ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ብሉይ ኪዳን አና አዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ እነማን ተፃፈ?

Jun 17, 2013 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ቅዱሳን መጻሕፍት የተጻፉት ከ1,600 ዓመታት በሚበልጥ ጊዜ ውስጥ በኖሩ 40 የሚያህሉ ሰዎች ነው። የሚገርመው ነገር ግን እነዚያ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መልእክት ምንጭ እንደሆኑ አልተናገሩም። ከጸሐፊዎቹ አንዱ "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ" በማለት በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፉ ተናግሯል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ሌላው ጸሐፊ ደግሞ "የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ" ብሏል። (2 ሳሙኤል 23:2) ከዚህ ለመመልከት እንደምንችለው ጸሐፊዎቹ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መልእክት ምንጭ የአጽናፈ ዓለሙ የበላይ ገዥ የሆነው አምላክ እንደሆነ ተናግረዋል።

የመጀመሪያዎቹ 5 የኦሪት መጽሐፍት በሙሴ እንደተጻፉ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ተናግረዋል። (ዘጸዓት. 17:14፤ 34:27፤ ኢያሱ. 8:31፤ ዳንኤል. 9:13፤ ሉቃስ 24:27፣ 44)

ከዚያም ኢያሱ፣ ሳሙኤል፣ ዳዊት፣ እና ሌሎችም ተከታዮቹን መጽሐፍት በአምላክ መንፈስ ተመርተው ጻፉ። እንደ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ህዝቅኤል የመሳሰሉትም ነቢያት የትንቢት መጽሐፍቱን ጽፈዋል።

የአዲስ ኪዳን ክፍል የሆኑትን 29 መጽሐፍት የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የነበሩት ሃዋርያት እና ሃዋርያው ጳውሎስ በግሪክኛ ቋንቋ ጽፈዋል።

- የተጻፈው ከ1513 ዓ.ዓ. እስከ 98 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 1,610 ዓመታት ውስጥ ነው።

- ከመጀመሪያዎቹ 39 መጻሕፍት መካከል አብዛኞቹ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተወሰኑት ክፍሎች ደግሞ በአረማይክ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን እነዚህ መጻሕፍት በአጠቃላይ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ወይም “ብሉይ ኪዳን” በመባል ይታወቃሉ።

- በግሪክኛ የተጻፉት የመጨረሻዎቹ 27 መጻሕፍት የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ወይም “አዲስ ኪዳን” በመባል ይታወቃሉ።
Aug 1, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...