትዋም ተመለሰች።
2፥4-5 ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ፣ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።

የሉቃስ ወንጌል 2፥16 ፈጥነውም መጡ፤ ማርያምንና ዮሴፍን፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።

የሉቃስ ወንጌል 2፥19 ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።

የሉቃስ ወንጌል 2፥34-35 ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም፦ እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ (ኢየሱስ) በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፣ ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።

የሉቃስ ወንጌል 24፥10 ይህንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያም እና ዮሐና፣ የያዕቆብም እናት ማርያም (ማለት የኢየሱስ እናት)፣ ከእነርሱም ጋር የነበሩት ሌሎች ሴቶች ነበሩ።

የሐዋርያት ሥራ
1፥14 እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም፣ ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።

(4) የኢየሱስ ደቀመዝሙር መግደላዊት ማርያም።
የማቴዎስ ወንጌል 27፥56 ከእነርሱም መግደላዊት ማርያም እና የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ።

የማቴዎስ ወንጌል 27፥61 መግደላዊት ማርያምም፣ ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።

የማቴዎስ ወንጌል 28፥1 በሰንበትም መጨረሻ፣ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።


የማርቆስ ወንጌል 15፥40-41 ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም (ማለት የኡየሱስ እናት ማርያም)፣ ሰሎሜም ነበሩ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የወጡ ሌሎች ብዙዎች ሴቶች ነበሩ።

የማርቆስ ወንጌል 15፥47 መግደላዊትም ማርያም፣ የዮሳም እናት ማርያም (ማለት የኡየሱስ እናት ማርያም) ወዴት እንዳኖሩት ይመለከቱ ነበር።

የማርቆስ ወንጌል 16፥1 ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም (ማለት የኡየሱስ እናት፣ የታናሹም የያዕቆብ እናት ማርያም)፣ ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ።

የማርቆስ ወንጌል 16፥9 ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።

የሉቃስ ወንጌል 8፥2 አሥራ ሁለቱም (ደቀ መዛሙርት) ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥.....

የሉቃስ ወንጌል 24፥10 ይህንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያም እና ዮሐና፣ የያዕቆብም እናት ማርያም፣ ከእነርሱም ጋር የነበሩት ሌሎች ሴቶች ነበሩ።

የዮሐንስ ወንጌል 20፥1 ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች።

የዮሐንስ ወንጌል 20፥11 ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤

የዮሐንስ ወንጌል 20፥16 ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ፦ ረቡኒ አለችው፤ ትርጓሜውም። መምህር ሆይ ማለት ነው።
20፥18 መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይህንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች።

(5) የአልዓዛር እና የማርታ እህት ቢታንያዊቷ ማርያም።

የሉቃስ ወንጌል 10፥39 ለእርስዋም (ለማርታ) ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።

የሉቃስ ወንጌል 10፥42 (ኢየሱስ ለማርታ) የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች፤ ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።

የዮሐንስ ወንጌል
11፥1 ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢታንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር።

የዮሐንስ ወንጌል 11፥2 ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር።

የዮሐንስ ወንጌል 11፥19 ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው (ስለ አልዓዛር) ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር።
11፥20 ማርታም ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር።

የዮሐንስ ወንጌል 11፥28 ይህንም ብላ (ማርታ) ሄደች፤ እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ፦ መምህሩ መጥቶአል፤ ይጠራሽማል፤ አለቻት።

የዮሐንስ ወንጌል 11፥31 ሲያጽናኑአት ከእርስዋ ጋር በቤት የነበሩ አይሁድም ማርያም ፈጥና እንደ ተነሣችና እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ፥ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።
11፥32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ (አልዓዛር) ባልሞተም ነበር አለችው።

የዮሐንስ ወንጌል 11፥45 ስለዚህ ወደ ማርያም ከመጡት፥ ኢየሱስም ያደረገውን ካዩት ከአይሁድ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤

የዮሐንስ ወንጌል 12፥3 ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ፣ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።

(6) የቀለዮጳ ሚስት ማርያም።
የዮሐንስ ወንጌል 19፥25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ። ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ (የኢየሱስ እናት ማርያም) ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።

የሉቃስ ወንጌል24
15 ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
16 ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
17 እርሱም፦ እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው።
18 ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ፦ አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው።


ይቀጥላል... (G.G.A.A )
Jan 9, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
Jan 9, 2013 ታርሟል
+1 ድምጽ
....የቀጠለ።


(7) የወንጌላዊው የማርቆስ እናት ማርያም።
(የማርቆስ ወንጌልን የጻፈው የማርቆስ እናት።)

የሐዋርያት ሥራ
12፥12 (ጴጥሮስ) ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።(8) ማርያ የተባለችው የሮሜ ቤተ ክርስቲያን ዋና አገልጋይ (መጋቢ)
ወደ ሮሜ ሰዎች 16 (ሓዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን ሲናገር)
6 ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

ይሄው ነው። ከእነዚህ ውጭ በቅዱስ መጽሓፍ ውስጥ ማርያም የተባለ የለም። ጸጋው ይብዛልን። ሰላም!
(G.G.A.A)
Jan 9, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
Jan 9, 2013 ታርሟል
0 ድምጾች
(1) የሙሴ እና የአሮን ታላቅ እህት ማርያም።
* ሳታገባ፣ ሳትወልድ የሞተች።
በልጅነቷ፣ ህጻን ወንድሟን (ሙሴን) ከውሃ ያተረፈች እና ለልዕልቷ "የሚታጠባ ሴት ልጥራልሽ?" ብላ የጠየቀች እና የጠራችላትም ነች። (ኦሪት ዘጸአት 2፡ 1-10።)(2) የዕዝራ ልጅ የሆነው የዬቴር ልጅት ማርያም።
*ታሪኳ ያልተጻፈላት።
ስለ እርሷ ብዙ አናውቅም። ከስሟ በቀር ታሪኳ አልተጻፈልንም።


(3) የኢየሱስ እናት ናዝራዊቷ ማርያም /ትልቅ ሴት/።
*ያገባች እና የወለደች።
አራቱም ወንጌላውያን ስለ እርሷ ጽፈውልናል። ወንጌላዊው ሉቃስ ከወንጌሉ በተጨማሪ በሓዋርያት ሥራ መጽሓፍ ላይም ጠቅሶአታል። ከውልደቱ እስከ መስቀሉ አጠገብ፣ እስከ ድል ትንሳኤው ዘገባ ድረስ ከኢየሱስ ጋር ተጠቅሳለች።


(4) የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መግደላዊት ማርያም።/ወጣት ማርያም/
*ያላገባች እና ያልወለደች።
አራቱም ወንጌላውያን ስለ እርሷ ጽፈውልናል። ወንጌላዊው ሉቃስ ሃብታም ሴት መሆኗን እና ኢየሱስን በገንዘባቸው ከሚያገለግሉት ሴቶች መካከል አንዷ መሆኗን ጽፎልናል። (ሉቃስ 8፡3)
በአራቱም ወንጌላት፣ በተለይ በትንሳኤው ዘገባ ውስጥ፣ ከሁሉም ሰው ይልቅ ቅድሚያ ተሰጥቶአታል። በትንሳኤ የተነሳውን ጌታ ከሰው ሁሉ ቀድማ (ከኢየሱስ እናት ክማርያም እንኳ ቀድማ) በመጀመሪያ ያየችው እርሷ ናት። የመጀመሪያዋ የትንሳኤው የአይን ምስክር እና የምስራች አብሳሪ ናት። ከእርሷ ቀጥሎ ሁለተኛዋ የትንሳኤው የአይን ምስክር የኢየሱስ እናት ማርያም ነች። ቀጥሎም ጴጥሮስ።


(5) የአልዓዛር እና የማርታ እህት ቢታንያዊቷ ማርያም /ወጣት ማርያም/።
*ያላገባች እና ያልወለደች።
እርሷም ጌታን ከፍቅር እና ከንስሓ (ይቅርታ ለመለመን) ሽቱ ከቀቡት ሁለት ሴቶች አንዷ ነች። (ዮሓ 11፡2 እና 12፡3)
ከወንድሟ እና ከእኅቷ ጋር አብራ የምትኖር ስትሆን ኢየሱስን ብዙ ጊዜ በቤታቸው ይቀበሉት እና ያስተናግዱት ነበር። ማርያም አብዛኛውን ጊዜ ከእግሩ ስር ቁጭ ብላ ከጌታ አፍ የሚወጣውን ቃል ተመስጣ ትማር ነበር። ታላቅ እኅቷ ማርታ ግን ለጌታ ያላትን ፍቅር ለመግለጽ፣ ወይም ጌታን ለማስደሰት ስትል በመስተንግዶ እና በጓዳ ስራ ትጠመድ ነበር። ጌታ ወንድማቸውን ጨምሮ ሶስቱንም እጅግ የሚወዳቸው ሲሆን፣ ለመስተንግዶ ከመሯሯጥ ይልቅ ወደ እርሱ ቀርበው ቃሉን እንዲማሩ መክሮአቸዋል። ሶስቱም ወላጅ አልባ እና ለጋ እድሜ የነበራቸው ሲሆን ውዱ ኢየሱስ ምርጥ እና አስተማማኝ ወዳጅም፣ ወላጅ አባትም፣ ወገንም፣ አለኝታም ሆኖላቸዋል። ድንገት ወንድማቸው በሞተ ጊዜም የታመኑት ጌታ አላሳፈራቸውም። ከሞት አስነስቶታል። ኢየሱስ ሆይ፣ ለእኔም የዘላለም መታመኛዬ፣ አባቴም አንተ ነህና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ አሜን።


(6) የቀለዮጳ ሚስት ማርያም /ወጣት ማርያም/።
*በቅርቡ ያገባች ነገር ግን ልጅ ያልወለደች።
ከአስራ ሁለቱ ሓዋርያት ሌላ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነው የቀለዮጳ ሚስት ናት። ከወንጌላዊው ዮሓንስ በቀር ስለ እርሷ የጻፈልን የለም። ዮሓንስም ቢሆን በአንድ ጥቅስ ብቻ ስሟን ከመጥቀሱ በቀር፣ ስለ እርሷ ሌላ መረጃ አልጻፈልንም። ስለዚህ ስለ እርሷ ብዙ አናውቅም።


(7) የወንጌላዊው የማርቆስ እናት ማርያም /ትልቅ ሴት/።
(የማርቆስ ወንጌልን የጻፈው የማርቆስ እናት።)
* ያገባች የወለደች።
ስለ እርሷ ብዙ አናውቅም። ሉቃስ ብቻ ያውም በአንድ ጥቅስ ጠቅሶአታል።(8) ማርያ የተባለችው የሮሜ ቤተ ክርስቲያን ዋና አገልጋይ (መጋቢ)
ስለ እርሷ ብዙ አናውቅም። ጳውሎስ ብቻ ያውም በአንድ ጥቅስ ጠቅሶአታል።

(G.G.A.A)
Jan 10, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
Jan 10, 2013 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...