ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መዳኒታችን ኢየሱስ ok

መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን አንተ እንለዋለን ? ፃድቃንን ለምን አንቱ እንላቸዋለን ? በዚህ ላይ እርሶ ምን ይላሉ ?
Dec 18, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ውድ ጠያቂ

በመሰረቱ "አንቱ" ኢትዮጵያዊ ባህል እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ የሚል አገላለጽ ባለማግኘቶ ሊገረሙ አይገባም።

በኢትዮጵያ ባህላችን ግን በእድሜ የገፉ ሰዎችን ወይም ማንነታቸውን በውል የማናውቃቸውን ሰዎች (ልክ እንደ እርስዎ) "እርስዎ" ወይም "አንቱ" ብለን እንጠራለን።

ይሁንና በኃይማኖታዊ ስሜት በእድሜ ከኔ የማይበልጠኝን ማንም ሰው "አንቱ" ከማለት እቆጠባለሁ።

ከዚህ ባለፈ ልምዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለምና ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ላሳይዎ አልችልም።

ከጠቀሞት ግን እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቱ፦
Quote:
ማቴዎስ 23፡6-8
"6 በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥
7 በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።
8 እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።"
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 23፡12 "ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።"
Quote:
የሉቃስ ወንጌል 20፡46 "ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤"
Quote:
ወደ ዕብራውያን 5፡5 "እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን። አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤"

ሰላም
Oct 1, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...