ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 21 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

my questions is spritual question that i am stucked on it.

1. መጀመሪያ እግዚአብሔር አዳምንና ሄዋንን ፈጠረ ግን ማን ነበር ጥቁር/ነጭ? ምክንያቱም በአለማችን ላይ ሁለት አይነት ሰው አለ ጥቁር ና ነጭ/ፈረንጅ የምንላቸው። መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ግን ምንም አይነት ማብራሪያ የለም ስለዚህ እግዚአብሔር ሁለቱንም ነው የፈተረው ወይስ ጊዘ ያመጣው ለዉጥ ነው?
2.በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር አይጸጸትም ይላል እንደገና ደግሞ እግዚአብሔር ስውን በመፍጠሩ ተፀፀተ ይላል እነዚህ ሁለት ቃሎች አይጋጩም? ምክንያቱም መጽሃፍ ቅዱስ አዪጋጭም ተብላል። በሌላም ክፍል ላይ ይሁዳን ታንቆ ሞተ እና አንጀቱ ትዘርግፎ ሞተ የሚል ሁለት ሃሳብ አለ። ትንሽ ግልጽ ሲላልሆነልኝ ነው።
Dec 31, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
የጌታ ጸጋ እና ሰላም ለሁላችን ይሁን፤ አሜን።

የአስቆሮቱ ይሁዳ እንዴት ሞተ?

የማቴዎስ ወንጌል 27
3 በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ (በኢየሱስ ) እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦
4 "ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ" አለ። እነርሱ ግን፦ "እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ" አሉ።
5 ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።
6 የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ " የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም" አሉ።
7 ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙ በት።
8 ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት (አኬልዳማ) ተባለ።

በተለይ 27 ቁጥር 5ን በደንብ እንመልከተው።


Matthew 27:5

(1) NET ©
So Judas threw the silver coins into the temple and left. Then he went out and hanged himself.

(2) NIV ©
So Judas threw the money into the temple and left. Then he went away and hanged himself.

(3) NASB ©
And he threw the pieces of silver into the temple sanctuary and departed; and he went away and hanged himself.


ከዚህ በግልጽ እንደምናየው የአስቆሮቱ ይሁዳ የሞተው ራሱን ሰቅሎ ወይም በገመድ ተንጠልጥሎ ነው። እኔ ከዚህ በቀር "አንጀቱ ተዘርግፎ ሞተ" ወይንም ደግሞ "ሁለት ሃሳብ አለ" የሚል ቃል በመጽሓፍ ቅዱስ አላገኘሁም።


የሐዋርያት ሥራ 1 (ጴጥሮስ ሲናገር)
16 ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤
17 ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና።
18 ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ፤ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤
19 በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው።

አስተውል በዚህ ክፍል "ይሁዳ አንጀቱ ተዘርግፎ ሞተ" አይልም።

በየትኛውም መዝገበ ቃላት ቢተረጎም "ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ፤ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ" የሚለው ቃል "አንጀቱ ተዘርግፎ ሞተ" ማለት አይደለም። ይልቁንም ታንቆ የሞተው ይሁዳ ከምን እንደ ደረሰ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ነው ይህ ክፍል የሚሰጠን።

ይሁዳ ታንቆ ሞተ። ሆኖም ቶሎ ያየው ወይም የሰማ ሰው አልነበረም። ምክንያቱም የዚያ ሰሞን ትኩስ ወሬ እና የሰውን ትኩረት በሙሉ የተቆጣጠረው የታላቁ መሲህ መያዝ እና መፈረድ ነበር።

መሲሁ በተሰቀለ ሰዓት፣ እና ከጥቂት ቀናት በኋላም በድል ትንሳኤ በተነሣ ጊዜ፣ የምድር መናወጥ፣ የአለቶች መሰነጣጠቅ፣ ናዳ፣ ጨለማ፣ ግርግር ... ወዘተ ነበረ። በዚህ ተደጋጋሚ መናወጥ ምክንያትም ተንጠልጥሎ እና አብጦ የከረመው የይሁዳ አካል ገመዱ ተበጥሶ፣ በግንባሩ ተደፋ፤ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ። እንዲህ አንጀቱ ተዘርግፎ እያለ ነው ገና አሁን የይሁዳን ሞት፣ ሰው ያየውና የሰማው። በዚህ ጊዜ "በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው።"


(1) መሲሁ በተሰቀለ ሰዓት የተከሰተ ነውጥ።
የማቴዎስ ወንጌል 27
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ
፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
54 የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ።

የሉቃስ ወንጌል 23
44 ስድስት ሰዓትም ያህል ነበረ፥ ጨለማም እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ሆነ፥ ፀሐይም ጨለመ፥
45 የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ።


(2) በመሲሁ ትንሳኤ ጊዜ የተከሰተ ነውጥ።
የማቴዎስ ወንጌል 28
1 በሰንበትም መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።
2 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።
3 መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።
4 (የመቃብሩ) ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ።

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የነበሩት ሁለቱ (ማቴዎስ እና ጰጥሮስ) ነገሩን በቅርበት የሚያውቁት በመሆናቸው በጥንቃቄ እና በትክክል ነው ስለ ይሁዳ የዘገቡልን። ከሁሉም በላይ ደግሞ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው ሁለቱንም የተጠቀመው። እናም መጽሓፍ ቅዱስ በፍጹም እርስ በርሱ ሊጋጭ አይችልም። ከተጋጨብን ችግሩ ያለው የእኛ አረዳድ ወይም አነባብ ላይ ነው።

ጌታ እግዚአብሔር የቃሉን ፍች ያብራልን። የጌታ ጸጋ ይብዛልን፤ አሜን።

(G.G.A.A)
Jan 9, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
Jan 9, 2013 ታርሟል
It's crystal clear. Thanks a lot. GOD bless you guys.
Amen. GOD bless you, too, with all the richness of His Holy Spirit, and with the light of His Word. Amen.
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...