ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 8 May 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ኢየሱስ ከሞት የተነሳው እራሱ ነው ወይስ እግ/ር ነው ያስነሳው?

ኢየሱስ ከሞት የተነሳው እራሱ ነው ወይስ እግ/ር ነው ያስነሳው?
Apr 12, 2013 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
አመሰግናለሁ ተባረክ
ጌታችን ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሄር አይደለምን ? ለዚህ ነው ጌታ ራሱ ሲናገር "ይህን ቤተ መቅደስ ኣፍርሱት ፥ በሶስተኛውም ቀን አነሳዋለሁ " ብሎ የተናገረ። አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚኣብሔር ነው የሚለውንም ቃል አንርሳ።
የተመለሰው መልስ ልክ አይመስለንም ( መቅደሱን አፍርሱት በሶስተያ ቀን አስነሳዋለሁ ሲብ የሚፈርሰው እና በሶስተያ ቀን የሚያስነሳው የተለያዩ 2አካሎች መሆናቸውን ነው ሚያሳየው
ወንድም፣ ዋናው ነገር ላንተ መሰለህ አልመሰለህ የሚለው አይደለም። ላንተ ተመቸህ አልተመቸህ የሚለው አይደለም። ላንተ ቢመስልህም ባይመስልህም ቃሉ የሰው አስተያየት ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነውና መቀበል ግድ ይልሃል። አነሣዋለሁ ማለት አነሣዋለሁ ነው እንጂ ይህ ቃል በራሱ 2 አካሎች መሆናቸውን አያሳይም።

የዮሐንስ ወንጌል 2፡
19 ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
20 ስለዚህ አይሁድ፦ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።
21 እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።
22 ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።
23 በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤
24-25 ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር። ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር። ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።

ይሁንና ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው ሌላ ባዕድ ወገን ሳይሆን የራሱ የኢየሱስ ውድ አባቱ ነው። ኢየሱስን የሚወድደው እና ኢየሱስ የደስታው ምንጭ የሆነለት አብ፣ ኢየሱስን ከሞት አስነሳው። ከፍጹም አምላክነቱ አንጻር ስታይ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ፍጹም አንድ ነው (የዮሐንስ ወንጌል 10፡ 26-30)

የኢየሱስን ትንሳኤ ብቻ ማወቅ በቂ አይደለም። ይህንንማ ማንም ማንም ያውቀዋል። ሰይጣንም እንኳ ያውቀዋል። ዋናው የሚያስፈልገን ነገር ለምን ተነሳ የሚለው ነው። እንዴት ተነሳ የሚለው ነው። ለምን ተነሳ ስንል እኛን ለማጽደቅ ተነሳ። አሜን፤ አቤቱ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ስራዬን ሰርተሃልና ለዘላለም ልትመሰገን ይገባሃል። ክብር ላንተ ይሁን። አሜን።
እንዴት ተነሳ ስንል ደግሞ ከሙታን መካከል የነበርነውን ብዙ ቢሊዮኖችን (ማለት እኛን) ከእርሱ ጋር አስነሳን። ከኃጢአታችን አጸደቀንና ከእርሱ ጋር ይዞን ተነሳ። ከእርሱ ጋርም በአብ ቀኝ አስቀመጠን። ሃሌ ሉያ!
ታዲያ የሚያሳዝነው ነገር፣ አንዳንድ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ትንሳኤ የሚናገሩትን ያህል ትንሳኤው ያመጣላቸውን ክብር ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም። በዚህ እግዚአብሔር አባታችን ይደሰታልን ወይስ ያዝናል?

ወደ ሮሜ ሰዎች 4
22 ስለዚህ ደግሞ (ለአብርሃም እምነቱ) ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።
23 ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ፤
24-25 ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን <<እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን>> ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ (እምነታችን ጽድቅ ሆኖ) ይቈጠርልን ዘንድ አለው።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡
4 ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥
5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥
6-7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ <<ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን>>።
8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

11 ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ።
12 በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፣ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፣ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ፣ ከእግዚአብሔርም (ማለት ከክርስቶስ) ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።
13 አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።
14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን (ማለት የተገረዙትን አይሁድ እና ያልተገረዙትን አህዛብ) ያዋሐደ፣ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥
16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ፣ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
17 መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
18 በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ (በመንፈስ ቅዱስ) ወደ አብ መግባት አለንና።


ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት

እግዚአብሔር ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉን ታላቅነት የተጠቀመው መቼ ነው? ሰይጣንን ከሰማይ ወርውሮ ሲፈጠፍጠው ነውን? አይደለም። ሰማይን እና ምድርን እና ሌሎች ፍጥረታትን ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣ ነውን? አይደለም። በኋላስ ሰማይን እና ምድርን ሲደመስስ ነውን? አይደለም። ወይስ በኋላ የክርስቶስን ተቃዋሚ በአፉ እስትንፋስ ብቻ ሲያጠፋው ነውን? አይደለም። የኤርትራን ባህር ለሁለት በከፈለ ጊዜ ነውን? አይደለም። አዎን የአብ ታላቁ ጉልበት ወይም የመጨረሻው <<የብርታቱ ጉልበት>> የታየው የሞትን ጣር አጥፍቶ ኢየሱስን ከሙታን ሲያወጣው ነበር። ለምን? ምክንያቱም አብ ያስነሳው ኢየሱስን ብቻ ሳይሆን፣ የእዳችን ዋጋ ተከፍሏልና ብዙ ቢሊዮኖችን (አማኞችን) ከልጁ ጋር ከሙታን አወጣን። ከዲያብሎስ ሰንሰለት ነጻ አወጣን። ጻድቅ አባት ሆይ፣ አዎን ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኗልና ለዘላለም አመሰንሃለሁ። አሜን።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡
18-19 ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን፣ በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን፣ ለምናምን <<ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት>> ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤
20-21 <<ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው>> ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ <<የብርታቱ ጉልበት ይታያል>>።
22 ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።
23 እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።

የአብ ሃይል የዋለው አንተን በልጁ ለማዳን ነው። (ሮሜ 1፡16) ወንድሜ ሆይ ልጠይቅህ። ይህን ማዳን አምነህ ተቀብለሃል ወይ? በምስጋና ተቀብለሃል ወይ? እውነት ቃሉ እንደ ሚለው ከልጁ ጋር አስነስቶ በላይ በቀኙ አስቀምጦሃልን? አሁን ተቀምጠሃልን? አምነህ ተቀብለሃልን? ትንሳኤው ያመጣልህን ክብር በእምነት ተቀበልኸው? ወይስ ገና ባለማመን ትኖራለህ? እንዲያው ብቻ ክርክርን በመናፈቅ ትኖራለህ? (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፥4-5) አዎን፤ ያለ እምነት አምላክን ማስደሰት ፈጽሞ አይቻልም። አዎን፤ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ አምነህስ ከሆነ ያመንኸውን ትናገረዋለህ። ጌታም በዚህ ይደሰታል።

4 መልሶች

0 ድምጾች
መጽሃፍ ቅዱስ ኢየሱስ ከሙታን እንደተነሳ፤ ከሙታን ያስነሳው ደግሞ እግዚአብሔር እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 5
30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ
2፥24 እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።

2፥32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤

3፥15 የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን።

4፥10 እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

5፥30 እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው

10፥38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
10፥39 እኛም በአይሁድ አገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን፤ እርሱንም በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት።
10፥40 እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤

13፥28 ለሞትም የሚያደርስ ምክንያት አንድ ስንኳ ባያገኙበት፥ ይገድለው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት፤
13፥29 ስለ እርሱም የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜ ከእንጨት አውርደው በመቃብር አኖሩት።
13፥30 እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች
10፥9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
15፥15 ደግሞም፦ ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም።
Quote:
ወደ ቆላስይስ ሰዎች
2፥12 በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ።
Quote:
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
1፥9-10 እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።
Apr 12, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
+1 ድምጽ
ጌታችን ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሄር አይደለምን ? ለዚህ ነው ጌታ ራሱ ሲናገር "ይህን ቤተ መቅደስ ኣፍርሱት ፥ በሶስተኛውም ቀን አነሳዋለሁ " ብሎ የተናገረ። አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚኣብሔር ነው የሚለውንም ቃል አንርሳ።
Apr 19, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
ውድ ወንድሜ እግዚኣብሔር አንድ መሆኑን መርሳት ሳይሆን፡ የመለኮትን የስራ ክፍፍል ለማሳየት ነው።

እ/ር ይባርክ
+1 ድምጽ
እግዚአብሔር ነው ያስነሳው
Aug 7, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
አዎን ለእኛ ሲል በእውነት የሞተውን ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው አባቱ እግዚአብሔር ነው። በመጀመሪያው መላሽ ምላሽ ውስጥ የተጠቀሱት ጥቅሶች በቂ ማስረጃ ናቸው።

የሥላሴን ትምህርት እውነት ለማድረግ ሲባል ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትልቅ እውነት መሻር የለብትም። ምክንያቱም ሥላሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም!

አንድ መላሽ በዮሐንስ 2፡19 ላይ ኢየሱስ የተናገረውን በመጥቀስ ኢየሱስ ራሱን አስነስቷል ብለው ለማሳመን ሞክረዋል። ይህን ጥቅስ እንደ ማስረጃ ብዙ ቲኦሎጂያን እንደሚያቀርቡት የታወቀ ነው። ግን እስቲ ጠጋ ብለን ጥቅሱን እናንብበው።

እግዚአብሔር እንደሚያስነሳው ለመናገር ኢየሱስ ምን ማለት ነበረበት?
"ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አባቴ ያስነሳዋል" - እና ምን ይገርማል? ሁሉን ቻይ አምላክ እንኳን አይደለም በሦስት ቀን በሰከንድ ሽራፊም ይህን በ46 ዓመታት የተገነባ ቤተ መቅደስ ሊያስነሳ ይችላል። በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ ቢል ኖሮ "እግዚአብሔር ታላቅ ነው" ብሎ ከመናገር የዘለለ የሰዎችን ትኩረት የሚስብ ጉዳይ አይሆንም ነበር፣ እንዲሁም ዮሐንስ ላይጽፈውም ይችል ነበር።

አዎን ኢየሱስ መናገር የነበረበትን ተናግሯል።

አንድ ምሳሌ እናክል፦ መዳን በክርስቶስ እንጂ በሌላ በማንም እንደሌለ እናውቃለን። (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ታዲያ ሃዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡16 ላይ፡
Quote:
"ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።"
በማለት ጢሞቴዎስን ሲመክር ሰዎችን ታድናለህ ብሎታል።

ታዲያ ጢሞቴዎስ ኢየሱስ ነበርን፣ ወይም አዳኝ ነበር ማለት ነውን? በፍጹም! ከዚያ ይልቅ ጢሞቴዎስ ሰዎችን ለማዳን የእግዚአብሔር ማዳን ምክንያት ሆኗል።

ጌታችን ኢየሱስም ከሞት ለመነሳቱ ምክንያት ሆኗል።
Quote:
ወደ ዕብራውያን 5፡7 "እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤"
Quote:
ወደ ዕብራውያን 5፡9-10 "ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።"
Quote:
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡8-9 "በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነበዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤"
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20 "እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።"
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 17፡31 "ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።"
Quote:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡20-21 "ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤"
Quote:
ወደ ዕብራውያን 13፡20 "በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥"
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡9 "ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤"

እንግዲህ እውነትንና መዳንን ከወደድን እግዚአብሔር በቃሉ የሚነግረንን "መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል"ና እግዚአብሔርን እንታዘዘው ዘንድ መንፈሱን ያድለን። (1 ሳሙኤል 15፡22)


ሰላም
Oct 1, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...