ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እየሱስ አምላክ አለው ?

Jul 15, 2013 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ 1 ሪፖርት
ውድ ወዳጄ ሆይ፣
ጌታ ኢየሱስ ራሱ አምላክ/እግዚአብሔር/ጌታ/ፈጣሪ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ (39ኙ ብሉይ ኪዳን እና 27ቱ አዲስ ኪዳን) ያስረዳል።

ኢየሱስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው

ዮሐንስ 1፡
1 በመጀመሪያው ቃል (ኢየሱስ) ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር (አብ) ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር (ወልድ) ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር (መንፈስ ቅዱስ) ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ (ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠረ)፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

ኤፌሶን 2፡
10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

ከእግዚአብሔር አብ ክብርን እና ምስጋናን የተቀበለ ብቸኛ አምላክ

ዕብራውያን 1፡
8 (እግዚአብሔር አብ ሲናገር) ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ (O GOD,)፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል (ዘላለማዊ ነህ) ፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ (መንፈስ ቅዱስ፣ ኢሳይያስ 61፡1 ሉቃስ 4፡17-19) ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ (ማቴዎስ 17፡5)
10 ይላል። ደግሞ:- ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ (አንተ ፈጣሪ አምላክ ነህ፤ አንተ ፈጠርካቸው)
11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።

2ኛ ጴጥሮስ 1፡
17 ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና።

ከኢየሱስ በቀር ሌላ የሚያድን የለም፤ አምላክም የለም

የሐዋርያት ሥራ 4፡
11 እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።
12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና

... ይቀጥላል


ከታች ከአንደኛው መላሽ እና ከአስተያየቶች በኋላ ያለውን ረጅም መልስ በትዕግስት ያነበበ ሰው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነት እና ፍጹም ሰውነት ይረዳልና ወረድ ብላችሁ በትዕግስት እንድታነብቡ እጋብዛለሁ።

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ለእናንተ ይሁን (ራእይ 22፡21) አሜን።

9 መልሶች

+1 ድምጽ
መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ላይ እግዚአብሔር የኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ይገልጻል። ለምሳሌ ያህል፦
Quote:
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡17 የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።

ራዕይ 1፡6 መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።

እነዚህ ጥቅሶች በእርግጥ ከቤተ ክርስቲያን ሥላሴ ትምህርት ጋር ይጋጫሉ። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በ1984 ባሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "አምላክ" የሚሉት ቃላት እንዲወጡ ተደርገዋል። ለምሳሌ ሁለተኛ ቆሮንቶስ 1፡3 እንዲህ ይነበባል።
"የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይባረክ።"

ንጹህ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት መቀበል የሚፈልግ ሁሉ፣ የመጨረሻ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን መስማት እንዳለበት ከመናገር በላይ ምንም አልልም።


ሰላም
Aug 1, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
...የቀጠለ

ደግሞም እግዚአብሔር (ወልድ) እንዲህ ብሏል፦ "ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ፤ ጎርፍም መጣ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ፣ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ፤ ጎርፍም መጣ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።" ኢየሱስም ይህን ነገር (ተናግሮ) በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና (ማቴዎስ 7፡24-29)

መላእክትንም ሆነ እኛን በሰላም ያኖረን አምላክ "ሁላችንን በስልጣኑ ቃል እየደገፈን" ነው (ዕብራውያን 1፡3)። የትኛውም መልአክ የዘላለም ህይወት ሊሰጠን አይችልም። እግዚአብሔር (ወልድ) ግን እንዲህ አለ፦

"እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም (የማታምን ከሆነ ከበጎቹ አለመሆንህን -ወይም የኢየሱስ በግ አለመሆንህን- ያሳያል ማለት ነው)። በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። እኔ እና አብ አንድ ነን።" (ነገር ግን የማያምኑት) አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ (ዮሐንስ 10፡ 26-31)

የትኛውም መልአክ ሁሉን ቻይ ስላይደለ ጸሎታችንን መስማት እና ማድረግ አይችልም። እግዚአብሔር አምላክ ግን እንዲህ አለ፦ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ... እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ (ዮሐንስ 14፡ 12-14)

የትኛውም መልአክ በሁሉ ቦታ፣ በሁሉ ጊዜ ከእኛ ጋር ለመገኘት አይችልም። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለ፦ "ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና" (ማቴዎስ 18፡ 20)። እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ ሰማይ ሊሄድ ሲል ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረው የመጨረሻ ቃል "በሉ ቻው" የሚል አልነበረም። እንዲህ የሚል የዋስትና ቃል ነበር፦ "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" (ማቴዎስ 28፡ 19-20)። አሜን።

ታላቅ ደስታ እና ዋስትና የሚሰጠን ምንድር ነው? እግዚአብሔር አምላክ ሁልጊዜ በያለንበት ቦታ ሁሉ ከእኛ ጋር የሚገኝ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት ወስዶ በኃያል ክንዱ ከክፉ የሚጠብቀን ታማኙ ጠባቂያችን እና የነፍሳችን እረኛ መሆኑ ነው (2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡17-18)

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤
25 በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።

መልካሙ እረኛ

ስለዚህ እንዲህ እያልን ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር መልካምነት እንዘምራለን፦

መዝሙር 23፡
1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥
የሚያሳጣኝም የለም።
2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል
በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3 ነፍሴን መለሳት፥
ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ
አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም
በትርህ እና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5 በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ
በጠላቶቼ ፊት ለፊት
ራሴን በዘይት ቀባህ፥
ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6 ቸርነትህ እና ምሕረትህ
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥
በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

እርሱም እረኛችን ታላቁ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲህ ብሎናል፦

ዮሐንስ 10፡
9 በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
10 ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
12 እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል፤ በጎቹንም ይበትናቸዋል።
13 ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለ ማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
14-15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ፤ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
16 ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ።
24 ...አይሁድም እርሱን ከበው፦ እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሪ ታቆየናለህ? አንተ ክርስቶስ እንደ ሆንህ ገልጠህ ንገረን አሉት።
25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
26 እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤
28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
30 እኔ እና አብ አንድ ነን።
31 አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
32 ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
33 አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

"ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን መላእክት"

ከአቀራረብህ እንደ ምረዳው ኢየሱስ ከየትኛውም ሰብአዊ ማንነት የበለጠ እና የተለየ መሆኑን አውቀህ፣ አሁን እርሱን ከሰማይ መላእክት ጋር እያነጻጸርህ ነው። በዚሁ ከቀጠልህበት ኢየሱስ በብዙ አቅጣጫ ከመላእክትም የበለጠ እና የተለየ መሆኑን፣ መላእክት ሁሉ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ለኢየሱስ የሚሰግዱ መሆናቸውን እንደ ምትደርስበት እርግጠኛ ነኝ (ዕብራውያን 1፡1-14)

ኢየሱስን ከመላእክት ጋር ስታስተያይ እርሱ 'ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን መላእክት ሁሉ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ቢል ምን ልንል ነበር?' ብለሃል። በአንድ በኩል ልክ ነህ፤ ኢየሱስ ቃል በቃል "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ብሎ አላወጀም። ይህን ለምን እንዳላደረገ ኢየሱስ ምክንያቱንም ገልጿል። እንዲህ በማለት፦ "እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግል እና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም" (ማርቆስ 10፡45)

ደግሞም ኢየሱስ ብዙ ነገሮችን በምሳሌ ያስተምር ነበር። ሰዎች ሁሉ በሚረዱት ሁኔታ፣ በተለይም "በአንድ አምላክ ብቻ" እናምናለን የሚሉት አይሁዳውያን በቀላሉ በሚረዱት መልክ "በምሳሌ" ያስተምራቸው ነበር። እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን፣ ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስም ጋር አንድ (ኤሎሂም) መሆኑን ለማሳየትም ይህን ዘዴ ተጠቅሞበታል። "ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ። በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም" (ማቴዎስ 13፡ 34-35)

ጌታ ሆይ "ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ?"

ኢየሱስ በምሳሌ ያስተምር የነበረው ስለ ምንድር ነው? የመጣበትን ታላቅ አላማ (ለእኛ ቤዛ መሆንን) ከመፈጸም ሳይደናቀፍ በዚያውም ልክ በጥንቃቄ እውነታውን በሙሉ ሳይሸፍን ለመናገር ነው። በተለይም ከማያምኑት ለይቶ ለሚያምኑት ደቀ መዛሙርቱ እውነታውን ሁሉ ለማሳወቅ ነው።

ማቴዎስ 13፡
10 ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ? አሉት።
11 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።
12 ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
13 ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ፣ እየሰሙም ስለማይሰሙ (ስለማያምኑ)፣ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።

14 "መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፤ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም፤
15 በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል" የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
16 የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።
17 እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን (ክርስቶስን) ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም (ድምጹን) ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።

ኢየሱስ በግልጽ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ብሎ ያላወጀው፣ ንግስናን ከመቀበልም የሸሸው (ዮሐንስ 6፥15)፣ ከሰዎች ክብርን ለመቀበልም ያልፈለገው (ዮሐንስ 5፡41-42) ስለ ምንድር ነው? አዎን ከሰማይ ወርዶ የመጣበትን ታላቅ ተልእኮ (በእርግማን በመስቀል ላይ ነፍሱን ለእኛ ለብዙዎች ቤዛ መስጠትን፤ ገላትያ 3፡13) ለመፈጸም እንቅፋት እንዳይሆንበት ነው (ማቴዎስ 16፡23፤ ገላትያ 5፡11፤ ሮሜ 14፡13፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡9)። ይሁን እንጂ ኢየሱስ የራሱን ማንነት መካድ አይችልምና እርሱ በርግጥ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ያህዌ ስለ መሆኑ በቂ መረጃዎችን ትቶልናል (ዕብራውያን 1፡8-12፤ ራእይ 22፡12-13፤ ራእይ 1፡8)

ይቀጥላል...
...የቀጠለ

ኢየሱስ የመጣበትን ታላቅ አላማውን ለመፈጸም እንቅፋት የሚሆኑበትን ነገሮች ሁሉ በጥንቃቄ አስወገዳቸው። እርሱ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) መሆኑን ያለ ጊዜው ቢያውጅ ኖሮ ምን ይከሰታል? አዎን ህዝቡ ሁሉ አምላካችን ብለው ያመልኩታል፤ "ትልቅ ወንበር" ሰርተውም ያስቀምጡታል፤ ያነግሱታል (ዮሐንስ 6፡15)፤ ሎሌዎቹ (አገልጋዮቹ) ይሆኑለታል (ዮሐንስ 18፡36፤ ማቴዎስ 20፡28፤ ማርቆስ 10፡45)። እንጂ ወደ መጣበት አላማ ወደ መስቀል ማንም አይወስደውም። ጥቂት አይሁዳውያን ደግሞ "የለም እግዚአብሔርን ተሳድቦአል፤ እንዴት ከእግዚአብሐር አብ ጋር አንድ ነኝ ይላል?" በማለት ሊሰቅሉት ቢመጡ እንኳ መላው ሕዝብ ሊከላከልለት ይነሣ ነበር (ዮሐንስ 18፡36፤ ማቴዎስ 21፡10)። በሕዝቡ መካከል መከፋፈል፣ የእርስ በርስ ጦርነት እና መተላለቅም ሊከሰት ይችል ነበር። በዚህ ሁኔታ ነገሩ ሁሉ ይበላሽ ነበር። ከሰማይ የወረደበት ታላቅ አላማም (ለእኛ ቤዛ መሆን) ሳይፈጸም በቀረ ነበር። የአምላክ ሃሳብ ግን ይህ አልነበረም፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና (ገላትያ 1፡4፤ ዮሐንስ 12፡24፤ ዮሐንስ 8፡20)። ይህ ሁሉ ተከስቶ ቢሆን ኖሮ፣ 'ክርስቶስ ይናቅ እና ይጣል ዘንድ ከዚያም ወደ ክብሩ ይመለስ ዘንድ ይገባዋል' የሚለው የመንፈስ ቅዱስ እና የነብያት ትንቢት ሳይፈጸም ይቀር ነበር (ማርቆስ 10፡45፤ ሉቃስ 24፡25-27፤ 44-48፤ ሉቃስ 18፡31፤ መዝሙር 22፤ ኢሳይያስ 53)

ማቴዎስ 16፡
20 ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ (እግዚአብሔር) እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው (አላማውን እስኪፈጽም ድረስ ማለት ነው -የሐዋርያት ሥራ 10፥42)
21 (አላማውም ምን እንደሆነ ሲገልጽ) ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎች እና ከካህናት አለቆች፣ ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ፣ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
22 ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።
23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።

ጌታ ኢየሱስ በምድር በኖረበት ዘመን ሁሉ ታላቅ ክብሩን (ዮሐንስ 17፡5፤ ማቴዎስ 25፡31) በሙላት እየገለጠ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ የመጣበትን ታላቅ ተልእኮ ለመፈጸም ራሱን እጅግ ዝቅ እያደረገ (ፊልጵስዩስ 2፡7-8)፣ በአባቱ እና በመንፈሱ (በአብ እና በመንፈስ ቅዱስ) ብቻ እየተደሰተ፣ በትህትና እና በጥንቃቄ እርምጃውን ወደ ፊት ቀጠለ። "እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፥ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል" (ማርቆስ 10፡33፤ ሉቃስ 18፡31፤ ማቴዎስ 20፡18)። "እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም" (ማቴዎስ 20፡28፤ ማርቆስ 10፡45)

እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ያህዌ (ክርስቶስ) መሆኑን ጊዜው እስኪደርስ እና ተልዕኮው እስኪፈጸም ድረስ ለብዙዎች መንገር አልፈለገም ነበር (ማቴዎስ 9፡31፤ ማርቆስ 5፡37-43፤ ሉቃስ 8፡51-56)። ከብዙ ዘመን በፊት እርሱ ከላይ ወደ ታች የፈጠፈጣቸው አጋንንትም እንኳ አውቀውት ስለነበረ እንዲናገሩ አይፈቅድላቸውም ነበር (ማርቆስ 1፡34፤ ሉቃስ 4፡41)። ሆኖም ጊዜው ሲደርስ ሰዎች በሚገባ እንዲያውቁት በቂ መረጃዎችን ትቶልናል (ዮሐንስ 13፡19፤ ዮሐንስ 8፡24፤ ዮሐንስ 16፡4፤ ራእይ 2፡23፤ ዮሐንስ 8፡24-25፤ ኢሳይያስ 48፡16)። እንግዲህ የአለምን ሕዝቦች እና ትውልዶች ሁሉ የማዳን ተልእኮ ይህን ያህል አስተዋይ፣ ጠንቃቃ፣ ንጹህ እና ብቁ አዳኝ ይፈልግ ነበር። ይህን በትክክል እና ያለ ጉድለት መፈጸም የሚችለውም ራሱ እግዚአብሔር ወልድ ብቻ ነበር።

"ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ"

ማቴዎስ 17፡
5 እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። እነሆም ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
6 ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ፤ እጅግም ፈርተው ነበር።
7 ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፦ ተነሡ አትፍሩም አላቸው።
8 ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
9 ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ (አላማዬ እስኪፈጸም ድረስ) ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው። (ማርቆስ 9፡9፤ ሉቃስ 9፡36)

"የምትወዱኝስ ብትሆኑ ... ደስ ባላችሁ ነበር"

ዮሐንስ 14፡
27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
28 እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።

ጌታ ኢየሱስ የምድር አገልግሎቱን አጠናቅቆ፣ ወደ ቀድሞ ክብሩ ወደ አባቱ ዙፋን የሚመለስበት ጊዜ መቃረቡን ሲያይ በደስታ እና በፈገግታ ይናገራል። በርግጥ በአካል ከእነርሱ ተለይቶ ስለሚሄድ የሚያፈቅሩት ደቀ መዛሙርቱ ከባድ ሃዘን ያዘኑ ቢሆንም (ዮሐንስ 16፡5-7) ኢየሱስ ግን መደሰት እንጂ ማዘን እንደ ሌለባቸው ይነግራቸዋል። ለምን? ምክንያቱም ኢየሱስ (እግዚአብሔር ወልድ) ወደ ቀድሞ ክብሩ፣ ወደ ገናናው ዙፋኑ፣ ወደ ሚበልጠው ስፍራ ሊመለስ ነው። በርግጥ ኢየሱስን የሚወድዱት ከሆነ በዚህ ሊደሰቱ ይገባቸዋል። ስለዚህም "የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር" አላቸው።

በምን? በቁመት ወይስ በውፍረት? ወይስ በእድሜ? ጌታ ኢየሱስ አባቴ ከእኔ ይበልጣል ሲል በምንድር ነው? አዎን በክብር ነው (ዮሐንስ 17፡5)። በመጀመሪያ ቃል የነበረው እግዚአብሔር (ዮሐንስ 1፡1) ሥጋ ሆኖ ወደ ምድር የመጣው (ዮሐንስ 1፡14) ለምንድር ነው? የሰዎችን ኃጢአት ሁሉ ለመሸከም (ኢሳይያስ 53፡4-6፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)፣ እና ክብሩን ትቶ በእኛ ፈንታ የውርደት ሞታችንን ለመሞት ነበር (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14-15)። ቅጣታችንን እርሱ ሊቀጣ እና እዳችንን ከፍሎ ከአባት ጋር ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ሊያስታርቀን የእኛን እርግማን እርሱ ተቀበለ (ገላትያ 3፡13)

ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ 33 አመት ሙሉ የኖረው የክብር ኑሮን ሳይሆን በኃጢአታችን ምክንያት ለእኛ የተገባውን የውርደት እና የድህነት ኑሮን ኖረ። በእነዚህ ጊዜያት ኢየሱስ በሚገባው መጠን አልከበረም ነበር (ዮሐንስ 7፡39፤ ዮሐንስ 5፡41-42)። እጅግ ተዋርዶ ነበር (ፊልጵስዩስ 2፡8)። በእኛ ፈንታ በመሆን ራሱን ባዶ አድርጎ ነበር (ፊልጵስዩስ 2፡7፤ ዮሐንስ 8፡50፣ 54)። ስለዚህ በክብር ከአብ አንሶ ነበር (ዮሐንስ 14፡28)። ከመንፈስ ቅዱስ አንሶ ነበር (ሉቃስ 12፡10፤ ማቴዎስ 12፡32)። ራሱ ከፈጠራቸው መላእክትም በክብር ጥቂት አንሶ ነበር (ዕብራውያን 2፡9)። ራሱ ከፈጠረው ከሰውም በታች ተዋርዶ ነበር (መዝሙር 22፡6-7)። ከሁሉ በታች ወርዶ ነበር።

ነፍስ አድን ዋናተኞች የሰጠመውን ሰው ለማዳን ከእርሱ በታች ጠልቀው በመውረድ ተሸክመው ወደ ላይ እንደ ሚያወጡት መድኃኒታችን ከእኛ በታች በመውረድ እኛን ተሸክሞ ወደ ላይ ወጣ። "ከእርሱ ጋርም አስነሣን" (ኤፌሶን 2፡7)። እርሱ ዝቅ ዝቅ ብሎ ከፍ አደረገን። እርሱ ተዋርዶ እኛን አከበረን። እርሱ ሰው ሆኖ እኛን ሰው አደረገን። እርሱ ድሃ ሆኖ ባለጠጎች አደረገን (2ኛ ቆሮንቶስ 8፡9)። ይህን ሁሉ በስኬት ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀድሞ ክብሩ ተመልሶ (ዮሐንስ 12፡23፤ ዮሐንስ 17፡5) በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ ቅዱስ መንፈሱንም ላከልን። ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አምልኮ እና ስግደት፣ ውዳሴ እና ዝማሬ ለአዳኛችን እና አምላካችን፣ ለፈጣሪያችን እና ወላጅ አባታችን (ኢሳይያስ 9፡6፤ ዕብራውያን 2፡14-15፤ ዮሐንስ 1፡13) ለእርሱ ይሁንለት - ፍጹም ሰው ፍጹም እግዚአብሔር ለሆነው። አሜን (ራእይ 1፡6)

ጌታ ኢየሱስ የእኔን እና የአንተን ጣጣ ለመጨረስ፣ የእኔን እና የአንተን ቅጣት ለመቀበል ይህን ያህል ትዕግስት እና ዋጋ ጠይቆታል። እርሱም አምላካችን አልደከመም አልታከተም በጥንቃቄ እና በስኬት ፈጸመው እንጂ (ማቴዎስ 17፡22፤ ማቴዎስ 26፡2፣45፤ ሉቃስ 9፡51፤ ዮሐንስ 10፡14-18፤ ማቴዎስ 16፡20-23)

ፊልጵስዩስ 2፡
5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።
6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን (እኩል መሆንን) መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
7 ነገር ግን "የባሪያን መልክ" ይዞ "በሰውም ምሳሌ" ሆኖ ራሱን "ባዶ" አደረገ፥
8 "በምስሉም እንደ ሰው" ተገኝቶ ራሱን "አዋረደ"፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

ታድያ በዚህ ሁሉ ትዕግስት እና ዋጋ መክፈል ውስጥ አልፎ ላዳነን ለመድኃኒታችን እና ለታላቁ አምላካችን ለክርስቶስ (ወደ ቲቶ 2፡12-13) our great God and Saviour ምላሻችን ምንድር ነው? እርሱ አምላክ እንዳልሆነ ለማሳየት የሌለ መረጃ እየፈለግን በመከራከር ውድ እድሜያችንን ማባከን ነውን? አይደለም። ምላሻችን ወድቀን እርሱን ማምለክ ብቻ ነው። በደሙ ዋጅቶናልና አምልኮአችንን ሊቀበል ይገባዋል (ራእይ 5፡9-10)

ስለዚህ ኢየሱስ በግልጽ ወይም ቃል በቃል "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ብሎ አለማወጁን ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ይህችን ግማሽ ክር ብቻ ይዘን ብንሮጥ፣ ሮጠን የምንደርሰው ወደ ስህተት ነው። ሌላ ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ። ሁሉን አዋቂው፣ እጅግ አስተዋይ እና ታላቅ መምህር የሆነው ኢየሱስ ቃል በቃል "እኔ ሰው ነኝ" ብሎም አልተናገረም።

ይሁንና ኢየሱስ፣ እርሱ ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን ተግባራዊ በሆነ ሁኔታ፣ አይሁዳውያን በቀላሉ በሚረዱት መንገድ አስተምሯል (መዝሙር 8፡2፤ ማቴዎስ 21፡16)። በንግግሩ፣ በትምህርቱ፣ በትዕዛዙ ሁሉ ይህን ገልጦአል (ማቴዎስ 7፡22፤ 22፡13፤ 23፡34፤ 25፡34፣ 40፤ ሉቃስ 12፥37፤ ማቴዎስ 24፥42)። እንዲሁም እርሱ ፍጹም ሰው መሆኑን ተግባራዊ በሆነ መንገድ፣ አይሁዳውያኑ በሚገባቸው ቋንቋ አስተምሯቸዋል። አዎን እርሱ ፍጹም ሰው ፍጹም እግዚአብሔር ነው። እርሱ አማኑኤል -ከእኛ ጋር ያለው እግዚአብሔር- ነው (ኢሳይያስ 7፡14፤ 8፡8፤ ማቴዎስ 1፥23)። እርሱ ዮሆሹዋ/ኢየሱስ - አዳኙ ያህዌ- ነው (ማቴዎስ 1፥21)። ከመጀመርያው ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በነብያት የተናገረው እግዚአብሔር እርሱ ነበር። ነብያት እነ ኢሳይያስ ያዩት እግዚአብሔር እርሱ ነው (ኢሳይያስ 6፡1፤ ዮሐንስ 12፡41)። ኢሳይያስ "የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ" ሲል የተናገረው ስለ እርሱ ነበር (ኢሳይያስ 40፡3፤ ዮሐንስ 1፡2፤ ማቴዎስ 3፡3፤ ማርቆስ 1፡2-3፤ ሉቃስ 3፡3-6)። ነብዩ ኢዩኤል "የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" ሲል የተናገረው የክርስቶስን ስም ስለ ሚጠሩ ሰዎች ነበር (ኢዩኤል 2፡32፤ ሮሜ 10፡13፤ የሐዋርያት ሥራ 2፡21፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡19)። የብሉይ ኪዳን አባቶች እነ አብርሃም ያዩት ኤል ሻዳይ - ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር- እርሱ ነው (ዘፍጥረት 17፡1፤ ዮሐንስ 8፡56-59)። "በእርሱ የመሎኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና" (ቆላስይስ 2፥9)

ዮሐንስ 8፡
56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።
57 አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት።
58 ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።
59 (ራሱን እንደ እግዚአብሔር በመቁጠሩ ተቆጥተው) ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው፤ ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።

ልብ በል ኢየሱስ "አባታችን አብርሃም" አላለም፤ ራሱን ከሰዎች ለይቶ "አባታችሁ አብርሃም" አለ። በዚህ ክፍል ኢየሱስ ራሱን የሚገልጠው እርሱ "የአብርሃም ልጅ" እንደ ሆነ ሳይሆን "የአብርሃም አምላክ" እንደ ሆነ ነው። ጌታ ኢየሱስ አብን እንኳ "አባታችን" ወይም "አምላካችን" ብሎ አልተናገረም። ሁልጊዜም ራሱን ለየት በማድረግ "ወደ አባቴ እና አባታችሁ፣ ወደ አምላኬ እና አምላካችሁ" ይላል (ዮሐንስ 20፡17)። አባታችን (የእናንተም የእኔም አባት) ወይም አምላካችን (የእናንተም የእኔም አምላክ) ብሎ ከቶ አልተናገረም። ከዚህ ይልቅ "እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው" በማለት ልዩነቱን ጠብቆ ይናገራል (ዮሐንስ 8፡54)። ጳውሎስም ይህን ስላስተዋለ በጥንቃቄ ይናገራል፤ ስለዚህ በቅዱሱ መንፈስ ተነድቶ በጻፋቸው መልእክቶች ሁሉ፣ ኢየሱስን እና እኛን ቀላቅሎ "የኢየሱስ እና የእኛ አባት ይባረክ" ከቶ አላለም፤ ወይም "የኢየሱስ እና የእኛ አምላክ ይባረክ" አላለም። ምክንያቱም ኢየሱስ እንደ እኛ ሰው ብቻ አይደለም። እርሱ የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ ፍጹም እግዚአብሔር ነው ፤ እንዲሁም ፍጹም ሰው ነው። ይህን ለማሳየት ጳውሎስ በጥንቃቄ እና በማስተዋል ሲናገር፣ እኛን ወደ ጎን በመተው "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ (ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው) እና አባት (ኢየሱስ እንደ ፍጹም አምላክ) ይባረክ" ይላል (ኤፌሶን 1፡3)። ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስም ይህን በማስተዋሉ እንዲህ ይላል፦ "ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም (እንድንሆን ላደረገ)፣ ለአምላኩ (ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው) እና ለአባቱም (ኢየሱስ እንደ ፍጹም እግዚአብሔር) ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን (ኢየሱስ እንደ ፍጹም እግዚአብሔር)፤ አሜን" (ራእይ 1፡6)

ይቀጥላል...
... የቀጠለ

ጌታ ኢየሱስ ቃል በቃል ወይም በቀጥታ "እኔ ሰው ነኝ" ብሎ እንዳልተናገረ ተመልክተናል። ታዲያ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ጌታ ኢየሱስ "እኔ የማርያም ልጅ ነኝ" ብሎም አልተናገረም። ግን ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ቃል በቃል "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ብሎ አልተናገረም፤ ግን ያ ማለት ምን ማለት ነው? አዎን ከዚህ የምንረዳው እርሱ እንደዚያ ነኝ ብሎ ለማወጅ አለመፈለጉን እና ስራውን ብቻ በትክክል ሰርቶ ወደ ቀድሞ የክብር ዙፋኑ መመለሱን ነው።

ቃል በቃል መናገሩ ብቻ ከታየማ ኢየሱስ "እኔ አዳኝ ነኝ" ብሎም እኮ አልተናገረም። ይሁን እንጂ እርሱ ብቸኛው የአለም አዳኝ መሆኑን (ዮሐንስ 3፡16-18፣ 36፤ ዮሐንስ 14፡6)፣ ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን (ሉቃስ 13፡23-30፤ ራእይ 22፡12-13፤ ሉቃስ 12፡35-38)፣ ደግሞም ፍጹም ሰው መሆኑን ተግባራዊ በሆነ መንገድ በግልጽ አስተምሯል፤ በንግግሩ፣ በተግባሩ፣ በትእዛዙ እና በምሳሌዎቹ ሁሉ ይህን ገልጧል።

ታላቁ መሲሕ ስለ ራሱ የተናገረው

ማቴዎስ 28፡
20 እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

ዮሐንስ 4፡
26 ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።

ዮሐንስ 6፡
35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።
48 የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።
51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።

ዮሐንስ 8፡
12 ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።
18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።

ዮሐንስ 10፡
7 ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
9 በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።

ዮሐንስ 10፡
11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
14-15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።

ዮሐንስ 11፡
25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል (አለ)

ዮሐንስ 14፡
6 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድ እና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ (በኩል ካልሆነ) በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

ዮሐንስ 15፡
1 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።
5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

የሐዋርያት ሥራ 18፡
9-10 ጌታም (ኢየሱስ) ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው።

ራእይ 1፡
17 (ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን በራእይ ሲያይ) ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
19 እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።

ራእይ 21፡
6 አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።

ራእይ 22፡
12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
13 አልፋ እና ዖሜጋ፥ ፊተኛው እና ኋለኛው፥ መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ።

ራእይ 1፡
8 ያለው እና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ (ክርስቶስ)፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።

ራእይ 22፡
16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥር (ፍጹም አምላክ) እና ዘር (ፍጹም ሰው) ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።

ዮሐንስ 5፡
24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

ዮሐንስ 10፡
26 እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
28 <<እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም>>።
29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
30 እኔ እና አብ አንድ ነን።
31 (የማያምኑት) አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።

እንግዲህ እንዳላመኑት አይሁዶች ታላቁ መሲሕ ለሚናገረው እምቢ እንዳንል ብቸኛውን አዳኛችንንም ለመውገር (ለመቃወም) እንዳንነሳ (ዕብራውያን 6፡4-8፤ ዕብራውያን 10፡26-31) ራሱ መሲሑ ማስተዋልን ይስጠን፤ አሜን።

ምንም እንኳ በእርሱ ማመን ስለ ማይፈልጉ እና ላለማመናቸው ምክንያት ለመስጠት ሲፈልጉ "እርሱ ቃል በቃል እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አልተናገረም" የሚሉ ሰዎች ቢኖሩም፣ ተመልሰው እነርሱ ራሳቸው ስለ ኢየሱስ የሚናገሩት በሙሉ፣ እርሱ ስለ ራሱ ያልተናገረውን ነው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እርሱ ስለ ራሱ ያላለውን ይናገሩበታል። ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ "እኔ ፍጡር ነኝ" ብሎ አልተናገረም። ከዚህ ይልቅ ተቃራኒውን ተናግሯል (ዮሐንስ 8፡23)። ዛሬ አንዳንዶች በድፍረት ከራሳቸው ፈልስፈው እንደ ሚናገሩትም "እኔ ከአምላክ ቀጥሎ በአጽናፈ አለሙ ሁሉ ላይ ሁለተኛው አለቃ ነኝ" ብሎም አልተናገረም። "እኔ የመላእክት አለቃ ነኝ" ወይም "እኔ ከመላእክት አንዱ ነኝ" ወይም "ከነብያት አንዱ ነኝ" ብሎም አላወጀም። "እኔ የዳዊት ልጅ ነኝ" ብሎም አልተናገረም።

እንዲያውም መሲሁ ከዳዊት ቤት እንደ ሚመጣ በትንቢት የተረዱት አይሁዳውያን ዘወትር "የዳዊት ልጅ፣ የዳዊት ልጅ" እያሉ ሲጠሩት ኢየሱስ አንድ እውነት ነገራቸው። ይኸውም የዳዊት ልጅ ብለው እንዳይጠሩት ይልቁንም የዳዊት ጌታ ብለው እንዲጠሩት "የይገባኛል ጥያቄ" ጠየቃቸው (ማቴዎስ 22፡41-46)

የዳዊት ጌታ እግዚአብሔር

"የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ እፈውስሃለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ" (2ኛ ነገስት 20፡5)

መዝሙረኛው ዳዊት በዘመኑ ሁሉ ፈጣሪውን ጌታውን ሲያገለግል እና ሲያመልክ ኖረ። ጌታውም አንድ እግዚአብሐር ኤሎሂም (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) ነው። (ኤል ማለት ዕብራይስጥ ሲሆን አምላክ /እግዚአብሔር ማለት ነው። ኤሎሂም ማለት ብዙ ቁጥር ሲሆን "አማልክት" እንደ ማለት ነው- ይህም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን የሚያመለክት ነው።) የዳዊት ጌታ የእኛም ጌታ ነው (ማርቆስ 12፡29)። ምክንያቱም "አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና" (ሮሜ 10፡12)

ዳዊት እንዲህ አለ፦

መዝሙር 16፡
2 እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።

መዝሙር 109፡
21 አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕረትህን በእኔ ላይ አድርግ፤ ምሕረትህ መልካም ናትና አድነኝ።

ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦

ማቴዎስ 22፡
41-42 ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት።
43-44 እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት "ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው" ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ (ክርስቶስን) ይጠራዋል?
45 ዳዊትስ (ክርስቶስን) ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።
46 አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።

በሌላ ጊዜም ኢየሱስ ራሱን "ጌታ" ብሎ በመጥራት፣ የእስራኤል ጌታ (ያህዌ) እርሱ መሆኑን ለአይሁድ ማኅበረሰብ በሚገባቸው ቋንቋ ተናግሯል (ሉቃስ 19፥30-34)። በሌላ ስፍራ ደግሞ፣ ስለ እስራኤል አምላክ ስለ ያሕዌ የተጻፈውን ቃል (መዝሙር 8፡1-2) ለራሱ በማድረግ፣ የያሕዌን ክብር እና ሞገስ በግልጽ ለራሱ በመውሰድ (ማቴዎስ 21፡15-16) ኢየሱስ ማንነቱን (እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን) ገልጦ እያሳያቸው ነበር። በርግጥም የእስራኤል ጌታ ያህዌ፣ የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር ሌላ ሳይሆን ራሱ ጌታ ኢየሱስ ነበር (ዕብራውያን 1፡8-12)። "የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?" (ኢሳይያስ 53፡1)

አምላክ እግዚአብሔር በስጋ እጅ የማይጨበጥ የማይዳሰስ፣ በስጋ አይን የማይታይ (የሐዋርያት ሥራ 9፡3፣ 7) ረቂቅ "የሕይወት መንፈስ" (ሮሜ 8፡2) ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ በአካል የጎበኘን፣ ሰዎች ያዩት የተመለከቱት፣ የጨበጡት፣ የዳሰሱት፣ ያዳመጡት እና ያናገሩት (1ኛ ዮሐንስ 1፡1-2) "በሰው ምሳሌ" የመጣ "የሕይወት ቃል" ነው (ፊልጵስዩስ 2፡7)፤ ሥጋ ሆኖ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው (ዮሐንስ 1፡1፣ 14)፤ ሰዎች እግሩን ይዘው ያመለኩት (የሰገዱለት) እርሱም አፉን ከፍቶ ያስተማራቸው ሕያው አምላክ ነው (ማቴዎስ 5፡1፤ 28፡9፤ ዮሐንስ 9፡35-38)። አምላካችን ኤሎሂም (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) አንድ መንፈስ አንድ ጌታ አንድ አምላክ ነው (ኤፌሶን 4፡4-6)

ይህን በተጨባጭ ሁኔታ የተረዳው እና ያመነው ደቀ መዝሙሩ ቶማስ ኢየሱስን "ጌታዬና አምላኬ" My Lord and my God ያለው ሲሆን (ዮሐንስ 20፡28)፣ ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስም "አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (our God and Saviour Jesus Christ)" ይለዋል (2ኛ ጴጥሮስ 1፡1)። ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስም ስለ አምላኩ ሲመሰክር "እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እርሱ እውነተኛ አምላክ እና የዘላለም ሕይወት ነው (the true God and eternal Life)" ካለ በኋላ እውነተኛ አምላክ ካልሆኑት ከሌሎች እንድንርቅ ሲመክረን ደግሞ "ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት (ከሐሰተኛ አማልክት) ራሳችሁን ጠብቁ" ይለናል (1ኛ ዮሐንስ 5:20-21)። እንደዚሁም ክርስቲያኑ ጳውሎስ "ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ (God) ነው፤ አሜን" ይላል (ሮሜ 9፡5)። እንደገናም ጳውሎስ "የተባረከው ተስፋችን ታላቁ አምላካችን እና መድኃኒታችን (our great God and Saviour) ኢየሱስ ክርስቶስ" መሆኑን እንድናውቅ እና እርሱንም "እግዚአብሔርን (ታላቁን አምላካችንን ክርስቶስን) በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር" ይመክረናል (ቲቶ 2፡12-13)። እንዲሁም በገዛ ደሙ (በራሱ ደም) የዋጀን ጌታ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ሲመሰክር "በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ..." ይላል (የሐዋርያት ሥራ 20፡28)

"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ። እርሱ ነውርን ንቆ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና" (ዕብራውያን 12፡1-2)። ከእነዚህ ሁሉ ምስክሮች በተጨማሪ ሌላም ጠንካራ ማስረጃ እናገኛለን።

ይኸውም ራሱ ክርስቶስ ማንም ከልካይ ሳይኖርበት የመጀመሪያውም የመጨረሻውም አምላክ (አልፋና ዖሜጋ) እርሱ መሆኑን በግልጽ ሲናገር "እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፤ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ" በማለት እርሱ ፈጣሪ አምላክ መሆኑን ይገልጣል (ራእይ 22፡12-13)። አዎን "ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል" (ራእይ 1፡8)። እንዲሁም ኢየሱስ ሲናገር ፦ "በዚያ ቀን (በፍርድ ቀን) ብዙዎች ፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል" እኔም እፈርድባቸዋለሁ በማለቱ (ማቴዎስ 7፡22) በሐሰተኛ እና አስመሳይ ሰዎች ላይ ዘላለማዊ ፍርድ የሚሰጠው፣ እና እነርሱም ወድቀው ምህረት የሚለምኑት ፈላጭ ቆራጭ ዳኛ፣ ፈጣሪ አምላክ እርሱ መሆኑን ይፋ አድርጓል። አዎን "በጉም የጌቶች ጌታ እና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ" ወደር የሌለው ታላቅ ጌታ ነው (ራእይ 17፡14)

እስቲ እናስተውል "እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ (ብድራቴ) ከእኔ ጋር አለ፤ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ" (ራእይ 22፡12-13) ማለት ምን ማለት ነው? "ፈጣሪ እግዚአብሔር እኔ ነኝ" ማለት አይደለምን? ታማኝ እና ጻድቅ አስተማሪ ሆኖ፣ ወይም እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንዲህ የተናገረ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም አልተገኘም።

ይቀጥላል...
... የቀጠለ

ኢሳይያስ 35፡
3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ።
4 ፈሪ ልብ ላላቸው ፦ እነሆ አምላካችሁ በበቀል፣ በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው።
5 (እርሱ ሲመጣ) በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል፤ የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።
6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።

በርግጥ አይዘገይም፤ በቶሎ እመጣለሁ ያለው አምላካችን እግዚአብሔር እንደ ቃሉ "እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም (ጭምር) ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ (ከእርሱ የተነሳ) ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል" (ራእይ 1፡7-8)

"እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል። በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፤ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል" (ዘካርያስ 14፡3-4)

ኢሳይያስ 40፡
9 የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፤ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ አንሺ፥ አትፍሪ ለይሁዳም ከተሞች ፦ እነሆ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።
10 እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር (ወልድ) እንደ ኃያል ይመጣል፤ ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል እነሆ፥ ዋጋው (ብድራቱ) ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።
11 መንጋውን (ሕዝቡን) እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
12 ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን፣ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? (እርሱ ብቻ ነው!)

ጳውሎስ ሲናገር "ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን (የእግዚአብሔር ወልድን) ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ፣ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም (ከእምነት) ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ" ብሎአል (የሐዋርያት ሥራ 20፡26-30)። የማይቀለበሰው ዘላለማዊ እውነት ይህ ነው። "እንኪያስ እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?" (ገላትያ 4፡16፤ ዮሐንስ 8፡40፣ 45-47)

"ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ (በአሮጌው ኪዳን ዘመን) በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን? በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል። ዳሩ ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል፥ የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል። ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና" (ዕብራውያን 12፡25-29)

ሰዎች በልባቸው እርሱን እንደ እግዚአብሔር እንደሚያዩት፣ ወደፊት የሚመጣው ትውልድም እርሱን እንደ አምላክ እንደ ሚያመልከው ኢየሱስ በትክክል ያውቅ ነበር። ኢየሱስ የሰዎችን የልብ አሳብ ሁሉ ያውቅ ነበር (ዮሐንስ 2፡24-25)። ያ ብቻም አይደለም። በጊዜው "ኢየሱስ እና አምላክ እንዴት እኩል ይሆናሉ?" ብለው በግልጽ የሚጠይቁ ብዙ ተቃዋሚዎችም በኢየሱስ አጠገብ ነበሩ (ዮሐንስ 10፡33፤ ዮሐንስ 5፡18)። ሆኖም ይህን ሁሉ እየሰማ፣ ክፋት የሌለበት ታማኙ አስተማሪ ኢየሱስ "እንዳታመልኩኝ ተጠንቀቁ እኔ ሰው ብቻ ነኝ" ብሎ አላስተማረም። ከዚህ ይልቅ እውነታውን ሲያስረዳ፣ ሰዎች ሁሉ አብን የሚያከብሩትን ያህል እርሱንም እንዲያከብሩት በግልጽ ጠይቋል (ዮሐንስ 5፡22-24)። አማኞቹን ሁሉ በእጁ መዳፍ የያዘው ፈጣሪ አምላክ (ዮሐንስ 10፡28፤ ኢሳይያስ 49፥16) እርሱ ራሱ መሆኑንም ተናግሯል፤ አብ እና እርሱ ፍጹም አንድ መሆናቸውንም አስተምሯል (ዮሐንስ 10፡30)። ና ወንድም እጋብዝሃለሁ፤ ተንኮል እና ስህተት የሌለበትን ይህን የፍቅር አምላክ አብረን እናምልከው። ወድቀንም እንስገድለት። የዘላለም እጣህም ያማረ እንደ ሚሆን መቶ በመቶ አስረግጬ እነግርሃለሁ፤ ከአምላክህ ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም በደስታ ትኖራለህ። እምቢ ካልህ ግን ቢያንስ የምህረት በር ከመዘጋቱ (ከመሞትህ) በፊት እርሱን ይቅርታ ጠይቀህ እንድትመለስ እና የዘላለም እጣህን እንድታሳምረው እመክርሃለሁ (ዕብራውያን 9፡27፤ ሉቃስ 23፥39-43)

አንድ ጊዜ ኢየሱስ አሥር ለምጻሞችን ፈወሰ። ከተፈወሱት ከአስሩ መካከል አንደኛው በታላቅ ድምጽ እየጮኸ ተመልሶ መጣና በኢየሱስ (በእግዚአብሔር) እግር ስር ሰገደ። ታድያ ጌታ ኢየሱስ ምን ቢለው ጥሩ ነው? አዎን ሕጸጽ የሌለበት ታማኙ መምህር "ተው እኔም እንዳንተ ሰው ነኝና እኔን እንዳታመልክ ተጠንቀቅ" አላለውም። ይልቁንም እንዲህ አለው፦ አንተ መጥተህ ለእግዚአብሔር መስገድህ ተገቢ ነው፤ እነዚያ ዘጠኙስ ለምን መጥተው አልሰገዱልኝም?

(ጌታ ኢየሱስ) "ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት አሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤ እነርሱም እየጮኹ፦ ኢየሱስ ሆይ አቤቱ ማረን አሉ። አይቶም፦ ሂዱ፥ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ አላቸው። እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥ እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ። ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ? ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ (በእግሬ ፊት ሊሰግዱ) የተመለሱ አልተገኙም አለ። እርሱንም፦ ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው" (ሉቃስ 17፡12-19)

ልብ በል በተለይ በአዲስ ኪዳን ዘመን ማገልገል እና መስገድ ያለብን ለአምላክ ብቻ እንደሆነ፣ ፍጡርንም ከቶ ማገልገል እንደ ሌለብን በማስጠንቀቂያም ጭምር ተነግሮናል (ሮሜ 1፡25)። "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ" (ማቴዎስ 4፡10)። ደግሞም ሌሎች ታማኝ አገልጋዮች ሰዎችም ሆኑ መላእክት "እኛ ሰዎች ብቻ ነን፤ ወይም እኛ ባሪያዎች ነን፤ እኛን እንዳታመልኩ ተጠንቀቁ፤ ለእኛ አትስገዱ" እያሉ ይናገሩ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 10፡25-26፤ 14፡11-18፤ ራእይ 19፡10)። የእነርሱ ጌታ የሆነው ታማኙ እግዚአብሔር (ኢየሱስ) ግን ስግደትን ተቀበለ (ዘጸአት 20፡1-6)

ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ "በሰው ልጅ" አምሳል

ጌታ ኢየሱስ ራሱን "የአብርሃም ልጅ፣ የዳዊት ልጅ፣ ወይም የማርያም ልጅ" ብሎ ከቶ አይጠራም ነበር። ከዚያ ይልቅ፣ ከአብርሃም በፊት የነበረ የአብርሃም አምላክ (ዮሐንስ 8፡56-59) እርሱ መሆኑን፣ የዳዊት ጌታ፣ የማርያም ፈጣሪ እርሱ መሆኑን ያስተምር ነበር። በሌላ በኩል "የሰው ልጅ፣ የእግዚአብሔር ልጅ" እያለ ኢየሱስ ራሱን ይጠራ ነበር። እርሱ የሰው ልጅ (ሰው) የእግዚአብሔር ልጅ (እግዚአብሔር) ነው። መሲሃችን (አዳኛችን) ሁሉ የሚገዙለት አምልኮ የሚቀበል አምላክ ነው፤ እንዲሁም "የሰው ልጅ" ነው።

የዳንኤል ራእይ

ዳንኤል 7፡
9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም (እግዚአብሔር አብ) ተቀመጠ። ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ (የዙፋኑ) መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።
10 የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር፤ ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር፤ ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ ...
13 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም "የሰው ልጅ የሚመስል" (ፊልጵስዩስ 2፡7-8) ከሰማይ ደመናት ጋር (ከላይ ከሰማይ ወደ ምድር) መጣ (ራእይ 1፡7)። በዘመናት ወደ ሸመገለውም (ወደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ) ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት (ኢሳይያስ 11፡2፤ 61፡1፤ ሉቃስ 4፡17-19፤ ሉቃስ 4፡1፤ የሐዋርያት ሥራ 10፡38)
14 ወገኖች እና አሕዛብ፣ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ (ለእግዚአብሔር ወልድ) ይገዙለት ዘንድ ግዛት እና ክብር መንግሥትም ተሰጠው። ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።
15 በእኔም በዳንኤል በሥጋዬ ውስጥ መንፈሴ ደነገጠች፥ የራሴም ራእይ አስቸገረኝ።
16 በዚያም ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ ስለዚህ ሁሉ እውነቱን ጠየቅሁት፤ እርሱም ነገረኝ፥ የነገሩንም ፍቺ አስታወቀኝ ...
21 እነሆም፥ ያ ቀንድ (መንግስት) ከቅዱሳን ጋር ሲዋጋ አየሁ፥
22 በዘመናት የሸመገለው (እግዚአብሔር ወልድ ወደ ምድር) እስኪመጣ ድረስ (ራእይ 22፡12)፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ (ያ ቀንድ) አሸነፋቸውም ...
25 በልዑሉም (በእግዚአብሔር ወልድ) ላይ ቃልን ይናገራል (ራእይ 17፡14)፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል። ዘመናትን እና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመን እና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም (ለአመት እና ለሁለት አመታት፣ እና ለግማሽ አመት ማለት ለሦስት አመት ተኩል) በእጁ ይሰጣሉ።
26 ነገር ግን ፍርድ ይሆናል፥ እስከ ፍጻሜም ድረስ (የልዑሉ ቅዱሳን) ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል።
27 መንግሥትም፣ ግዛትም፣ ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ (ለልዑሉ) ይገዙለታል፤ ይታዘዙለትማል።
28 የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው።

ይገርማል፤ ይህ የዳንኤል ዘመን ገና የአሮጌው ኪዳን ዘመን ቢሆንም፣ ማለት በዚህ ጊዜ ኢየሱስ መሎኮታዊ ቃል ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆኖ የሚኖር ቢሆንም (ዮሐንስ 1፡1፤ ፊልጵስዩስ 2፡6)፣ ገና ስጋ ሆኖ በአካል ባይገለጥም (ዮሐንስ 1፡14)፣ ጌታ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ክፍል ላይ ወደ ፊት ሊሆን ያለውን ነገር ሲገልጥ እግዚአብሔር ወልድን "በሰው ልጅ አምሳል" ገልጾታል። ይህም ገና ወደ ፊት ለሚሆነው ጥላ የሆነ ትንቢታዊ እይታ ነው (ዕብራውያን 10፡1፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡10-12)። የሰዎች የመቼት (መቼ እና የት) ጥያቄ እዚህ ጋር ስፍራ የለውም። ታላቁ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለነቢያቱ አንዴ የተናገረውን ቃል ልክ እንደ ተፈጸመ አድርጎ ይቆጥረዋል (ኢሳይያስ 55፡10-11)። በመሆኑም ገና በጊዜው እስኪፈጸም ድረስ ሳይጠብቅ፣ አሁኑኑ እንደ ተፈጸመ አድርጎ ይናገራል። ምክንያቱም፣ ምንም እንኳ የሚፈጸምበት ጊዜ ቢለያይም፣ አምላክ አንዴ ተናገረ ማለት ሆነ ማለት ስለሆነ ነው (ማቴዎስ 21፡19)

ይቀጥላል ...
... የቀጠለ

"300 አመታት"

በመቀጠልም "ኢየሱስ ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ ካረገ 300 ዓመታት በኋላ የተደነገገን እምነት ይዘን..." በማለት ራስህን ስታታልል እና ከእውነቱ ለመሸሽ ስትሞክር ትታያለህ። መቼም ይሁን መቼ (ጥንትም ይሁን ዛሬ) ሰዎች የደነገጉትን የትኛውንም ነገር አትመን። አማኝ ከሆንህ ካንተ ጋር ያለው የቅርብህ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር (ማቴዎስ 28፡20) ሲናገርህ ያዳመጥከውን፣ ህያው ቃሉ (መጽሐፍ ቅዱስ) የሚነግርህን ዘላለማዊ እውነት ብቻ እመን፤ ይህ ያዋጣሃል፤ ያሻግርሃል፤ ድልን ይሰጥሃል። ሃሰተኛ አስተማሪዎችን ለመገሠጽ አማኞች ተሰባስበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መግለጫ ሊሰጡ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ተሰባስበው ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ሌላ መግለጫ ሊያወጡ ይችላሉ። የቱ ነው ትክክል? የሚለውን የምንመዝንበት "የመቅደሱ ሚዛን" (ዘጸአት 30፡13፣ 24) የእግዚአብሔር ሕያው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ራስህን አታታልል። ሰው ደነገገ እያልህ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አትሽሽ። ሰይጣንም እኮ መካድ ያልቻለውን ዘላለማዊ እውነት "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ፤ ማን እንደሆንህ አውቄያለሁ፤ የእግዚአብሔር ቅዱሱ" ሲል ተናግሯል (ማቴዎስ 8፡29፤ ማርቆስ 1፡24፤ 3፡11፤ 5፡7)። ታድያ ይኼ ማለት ሰይጣን ደነገገው ማለት አይደለም። ማንም ይናገረው ማን፣ መቼም ይናገረው የትም በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመዝነው ነገሩ ትክክል ሆኖ ከተገኘ ማመን ግዴታችን ይሆናል። አሊያም አናምንም ብለን አሽቀንጥረን መጣል ምርጫችን (መብታችን) ይሆናል፤ ይህን መብታችንን ብንጠቀመው ግን ዘላለማዊ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ ነው።

እንዲያው የሆነውስ ቢሆን "ኢየሱስ ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ ካረገ (ጥቂት) 300 ዓመታት" ብቻ በኋላ የነበረው ትምህርት ነው የሚታመነው? ወይስ ከ1900 አመታት ገደማ በኋላ አሜሪካውያኑ እነ ፓስተር ቻርለስ ራስል (ከ1879 ጀምሮ) እና እነ ጆሴፍ ኤፍ ራዘርፎርድ (ከ1917 ጀምሮ) በየጊዜው "እምነታቸውን" የበለጠ እያሳደጉ (በየጊዜው አዲስ ነገር እየጨመሩ) ያስተማሩት ትምህርት ነው የሚታመነው? ይሁን ሁለቱም ቢሆኑ በቃሉ ይመዘኑ። ቃሉ እውነት ነውና፤ ቃሉ ጥንታዊም አይደል ዘመናዊም አይደል ዘላለማዊ ነውና።

በእውነት አንተም እንዳልኸው፣ በቅድሚያ በውስጣችን የሞላነውን ምድራዊ እና ሰብአዊ "እውቀት" ጥለን፣ ያለማመን እልከኝነትንም አስወግደን "'እምነታችንን' ወደ መጽሐፉ" ማንበብ ትተን፣ ለመማር በተዘጋጀ ልብ "መጽሐፉን ብቻ ብናነብብ እውነታው ፍንትው ብሎ ይታየናል።"

ኢሳይያስ 48፡4
ኤርምያስ 3፡17
ሆሴዕ 4፡16
ዘዳግም 21፡18-21
መክብብ 7፡17።

ዕብራውያን 3፡
8-9 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት፣ የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት፣ በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
13 ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤
15 ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።

ዕብራውያን 4፡
7 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።

ያዕቆብ 1፡
21 ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
22 ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
23 ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
24 ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
25 ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ (ቃሉን) ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።

ራእይ 22፡
20 ይህን የሚመሰክር፦ አዎን በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና።
21 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
0 ድምጾች
ውድ ወዳጄ፣
ጌታ ኢየሱስ ራሱ አምላክ/እግዚአብሔር/ጌታ/ፈጣሪ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ (39ኙ ብሉይ ኪዳን እና 27ቱ አዲስ ኪዳን) ያስረዳል።

ኢየሱስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው

ዮሐንስ 1፡
1 በመጀመሪያው ቃል (ኢየሱስ) ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር (አብ) ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር (ወልድ) ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር (መንፈስ ቅዱስ) ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ (ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠረ)፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

ኤፌሶን 2፡
10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

ከእግዚአብሔር አብ ክብርን እና ምስጋናን የተቀበለ ብቸኛ አምላክ

ዮሐንስ 13፡
32 እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን (ክርስቶስን) ያከብረዋል፤ ወዲያውም ያከብረዋል።

ዕብራውያን 1፡
8 (እግዚአብሔር አብ ሲናገር) ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ (O GOD,)፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል (ዘላለማዊ ነህ) ፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ (መንፈስ ቅዱስ፣ ኢሳይያስ 61፡1 ሉቃስ 4፡17-19) ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ (ማቴዎስ 17፡5)
10 ይላል። ደግሞ:- ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ (አንተ ፈጣሪ አምላክ ነህ፤ አንተ ፈጠርካቸው)
11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።

2ኛ ጴጥሮስ 1፡
17 ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና።

ከኢየሱስ በቀር ሌላ የሚያድን የለም፤ አምላክም የለም

የሐዋርያት ሥራ 4፡
11 እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።
12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።

ኢሳይያስ 43:
11-12 እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ <<ምስክሮቼ ናችሁ>>፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ።

ኢሳይያስ 43፡
10 ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ <<ምስክሮቼ ናችሁ>> ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይሆንም።

ኢሳይያስ 44፡
8 አትፍሩ አትደንግጡም ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? <<እናንተ ምስክሮቼ>> ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም።

ራእይ 22፡
12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
13 አልፋ እና ዖሜጋ፥ ፊተኛው እና ኋለኛው፥ መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ።
14 ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፣ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
15 ... ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ።

የሐዋርያት ሥራ 1፡
8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም፣ በይሁዳም ሁሉ፣ በሰማርያም፣ እስከ ምድር ዳርም ድረስ <<ምስክሮቼ ትሆናላችሁ>> አለ።

ኢየሱስ/እግዚአብሔር/ መልካም እረኛችን ነው

መዝሙር 23፡ (ዳዊት ሲዘምር)
1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።

ዮሐንስ 10፡ (ራሱ እግዚአብሔር ወልድ ሲናገር)
11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል...
14-15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ፣ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ፤ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።

የኢየሱስ ቃል አያልፍም

ኢሳይያስ 40፡ (ነቢዩ ኢሳይያስ ሲናገር)
8 ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን (የእግዚአብሔር) ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

ማቴዎስ 24፡ (ጌታ ኢየሱስ ሲናገር)
35 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
ማርቆስ 13፡
31 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
ሉቃስ 21፡
33 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።

ጌታ ኢየሱስ ብቻ እውነተኛው አምላክ /the true God/ ሲሆን ከሌሎቹ ሐሰተኛ አማልክት (ከጣዖታት) ግን ልንጠበቅና ልንርቅ ይገባናል።

ይሁዳ 1፡
4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ Our God (ራእይ 22፡21) በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንን እና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ፣ ጌታ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ <<የማያምኑትን>> በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።

ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ሲመክረን፦

1ኛ ዮሐንስ 5፡
20 የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን። እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክ እና የዘላለም ሕይወት ነው (He is the true God and the eternal Life)
21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

ኢየሱስ ኃያሉ/ኃይለኛው እግዚአብሔር ነው፤ የዘላለም አባታችንም ነው

ኃያሉ አምላክ

ኢሳይያስ 9፡
6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት Mighty GodEternal Father፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ነህምያ 9፡
32 አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንን እና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅ እና <<ኃያል የተፈራኸውም አምላክ>> ሆይ፥ ...

ኢሳይያስ 10፡
21 የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።

ኤርምያስ 32፡
18 ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ስምህ ታላቅ እና ኃያል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

1ኛ ጴጥሮስ 5፡
6 እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው/ከኃያሉ/ ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
7 እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

የዘላለም አባት

ኤፈሶን 4፡
6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።

"ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ Mighty Godየዘላለም አባት Eternal Father ፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ፣ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል" (ኢሳይያስ 9፡6-7)

ዕብራውያን 2፡
14-15 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ (አባት) ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።

በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ መሎኮታዊ አባት አለን። እንጂ ሁለት ወይም ሦስት አባቶች የሉንም። መንፈሳችንን የወለደው (ዮሐንስ 3፡6) እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ "የመናፍስት አባት" ነው (ዕብራውያን 12፡9)። ስጋችንን የወለዱ ምድራዊ ወላጆች "የስጋችን አባቶች" (ዕብራውያን 12፡9) ናቸው። የምድራዊ ወላጆች አባትነት ጊዜያዊ እና በሞት ጊዜ የሚያበቃ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር ወልድ) ግን ዘላቂ እና አስተማማኝ፣ የማይጥል የማይከዳ የዘላለም አባት ነው (ኢሳይያስ 9፡6)። ይህ ማለት ክርስቶስ በሁኔታዎች ተመስርቶ ወይም ከጊዜ ጋር ተለውጦ "ከእንግዲህ ልጄ አይደለህም" የማይል፣ የማይተወን፣ የማይጥለን (ዮሐንስ 13፡1፤ ዕብራውያን 13፡5-6) እውነተኛ አፍቃሪ ወላጅ፣ የዘላለም አለኝታ መሆኑን ያሳያል።

እንዲሁም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት (በክርስቶስ በማመናችን) እግዚአብሔር አብ አባታችን ነው (ዮሐንስ 1፡12-13)በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ <<በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ>> ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን (ኤፌሶን 1፡5)<<በእምነት>> በኩል ሁላችሁ <<በክርስቶስ ኢየሱስ>> የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና (ገላትያ 3፡26-27)። ታዲያ ስንት አባቶች አሉን? አዎን፤ አንድ አባት ብቻ። በኤፌሶን 4፡4-6 ላይ እንደ ተጻፈው አንድ መንፈስ ... አንድ ጌታ ... አንድ አምላክ - ኤሎሂም (መንፈስ ቅዱስ ወልድ አብ) አንድ እግዚአብሔር የሁሉም አባት አለን።

ክርስቶስ ኢየሱስን በመቀበላችን እና በማመናችን በእርሱ በኩል አብ አባታችን ሆኖአል (ገላትያ 3፡26፤ ሮሜ 5፡10-11፤ ዮሐንስ 1፡12-13)። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ እንደ ሚያረጋግጡልን በክርስቶስ ውስጥ ካልሆንን አብ ከቶ አያስጠጋንም፤ አይቀበለንም፤ አያውቀንም (ዮሐንስ 14፡6፤ ዕብራውያን 7፡25፤ ዮሐንስ 3፡18፣ ዮሐንስ 3፡36)። አብ ወደ ተቀመጠባት ቅድስቲቷ ስፍራ መግባት እና ከእርሱም ጋር መሆን የሚፈቀድልን፣ ኃጢአተኛ በሆነው በራሳችን ስጋ ሳይሆን እጅግ ንጹህ በሆነው በኢየሱስ ስጋና ደም በኩል (በመጋረጃው በኢየሱስ ተሸፍነን) ከመጣን ብቻ ነው (ዕብራውያን 10፡19-20)። አብ ራሱ በፍቅሩ ቢስበንም አስቀድሞ ወደ ራሱ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ያመጣናል (ዮሐንስ 6፡44፤ ቆላስይስ 1፡13-14፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡9)። መቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ በጌታ ኢየሱስ እንዲያምን እና አምኖ እንዲድን አምላክ ራሱ መልአኩን ልኮ የመዳንን መንገድ አሳየው (የሐዋርያት ሥራ 10፡1-3፣ 22)። ለምን? ምክንያቱም ሰው መዳን የሚችለው ለኃጢአቱ ማስተሰርያ በሆነው በክርስቶስ ብቻ ነው (1ኛ ዮሐንስ 4፡10፤ የሐዋርያት ሥራ 4፡12፤ 1ኛ ዮሐንስ 5፡11)። አምላክ (እግዚአብሔር) ራሱ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ፈቃድ ይረዳናል። እንዲሁም የእግዚአብሔር ጸጋ የሚሰጠን እንደ አምላካችን "እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን" ነው።

ሮሜ 15፡
5-6 በአንድ ልብ ሆናችሁ፣ በአንድ አፍ እግዚአብሔርን፥ እርሱም <<የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት>> ፥ ታከብሩ ዘንድ፥ የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ <<እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ፈቃድ>> እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ መሆንን (መስማማትን) ይስጣችሁ። (አሜን።)

ከዚህ ክፍል በቀላሉ እንደ ምንረዳው በአንድ ልብ ሆነን፣ በአንድ አፍ እግዚአብሔር (አብን) እንድናከብር አምላክ ራሱ እርስ በርስ መስማማትን (በአንድ አሳብ መሆንን) ይሰጠናል። ነገር ግን አምላክ (ማለት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ) ይህን መስማማት የሚሰጠን ዝም ብሎ ሳይሆን "እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ (ወልድ) ፈቃድ" ነው። እንዲሁም ደግሞ ከዚህ ክፍል እንደ ምናየው እግዚአብሔር አብ ማለት ከኢየሱስ የተለየ ሌላ ወገን ሳይሆን፣ የራሱ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት" ነው። ኢየሱስ ሲናገር "እኔ እና አባቴ አንድ ነን" እንዳለው (ዮሐንስ 10፡30)

ሙሉ አዲስ ኪዳንን ስናይ "የኢየሱስ ክርስቶስ አባት" የሚለው ስያሜ የአብ መጠሪያ ወይም መለያ ሆኖ እናገኘዋለን። እንዲሁም ደግሞ "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ" የሚለው ስያሜ የወልድ መጠሪያ ወይም መለያ ሆኖ እናገኘዋለን። መንፈስ ቅዱስም "የኢየሱስ (የእግዚአብሔር) መንፈስ" ተብሎ ሲጠራ እናያለን (የሐዋርያት ሥራ 16፡7፤ ሮሜ 8፡9፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡11)። ይህም የሚያሳየን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የማይነጣጠሉ ፍጹም አንድ ወገን መሆናቸውን ነው።

በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ እኛን ኃጢአተኞችን የሚያድን ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ (ቲቶ 2፡11) አግኝተናል (ሉቃስ 1፡30፤ ሉቃስ 4፡22፤ የሐዋርያት ሥራ 15፡11፤ ሮሜ 1፡5፤ ሮሜ 3፡23-24፤ 6፡23፤ 12፡6፤ 2ኛ ተሰሎንቄ 1፡11-12፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡9)። "እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና፤ ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋ እና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ" (ዮሐንስ 1፡16-17)። እርሱ በጸጋው አዳነን። "ጸጋውንም በጥበብ እና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን" (ኤፌሶን 1፡8፤ የሐዋርያት ሥራ 2፡33)

"በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር (አብ) ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር (ወልድ) ነበረ... ቃልም ሥጋ (ሰው) ሆነ፤ <<ጸጋን እና እውነትንም>> ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን" (ዮሐንስ 1፡1፣ 14)

ይቀጥላል...
Oct 8, 2013 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
Feb 7, 2014 child of Jesus ታርሟል
... የቀጠለ

ይህ ጸጋ የተሰጠን ምን ስላደረግን ወይስ ምን ስለ ሆንን ነው? እውነተኛውን ሕያው አምላክ ክርስቶስን እየካድን "የአምላክ ምስክሮች ነን" ብለን ራሳችንን ስለ ሰየምን ነውን? አይደለም (ገላትያ 1፡6)። ወይስ መልካም ስላደረግን ወይስ በጾም በጸሎት ብዛት ነውን? አይደለም። በእውነተኛው አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመንን ብቻ ነው። ሐዋርያው እንዲህ አለ፦ "በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ" (1ኛ ቆሮንቶስ 1፡4፤ ኤፌሶን 6፡24)። በእርሱ ማመን ማለት ለጠላቶቹ የሞትን ያህል ይከብዳቸዋል፤ ለእኛ ለልጆቹ ግን እጅግ ጣፋጭ እና አስደሳች ነገር ነው።

ሐዋርያው እንዳለው በርግጥም "ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነ እና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ" (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15)። በእርሱ በወልድ የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድን፣ የሚያጸና እና የሚያሻግር (የሐዋርያት ሥራ 20፡32) ታላቅ ጸጋ፣ ፍቅር እና ምሪት እንዲያው በነጻ (ያለ ምንም ክፍያ) በየዕለቱ የሚፈስስልን ከየት/ከማን ነው? አዎን፤ ወሰን የሌለው ይህ ታላቅ ጸጋ (ሮሜ 5፡20-21፤ ያዕቆብ 4፡6) ሁልጊዜ የሚፈስስልን ከአንዱ አምላክ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ (ከኤሎሂም) መሆኑን እናውቃለን። ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና ፦ "የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም (የአብ) ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት (አብሮነት፣ ምሪት) ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን" (2ኛ ቆሮንቶስ 13፡14)። የእርሱ አብሮነት እና ሬድኤቱ አይለየን።

ጸጋው ሁሉ ነገራችን ነው። የሆንነውን የሆንነው ከጸጋው የተነሳ ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡10)፤ ያለንን ሁሉ ያገኘነውም ከጸጋው የተነሳ ነው። ያቆመን (1ኛ ጴጥሮስ 5፡12) እና ሰው ያደረገን፣ ያዳነን (ኤፌሶን 2፡8፤ ሮሜ 3፡23-24፤ 6፡23) እና እስከ መጨረሻውም የሚያጸናን ጸጋው ነው (ዕብራውያን 13፡9፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡10፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1፤ ቆላስይስ 3፡16)። በጸጋው ጸድቀናል፤ በጸጋው "የዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች" ሆነናል (ቲቶ 3፡6-7)። ጸጋው ይበቃናል (2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9)። የወደፊት ተስፋችንም ጸጋው ብቻ ነው (1ኛ ጴጥሮስ 1፡13)። ይህን ድንቅ ጸጋ ሁልጊዜ የሚሰጠን አምላክ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን (ራእይ 1፡5-6)። ታዲያ እንዲህ አይነት ታላቅ ጸጋ በየዕለቱ በገፍ የሚሰጠን እንዲያው ዝም ብሎ ወይም በአቦ-ሠጥ ሳይሆን፤ እንደ አምላካችን "እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን" ነው። ስለ ማይነገር ስጦታው ክርስቶስ (እግዚአብሔር) የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን (2ኛ ቆሮንቶስ 9፡15፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡18)

ኤፌሶን 4፡
7 ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን

"እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፣ በሚያስፈልገንም ጊዜ (በየትኛውም ጊዜ ሁሉ) የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ" (ዕብራውያን 4፡16)። አሜን።

ጸጋው እጅግ አስፈላጊያችን ስለ ሆነ መጽሐፍ በተደጋጋሚ በጸጋው ይመርቀናል፦

ሮሜ 16፡
20 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
24 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

1ኛ ቆሮንቶስ 16፡
23 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

ገላትያ 6፡
18 ወንድሞች ሆይ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን። (እንዲሁም ፊልጵስዩስ 4፡23፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡28፤ 2ኛ ተሰሎንቄ 3፡18፤ ፊልሞና 1፡25፤ ራእይ 22፡21)

መጽሐፉ ጣፋጭ እና ሕያው የሆነውን ዘላለማዊ መልእክቱን አጠናቅቆ ሊለየን ሲልም የመጨረሻውን ሰላምታ የሚሰጠን እና የሚሰናበተን የጸጋውን ቡራኬ በመናገር ፦ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን" በማለት ነው (ራእይ 22፡21)። ጸጋው ሁልጊዜ በየትኛውም ስፍራ ከእኛ ጋር የሚቀጥል ስለ ሆነ (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡21፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡22)፤ ድል ሰጪ እና አሻጋሪ ስለሆነ፤ ጌታ እስኪገለጥ ድረስ መጽሐፉ እኛን "ለእግዚአብሔር ጸጋ በአደራ" ይሰጣል። ይህም ጳውሎስ የኤፌሶንን ክርስቲያኖች ሲለያቸው እነርሱን "ለጸጋው ቃል አደራ" እንደ ሰጣቸው ነው (የሐዋርያት ሥራ 14፡26፤ 15፡40፤ 20፡32)። "እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም" (1ኛ ቆሮንቶስ 1፡7)። አሜን።

ይህ ታላቅ ጸጋ እንዳረፈብህ በምን ታውቃለህ? ጸጋው ካረፈብህ የሌላ የማንም ሳይሆን የጌታ ኢየሱስ ምስክር ትሆናለህ። "ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ (ምክንያቱም) በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው" (የሐዋርያት ሥራ 4፡33)። ጸጋው ካረፈብህ ሌላ ነገር እየሰበክህ ውዷን እና ትንሿን እድሜህን አታባክንም፤ የአምላክህን ባለጠግነት ይኼውም "ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት" ብቻ ትሰብካለህ (ኤፌሶን 3፡8-9)። ምክንያቱም "አንዱ ጌታ ኢየሱስ የሁሉ ጌታ ነውና አምነውት ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነውና" (ሮሜ 10፡12)

"ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት (ይህ የክርስቶስ ባለጠግነት) ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ <<ጸጋ>> ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለእኔ ተሰጠ" (ኤፌሶን 3፡8-9)

ኢየሱስ አምላካችን እና አባታችን ራሱ ጌታችንም ነው

1ኛ ተሰሎንቄ 3፡
11 አምላካችን እና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እናንተ መንገዳችንን ያቅና፤ (ነጠላ መሆኑን አስተውል - ያቅኑ አይልም ያቅና ይላል፤ ምክንያቱም ስለ አንዱ አምላክ ስለ ክርስቶስ (እግዚአብሔር) ብቻ እየተናገረ ነው -ይሁዳ 1፡4)
12-13 ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር ወልድ) ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችን እና በአባታችን (በመንፈስ ቅዱስ እና በአብ) ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን (እንደ ምናፈቅራችሁ) ጌታ (አምላካችን እና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ) እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን፣ ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ፤ ይጨምርም።

አንድ መንፈስ አንድ ጌታ አንድ አምላክ (ኤሎሂም) የሁሉም አባት

ኤፌሶን 4፡
4 በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ (መንፈስ ቅዱስ) አለ፤
5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።
7 ነገር ግን እንደ ክርስቶስ (እንደ አምላክ) ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን።

ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ አምላክ

ሮሜ 9፡
5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ (የተመሰገነ) አምላክ (እግዚአብሔር) God ነው፤ አሜን።

ዮሐንስ 3፡
31 ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው (ክርስቶስ) ከሁሉ በላይ ነው

ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ኪዳን አንድ እውነት ያስተምረናል። ይኸውም እግዚአብሔር አብ ወይም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ዘመን የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ... የያዕቆብ... የኤልያስ... አምላክ፣ የእስራኤል አምላክ... የሠራዊት አምላክ... ወዘተ እየተባለ በብዙዎች ስም (ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ስም) መጠራቱ አሁን በአዲስ ኪዳን እንደ ቀረ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር አምላክ የማንም ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ አማኞችም በኪዳናቸው መሰረት መናገር እና መጸለይ ይገባቸዋል፤ እንጂ የአሮጌውን ኪዳን ስርዓት የሙጥኝ ማለት አይገባቸውም። ማንም አምላክን ማስደሰት የቻለ የለም፤ ኢየሱስ ብቻ ግን አባቱን ፍጹም አስደሰተ። ማንም አምላክን ታዝዞ በመታዘዝ የፈጸመ አልተገኘም፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ግን ብቻውን አምላክን ፈጽሞ ታዘዘ። መታዘዝ የሚያስከፍለውን ዋጋ፣ ውርደት እና መከራ ሁሉ በትጋት እና በፈቃደኝነት ከፈለ።

ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔርነቱ ክብር ከሚኖርበት የከፍታ ስፍራ ዝቅ ብሎ ሊመጣ ታዛዥ ሆነ። እንደ ሰው፣ እንዲያውም ከሰውም ዝቅ ብሎ እንደ ባርያ ታዘዘ (ፊልጵስዩስ 2፡9-11፤ መዝሙር 22፡1-8)። እኛ ሰዎች ኃጢአተኞች ነበርን። እርሱ ግን ከኃጢአተኞችም በታች ወርዶ ኃጢአት ሆነ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)፤ እኛ በበደላችን ምክንያት ርጉሞች ነበርን (ገላትያ 3፡10)። እርሱ ግን ከርጉሞች በታች ወርዶ ራሱ ርግማን ሆነ (ገላትያ 3፡13)። ይህ ሁሉ ዋጋ መክፈል ስለምን? አዎን ፍቅር ግድ ስላለው ነው። በእኛ ፍቅር፣ በእኔ እና በአንተ ፍቅር ልቡ ስለተያዘ እኛ በኃጢአታችን ምክንያት እንዳንጠፋ፣ እዳችንን ለመክፈል እርሱ ይህን ሁሉ ዋጋ ስለ እኛ ለመክፈል ፈቃደኛ ሆነ (ቲቶ 2፡14)። ታላቁ ፍቅር ይኼ ነው፤ በሰማይም ሆነ በምድር ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም (ዮሐንስ 15፡13)። ከዚህ ሁሉ ስኬታማ ቤዛነት በኋላ አብ ራሱ ኢየሱስን ከፍ ከፍ አደረገው (ፊልጵስዩስ 2፡9-11፤ የሐዋርያት ሥራ 5፡31)

ብዙዎች ዛሬ "አምላክ ፍቅር ነው" በማለት እውነታውን ይናገራሉ፤ ጥቅሱንም እንደ ዓረፍተ ነገር ይጠቅሳሉ። ይሁን፤ ያ ጥሩ ነው። የሚያሳዝነው ግን ምን መሰለህ? እነዚህ ሰዎች ፍቅር የሆነው ይህ እግዚአብሔር ማን መሆኑን (ኢየሱስ መሆኑን) አለማወቃቸው (ዮሐንስ 9፡29፤ 2ኛ ተሰሎንቄ 1፡8፤ ዮሐንስ 14፡5፤ ዮሐንስ 16፡3፣ 18)፣ እርሱን አለማመናቸው (ዮሐንስ 3፡36)፣ በእርሱ አለመታመናቸው (1ኛ ጴጥሮስ 1፡13፤ ፊልጵስዩስ 3፡3፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡1)፣ ታላቁን ፍቅሩን አለመቀበላቸው፣ ከታላቁ ፍቅሩም ተቋዳሽ አለመሆናቸው (መኃልይ 1፡2፣ 4) እና ለእርሱ ያላቸው ፍቅርም የአፍ ብቻ መሆኑ ነው (ራእይ 2፡4)

ይሁንና ኢየሱስ በዚህ ምድር ሳለ እግዚአብሔር አብን "አባት ሆይ" እስከ ሚል ድረስ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን "አምላኬ አምላኬ" እስከ ሚል ድረስ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ፈጽሞ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። በአምላካችን (በመንፈስ ቅዱስ) እና በአባታችን (በአብ) ፈቃድ እግዚአብሔር ወልድ ራሱን ስለ እኛ ሰጠ (ገላትያ 1፡4)። ከዚያም በኋላ አባቱ ኢየሱስን (ወልድን) ሲያሞግሰው እና ስለ እርሱ ሲመሰክር "አምላክ ሆይ O God፣ ዙፋንህ እኮ እስከ ዘላላም ድረስ ነው፤ አንተ በጣቶችህ ሰማይን ፈጥረሃል፤ ምድርንም መስርተሃል" ይለዋል (ዕብራውያን 1፡8-12)

ለምንድር ነው ሰው የራሱን ሃይማኖት ከመቀየር ይልቅ መጽሐፍ ቅዱሱ ቢቀየር የሚመኘው? መጽሐፉ ኢየሱስ ፈጣሪ አምላክ ነው ይላል። ደግሞም ኢየሱስ በኋለኛው ዘመን እኛን ለማዳን ሰው ሆነ ይለናል። ሰው በሆነ ጊዜም ጋጠ ወጥ እና አምላክ የለሽ /atheist/ አመጸኛ ወይም ከሃዲ አልነበረም። ይልቁንም አምላክ ያለው እና አምላክ ሁልጊዜም የተደሰተበት፣ አምላክ ያላዘነበት እንዲሁም አንዳች ነቀፋ ያላገኘበት ንጹሁ ሰው፣ በታሪክ ብቸኛው ሰው ኢየሱስ መሆኑን መጽሐፉ ይገልጣል። ያ ብቻም አይደለም ሰዎችም (ከሳሾቹም ሳይቀር)፣ ሰይጣን እና አጋንንቱም አንዳች ነቀፋ ሊያገኙበት አልቻሉም።

አምላክ

ማርቆስ 9፡
7 ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው። ከደመናውም፦ የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

ሉቃስ 9፡
34 ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
35 ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
36 ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።

ማቴዎስ 3፡
17 እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

ማቴዎስ 17፡
5 እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

2ኛ ጴጥሮስ 1፡
17 ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርን እና ምስጋናን ተቀብሎአልና።

ይቀጥላል...
... የቀጠለ

ሰዎች

ማቴዎስ 27፡
24 ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ፦ "እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ" ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።

ሉቃስ 23፡
4 ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፦ በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ።
14 ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት፤ እነሆም፥ በፊታችሁ መርምሬ ከምትከስሱበት ነገር አንድ በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም።
15 ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም።

22 ሦስተኛም፦ ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም።

ዮሐንስ 18፡
38 ጲላጦስ፦ እውነት ምንድር ነው? አለው። ይህንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጥቶ፦ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም።

ዮሐንስ 19፡
6 ጲላጦስም፦ እነሆ ሰውዬው አላቸው። የካህናት አለቆችና ሎሌዎች ባዩትም ጊዜ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት አላቸው።

ማቴዎስ 27፡
3 በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦
4 ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን፦ እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉት።

አጋንንት

ማርቆስ 1፡
24 እርሱም፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ።
25 ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።

ሉቃስ 4፡
34 ተው፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ አለ።
35 ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።

ኢየሱስ እንዲህ ዓይነት ፍጹም ሰው ነበረ፤ ነው። ከሰዎችም ሁሉ ይለያል። ከነቢያት፣ ከፋላስፋዎችም ሁሉ ይበልጣል። ምክንያቱም እነዚያ ሁሉ ተንኮል አለባቸው ኢየሱስ ግን ተንኮል አልተገኘበትም። እነዚያ ሁሉ ሰውን ይጠሉ፣ ይሰድቡ፣ ወይም ይገድሉ፣ ወይም የራሳቸውን ትምህርት ያልተቀበለውን ሰው ያሳድዱ ነበር። በግድ የራሳቸው ተከታይ ያደርጉ ነበር። ኢየሱስ ግን ማንንም አልጠላም፤ ማንንም አልተሳደበም (ዮሐንስ 8፡15)፣ ማንንም አልዛተም፣ ማንንም አልገደለም። ያ ብቻ አይደለም እነዚያ ሁሉ ሰይፍና ጦር ይመዝዙ ነበር። ኢየሱስ ግን "ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ" ብሎ አስተማረ (ማቴዎስ 26፡52)። ኢየሱስ አንድም ሰይፍ ሳያነሳ አንድም ጦር ሳያስከትት ወይም ታጣቂዎችን ሳያሰልፍ፣ በፍቅሩ እና በውበቱ ብቻ እየማረከ (እያሸነፈ) ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ቢሊዮኖችን የራሱ አደረገ (እኔንም ጨምሮ ማለት ነው፤ ክብር ለእርሱ ይሁንለት፤ አሜን)

ፍጹም ሰው

1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡
5 አንድ እግዚአብሔር (አምላክ) አለና፥ በእግዚአብሔር (በአምላክ) እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው (አስታራቂው) ደግሞ አንድ (ብዙ ሳይሆን አንድ ብቻ) አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

በዚህ ቃል እንደምናየው፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ከፍጹም ሰውነቱ አንጻር ስናየው እርሱ እጅግ ቅዱስ በሆነው አምላክ (በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) እና ኃጢአተኛ በሆኑት ሰዎች መካከል የሚቆም ብቸኛው (አንዱ) መካከለኛ፣ አስታራቂ፣ አማላጅ (ዕብራውያን 7፡25)፣ አቀራራቢ፣ ብቸኛው ሊቀካህናት ነው (ዮሐንስ 14፡6፤ ሮሜ 8፡34)። አንድ እግዚአብሔር ብቻ እንዳለን፣ እንደዚያው ያህል መካከለኛ አስታራቂውም አንድ ብቻ መሆኑን ማወቅ አለብን፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው ማለት ነው)። ፍጹም ሰው ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ በቀር ሌሎች ሁሉ፣ ነቢያትም ሐዋርያትም ቢሆኑ፣ እንኳን ለእኛ አማላጅ ወይም አስታራቂ ሊሆኑ፣ ራሳቸውንም መርዳት ወይም ማዳን የማይችሉ ለራሳቸውም አዳኝ የሚያስፈልጋቸው ናቸው (ሮሜ 7፡24-25፤ ማርቆስ 8፡37፤ ማቴዎስ 16፡26፤ ዮሐንስ 5፡45፤ ሉቃስ 16፡25-31፤ ራእይ 6፡9-10፤ ሮሜ 11፡2-4)። ምክንያቱም "ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል። (ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ) በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት (በማመን ብቻ) የሚገኝ፣ በደሙም (ማለት በኢየሱስ መስዋዕትነት) የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው። ይህም በፊት የተደረገውን (ያደረግነውን) ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው (እግዚአብሔርም) ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው። ራሱም ጻድቅ እንደሆነ (እንደዚያው ያህል) በኢየሱስም የሚያምነውን እንደሚያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን (እግዚአብሔር) ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው" (ሮሜ 3፡22-26)

በኢየሱስ ፍጹም ሰውነት (ዮሐንስ 1፡14) አማካይነት በአንዱ መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ወደ አብ ለመግባት ድፍረት አለን። "በእርሱ (በወልድ) ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና" (ኤፌሶን 2፡18)። "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ (በፍጹም ሰውነቱ) ወደ ቅድስት (አብ ወደ አለባት ስፍራ) በኢየሱስ ደም፣ በመጋረጃው ማለት በሥጋው (በፍጹም ሰውነቱ) በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ በእግዚአብሔርም (በአምላክ) ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን (ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው) ስላለን፥ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን (በኢየሱስ ደም) ተረጭተን (1ኛ ጴጥሮስ 1፡1-2)፣ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ (በክርስቶስ ኢየሱስ ቃል) ታጥበን (ዮሐንስ 15፡3)፣ በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ። የተስፋን ቃል የሰጠው (አምላክ) የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ። ለፍቅር እና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ" (ዕብራውያን 10፡19-24)

የሐዋርያት ሥራ 2፡
22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች፣ በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤
23 እርሱንም፣ በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።
24 እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
23 ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


ይቀጥላል ...
0 ድምጾች
የቀጠለ...

1ኛ ዮሐንስ 3፡
5 እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
22 እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም።

ሉቃስ 23፡
15 ሄሮድስም ደግሞ (በኢየሱስ ላይ) ምንም አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም።
41 ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ (ኢየሱስ) ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው።

ክርስቶስ ስለ ራሱ ፍጹምነት /ንጽህና/ ይናገራል

ዮሐንስ 8፡
46 ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም? (ዛሬም ቢሆን ጌታ ኢየሱስ ሰዎችን እንዲህ ይጠይቃል)

ዮሐንስ 8፡
29 የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም።

ዮሐንስ 10፡
25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ አታምኑምም። እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
26 እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
30 እኔ እና አብ አንድ ነን።
31 አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
32 ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
33 አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

በመጨረሻም ኢየሱስ ሰው በሆነ ጊዜ አምላክ የለሽ እና ሕገ ወጥ ሳይሆን አምላክ ያለው ፍጹም ሰው መሆኑን መጽሐፉ ያስረዳል። ደግሞም ኢየሱስ ሥጋ ከመልበሱ በፊት፣ ሥጋ ከለበሰም በኋላ የሁሉ ጌታ የሆነ ፈጣሪ አምላክ መሆኑን መጽሐፉ ይገልጣል። ስለዚህ የመጽሐፉ አማኝ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ፣ ሙሉ መጽሐፉ የሚነግረውን ማመን አለበት እንጂ አንድ ጥቅስ ብቻ (ወይም ጥቂት ጥቅሶችን ብቻ) መርጦ ማመን እና ለሎቹን ጥቅሶች መሸሽ/መፍራት የለበትም።

የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው የስብዕና ሥላሴ እና የመሎኮት አንድነት አስተምህሮም ቢሆን ራሱ ኢየሱስ ያስተማረው ሰማያዊ እውነት ነው እንጂ ቤተ ክርስቲያን የወለደችው ተረት አይደለም። (ሥላሴ ማለት በግዕዝ ሦስትነት ማለት ነው)። ታላቁ መምህር እና ገናናው ጌታ፣ ሁልጊዜ እውነትን ብቻ የሚያስተምር አባት ክርስቶስ ኢየሱስ በትዕዛዙ፣ በትምህርቱ እና በኑሮው የስብዕና ሦስትነትን የመሎኮት አንድነትን አስተምሯል።

(1) በትዕዛዙ

ማቴዎስ 28፡
19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ (1) በወልድ (2) እና በመንፈስ ቅዱስ (3) ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

(2) በትምህርቱ

ዮሐንስ 15፡
26 ዳሩ ግን እኔ (1) ከአብ (2) ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ (3) በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።

ዮሐንስ 8፡
16 የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው።
17 የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል።
18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ (1)፥ የላከኝም አብ (2) ስለ እኔ ይመሰክራል። "እኔ እና አብ አንድ ነን" (ዮሐንስ 10፡30)

(3) በኑሮው

ማቴዎስ 3፡
16 ኢየሱስም (1) ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ (2) እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
17 እነሆም፥ ድምፅ (3) ከሰማያት መጥቶ ፦በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

እንዲሁም መጽሐፍ እግዚአብሔር አብ አባታችን መሆኑን (ልጆቹ መሆናችንን) ፣ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን መሆኑን (ባሪያዎቹ መሆናችንን)፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪያችን/አምላካችን/ መሆኑን (ተከታዮቹ መሆናችንን) ይገልጣል።

ሮሜ 8፡
14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።

ገላትያ 1፡
3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን። (አሜን።)

የኢየሱስ ክርስቶስ (የእግዚአብሔር) ባሪያዎች ነን

ሉቃስ 12፡ (ጌታ ኢየሱስ ሲናገር)
35 ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
36 እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ።
37 ጌታቸው (ኢየሱስ) በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
38 ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው።

ፊልጵስዩስ 1፡
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስ እና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳት እና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን (አሜን)

ዕዝራ 5፡
11 እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን

ዳንኤል 3፡
26 የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደ ሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ፦ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም፥ ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።

የሐዋርያት ሥራ 16፡
17 እርስዋ ጳውሎስን እና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
16 (ከኃጢአት) አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።

ራእይ 2፡ (ጌታ ኢየሱስ ሲናገር)
20 ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑ እና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውን እና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ።

ሮሜ 1፡
1-2 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ፣ (ጌታ) በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።

2ኛ ጴጥሮስ 1፡
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ እና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ (our God and Saviour Jesus Christ) ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ...

ያዕቆብ 1፡
1 የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ይሁዳ 1፡
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ...

ሉቃስ 17፡
6 ጌታም (ኢየሱስ) አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል <<እምነት ቢኖራችሁ>> ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።
7 ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው?
8 የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለው አይደለምን?
9 ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?
10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ <<የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል>> በሉ።

የእርሱን የበላይ ገዥነት አልቀበል ያሉትን ሰዎች በመጨረሻው ቀን እንደ ሚበቀላቸውም ጌታ ተናግሯል፦

ሉቃስ 19፡
27 ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።

2ኛ ቆሮንቶስ 13፡
14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
Oct 9, 2013 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
Jan 11, 2014 child of Jesus ታርሟል
ለዚህ ምላሽ የሰጠሁትን መልስ ከታች ማግኘት ይቻላል።

ሰላም
0 ድምጾች
child of Jesus

በመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ላይ ቃላትን ሲጨምሩ ጠንቀቅ እያሉ ቢሆን መልካም ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ዮሐንስ 1፡1-3 ላይ አብ፣ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ የሚሉ ቃላቶች የሉም።

የቁጥር 1 ሦስተኛ ክፍል፡ "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" በሚለው አተረጓጎም (language translation) ሁሉም ተርጓሚዎች አይስማሙም። ለምን? ምክንያቱም የዮሐንስ ወንጌል በተጻፈበት ኮይነ ግሪክኛ ያለ የሰዋሰው ህግ ይህን ድምዳሜ እንዳንሰጥ ስለሚያደርገን። "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር (ግሪክኛ፣ "ቶን ቴኦን") ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር (ግሪክኛ፣ "ቴኦስ") ነበረ።" በዚህ ጥቅስ ላይ ቴኦስ (አምላክ) የሚለው የግሪክኛ ስም በሁለት መንገዶች ተቀምጧል። ከመጀመሪያው ስም በፊት ቶን የሚል የግሪክኛ ጠቃሽ አመልካች (article) ገብቷል፤ በመሆኑም በዚህ ቦታ ላይ ቴኦስ የሚለው ቃል የታወቀን አካል ማለትም ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ያመለክታል። ከሁለተኛው ስም በፊት ግን ምንም ዓይነት ጠቃሽ አመልካች አልገባል፤ ይህም ባህርይን ያመለክታል። እዚህ ቦታ ላይ ጠቃሽ አመልካች ያልገባው በስህተት ነውን?

የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው ኮይኔ ተብሎ በሚጠራው ተራው ህዝብ በሚግባባበት ግሪክኛ ነበር፤ ይህ ዓይነቱ ግሪክኛ የጠቃሽ አመልካችን አጠቃቀም በተመለከተ ግልጽ የሆነ የሰዋስው ሥርዓት አለው። የአንድ ዓረፍተ ነገር ባለቤትም ሆነ ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ካላቸው "ሁለቱም የታወቁ፣ አንድ ዓይነትና ምንም ልዩነት የሌላቸው ናቸው፤ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ሊተካው ይችላል።" ለምሳሌ ማቴዎስ 13፡38 "እርሻውም (ግሪክኛ፣ ሆ አግሮስ) ዓለም (በግሪክኛ፣ ሆ ኮስሞስ) ነው" ይላል። ከሰዋሰው ህግ አንጻር ይህን ዓረፍተ ነገር "ዓለሙም ዕርሻው ነው" ብሎ ማስቀመጥም ይቻላል።

ይሁንና በዮሐንስ 1፡1 ላይ እንደምናገኘው የአንድ ዓረፍተ ነገር ባለቤት ጠቃሽ አመልካች ኖሮት ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ባይኖረውስ? "እንዲህ ባለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ ባለቤቱና ተሳቢው አንድ ዓይነት፣ እኩል እንዲሁም ምንም ልዩነት የሌላቸው አይደሉም።" በተመሳሳይ መልኩ የተቀመጠን ሌላ ጥቅስ ብንመለከት፡
Quote:
የማርቆስ ወንጌል 8፡33 እርሱ ግን ዘወር አለ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና። ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን (ግሪክኛ፣ "ዲያብሎስ")፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና አለው።

በምሳሌ ለማስረዳት "አምላክ ብርሃን ነው" የሚለውን 1ዮሐንስ 1፡5ን እንውሰድ። እዚህ ጥቅስ ላይ "አምላክ" በግሪክኛ ሆ ቴኦስ ሲሆን ጠቃሽ አመልካች አለው። ይሁን እንጂ "ብርሃን" በግሪክኛ ፎስ የሚለው ቃል ጠቃሽ አመልካች አልገባለትም። ምንጊዜም ቢሆን አንድ ሰው፣ አምላክ ብርሃን እንደሆነ መናገር ይችላል፤ ብርሃን አምላክ እንደሆነ ግን መናገር የሚቻለው ሁልጊዜ አይደለም። ሌላ ምሳሌ "አምላክ (ሆ ቴኦስ) መንፈስ ነው" ዮሐንስ 4፡24፣ "አምላክ (ሆ ቴኦስ) ፍቅር ነው" 1 ዮሐንስ 4፡16። በሁለቱም ጥቅሶች ላይ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ጠቃሽ አመልካች ያለው ሲሆን "መንፈስ" እና "ፍቅር" የሚሉት ተሳቢዎች ግን ጠቃሽ አመልካች አልገባላቸውም። ስለዚህ የዓረፍተ ነገሮቹ ባለቤትና ተሳቢዎች እርስ በርስ ሊተካኩ አይችሉም። እነዚህ ጥቅሶች "መንፈስ አምላክ ነው" ወይም "ፍቅር አምላክ ነው" ተብለው ሊቀመጡ አይችሉም። ይችላሉ እንዴ?

ቁጥር 3 ላይ "ሁሉ በእርሱ ሆነ" የሚለውን "ኢየሱስ ፈጣሪ ነው" ለማለት ተጠቅመዋል። ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጽፍ በግሪክኛ "ዲያ አውቶው" የሚል ቃል እዚህ ቦታ ላይ ተጠቅሟል። ይህ ምን ማለት ነው? ዲያ የሚለው ቃል ትክክለኛ ፍቺ "በ ... በኩል" (በእንግሊዝኛ THROUGH) ማለት ነው። ይህን በመከተል የ1954ቱ መጽሐፍ ቅዱሳችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ "በእርሱ በኩል" ብሎ ተርጉሞታል። ለምሳሌ ያህል፦
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 1፡7 "ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።"
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 2፡22 "የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤"
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 3፡16 "በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።"
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 13፡38-39 "እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።"
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8፡6 "ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።"
Quote:
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡9 "በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።"

ዕብራውያን 1፡1-2 ላይ "እግዚአብሔር ... ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ... ተናገረን" በማለት ፈጣሪ በኢየሱስ ተጠቅሞ ዓለምን ፈጠረ ከሚለው ጋር አያይዘን ዮሐንስ 1፡3ን በትክክል ስንተረጉመው (translation) "ሁሉ በእርሱ በኩል ሆነ" ይለናል ቃሉ።


ኤፌሶን 2፡10፦ ይህ ጥቅስ ስለአዲስ ሰውነት የሚያወራ እንጂ በዘፍጥረት ላይ ስለተጻፈው ፍጥረት አይደለም። ደግመው ሙሉ ምዕራፉን ያንብቡት።

እርስዎ እንዳሉት የሐዋርያት ሥራ 4፡11-12 እና ኢሳይያስ 43:11-12 እንደሚነግሩን፡ የሚያድን አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ የሚያድነን ግን በክርስቶስ በኩል ነው። ልጁን ልኮ እንዲሞት ያደረገውም ለዚህ ነው። ዮሐንስ 3፡16፦ "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።" በማለት የዚህን ዝምድና ያስረዳል።

አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ፡ የእስራኤል መስፍን የነበረው ኦትንኤል (ጎቶንያል) አዳኝ ተብሎ ነበር (መሳፍንት 3፡9) ናኦድ የተባለ መስፍንም በተመሳሳይ አዳኝ ተብሏል (መስፍንት 3፡15)። እንግዲህ ምን እንላለን? ጎቶንያል እና ናኦድ እግዚአብሔር ነበሩ ወይስ እግዚአሔር በነዚህ ሰዎች ተጠቅሞ እስራኤልን ከጠላቶቻቸው አዳነ እንላለን? - ጆሮ ያለው ይስማ።


ሌላው በይሁዳ 4-5 ላይ ያለው ነው። አዎን፣ ይሁዳ 4-5 እንዳለው ኢየሱስ በዋጋ የገዛን ብቸኛ ጌታችን ነው። (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡20፣ 7፡23፤ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡1፤ ኤፌሶን 4፡5) ነገር ግን በሐዋርያት ሥራ 2፡36 ላይ "ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው" የሚገልጸውን ክፍል አብረው ቢገልጹት ሃሳቡ ምንኛ የተሟላ ይሆን ነበር!

1ኛ ዮሐንስ 5፡20 ላይ ያለው ሐሳብ ምንድነው? ስለ ሁለት ወይስ አንድ አካል የሚያወራው? ሐዋርያው ዮሐንስ "ልጁ" ብሎ እየተናገረ ያለው "ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ" ስለሆነለት አካል እንደሆነ ነግሮናል። በአጽንዖት ያንብቡት። ሐዋርያው ዮሐንስ ኢየሱስ ራሱ በዮሐንስ 17፡3 ላይ አባቱን "ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ" በማለት የተናገረውን ቃል እየተጻረረ አልነበረም። ነጥቤ ግልጽ ካልሆነልዎ ጥቅሱን በሌሎች ቋንቋዎች ለምሳሌ በእንግሊዝኛ ይመልከቱት።

ሥላሴ የቤተክርስቲያን ተረት ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንደሆነ ተናግረው ማስረጃዎትን አቅርበዋል። ከማስረጃዎ አንዱ በጥቅሉ ኢየሱስን እግዚአብሔርንና መንፈስ ቅዱስን በአንድነት የተጠቀሱባቸውን ቦታዎች ዘርዝረዋል። ጥሩ እይታ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ አብርሃም ይስሃቅና ያዕቆብን በአንድነት በብዙ ቦታ ላይ ይጠቅሳል። ምናልባት አንድነት በሦስትነት ያላቸው የሆነ ነገር ይሆኑ? ያዕቆብ ዮሐንስና ጴጥሮስ በተደጋጋሚ በአንድ ላይ ተጠቅሰዋል። እነዚህስ አንድነት በሦስትነት ያላቸው የሆነ ነገር ይሆኑ? ሐዋርያው ጳውሎስ በ1 ጢሞቴዎስ 5፡21 ላይ ኢየሱስን እግዚአብሔርንና መላእክትን በአንድነት ጠቅሷል። እንግዲያው መላእክቱም የሥላሴ ክፍል ይሆኑ?

ኢየሱስ ፍጹም ሰው ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር አምላኩ ነበር ብለዋል። ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላስ? ቀድሞ ሳውል ይባል የነበረው ጳውሎስ ክርስቲያን የሆነው ኢየሱስ ወደሰማይ ከሄደ በኋላ እንደነበር የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ይነግረናል። በመሆኑም ጳውሎስ በአሁን ጊዜ የጻፋቸው ዓረፍተ ነገሮች ኢየሱስ በሰማይ እያለ ያለውን ዝምድና ያሳይል። ታዲያ ጳውሎስ እግዚአብሔር ለኢየሱስ አምላኩ ነው ሲል ለእርሶ ምን ማለት ነው? (2 ቆሮንቶስ 1፡3፣ ኤፌሶን 1፡3፣ 17) ኢየሱስ የበታቹ እንደሆነና ለእግዚአብሔር አብ እንደሚገዛ የሚናገረውስ ነገር ምን ማለት ነው? (1ኛ ቆሮንቶስ 11፡3፤ 3፡23፤ 15፡23-28) የሥላሴ አማኞች ስለ ሥላሴ ሲነሳ መቼት የሚባል ነገር ባይኖር ደስተኞች ናቸው። ከዘፍጥረት ጠቅሰው "ኢየሱስ በስጋው ወራት ሳለ የተነገረ ነው" ቢሉ ይቀላቸዋል! ኢየሱስ ሰው ሲሆን ከመላእክትም እንኳ አንሶ እንደነበር መጽሐፉ ይናገራል። (ዕብራውያን 2፡7) ወደሰማይ ከሄደ በኋላ ግን ከነርሱ እጅግ እጅግ ይበልጣል። (ዕብራውያን 1፡4)

በእርሶ የኤቲስት ትርጉምና ትንታኔ መሰረት እግዚአብሔር መቼውንም አምላክ ኖሮት አያውቅም፣ ስለዚህ አምላክ የለሽ (ኤቲስት) ነው እንበለው? መልሶ ወዴት እንደሚያመራ በደንብ ያጢኑት።

"የመጽሐፉ አማኝ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ ሙሉ መጽሐፉ የሚነግረውን ማመን አለበት እንጂ አንድ ጥቅስ ብቻ (ወይም ጥቂት ጥቅሶችን ብቻ) መርጦ ማመን እና ለሎቹን ጥቅሶች መሸሽ/መፍራት የለበትም" ብለዋል። እውነት ነው፣ እንደ ቃልዎ እርስዎም ሁለቱንም ጽንፍ አብራርተው ቢነግሩን መልካም ነበር። እንዲያው በደፈናው ይህን ሃቅ ጠቅሶ ዞር ማለት አያስኬድም። አይ ካሉ በቀደምውና በዚህ መልስ የጠቀስኳቸውን ጥቅሶች እርስዎ ካነሱዋቸው ሃሳብና ጥቅሶች ጋር አዛምደው ይመልሱልን።

የቤተክርስቲያን ተረት ስላሉት ግን ትንሽ ልበል። ታሪክ እንደሚነግረን በ325 ዓ.ም የተካሄደው የኒቂያ ጉባኤ "ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሆነ" ደነገገ። ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ ባሉት ዓመታት በጉዳዩ ላይ የከረሩ ክርክሮች ተካሂደው ነበር። በዚህ ወቅት ከኒቅያ ጉባኤ ውሳኔ በተቃራኒው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አይደለም የሚሉ ወገኖች ተደማጭነት አግኝተው ነበር። በኋላ ግን ንጉሰ ነገስት ቲዎዶሽየስ ይህን ሃሳብ በሚቀበሉ ሰዎች ላይ ታላቅ ውሳኔ አስተላለፈ። በመሆኑም የሥላሴ ጽንሰ ሃሳብ ይበልጥ ግልጽ የሆነ ድንጋጌ እንዲኖረው በ381 ዓ.ም የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ተሰየመ። በውጤቱም የዛሬው የሥላሴ ትምህርት መሰረቱን አገኘ።

አንዳንድ የቤተክርስቲያን "አባቶች" እነዚህ ጉባኤዎች ከሃዲዎችን ለማውገዝ እንጂ ሥላሴን ለመፍጠር አይደለም ብለው ይከራከራሉ። እውነታው ግን ከዚያ የተለየ ነው። ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ "አባቶች" የጻፏቸው መጽሐፍት ለዚህ ትልቅ ማስረጃ ናቸው። ሰማዕቱ ጀስቲን (በ165 ዓ.ም ገደማ የሞተ)፣ ኢራንየስ (በ200 ዓ.ም ገደማ የሞተ)፣ የግብጹ ቅሌምንጦስ (በ215 ገደማ ዓ.ም የሞተ)፣ ተርቱሊያን (በ230 ዓ.ም ገደማ የሞተ)፣ ሂፖሊተስ (በ235 ዓ.ም ገደማ የሞተ) እና ኦሪገን (በ250 ዓ.ም ገደማ የሞተ) በኢየሱስና በእግዚአብሔር ዙሪያ ስለጻፉት ነገር ከታሪክ መዛግብት ማግኘት ይቻላል።


ሰላም
Oct 12, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
<<ቃልም በእግዚአብሔር (ግሪክኛ፣ "ቶን ቴኦን") ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር (ግሪክኛ፣ "ቴኦስ") ነበረ።" በዚህ ጥቅስ ላይ ቴኦስ (አምላክ) የሚለው የግሪክኛ ስም በሁለት መንገዶች ተቀምጧል።>>

የምትናገረው የተቃዋሚዎችን መንገድ የተከተለና እውነትነት የሌለው ቢሆንም፣ በአማርኛም እኮ በሁለት መንገድ ተቀምጧል፦
1ኛ "በእግዚአብሔር" ይላል
2ኛ "እግዚአብሔር" ይላል

ወይም አንተ እንዳልኸው
1ኛ "በእግዚአብሔር ዘንድ" (ግሪክኛ፣ "ቶን ቴኦን")
2ኛ "እግዚአብሔር" (ግሪክኛ፣ "ቴኦስ")

ታዲያ የራስህን ትርጉም ለመስጠት እንዴት ደፈርህ?

<<ከመጀመሪያው ስም በፊት ቶን የሚል የግሪክኛ ጠቃሽ አመልካች (article) ገብቷል፤ ... ከሁለተኛው ስም በፊት ግን ምንም ዓይነት ጠቃሽ አመልካች አልገባል>>
ስትል ምን ማለትህ ነው? ባንተ አባባል ሁለት አማልክት ማለትም <<የታወቀ አካል ማለትም ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ>> እና <<ያልታወቀ አካል ማለትም ሁሉን ቻይ ያልሆነው አምላክ>> አሉ ማለትህ ነው? ነገሩ እርሱ ባንተ ዘንድ ያልታወቀ መሆኑ አያስገርምም። አንተ በእርሱ ዘንድ ያልታወቅህ ከሆንህ ግን ተስፋ ቢስ ነህና በጣም የሚያሳዝን ይሆናል።
ወዳጅ ስም-አልባ

የጻፍኩትን በደንብ አንብበኸው/ሽው ቢሆን ኖሮ ይህን መልስ አትሰጠኝም ነበር።

በግሪክኛ "ቶን" ማለት "በ" ማለት አይደለም። ጠቃሽ አመልካች (article) ምን ማለት እንደሆነ አስቀድሞ ሊገባህ ያስፈልጋል። "በእግዚአብሔር ዘንድ" የሚለው የአማርኛ ሐረግ እኩያ የሆነው የግሪክኛ ሐረግ "ፕሮስ ቶን ቴኦን" ነው። ቃል በቃል በእንግሊዝኛ ሲቀመጥ "WITH THE GOD" ይሆናል። እናም "ፕሮስ" ማለት "በ...ዘንድ"፣ "ከ...ጋር"፣ "WITH" ማለት ሲሆን፣ "ቶን" ማለት በቀጣይ የተጠቀሰውን ስም ማንነት የሚገልጽ አመልካች ወይም article ነው። "Man" ለሚለው "ሰው" እና "The man" ለሚለው "ሰውየው" እንደምንለው ማለት ነው አጠቃላይ ቁም ነገሩ።

"ተቃዋሚዎች" ያልኸው ግን ምን እንደሆነ አልገባኝም። ሰውን ለመቦደን ከመጣር አመለካከቴን ብትሟገተው ይሻላል።

"ሁለት አማልክት" ላልኸው፣ የኔ እምነት መጽሐፉን መስማት፣ ከተጻፈው አለማለፍ ነውና (1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6) ሐዋርያው ጳውሎስ በዚሁ መልእክቱ 8፡5-6 ላይ ያሰፈረውን በጥሞና እንድታነብ እጋብዝሃለሁ።

"5 መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥

6 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።"


ሰላም
በርግጥ ያንተ "እምነት መጽሐፉን መስማት፣ ከተጻፈው አለማለፍ" ከሆነ (1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6) ሐዋርያው ጳውሎስ "ታላቁ አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ" (ወደ ቲቶ 2፤ 12-13) መሆኑን የጻፈውንም ማመን አለብህ።
ቲቶ 2፡13፡ "እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን..." በማለት በከፊል ይነበባል።

የተጻፈውን በደንብ አምንበታለሁ። ችግሩ ያለው ማመን በምንፈልገውና በምናነበው መካከል ነው። አንተ ስለ አንድ አካል (ስለ ኢየሱስ ብቻ) እንደተነገረ አድርገህ ታነባለህ። እኔ ደግሞ ስለ "ታላቁ አምላካችን" (ስለ እግዚአብሔር) "እና" ስለ "ኢየሱስ ክርስቶስ" ክብራማ መገለጥ እየተናገረ እንዳለ እገነዘባለሁ። እናስ ... ዳኛው ማን ነው? እስቲ ጥቂት ጥቅሶችን ጨምርና አስብበት፦

ኤፌሶን 5፡5፡
"ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።"

2 ተሰሎንቄ 1፡12፡
"ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር ..."

1 ጢሞቴዎስ 5፡21፡
"አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።"

1 ጢሞቴዎስ 6፡13፡
"ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤"

2 ጢሞቴዎስ 4፡1፡
"በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤"

መዝሙር 2፡1-2፡
"... የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። "

ራዕይ 5፡13፡
"... በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።"

ራዕይ 7፡10፡
"በታላቅም ድምፅ እየጮሁ። በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ።"

ለእምነት ይህ ይበቃል።
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፥16-17
ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።

አሜን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና አባታችን እግዚአብሔር ልባችንን በእውነቱ ላይ ያጽኑልን!
0 ድምጾች
ውድ ወዳጄ ሆይ፣
በቅድሚያ አንቱ ስላልከኝ ጌታን አመሰግናለሁ። በመቀጠልም <<ዮሐንስ 1፡1-3 ላይ አብ፣ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ የሚሉ ቃላቶች የሉም>> በማለት "ያላወቅሁትን" አዲስ ነገር ስላሳወቅኸኝ አመሰግናለሁ። ከአቀራረብህ፣ ከመልስህ እና ከምታነሣቸው ጥያቄዎችህ እንደ ተረዳሁት በእድሜህም ሆነ በመንፈሳዊ ዕውቀትህ ልጅ ስለ መሰልከኝ አንተ ብዬ ብጽፍልህ ቅር እንደ ማይልህ አሰብኩ። እስቲ አንተ ያነሳሃቸውን ጥያቄዎች በዝርዝር እንመልከታቸው። ከሁሉ አስቀድሜ በመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የተለመደውን ክቡር እና መንፈሳዊ ሰላምታ አቀርብልሃለሁ።

"ከእግዚአብሔር ከአባታችን (ከእግዚአብሔር አብ)፣ ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን (ከእግዚአብሔር ወልድ) ጸጋ እና ምሕረት ሰላምም (ለአንተ) ይሁን፤ (አሜን)(1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡ 2)

" 'ቃልም እግዚአብሔር ነበረ' በሚለው አተረጓጎም (language translation) ሁሉም ተርጓሚዎች አይስማሙም" ብለሃል። ልክ ብለሃል። ለምሳሌ አንተ አትስማማም። እንደ አንተ ያሉ ሰዎችም አይስማሙም። አንተ የምትከተላቸው ሰዎችም አይስማሙም፦ ለምሳሌ ቻርለስ ራስል። የቃሉ አማኞች ግን ይስማማሉ። ለምን? ምክኒያቱም ዮሐንስ 1፡1 ባይጻፍ ኖሮ እንኳ (የለም፤ መንፈስ ቅዱስ ለአንዴና ለዘላለም ጽፎታል)፣ "ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደነበረ እና በኋለኛው ዘመን እኛን ለማዳን ራሱን አዋርዶ እጅግ ዝቅ እንዳለ፣ አባቱ ግን የተሰቀለውን ኢየሱስን መልሶ ጌታና ክርስቶስ እንዳደረገው (የሐዋርያት ሥራ 2:36)፣ አብዝቶ እንዳከበረውም" የሚናገሩ ሌሎች በጣም ብዙ ጥቅሶች ስላሉ ነው።

ጌታ እና ክርስቶስ (መሲሕ)

መቼትን በጣም እንደምትወድ ጽፈህልኛል። ስለዚህ የሐዋርያት ሥራ 2:36ን መቼት ልብ ብለህ አስተውል፤ "እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን..." ይላል። ይህም ስለ እኔ እና ስለ አንተ ኃጢአት ጌታ ኢየሱስ የተሰቀለበትን እና የተዋረደበትን ጊዜ ያመለክታል። እንዲህ የተዋረደውን ኢየሱስን "...እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ" ይላል። መቼት (መቼ እና የት) የሚባለውን አስተዋልህ? (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡7)። በተረፈ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ከመሰቀሉ እና ከመዋረዱ በፊት በራሱ ክብር የነበረው የክብር ጌታ ነበረ። ችግሩ ግን ልክ እንደ ዛሬው ብዙ ሰዎች እርሱን አላወቁም ነበር።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡
8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።

ዮሐንስ 17፡
5 አሁንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።

በምድር እያለ በማስተማሩ ወራትም እርሱ ክርስቶስ (መሲሕ) እና ጌታ ነበር

ዮሐንስ 13፡ (ጌታ ኢየሱስ ሲናገር)
13 እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።

ዮሐንስ 4፡
41 ስለ ቃሉ ከፊተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ፤
42 ሴቲቱንም፦ አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም፥ እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን ይሉአት ነበር።

ዮሐንስ 4፡
25 ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።
26 ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።

ቃል ሥጋ ሆኖ በተወለደ ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እና ጌታ ነበር

ሉቃስ 2፡
10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

ጥንት በሥጋ ከመምጣቱ በፊት በሰማይ እያለም እርሱ ክርስቶስ (መሲህ) እና ጌታ ነበረ (መዝሙር 2፡1-12)

ማቴዎስ 22፡
43-44 እርሱም (ኢየሱስ ሲናገር)፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ (ክርስቶስን) ይጠራዋል?
45 ዳዊትስ (ክርስቶስን) ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።
46 አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።

ዛሬም በአብ ቀኝ እያለ እርሱ ክርስቶስ እና ጌታ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 1፡
2 በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ "በክርስቶስ" ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት...

እርሱ ሁልጊዜም ያው ነው። አይለወጥም፤ አያረጅም፤ አይታክትም።

ዕብራውያን 13፡
8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።

ዕብራውያን 1፡ (አብ ስለ ልጁ እንዲህ ይላል)
11 "እነርሱም (ሰማይ እና ምድር ፍጥረት ሁሉ) ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።"

ይህም የሚያሳየን "የሚናወጡት ይኸውም የተፈጠሩት የሚወገዱ መሆናቸውን" (ዕብራውያን 12፡27 አ.መ.ት) እና ያልተፈጠረው ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር የሆነው ፈጣሪ ግን የማይለወጥ መሆኑን ነው።

ሚልክያስ 3፡
6 እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

ውድ ወንድሜ ሆይ፣ በምንም አይነት ርዕስ ላይ ሰዎች ሁሉ እንዲስማሙ አትጠብቅ። ሰዎች ሁሉ የተስማሙበትን ነገር አምናለሁ ካልክ ምንም የምታምነው ነገር አይኖርም ማለት ነው። አንዳንድ ከሐዲዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ነን በማለት ክህደትን ወይም ስህተትን ያስተምራሉ። ለምሳሌ "ሁለት እግዚአብሔሮች እንዳሉ፣ ትልቁ እግዚአብሔር አብ እንደሆነ፤ ደግሞ ትንሹ እግዚአብሔር ኢየሱስ እንደሆነ" ጽፈዋል። እነዚህ ወገኖች ምንም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ነን ቢሉም፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅል ሐሳብ ያልገባቸው ናቸውና እግዚአብሔር (ጌታ) አንድ ነው የሚለውን ዘላለማዊ ቃል የካዱ ናቸው። (እግዚአብሔር ማለት ግዕዝ ሲሆን በአማርኛ ጌታ፣ በእንግሊዝኛ THE LORD ማለት ነው። መዝሙር 34፡8)

እግዚአብሔር (ጌታ) አንድ ብቻ ነው

"መምህራችን፣ ሊቃችን እና አባታችን" አንድ ጌታ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሲሆን እርሱም በቅደም ተከተል respectively "አንድ መንፈስ አንድ ጌታ አንድ አምላክ" (ኤፌሶን 4፡4-6) ነው።

ማርቆስ 12፡
29 ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፡- እስራኤል ሆይ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው
30 አንተም በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ፣ በፍጹምም አሳብህ፣ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

ዘዳግም 6፡
4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው

ዕብራውያን 3፡
4 እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና፥ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው።

ዘካርያስ 14፡
9 እግዚአብሔርም (ወልድ) በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።

ሚልክያስ 2፡
10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?

ያዕቆብ 4፡
12 ሕግን የሚሰጥ እና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?

ማቴዎስ 23፡
10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።

ስንደክምም ሆነ ስንበረታ ሁልጊዜ እጅግ የሚያፈቅረን (ዮሐንስ 15፡13) የዘላለም አባታችን ክርስቶስ (ኢሳይያስ 9፡6) እንዲህ ሲል አዝዞናል፦

ማቴዎስ 23፡
8 እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ (መንፈስ ቅዱስ) ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።
10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፤ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።

እናንተ ግን መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ (መንፈስ ቅዱስ) ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ (ማቴዎስ 23፡8)

የክርስቶስን ወንጌል ማስተማር የመምህርነትን ሥራ መፈጸም መልካም ነው (ኤፈሶን 4፡11)። ሆኖም መምህር፣ መምህር እየተባባሉ መጠራራት ወይም ሌሎችን እንደዚያ ብሎ መጥራት ተገቢ አይደለም። "ሁላችን ወንድማማች" ስለ ሆንን ወንጌል ማስተማር የበላይ መሆንን አያሳይም። ሁላችንም በክርስቶስ ደም ተዋጅተን ካህናት ሆነናል። በርግጥ እንደ ኢትዮጵያ ባህል ክህነት በቆሎ ትምህርት እና "በሊቃውንት" በማስመስከር የሚገኝ ሹመት ሳይሆን፣ ይህን ያህል ቀላል ነገር ሳይሆን፣ ከሰማይ በመጣ ታላቅ መስዋዕትነት ይኸውም በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የተገኘ ወደር የለሽ ጸጋ ነው። የምናገኘውም በእኛ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ስራ ነው (ኤፌሶን 2፡18፤ ኤፌሶን 1፡5፤ ሮሜ 11፡6)። ከእኛ የሚጠበቀው አዳኙን ክርስቶስን ማመን ብቻ ነው (ሮሜ 3፡24፤ ገላትያ 2፡16)

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ (ካህን ሥራው መሥዋዕትን ማቅረብ ነው)

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ።

ራእይ 1፡
6 ለወደደን (ላፈቀረን)፣ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፣ መንግሥትም (እንድንሆን ላደረገ)፣ ለአምላኩ (ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው) እና ለአባቱም (ኢየሱስ እንደ ፍጹም አምላክ) ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን (ኢየሱስ እንደ ፍጹም አምላክ)፤ አሜን።

ራእይ 5፡ (ዝማሬ ለአምላክ በሰማይ ዙፋኑ ፊት)
9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋም ሁሉ፣ ከወገንም ሁሉ፣ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

ራእይ 20፡
6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር (ከእግዚአብሔርና ክርስቶስ ጋር) ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ (ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል- ከእርሱ ጋር)

አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ (ማቴዎስ 23፡9)

ብጹዕ አባታችን፣ ቅዱስ አባታችን፣ የነፍስ አባት፣ የንስሓ አባት፣ የክርስትና አባት፣ ሁሉ ነገራችን እግዚአብሔር (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) ነው። የእግዚአብሔርን መልካም አባትነት እና ጣፋጭ አባታዊ ፍቅሩን ያላወቀች ነፍስ አባት ፍለጋ መባከኗ የማይቀር ነው። ያገኘችውንም መንፈሳዊ የሚመስል ሰው ሁሉ "የነፍስ አባት፣ የቤተ ክርስቲያን አባት" ወዘተ እያለች ለመሰየም ትዳዳለች። ሆኖም ሁሉን እርግፍ አድርጋ በመተው እውነተኛው ወላጅ አባቷ (ዮሐንስ 1፡13፤ ያዕቆብ 1፡18፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡3-5) እግዚአብሔር ጋር እስካልመጣች ድረስ እፎይታ አይኖራትም። አባታችን "ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ" ብሎአል (ዮሐንስ 14፡18)። እርሱ አባታችን ስለሆነ (ኢሳይያስ 9፡6) "እኔ አባት እሰጣችኋለሁ" አላለም። ከዚህ ይልቅ አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ ሲል አዘዘን።

ይህን ትዕዛዙን ልንጠብቅለት ይገባል ፦

ዮሐንስ 14፡
15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።

ዮሐንስ 14፡
21 ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው። የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።

ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፤ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ (ማቴዎስ 23፡10)

ሊቅ (ነጠላ)፣ ሊቃውንት (ብዙ ቁጥር)፣ ሊቀ ሊቃውንት (የሊቃውንት ሁሉ ሊቅ)፣ ሊቀ ካህናት (የካህናት የበላይ ካህን)፣ ሊቀ ዲያቆን፣ ሊቀ ጳጳስ፣ ተብላችሁ አትጠሩ። ሌሎችንም እንደዚያ ብላችሁ አትጥሩ። ምክንያቱም ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፤ እናንተ ሁላችሁም ወንድማማች ናችሁ እንጂ በእናንተ መሓል ሊቅ (የበለጠ) እና ደቂቅ (ያነሰ) ብሎ ክፍፍል የለም - ሲል ይመክረናል ጌታ አምላካችን የምንወደው አባታችን። ብዙ ሰዎች ይህን መቀበል መራራ ስለሆነባቸው እነርሱ በሆነ መንገድ ከሌሎች አማኞች የሚበልጡ መሆናቸውን ለማስረዳት እና ለማሳመን ይተጋሉ። እውነተኛ አማኞች ግን አሁንም አይናቸውን ከአባት ላይ አያነሱም፤ ወደ አባት መሳዮች አይዞሩም። አይናቸውን ከሊቅ ላይ አንስተው ወደ ሊቅ መሳዮች አይዞሩም። እንዲሁም አይናቸውን ከመምህር ላይ አንስተው ወደ መምህር ነን ባዮች አይዞሩም።


አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው

ኢሳይያስ 6፡
3 አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።

ሮሜ 10፡
9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም (ሌላ ባዕድ ወገን ሳይሆን የራሱ የኢየሱስ አባት አብ) ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
10 ሰው በልቡ (ኢየሱስ ጌታ መሆኑን) አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
11 መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
12 በአይሁዳዊ እና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው።
13 የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና (ኢዩኤል 2፡32፤ የሐዋርያት ሥራ
2፡21፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡19)


ይቀጥላል...
Oct 21, 2013 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
Feb 9, 2014 child of Jesus ታርሟል
... የቀጠለ

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡
8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ (ኢየሱስን) ባልሰቀሉትም ነበር።

ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም። አንድ የነፍሳችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር) አለን፤ አንድ የዚህ አለም ጌታ ገንዘብ አለ፤ ከሁለቱ ለአንዱ ብቻ እንገዛለን።

የሐዋርያት ሥራ 7፡
59 እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
60 ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። (ኃጢአታችንን ይቅር ማለት የሚችል አንድ ጌታ ብቻ አለ።)

ማቴዎስ 6፡
24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔር እና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

ይሁዳ 1፡
3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ (ራዕይ 22፡21) በሴሰኝነት ይለውጣሉ። ንጉሣችንን እና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል። (ኢሳይያስ 43፡11፤ 44፡24)

ዘዳግም 32፡
39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ ከእጄም የሚያድን የለም።
40 እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ እንዲህም እላለሁ፦ ለዘላለም እኔ ሕያው ነኝና (ራእይ 1፡18)
41 የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥ እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ (ሉቃስ 19፥27)፥ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ።

ዮሐንስ 11፡
15 ሰባተኛው መልአክ ነፋ። በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል
16 የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው
17 ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ፦

"ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
18 አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያት እና ለቅዱሳን፣ ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾች እና ለታላላቆችም (ለእያንዳንዳቸው እንደ ሥራቸው) ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ" (አዎን፤ አሜን)

ታዲያ ወንድሜ ሆይ ማመን ያለብህ የቱን ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ጥቅሶች የተብራራውን እውነት? ወይስ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ነን የሚሉ ሰዎች የጻፉትን ትንተና? ልብ በል እነዚያ ሰዎች በራሳቸው ትርጉም ለተረጎሙት መጽሐፍ (ለምሳሌ አዲስ አለም ትርጉም) የሚሰጡት የራሳቸው የሆነ ትንታኔ አላቸው። ከዚህም መካከል ስለ "ኮይኔ ግርክኛ የሰዋሰው ህግ" የሚሰጡት ትንታኔ ይገኝበታል። ያንን ቀድተህ ለእኔ የጻፍክልኝ ማለት ነው። ልብ በል የሚሰጡት ትንታኔ ዋና አላማ ሁለት ነው። አንደኛ፣ ጥቅሶችን በመውሰድ የጥቅሶቹን መንፈሳዊ እውነት ከመናገር ይልቅ የዚህን አለም ጥበብ እና አመክንዮ/logic/ ማዕከል በማድረግ ክርክር ማንሳት ነው። ሁለተኛ አንዳች መልካም ነገርን ለማስጨበጥ ሳይሆን፣ ሰዎች ወደ ነፍሳቸው አዳኝ እንዲጠጉ እና እንዲጣበቁ የሚያደርግ ሳይሆን፣ ሰዎች ሁሉ በአዳኛቸው ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር እና እምነታቸውን እንዲጥሉ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች (ለምሳሌ ዮሐንስ 1፡1) ስህተት እንደሆኑ ለማሳየት የታለመ ነው። አንድ እውነት ልንገርህ። የትኛውም ትምህርት ወደ ክርስቶስ የበለጠ የሚያጣብቅህ ካልሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም።

አብን እንደምታከብረው ወልድንም እንድታከብረው አብ ራሱ ይፈልግብሃል።
ለምን? ምክኒያቱም የአብን የዘላለም ዕቅድ የፈጸመው፣ አንተን እና መሰሎችህን ከአብ ጋር ያስታረቀው እግዚአብሔር ወልድ ነውና።

ዮሐንስ 5፡
22-23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ (አብ) ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።
24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ (ይህን) ቃሌን የሚሰማ፣ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነበረ፤ ነው።

(1) በሰው ምሳሌ ተገለጠ፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኘ

ፊልጵስዩስ 2፡
6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን (እኩል መሆኑን) መቀማት (መንጠቅ) እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ <<በሰውም ምሳሌ>> ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
8 <<በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ>> ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

(2) ቃልም እግዚአብሔር ነበረ

ዮሐንስ 1፡
1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ... ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

ይቀጥላል...
0 ድምጾች
...የቀጠለ

(3) የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር ወልድ ነበር

ዘፍጥረት 1፡
1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።

ዕብራውያን 1 ፡
8 (እግዚአብሐር አብ) ስለ ልጁ ግን (እንዲህ ይላል)፦ አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ ...ጌታ ሆይ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤
11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

ኤርምያስ 51፡
15 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። ...
18 እነርሱም ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።
19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፥ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
(ኢሳይያስ 45፡11-12፣ 18)

(4) የታመነው ፈጣሪ የነፍሳችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

ጌታ መንፈስ ቅዱስ በጴጥሮስ ሆኖ ሲናገር እንዲህ አለ፦
1ኛ ጴጥሮስ 4፡
19 ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ (ለታማኙ ፈጣሪያቸው) አደራ ይስጡ።

በመንፈስ ቅዱስ የተመራው እስጢፋኖስም ያደረገው ይህንኑ ነው፦

የሐዋርያት ሥራ 7፡
59 እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
60 ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። (ከእኛ በላይ ክርስቲያን መሆኑ የተረጋገጠለት እስጢፋኖስ ነፍሱን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ሰጥቶአል።)

እንዲሁም ኤልያስ ወደ ታመነው ፈጣሪ ጸለየ፦
1ኛ ነገሥት 19፡
4 እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል አሁንም፥ አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና (ጌታ ሆይ) ነፍሴን ውሰድ ብሎ እንዲሞት ለመነ።

ሕዝቅኤል 18፡ (ፈጣሪ አምላክ ሲናገር)
4 እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት።

(5) ክርስቶስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነበረ፤ እርሱም የእነ ጴጥሮስ አምላክ ነው

ኢሳይያስ 8፡
13 መፈራታቸውንም አትፍሩ፣ አትደንግጡ። ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት። የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።

ከእኛ በላይ ክርስቲያን መሆኑ የተረጋገጠለት፣ የበጉ ሐዋርያ የሆነው ጴጥሮስ "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት" የሚለውን ይህን የብሉይ ኪዳን ቃል ሲረዳው እና ይህ የሠራዊት ጌታ ማን መሆኑን ሲመሰክር "ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት" ይላል፦

1ኛ ጴጥሮስ 3፡
15 ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ፣ አትናወጡም። ዳሩ ግን ጌታን (የሠራዊት ጌታን) እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት።

መላእክት የሠራዊት ጌታን ሲቀድሱት (ቅዱስ ቅዱስ ሲሉት) እንዲህ ይላሉ፦

ኢሳይያስ 6፡
2 ሱራፌልም ከእርሱ (ከአምላክ) በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
3 አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች፤ እያለ ይጮኽ ነበር።
4 የመድረኩም መሠረት ከጯኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።

1ኛ ጴጥሮስ 3፡
15 ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ፤ አትናወጡም፤ ዳሩ ግን ጌታን (የሠራዊት ጌታን) እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት

(6) በሉዓላዊ ስልጣን የሚናገር ኢየሱስ (እግዚአብሔር)

ነቢያት እንዲህ ይላሉ፦
1ኛ ሳሙኤል 15፡
2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል...
2ኛ ሳሙኤል 7፡
8 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል...
1ኛ ዜና 17፡
7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል....
ኢሳይያስ 1፡
24 የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል... እያሉ ነቢያት ተናገሩ።

እንዲሁም መላእክትም፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል... ብለው ተናግረዋል (ዘካርያስ 1፡14፤ 3፡6-10)

ዳሩ ግን እግዚአብሔር (ኢየሱስ) ራሱ ሲናገር በሉዓላዊ ስልጣኑ እንዲህ ይላል፦

የማቴዎስ ወንጌል
5፡22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፡28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፡32 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፡34 እኔ ግን እላችኋለሁ።
5፡39 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፡44-45 እኔ ግን እላችኋለሁ፥

የማቴዎስ ወንጌል
8፡11 እላችኋለሁም፥
10፡15 እውነት እላችኋለሁ፥
11፡9 አዎን እላችኋለሁ፥
11፡22 ነገር ግን እላችኋለሁ፥
11፡24 ነገር ግን እላችኋለሁ፥
12፡6 ነገር ግን እላችኋለሁ፥
12፡31 ስለዚህ እላችኋለሁ፥
12፡36 እኔ እላችኋለሁ፥
ሕዝቅኤል 13፡15 እኔ... እላችኋለሁ።

(7) እረኛዬ ኢየሱስ (እግዚአብሔር)

ነቢያት እንዲህ አሉ፦
መዝሙረ 23 ፡
1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው።

እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ) ራሱ ሲናገር እንዲህ አለ፦
ዮሐንስ 10፡
11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ።
14 መልካም እረኛ እኔ ነኝ።

የእግዚአብሔር (የክርስቶስ) ሕዝብ ነን። የእኛ የሕዝቡ እረኛ፣ የነፍሳችን ጠባቂ ክርስቶስ (እግዚአብሔር) ነው። እኛን የሚያሳድድ ማንም ቢኖር እኛን ሳይሆን አምላካችንን እግዚአብሔርን ያሳድዳል። ስለዚህ አምላካችን ራሱ በኃላፊነት ይጠይቀዋል።

የሐዋርያት ሥራ 9፡
4 (ክርስቲያኖችን አሳዳጁ ሳውል) በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን (የክርስቶስን) ድምፅ ሰማ።
5 (ሳውል፦) ጌታ ሆይ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው።

ዘዳግም 32፡ (አምላክ እስራኤልን)
10 በምድረ በዳ በጥማት፥
የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤
ከበበው ተጠነቀቀለትም፤
እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።

መዝሙር 17፡
7 የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው (አምላክ ሆይ)፥ ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው።
8 እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፥
9 ከሚያስጨንቁኝ ከኃጢአተኞች፥ ነፍሴንም ከሚከብቡአት ከጠላቶቼ።

ዘካርያስ 2፡
8 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፤ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።

(8) የአምላካችን (የኢየሱስ) ቃል

ነብዩ ኢሳይያስ እና ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲመሰክሩ እንዲህ ይላሉ፦
ኢሳይያስ 40፡
8 የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

1ኛ ጴጥሮስ 1፡
24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤
25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።

እግዚአብሔር/ኢየሱስ/ ራሱ ሲናገር እንዲህ አለ፦
ማቴዎስ 24፡
35 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
ማርቆስ 13፡
31 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
ሉቃስ 21፡
33 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።

(9) የእነ ጴጥሮስን አምላክ እናመልከዋለን

አንዳንድ ተቃዋሚዎች "ኢየሱስ አምላክ መሆኑን እንቀበላለን" ይላሉ። ነገር ግን ኢየሱስን አምላካቸው አድርገው አይቀበሉትም። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ (እግዚአብሔር፣ God) ወይም ኃያል አምላክ (ኃያል እግዚአብሔር፣ Mighty God) ብቻ ሳይሆን እርሱ ለእኛ ለሰው ልጆች አምላካችን እና አዳኛችን our God and Saviour ነው። ማለት እርሱ ፈጣሪያችን፣ አባታችን እና ጌታችን በገዛ ደሙ የዋጀን እግዚአብሔር ነው (የሐዋርያት ሥራ 20፡28፤ ቆላስይስ 1፡15-16፤ ዕብራውያን 1፡8-12፤ ዮሐንስ 1፡3፣ 10፤ ኤፌሶን 2፡10፤ ዮሐንስ 1፡1)። ልብ በል የትኛውም ፍጡር አምላካችን አይደለም። ፈጣሪ ብቻ አምላካችን እና ጌታችን ነው። "እስራኤል ሆይ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" (ማርቆስ 12፡29)። ከእርሱ በቀር ጌታ የለንም (ይሁዳ 1፡4፤ ማቴዎስ 6፡24፤ ሉቃስ 16፡13)። አንዱ ጌታ እርሱ አምላካችን አዳኛችንም (መድኃኒታችን) ነው።

አምላኬ እና አዳኜ my God and Saviour ፣ አባቴ እና መታመኛዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እኔ የተፈጠርኩት በእርሱ ነው (ኤፌሶን 2፡10)። የተፈጠርኩትም ለእርሱ ነው (ሮሜ 11፡36)። "የሚታዩት እና የማይታዩትም (ረቂቅ ፍጡራን)፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት፣ ወይም አለቅነት፣ ወይም ሥልጣናት፣ በሰማይ እና በምድር ያሉት ሁሉ (እኔንም ጨምሮ)፣ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱም ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል" (ቆላስይስ 1፡15-17)። ወዳጄ ሆይ፣ ለአንተስ አምላክህ እና አዳኝህ your God and Saviour መታመኛ አባትህ ማን ነው? እኔ የክርስቶስ ነኝ። ወዳጄ አንተስ የማን ነህ? (ማርቆስ 9፡41፤ ሮሜ 15፡15-16፤ ሮሜ 16፡16፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡22፤ 12፡27፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡23፤ ገላትያ 3፡29፤ 5፡24፤ ሮሜ 8፡9፤ ቆላስይስ 1፡7፤ 4፡12፤ ራእይ 20፡6)

2ኛ ጴጥሮስ 1፡
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ (our God and Saviour Jesus Christ) ጽድቅ፣ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ... ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ (አሜን)

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የእስራኤል አምላክ ያህዌ (እግዚአብሔር) ባይሆን ኖሮ፣ አይሁዳዊ የነበረው ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ሲናገር "አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ" our God and Saviour Jesus Christ አይልም ነበር። ምክንያቱም ጴጥሮስ የሚከተለውን የብሉይ ኪዳን ሕግ ያከብራልና፦

ዘጸአት 20፡
1 እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ
3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ
4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛ እና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፣ (ነገር ግን)
6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።


(10) የእነ ጳውሎስን ታላቅ አምላክ እናመልከዋለን

ቲቶ 2፡
12-13 ይህም ጸጋ...የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን (our great God and Saviour Jesus Christ) ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል።
14 መድኃኒታችንም /our Saviour/ ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
15 ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።

ታላቅ አምላክ (great God)

በምንድር ነው ታላቅ የሆነው? በሠራዊቱ (በተከታዮቹ) ብዛት እና አቋም ነው? ወይስ ታላቅ የሆነው ከሌሎች "አማልክት" በዕድሜ ቀዳሚ በመሆኑ ነው? አይደለም። ኢየሱስ ታላቅ የሆነው ወደር በሌለው ስልጣኑ እና በገናናው ክብሩ ነው። ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተመሰገነው እግዚአብሔር (God) እርሱ ነው (ሮሜ 9:5)። አዎን "ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው፤ የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው" (ዮሐንስ 3፡31፤ መዝሙር 118፡ 27-29)

መዝሙር 145:
3 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም።

(11) ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር

ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ በዙፋኑ ፊት እንቆማለን፤ ፈጣሪያችንን እናመሰግናለን (ዘጸአት 15፡2)፤ የትኛውንም ፍጡር አናመሰግንም ምክንያቱም አምላካችን ቀናተኛ አምላክ ነውና፤ ክብሩንም ለማንም አይሰጥምና።

መዝሙር 18፡
1 አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ...
3 ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።

1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡
12 ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ። (ጳውሎስ በአጠገቡ በአካል ያላገኘውን ኢየሱስን፣ በስልክ፣ በኢሜል ወይም በዴብዳቤ ያላገኘውን ኢየሱስን በመንፈስ ሆኖ ያመሰግነዋል፤ ይህ አይነት ምስጋና አምልኮ በመባል ይታወቃል።)

ጌታ ኢየሱስ እና አብ አንድ አምላክ ባይሆኑ ኖሮ፣ አሊያም ኢየሱስ ከአብ የተለየ ወይም ያነሰ "ሌላ አምላክ" ቢሆን ኖሮ ጳውሎስ ስሙን ጠርቶ አያመሰግነውም ነበር። ምክንያቱም ጳውሎስ ከእኛ ይልቅ ብሉይ ኪዳንን ጠንቅቆ የሚያውቅ አይሁዳዊ የነበረ ነው። እንዲህ የሚለውን የብሉይ ኪዳን ሕግ ጠንቅቆ ያውቃል፦ "የሌሎችን አማልክት ስም አትጥሩ፥ ከአፋችሁም አይሰማ" (ዘጸአት 23፡13)። እነሆ ዛሬም የጳውሎስን አምላክ ይኼውም የእኛን አምላክ ክርስቶስን እናመሰግነዋለን። ለምን? አዎን ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር እርሱ ነውና። አምላኬ ሆይ አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ አሜን።

ስግደት ለአምላክ በሰማይ ዙፋኑ ፊት

ራእይ 5፡
8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶች እና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ (በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ወደቁ)

ጸሎት ወደ አምላክ ነው

ራእይ 5፡
8...መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶች እና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናን እና የቅዱሳን (የአማኞች) ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።

ይቀጥላል....
Oct 21, 2013 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
Jan 12, 2014 child of Jesus ታርሟል
...የቀጠለ

ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ

ዘጸአት 15፡
1 በዚያም ጊዜ ሙሴ እና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱን እና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

አምላኬ ሆይ ለአንተ እዘምራለሁ

መሣፍንት 5፡
3 ነገሥታት ሆይ ስሙ፤
መኳንንት ሆይ አድምጡ፤
እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥
ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።

መዝሙር 104፡
33 በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።

ራእይ 5፡
9-10 ...መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋም ሁሉ፣ ከወገንም ሁሉ፣ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥት እና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

ሰማያዊ ዝማሬ እና መንፈሳዊ ቅኔ ለእግዚአብሔር ብቻ የተገባ ነው። በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት የሚመለከው ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ ከእግዚአብሔር የተለየ ሌላ አካል አይደለም።

ኤፌሶን 5፡
17 ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
18 መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤
19 በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ
20 ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን (መንፈስ ቅዱስን) እና አባታችንን (አብን) ስለ ሁሉ አመስግኑ።
21 ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።

የሐዋርያት ሥራ 16፡
25 በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ (በዝማሬ) ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር
26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።
27 የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
28 ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ። ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ።
29 መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤
30 ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? አላቸው።
31 እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ (በእግዚአብሔር ወልድ) እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።
32 ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው።
33 በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር (በጌታ በኢየሱስ ስም) ተጠመቀ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)
34 ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም (በእግዚአብሔር ወልድ) ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ።

ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ሲሆን ሌላ ማንም ሰው ወይም ነቢይ ግን እግዚአብሔር አይደለም፤ አልነበረም፤ አይሆንምም።

መላእክት ሁሉ ፈጣሪያቸውን ኢየሱስን ያመልኩታል

ራእይ 5፡
11 አየሁም፥ በዙፋኑም፣ በእንስሶቹም፣ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋት እና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥
12 በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይል እና ባለ ጠግነት፣ ጥበብም፣ ብርታትም፣ ክብርም፣ ምስጋናም፣ በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።

መላእክት ኢየሱስን እንዲያመልኩት አብ ይፈልጋል። ለምን? ምክንያቱም አብ እና ወልድ ፈጽሞ የማይነጣጠሉ አንድ ናቸው (ዮሐንስ 10፡30)

ዕብራውያን 1፡
6 (እግዚአብሔር አብ) ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ (ለበኩሩ ለኢየሱስ) ይስገዱ ይላል።

ፍጥረት ሁሉ ፈጣሪን ያመሰግናል።

ራእይ 5፡
13 በሰማይ እና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከት እና ክብር፣ ምስጋናም፣ ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም (ለኢየሱስ) ይሁን ሲሉ ሰማሁ።
14 አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።

አየህ? ኢየሱስ ማለት ፍጥረት ሁሉ በዙፋኑ ፊት የሚያመልኩት አምላክ ነው። ልብ በል ፍጥረታት ሁሉ ሌላውን ፍጡር አያመልኩም አንድ ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ እንጂ። በእግዚአብሐር ዙፋን ፊት አምልኮ የሚቀበል ሌላ ደባል አካል ወይም ፍጡር እንደ ሌለ እግዚአብሔር ብቻውን አምልኮ እንደሚቀበል መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጣል። "የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ" (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡7)

እግዚአብሔር እና በጉ አይነጣጠሉም

ራእይ 5፡13
ራእይ 20፡6
ራእይ 21፥22-23
ዮሐንስ 14፡23
ዮሐንስ 14፡7-11
የሐዋርያት ሥራ 16፡31፣ 34

ኤፌሶን 2፡
12 በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፣ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፣ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ፣ ከእግዚአብሔርም (ከክርስቶስም) ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ (ያለ እግዚአብሔር) ነበራችሁ።

1ኛ ቆሮንቶስ 9፡
21 ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ህግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ (በእግዚአብሔር) ሕግ በታች ሳለሁ (ስኖር)፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ።

ራእይ 22፡
1 በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን (ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል-ዙፋን) የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።
2 በወንዙም ወዲያ እና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።
3 ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን (ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል-ዙፋን) በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
4 ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል ።
5 ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃን እና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።

ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል፣ ባሪያዎቻቸው ያመልኳቸዋል ሳይሆን ባሪያዎቹ ያመልኩታል ይላል። ማንን? እግዚአብሔርንና በጉን። ፊቶቻቸውን ያያሉ ሳይሆን ፊቱን ያያሉ ይላል። እንዲሁም ስሙም ይላል ስሞቻቸው አይልም፣ ...ያበራላቸዋል ይላል ያበሩላቸዋል አይልም (ራእይ 21፥23)

መዝሙር 2፡
1 አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ?
2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ።
3 ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል።
4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
(እግዚአብሔር የሳቀበት ሰው በከፍተኛ አደጋ ላይ ነው፤ ይህ ሰው አይለማም፤ አይበረክትም፤ የሚያድነውም የለም።)
5 በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።
6 እኔ ግን ንጉሤን (ኢየሱስን) ሾምሁ፤ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።
7 ትእዛዙን እናገራለሁ እግዚአብሔር አለኝ፦ "አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።
8 ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
9 በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።"
(ራእይ 2፡26-27)
10 አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።
11 ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
12 ተግሣጹን ተቀበሉ፤ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።

ሉቃስ 17፡
11 ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ (ጌታ ኢየሱስ) በገሊላና በሰማርያ መካከል አለፈ።
12 ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት አሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤
13 እነርሱም እየጮኹ፦ ኢየሱስ ሆይ፥ አቤቱ፥ ማረን አሉ።
14 አይቶም፦ ሂዱ፥ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ አላቸው።
15 እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥
16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።
17 ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ?
18 ከዚህ ከልዩ ወገን (ከሳምራዊ) በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ (በእግሬ ፊት ሊሰግዱ) የተመለሱ አልተገኙም አለ።
19 እርሱንም፦ ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።

እግዚአብሔርና ኢየሱስ ከቶ አይነጣጠሉም (ዮሐንስ 14፡10-11፣ 24)። ይህ ሳምራዊ ለማን ነው የሰገደው? ለእግዚአብሔር ወይስ ለኢየሱስ? አዎን ምንም ልዩነት የለውም። ለእግዚአብሔር መስገድ ለኢየሱስ መስገድ ነው። ለኢየሱስ መስገድም ለእግዚአብሔር መስገድ ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር (ወልድ) ነው። እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም አንድ አምላክ ኤሎሂም ነው።

ዛሬ ብዙዎች ኢየሱስን ሳያውቁ እግዚአብሔርን እናመልካለን ይላሉ። በመሰረቱ አንድ ሰው እግዚአብሔርን የሚያመልክ ከሆነ ያ ሰው ቢያውቅም ባያውቅም ጌታ ኢየሱስን እያመለከ ነው። ለምን? ምክንያቱም ከኢየሱስ ውጭ የሚኖር ወይም ከኢየሱስ ተለይቶ የሚመለክ ሌላ እግዚአብሔር የለምና። ይሁን እንጂ አንድ ሰው ኢየሱስን ሳያውቅ እግዚአብሔርን አመልካለሁ የሚል ቢሆን፣ ታላቁን አምላክ ራሱን ኢየሱስን እያመለከ (ቲቶ 2፡12-13) ቢሆንም፣ የሚያመልከውን እግዚአብሔርን (ኢየሱስን) ማን እንደ ሆነ ስላላወቀው ገና አልዳነም። የዘላለም ሕይወትም የለውም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ቆርነሌዎስ ነው (የሐዋርያት ሥራ 10፣11)። ቆርነሌዎስ እግዚአብሔርን የሚያመልክ ቢሆንም፣ የሚያመልከውን እግዚአብሔርን (ክርስቶስን) ገና ስላላወቀው፣ መዳን እንዲችል ክርስቲያኑ ጴጥሮስ ክርስቶስን (እግዚአብሔርን) ሰበከለት። ቆርነሌዎስ የሚያመልከውን እግዚአብሔርን አውቆ ሲያምንበት ዳነ፤ የዘላላም ሕይወትንም አገኘ። እንዲሁም የወህኒው ጠባቂ ፖሊስ በእግዚአብሔር (በኢየሱስ ክርስቶስ) አምኖ ስለዳነ "ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ" (የሐዋርያት ሥራ 16፡25-34)

ወደ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) መጸለይ፣ ምጽዋት መስጠት፣ መልካም መስራት ጥሩ ነገሮች ናቸው። ግን እግዚአብሔርን (ክርስቶስን) አለማወቅን ሊያካክሱልን አይችሉም። እግዚአብሔርን አለማወቅ፣ ማለትም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ መሆኑን አለማመን ታላቁ ኃጢአት ነው። (ዮሐንስ 16፡3፣ 8-9፤ ዮሐንስ 17፡3፤ ኢሳይያስ 1፡1-2) ታላቁ መልካም ሥራም ሌላ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስን ማመን ነው (ዮሐንስ 6፡28-29)። ለአዲስ ኪዳን አማኞች ከተሰጡት ሁለት ትዕዛዛትም፣ አንደኛው አብ የሰጠን ትዕዛዝ ጌታ ኢየሱስን ማመን ነው፤ ሁለተኛው ራሱ ጌታ ኢየሱስ የሰጠን ትዕዛዝ፣ እርስ በርሳችን እንድንፋቀር ነው (1ኛ ዮሐንስ 3፡23፤ ዮሐንስ 13፡34-35፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡1)። ማንም ጌታ ኢየሱስን (እግዚአብሔር ወልድን) አምኖ የእርሱን ስም በእምነት ቢጠራ፣ ሌላ ምንም መልካም ነገር ሳይሰራ በዚህ ብቻ (በእምነት ብቻ) ይድናል፤ የዘላለም ሕይወትንም ወዲያውኑ ይቀበላል (ሉቃስ 23፡42-43፤ መዝሙር 91፡14፤ ሮሜ 10፡13፤ ኢዩኤል 2፡32፤ ሐዋርያት ሥራ 2፡21፤ ሮሜ 3፡28፤ ሮሜ 4፡4-5፤ ሮሜ 11፡6)። ከዳነ በኋላ ግን መልካም በመስራት፣ ሰዎችን በመርዳት ይደሰታል፤ ይዝናናል። በዚህም ፈጣሪ አምላክ ተጨማሪ ሽልማቶችን (አክሊል፣ ሽልማት፣ ደመወዝ፣ ምስጋና) ይሰጠዋል። የዳነ ሰው መልካም መስራት አያስፈልገኝም ብሎ አይናገርም። ምክንያቱም "በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው" (ያዕቆብ 4፡17)

ይህ በእምነት ብቻ መዳን፣ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ ውሳኔ ነው። ማንም ሊቃወም ወይም አስተያየት ሊሰጥበት ወይም ሊያሻሽለው አይችልም። መንፈስ ቅዱስ መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው ሲል የማያወላውል አቋሙን ይናገራል (የሐዋርያት ሥራ 4፡12)። አብ "ወደ እኔ ኑ ኢየሱስን አትስሙት" ከማለት ይልቅ በተቃራኒው "በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (በክርስቶስ) አድናችኋለሁ (ሆሴዕ 1፡7፤ ዘካርያስ 10፡12፤ 12፡5)፤ የምወደው ልጄ እርሱ ነው፤ እርሱን ስሙት፤ ታዘዙት" ሲል የማይነቃነቅ አቋሙን ይገልጻል (ማቴዎስ 17፡5፤ ማርቆስ 9፡7፤ ሉቃስ 9፡35)። እንዲሁም ራሱ እግዚአብሔር ወልድ "ማንም በእኔ በኩል ካልሆነ ወደ አብ የሚመጣ የለም፤ በሩ እኔ ነኝ" በማለት እውነታውን በግልጽ ያስረዳል (ዮሐንስ 10፡9፤ 14፡6)

አንድ እውነት ማወቅ አለብን። መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው (የሐዋርያት ሥራ 4፡12)። በብሉይ ኪዳን ሰዎች ይመጣል የተባለውን መሲህ በማመን ዳኑ። በአዲስ ኪዳን ደግሞ በመጣው መሲህ በማመን ዳኑ (ዕብራውያን 11፡39-40)። እውነቱን እና ግልጹን ለመናገር፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ፣ መዳን በወልድ ነው እንጂ ነጥሎ አብን ወይም መንፈስ ቅዱስን በማመን መዳን አይገኝም። እንዲሁም ወልድም ስለ ማይነጠል፣ በወልድ የሚያምን በርግጥ በአብ ያምናል፤ በመንፈስ ቅዱስ ያምናል። ነጥሎ በወልድ ብቻ ማመን፣ ቢፈልጉ እንኳ ከቶ የማይቻል ነው። መዳን በክርስቶስ ብቻ ለምን ሆነ? ምክንያቱም ሰዎችን ለማዳን ሰው ሆኖ የእነርሱን ቅጣት በመቀበል ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስታረቃቸው እርሱ ስለሆነ ነው። በሰው ልጆች ላይ ለመፍረድም ሆነ እነርሱን ለማዳን፣ የሰዎችን ኃጢአት ለመቁጠርም ሆነ ይቅር ለማለት ስልጣን ያለው እርሱ ነው። (ዮሐንስ 5፡22፣ 23፣ 27፤ የሐዋርያት ሥራ 7፡60፤ ዕብራውያን 2፡17)። ስለዚህ በወልድ ስናምን ወደ አብ ወደ መንፈስ ቅዱስም መቅረብን እናገኛለን (ኤፈሶን 2፡18)። አብ እና መንፈስ ቅዱስም የሚደሰቱት በዚህ ብቻ ነው። ይህ የኤሎሂም (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) ዘላለማዊ እቅድ እና የተሳካም ሥራ ስለሆነ ከዚህ መንገድ ውጭ አምላክ ማንንም አይቀበልም።

ይቀጥላል...
... የቀጠለ

ስለዚህ ጸሎታቸው፣ ጾማቸው፣ ምጽዋታቸው፣ በጎ ስራቸው ሁሉ ሰዎችን ከኃጢአት እና ከቅጣት ሊያድናቸው አይችልም። ብቸኛውን አዳኛቸውን፣ የእነርሱን ቅጣት የተቀበለውን፣ ዕዳቸውን የከፈለላቸውን እና በገዛ ደሙ የዋጃቸውን (ከቅጣት ያስተረፋቸውን) እግዚአብሔርን (ክርስቶስን) እስካላወቁ ድረስ፤ በእርሱ ጉያ እስካልተሸሸጉ ድረስ።

አዎን ጌታ ኢየሱስን እስካላመኑ ድረስ፣ መዳን በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ወይም የአብ ምስክር ነኝ ብሎ ራስን በመሰየም፣ ወይም በአገልግሎት ብዛት ወይም መልካም ሥራን በማብዛት በጭራሽ አይገኝም። ለምን? ምክንያቱም የመልካም ሥራችን ብዛት አንዲቷን ኃጢአታችንን እንኳ ለማካካስ አይችልም። የእድሜ ዘመን ኃጢአታችንን ታዲያ ምን ሊያካክሰው ይችላል? የኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ መስዋዕትነት ብቻ። የእግዚአብሔር ሕግ የሚጠይቀው የኃጢአት ክፍያ መልካም ሥራ እንዲሆን አይደለም። ያ የእኛ ባህል ሊሆን ይችላል። የእግዚአብሔር ሕግ ግን ለኃጢአታችን የሚጠይቀው ክፍያ ሞት ነው። ኃጢአት የሰራ ማንኛውም ሰው ዘላለማዊ ሞትን በመሞት የኃጢአቱን ዋጋ እንዲከፍል የእግዚአብሔር ሕግ ያስገድዳል (ሮሜ 6፡23)። እኛ ግን ትንሿን መልካም ስራችንን ይዘን ለኃጢአታችን ክፍያ እንድትሆንልን እግዚአብሔርን ልናሳምን እንሞክራለን። ምስኪኖች!

ለመሆኑ አንድ ሆቴል ገብተህ ያለውን ምርጥ ምግብ እና መጠጥ፣ ማደሪያ ሁሉ ከተጠቀምህ በኋላ አንዳንድ ውድ ብርጭቆዎችንም ከሰባበርህ በኋላ የሆቴሉ ህግ 15 ሺህ ብር እንድትከፍል ቢጠይቅህ አንተ ግን አለኝ የምትለውን ትልቅ ነገር ይዘህ በመቅረብ "እባካችሁ ያለኝ ሀብቴ በሙሉ ይህ ነውና ተቀበሉኝ" ብለህ 15 ሣንቲም ብቻ ብታቀርብላቸው የሚከተለው ምን ይሆን? እግዚአብሔር የሚጠይቀንን እንመልስ። እንጂ በእርሱ ላይ አንዘብት። የሚከተለው ምን እንደሆነ እናውቃለንና (ዕብራውያን 2፡1-4፤ ዕብራውያን 12፡25፣ 29፤ ዮሐንስ 3፡18፣ 36፤ ዕብራውያን 10፡26-31)

ዕብራውያን 10፡
26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወድደን ኃጢአት (ዮሐንስ 16፡9) ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥
27 የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ፣ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።
28 የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት (ምስክሮች) ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል (ይገደላል)
29 የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ (የካደ)፣ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ (የቀደሰንን የክርስቶስን ክቡር ደም እንደ ተራ ነገር የቆጠረ)፣ የጸጋውንም መንፈስ (መንፈስ ቅዱስን) ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?
30 በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል
31 በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር የሚጠይቀንን እንመልስ። ለመሆኑ እግዚአብሔር የሚጠይቀን ምንድር ነው? "ኃጢአት የሰራ ሁሉ በዘላለም ሞት ይቀጣ፤ ከዚህ ማምለጥ የሚፈልግ ግን በቅዱሱ አምላክ በልጄ በኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ መስዋዕትነት <<በማመን>> ወደ እርሱ ያምልጥ እና ይሸሸግ (ሮሜ 6፡23)። በቅዱሱ መንፈሴም ይታተም፤ እኔ መአቴን እና መቅሰፍቴን ሁሉ በኃጢአተኞች ላይ ከማፍሰሴ በፊት።" የእግዚአብሔር ጥያቄ ወይም ትዕዛዝ በክርስቶስ ኢየሱስ እንድናምን ነው (1ኛ ዮሐንስ 3፡22-23፤ ዮሐንስ 6፡28-29፤ ዮሐንስ 6፡40፤ ዮሐንስ 3፡16-18፤ 1ኛ ዮሐንስ 5፡8-13)

1ኛ ዮሐንስ 5፡
8 (ስለ ክርስቶስ) የሚመሰክሩት መንፈሱ እና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ ።
9 የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።
10 በእግዚአብሔር ልጅ (በክርስቶስ) የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር (በክርስቶስ) የማያምን (ግን) እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ (እግዚአብሔርን) ሐሰተኛ አድርጎታል።
11 እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ (በኢየሱስ ክርስቶስ) እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
13 የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።

አየህ፤ የአምላክ ጥያቄ ወይም ትዕዛዝ ከባድ አይደለም (1ኛ ዮሐንስ 5፡3፤ ማቴዎስ 11፡30)፤ እጅግ በጣም ቀላል እና በደስታ የምንፈጽመው ነው (ከሙሴ ሕግ ጋር አነጻጽረው -የሐዋርያት ሥራ 15፡5፣ 10)፤ በክርስቶስ ማመንን ብቻ ይጠይቃል። ዳሩ ግን በክርስቶስ ለማያምኑ ኃይማኖተኞች አሁንም ትዕዛዞቹ እጅግ በጣም የከበዱ ሆነው መታየታቸው አልቀረም።

(12) ለእያንዳንዱ ሰው ዋጋውን የሚሰጥ የሰማይ ጌታ

ራእይ 11፡
15... በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል
16 የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው
17 ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
18 አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ። ለባሪያዎችህም፣ ለነቢያትና ለቅዱሳን፣ ስምህንም ለሚፈሩት፣ ለታናናሾች እና ለታላላቆችም <<ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ>>፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።

ራእይ 22፡ (ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ)
11 ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ <<ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን>> እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
14 ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፣ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
15 ውሻዎችና አስማተኞች፣ ሴሰኛዎችም፣ ነፍሰ ገዳዮችም፣ ጣዖትንም የሚያመልኩት፣ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። (የመላእክት ጌታ አንዱ እግዚአብሔር ነው) እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።
17 መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና (ወደ ጌታ ኢየሱስ ና) ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም (ወደ ጌታ ኢየሱስ) ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።

በመቀጠልም ከሌላ ምንጭ በትዕምርተ ጥቅስ ጠቅሰህ "ወርቃማ እና የክርክርህ መሰረት" የሆነ ሕግ አስቀምጠሃል። እንዲህ ስትል፡- የአንድ ዓረፍተ ነገር ባለቤትም ሆነ ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ካላቸው "ሁለቱም የታወቁ፣ አንድ ዓይነት እና ምንም ልዩነት የሌላቸው ናቸው፤ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ሊተካው ይችላል።"

ለመሆኑ ይህን "ወርቃማ ሕግ" ያገኘኸው፤ ምንጩ ከየት ነው? ሟች እና አላፊ ከሆነው ከሰው ነው? ከዚህ አለም ጥበብ እና ጥበበኞች ነው? ወይስ ሰማይ እና ምድር ካለፉ በኋላም ከማያልፈው የክርስቶስ ቃል ነው? የጠቀስከውስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው? ወይስ ከሰው? ሁልጊዜስ እውነት ነው? የማይሻርስ እውነት ነው? ለመሆኑ አንተ እንዳልከው በዚህ ህግ፣ ሰዎች ሁሉ ይስማማሉን? ካልተስማሙስ "ወርቃማው" መሰረትህ በአንዴ ሊፈርስ ነው? በእርሱ ላይ የገነባኸው ያ ሁሉ ክርክርህስ በአንዴ ሊናድ ነውን? ለመሆኑ ይህ "መሰረታዊ" ሕግህ ማን የደነገገው ነው? የክርስቶስ ሕግ ነው ወይስ የሰዎች ሕግ? በዚህ ሕግ ተመስርተህ የምትናገረውስ ነገር ያዋጣሃልን? ቤትህስ በአለት ላይ የተመሰረተ ነውን ወይስ በአሸዋ ላይ? "አሕዛብ በአእምሮአቸው /በእውቀታቸው/ ከንቱነት እንደሚመላለሱ" ብትመላለስ ይሻልሃል ወይስ ጌታ ኢየሱስን በሚያከብረው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ብትመላለስ ይሻልሃል? ምርጫው ያንተ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው ነው /perfect God and perfect Man/። ከአምላክነቱ አንጻር ስናየው ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ፈጽሞ አንድ የሆነ እና ከቶ የማይነጣጠል እኩል ክብር እና ስልጣን ያለው ነው፤ አለም ሳይፈጠር በፊት ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ፣ አምልኮንም የሚቀበል ፍጹም አምላክ ነው፤ የአማኞቹም ዘላለማዊ አባትና ኃያል አምላክ ነው፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነው። ከሰውነቱ አንጻር ስናየው እርሱ የሰው ልጅ ሰው ነው። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን የመሰለ በንጹህ ኑሮ አብን ያስደሰተ፣ ራሱም በመንፈስ ቅዱስ የተደሰተ ፍጹም ሰው ነው፤ የአማኞችም ሊቀካህናት እና በኩር ወንድም ነው።

ወንድሜ ሆይ በየአመቱ የሚመጡ አዳዲስ የክህደት ወሬዎች እና ትምህርቶች ሊያስደንቁህ ወይም ሊማርኩህ አይገባም።

ኤርምያስ 51፡
45 ሕዝቤ ሆይ፥ ከመካከልዋ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ።
46 በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፤ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፥ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ፥ በምድርም ላይ ግፍ ይመጣል፥ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።
47 ስለዚህ፥ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል።

(13) ጸሎትን የሚሰማ እግዚአብሔር

ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ነው፤ እንጂ ወደ መልአክ ወይም ወደ ሌላ ፍጡር ጸሎት አይደረግም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሚያስተምረን ጸሎት ማለት በመንፈስ ከፈጣሪ ጋር መነጋገር ማለት ነው። ከእኛ ይልቅ ክርስቲያን መሆኑ የተረጋገጠለት ሐዋርያው ወንድም ጳውሎስ በጸሎት ከአምላኩ ከፈጣሪው ጋር ተነጋግሯል። ጳውሎስ ጣዖታዊ አልነበረምና ወደ ፍጡር ወይም ወደ መልአክ አልጸለየም፤ ዳሩ ግን ወደ ልዑልና ህያው አምላክ፣ ወደ ሰማይና ምድር ፈጣሪ ወደ እግዚአብሔር ወልድ ጸለየ።

ይቀጥላል ...
+1 ድምጽ
...የቀጠለ

የሐዋርያት ሥራ 22፡
17 ወደ ኢየሩሳሌምም ከተመለስሁ በኋላ በመቅደስ ስጸልይ ተመስጦ መጣብኝ፥
18 እርሱም (አምላክ)፦ ፍጠን ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፥ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና ሲለኝ አየሁት።
19 እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በምኵራብ ሁሉ እኔ በወኅኒ አገባና እደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ያውቃሉ፤
20 የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ።
21 እርሱም (አምላክ)፦ ሂድ እኔ ወደ አሕዛብ ከዚህ ወደ ሩቅ እልክሃለሁና አለኝ።

እርሱም... ስለኝ አየሁት፦ የእውነተኛ አማኞች መለያ ይህ ነው፤ አማኞች በጸሎት ከአምላካቸው ጋር ሲነጋገሩ አምላካቸው በመንፈሱ ይናገራቸዋል፤ ምሪትንም ይሰጣቸዋል፤ መንገዱንም ያሳያቸዋል። ክርስትና የእውቀቶች እና የትምህርቶች ክምችት አይደለም፤ ከአምላክ ጋር ባለህ ጉዞ የምትደሰትበት ህይወት ነው እንጂ።

ብዙዎች ያላዩትን ድምጹንም ከቶ ያልሰሙትን አምላክ የሚሉትን አካል ያናግሩታል። እርሱ ግን ከቶ አይናገራቸውም። ጭራሽ የሚያውቃቸውም አይመስልም። ጌታ ኢየሱስን ግን ሰዎች አይተውታል፤ ሰምተውታል፤ ዳስሰውታል፤ አምነውበታልም (1ኛ ዮሐንስ 1፡1-4)፤ በኢየሱስም ተራኪነት አብን (አባትን) እና እርሱ የሰጠውን ተስፋ መንፈስ ቅዱስን አውቀዋል። ጌታ ኢየሱስን ሲያመልኩት እርሱም በምላሽ ጸሎታቸውን ሲያደምጥ እና ሲመልስ ይታያሉ። አቤቱ አምላክ ሆይ፣ የሃይማኖት መልክ ይዘው ኃይልህን ግን ክደው ለሚቸገሩት ማስተዋልህን ለግሳቸው። በታላቅ ስምህ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አሜን።

ጌታ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን... በወኅኒ አገባና እደበድብ እንደ ነበርሁ፦ ወንድም በማን ታምናለህ? እምነትህን የጣልኸው በማን ላይ ነው? ለነፍስህ፣ ለዘላለም ቤትህ ተስፋ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? መሰደድ እና መደብደብ ካለብህስ የማንን ስም ሰብከህ መደብደብ ይሻላል? አዎን እንደ ቀደሙት ሐዋርያት እንደ እውነተኞቹ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ስም ሰብከን ስለ ስሙ መከራን እንቀበላለን።

የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም... በአዲስ ኪዳን ማለት በክርስትና ዘመን የምናነበው በሙሉ ስለ ኢየሱስ ሰማዕቶች ነው። አንተስ ወንድም ሰማዕት መሆን ካለብህ የማን ሰማዕት ልትሆን ወሰንህ? (ሰማዕት ማለት ግዕዝ ሲሆን በአማርኛ ምስክር ማለት ነው። በዚህ ቦታ ቃሉ የሚያሳየው የአምላካቸውን የኢየሱስን ስም በመመስከር እና በምስክርነታቸውም በመጽናት እስከ ሞት ድረስ የሄዱ አማኞችን ያመለክታል።)

እርሱም (አምላክ)፦ ሂድ እኔ ... እልክሃለሁና አለኝ፦ አምላክ ነቢያትን፣ አስተማሪዎችን፣ እንዲሁም መላዕክትን (የዮሐንስ ራእይ 22፡16) ይልካል። ወደ የት? ወደ ሰዎች። ለምን? ቃሉን ሰምተው ወደ እምነትና ወደ ንስሃ እንዲመለሱ። ጌታ ኢየሱስ ባሪያውን ጳውሎስን ወደ አህዛብ በመላኩ ዛሬ የኢየሱስ (የእግዚአብሔር) ወንጌል አህዛብ ወደ ነበርነው ወደ እኛ ደርሷል። ፍቅር የሆነውን ወንጌሉን (የምስራቹን ዜና) በባሪያው በኩል ወደ እኛ የላከ ልዑል እግዚአብሔር ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን።

የኢየሱስ (የእግዚአብሔር) ወንጌል
ሮሜ 15፡18-19፤
1ኛ ቆሮንቶስ 9፡12፤
2ኛ ቆሮንቶስ 10፡14፤
ገላትያ 1፡7
ማርቆስ 1፡1፤
ሮሜ 1፡1-2፤
2ኛ ቆሮንቶስ 2፡12፤
2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4፤
2ኛ ቆሮንቶስ 9፡13፤
2ኛ ቆሮንቶስ 10፡14፤
ፊልጵስዩስ 1፡27፤
1ኛ ተሰሎንቄ 3፡2፤
2ኛ ተሰሎንቄ 1፡8።

ማናቸውንም ነገር ማድረግ ወደሚቻለው ወደ ኤል ሻዳይ እንጸልያለን፤ ጸሎት የሚጸለየው ወደ እርሱ ነውና (ኤል ሻዳይ ማለት ዕብራይስጥ ሲሆን ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ማለት ነው)

ኤል ሻዳይ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦

ዮሐንስ 14፡
12 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል (የጸሎቱን መልስ ያገኛል)
13 እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር <<በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ>>።
14 <<ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ>>።

በእኔ የሚያምን... ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፦ ወንድም መቶ በመቶ በጌታ በኢየሱስ ማመን አለብህ። እርሱ "በስሙ የምትለምነውን ሁሉ ለማድረግ" የሚቻለው ዘላለማዊ አምላክ መሆኑን ማመን አለብህ። በርግጥ ካመንህ በስሙ ለምነህ የጸሎትህን መልስ ትቀበላለህ። እርሱ የሰራቸውን አይነት ታላላቅ ሥራዎችንም መስራት ከዚያም በላይ መስራት ይቻልሃል። ብዙዎች ጸሎት ተራራ እንደ መግፋት የሆነባቸው ለምንድር ነው? ጸሎታቸውም መልስ እንደማያገኝ የሚያስቡት ለምንድር ነው? አዎን ክርስቶስን እና ሃይሉን ስለማያምኑ ወይም ስለካዱ ነው። "የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡ 5)

እውነተኛ አማኞች ግን ወደ አምላካቸው ወደ ኢየሱስ (ወደ ቲቶ 2፡ 12-13) ጸልየው የጸሎታቸውን መልስ እየተቀበሉ ነው ። የእኛ ጌታ ኢየሱስ በምድረ አለም ዙርያ በተለያየ ሥፍራ ያሉ አማኞቹ በሙሉ በስሙ የሚጸልዩትን ጸሎት መስማት የሚችል፣ የሚለምኑትን ማናቸውንም ነገር ለማድረግ ኃይል ያለው (ኤል ሻዳይ) ነው። ይህን ካላመንህ ወይም ከተጠራጠርህ እድሜህን ሙሉ ብትጸልይ ከእግዚአብሔር አንዳች ነገር የምታገኝ አይምሰልህ።

ያዕቆብ 1፡
6 ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።
7-8 ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።

ኢየሱስ እንደ ፍጹም ሰው አሁን በአጠገባችን በአካል ባይገኝም እርሱ ፍጹም አምላክ (perfect God) ነውና በአለም ዙርያ ሁሉ ከአማኞቹ ጋር ለመገኘት ቃል ገብቶልናል (ማቴዎስ 28፡20)። እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር (ወልድ) ነውና ማናቸውንም ነገር በስሙ ብንለምነው ሊያደርግልን ቃል ገብቶልናል። ሰማይና ምድር ካለፉ በኋላም ይህ ቃሉ አያልፍም። ለምን? ምክንያቱም እርሱ ኃያል አምላክ ስለሆነ ቃሉ ዘላለማዊ ስልጣን አለው (ኢሳይያስ 9፡6)። ዛሬም ህያው አምላካችን ኤል ሻዳይ ለሚሰማው ሁሉ ይናገራል እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ ... አብም ስለ ወልድ እንዲከበር <<በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ ፤ ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ>>(ዮሐንስ 14፡ 12-14)

ክርስቲያኑ እስጢፋኖስ ወደ አምላኩ ወደ ነፍሱ ፈጣሪ ወደ ኢየሱስ ጸለየ።
ጸሎት ከአምላክ ጋር መነጋገር ሲሆን እስጢፋኖስም ይህን አደረገ።

የሐዋርያት ሥራ 7፡
55 (እስጢፋኖስ) መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር (አብ) ቀኝ ቆሞ አየና፦
56 እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም (ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ኢየሱስ) በእግዚአብሔር (አብ) ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።
57 (ተቃዋሚዎችም) በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፥ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፥
58 ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ።
59 እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
60 ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ... ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና ፦ አንድ ተቃዋሚ ወዳጄ ከእኔ ጋር ሲነጋገር በዚህ ክፍል ጥያቄ አስነሳ፤ ከምንነጋገርበት ርዕስ ዘልሎ ወጣና ፦ "እስጢፋኖስ ያየው አብን እና በቀኙ የቆመውን ኢየሱስን ብቻ ነው እንጂ ሶስት ወንበር ላይ ጎን ለጎን የተቀመጡ ሶስት አካላትን አላየም፤ በአጠገባቸው መንፈስ ቅዱስን ያላየው ለምንድር ነው? የስላሴ ትምህርት ውሸት መሆን አለበት!" አለ።

እኔም እንዲህ አልኩት፦ ወዳጄ ሆይ፣ ከርዕሳችን ለምን ፈጥነህ ወጣህ? ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ጋር ቂም አለብህ እንዴ? ቶሎ ቁጣህን ስትገልጥ አይቼሃለሁ። ምነው አይኖችህ ተከፍተው ተመልከት እንጂ። ቃሉ እኮ በሶስት ወንበር ስለተቀመጡ ሶስት አካላት አልተናገረም፤ ጌታ ኢየሱስ ከምድር ሊሄድ ሲል "እኔ እሄዳለሁ ሌላ አጽናኝ እልክላችኋለሁ" ብሎ ቃል በገባው መሰረት መንፈስ ቅዱስ እታች ምድር ላይ ከትንንሽ ልጆቹ ከእኛ ጋር ነው። ወልድ ደግሞ ከአብ ጋር እላይ በዙፋኑ ላይ ነው። እስጢፋኖስ አብን እና ወልድን ያየው እኮ በምድር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ነው (የሐዋርያት ሥራ 7፡ 55)። ሆኖም እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስፍራ አይወሰንምና ቁጥጥ ብሎ ትንሽ ወንበር ላይ የሚወሰን ሳይሆን በስፍራዎች ሁሉ የሚገኝ (ማቴዎስ 18፡20፤ ማቴዎስ 28፡20፤ ራእይ 3፡20፤ ዮሐንስ 14፡23፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡ 22) ኃያል አምላክ ነው።

መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ... እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ ፦ ወዳጄ ሆይ መንፈስ ቅዱስን ተሞልተሃልን? መንፈስ ቅዱስን ስትሞላ የምታየው ሌላ ነገር ሳይሆን ወልድን እና አብን ነው። መንፈስ ቅዱስን ስትሞላ ጌታ ኢየሱስን ታከብረዋለህ። ጌታ ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር "እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና" አለ። (ዮሐንስ 16፥14)

ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፦ ወዳጅ በእውነት ስለ ኢየሱስ ለመወገር (ለመገደል) ዝግጁ ነህ? ብዙዎች በኢየሱስ እንደ ሚያምኑ ሊናገሩ ይችላሉ። ነገር ግን በፍጹም ልባቸው አያምኑትምና ስለ እርሱ ዋጋ ለመክፈል አይፈቅዱም። (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡5-18)

ኢየሱስን በማመንህ ምክንያት ቤተ ሰቦችህን እንድታጣ ወይም ነፍስህን እንድታጣ የሚያስገድድ ሁኔታ ቢፈጠር ይህን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነህ? ጌታ እንዲህ ብሏል፦

ሉቃስ 14፡
26 ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር (ዮሐንስ 14፡6) አባቱንና እናቱን፣ ሚስቱንም፣ ልጆቹንም፣ ወንድሞቹን፣ እኅቶቹንም፣ የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ (ከእነዚህ ሁሉ አስበልጦ እኔን ባይወድድ)፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
27 ማንም መስቀሉን (መከራውን) ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

ሉቃስ 14፡
33 እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው (ስለ እኔ የትኛውንም ዋጋ ለመክፈል የማይፈቅድ) ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

ማርቆስ 8፡
34 ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።
35 ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።
36 ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
37 ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
38 በዚህም በዘማዊ እና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔ እና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ (ክርስቶስ) ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።

ጌታ ኢየሱስ በስጋ ከመገለጡ በፊት ቃል የነበረ የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ራሱ በመሆኑ፣ ሰዎች ሁሉ በሙሉ ልባቸው እርሱን እንዲያምኑት ይፈልጋል። ደግሞም በምንም ምክንያት እንዳይክዱት ይጠይቃል። ለሚክዱትም ዘላለማዊ ቅጣት እንደ ሚጠብቃቸው ያስጠነቅቃል፤ እንዲህ በማለት፦

ማቴዎስ 10፡
27 በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት (በአደባባይ) ላይ ስበኩ።
28 ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ...
32 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ፣ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤
33 በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ፣ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።


ይቀጥላል....
Nov 5, 2013 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
Jan 24, 2014 child of Jesus ታርሟል
...የቀጠለ

ራእይ 2፡
8 ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦...
10 ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን፤ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።

ጌታ ለጳውሎስ ሲናገር፦
የሐዋርያት ሥራ 26፡
17-18 የኃጢአትንም ስርየት (ያገኙ ዘንድ) <<በእኔም በማመን>> በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።

ይህን የተረዳው ጳውሎስም ሲናገር፦
ገላትያ 2፡
16 ነገር ግን ሰው <<በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን>> እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ <<በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል>>።

ፊልጵስዩስ 3፡
8-9 አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ <<በክርስቶስም በማመን>> ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ።

እስጢፋኖስም ፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ...
ተንበርክኮም ፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ
፦ ልክ ነብዩ ኤልያስ ነፍሱን እንዲቀበል ወደ አምላክ እንደተጣራ፣ እስጢፋኖስም ወደ ታመነው አምላክ (ወደ ኢየሱስ) በመጸለይ ነፍሳችንን ለመቀበል ብቸኛው ባለመብት ማን መሆኑን ይመሰክራል። ፍጹም ሰው ፍጹም እግዚአብሔር የሆነው ክርስቶስ የታመነ ፈጣሪ የነፍሳችን ባለቤት ነው (1ኛ ጴጥሮስ 4፡19)። እንዲሁም የሰዎችን ኃጢአት ለመቁጠርም ሆነ ይቅር ለማለት ሉዓላዊ ስልጣን ያለው ብቸኛው ባለ መብት ኢየሱስ መሆኑን እስጢፋኖስ ሲመሰክር ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ

ኃጢአትን ይቅር የሚል እግዚአብሔር

(ማቴዎስ 9፡2-5፤ ማርቆስ 2፡5-9፤ ሉቃስ 5፡20-23፤ ሉቃስ 7፡48፤ ኤፌሶን 1፡7)

መዝሙር 103፡
1 ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን።
2 ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤
3 ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥
4 ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥
5 ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
6 እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።

መዝሙር 25፡
11 አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና <<ስለ ስምህ>> ይቅር በለኝ።
1ኛ ዮሐንስ 2፡
12 ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ <<ስለ ስሙ>> ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።

ፈዋሽ አምላካችን ኢየሱስ (እግዚአብሔር)

ማቴዎስ 9፡
2 እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ "ኃጢአትህ" ተሰረየችልህ አለው (...ሽባውም ተፈወሰ)

መዝሙር 103፡
2 ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤
3 "ኃጢአትሽን" ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ።

የሐዋርያት ሥራ 9፥
33 በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ።
34 ጴጥሮስም፦ ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ አለው።

ምንም እንኳ ኢየሱስ አሁን እንደ ፍጹም ሰው በጴጥሮስ አጠገብ በአካል ባይገኝም፣ ከትንሳኤው በኋላ በአካል ወደ ሰማይ ያረገ ቢሆንም፣ አማኙ ጴጥሮስ በመንፈስ ሆኖ የአምላኩን የኢየሱስን (የእግዚአብሔርን) ስም ይጠራል። ኢየሱስ ፍጹም ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጹም አምላክ እግዚአብሔር በመሆኑ በየትኛውም ስፍራ ከአማኞቹ ጋር ለመገኘት ቃል ገብቶልናል (ማቴዎስ 28፡20፤ ማቴዎስ 18፡20)። እንዲሁም እርሱ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር (ኤል ሻዳይ) በመሆኑ "ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ" ሲል ቃል ገብቶልናል (ዮሐንስ 14፡13-14)። ጌታ ኢየሱስ "እነሆ እኔ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" (ማቴዎስ 28፡20) ብሎ ቃል በገባው መሠረት፣ ጴጥሮስ አምላኩን ታምኖ በጸሎት ሲጠራው እና የጸሎቱንም መልስ ሲቀበል እናያለን። ፈዋሻችን አምላካችን ኢየሱስ (እግዚአብሔር) እንዲህ ብሎ ነበር ፦ "እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና" (ዘጸአት15፡26)። ልብ በል ጴጥሮስ የፍጡራንን ወይም የመላእክትን ስም አልጠራም። በታማሚው በኤንያ ላይ የአምላኩን የሕያው እግዚአብሔርን ስም ጠራ፦ "ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ" አለው። የጸሎቱንም መልስ ተቀብሏል፦ (ኤንያ) ወዲያው ተነሣ። በልዳ እና በሰሮናም የሚኖሩ ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ (ኢየሱስ) ዘወር አሉ (የሐዋርያት ሥራ 9፥35)። ዛሬም ቢሆን ታላቁ አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ our great God and Savior Jesus Christ (ቲቶ 2፡13) የመፈወስ ኃይል አለው።

...ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥ እያመሰገነውም "በእግሩ ፊት" በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ። ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ? ከዚህ ከልዩ ወገን (ከሳምራዊው) በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ (በእግሬ ፊት ሊሰግዱ) የተመለሱ አልተገኙም አለ። እርሱንም፦ ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው (ሉቃስ 17፡ 15-19)

ጸሎት ማለት ከአምላክ ጋር መነጋገር ማለት ነው። የክርስቶስ ደቀ መዝሙር (ክርስቲያን) የሆነው ሐናንያ በጸሎት ከአምላኩ ከፈጣሪው ጋር ተነጋገረ። ልብ በል፤ ሐናንያ ጣዖታዊ ወይም አህዛባዊ አልነበረም፤ አምላክን ትቶ ወደ ፍጡር ወይም ወደ መልአክ፣ ወይም ወደ ክፉ መናፍስት አልተናገረም፤ ወደ ህያው አምላክ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ እንጂ። እንዲሁም ጳውሎስ በጸሎት ከፈጣሪ ጋር ተነጋገረ (2ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-9)። ይህ ጌታ ዛሬስ ካንተ ጋር ተነጋግሮ ያውቃልን? ወይስ እርሱን ስለ ማታምነው እና ኃይሉን ስለ ካድኸው ገና በሩቅ እንዳለህ ይሰማሃል?

የሐዋርያት ሥራ 9፡
10 በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ። ጌታም (ኢየሱስ) በራእይ፦ ሐናንያ ሆይ፥ አለው። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ አለ።
11 ጌታም፦ ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፥ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤
12 እነሆ፥ እርሱ (ሳውል) ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ (አይኑ እንዲከፈት) እጁን (በእርሱ ላይ) ሲጭንበት (ሳውል) አይቶአል አለው።
13 ሐናንያም መልሶ፦ ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤
14 በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው አለ።
15 ጌታም፦ ይህ (ሳውል) በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤
16 ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና አለው።
17 ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ።
18 ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥
19 መብልም በልቶ በረታ። በደማስቆም ካሉት ደቀ መዛሙርት ጋር ጥቂት ቀን ኖረ።
20 ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራቦቹ ሰበከ።

(14) ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው፤ በእግዚአብሔር (በክርስቶስ) እመን፤ ትድናለህ

የሐዋርያት ሥራ 16፡ (በወኅኒ ቤት ውስጥ)
25 በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስ እና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን (ክርስቶስን) በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር።
26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።
27 የወኅኒውም ጠባቂ (ወታደር) ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
28 ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ።
29 (ወታደሩ) መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤
30 ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
31 እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ (በእግዚአብሔር ወልድ) እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።
32 ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን (የክርስቶስን) ቃል ተናገሩአቸው።
33 በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር (በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም -የሐዋርያት ሥራ 2፡38) ተጠመቀ፤
34 ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ <<በእግዚአብሔርም (በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ) ስላመነ>> ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ።

ለመሆኑ እነ ጳውሎስ በወኅኒ የታሰሩት ስለ ምን ነበር? ከኢየሱስ ውጭ የሆነ አምላክ ሰብከው ነውን? አይደለም። የተሰቀለውን አምላክ ክርስቶስን ስለ ሰበኩ ነው እንጂ (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡ 10-13)። አንተስ የማን ሰባኪ ነህ? የማን ምስክር ነህ? ወዳጄ ሆይ አጭሯን ዕድሜህን በከንቱ አታባክን። እንደ ጳውሎስ ከጌታ እጅ የጽድቅ አክሊል ተሸላሚ መሆን ከፈለግህ የተሰቀለውን አምላክህን ስበክ፤ እንጂ ከእርሱ ውጭ የሚኖር "ሌላ አምላክ" ፈጥረህ ሃይማኖትህን እየሰበክህ በከንቱ አትድከም።

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡
8 በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን <<ኢየሱስ ክርስቶስን>> አስብ፤
9 ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር (የኢየሱስ ክርስቶስ) ቃል ግን አይታሰርም (ማቴዎስ 24፡35)
10 ስለዚህ እነርሱ (የተመረጡት) ደግሞ <<በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን>> ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር (በመከራ) ሁሉ እጸናለሁ።
11 ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፦ ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤
12 ብንጸና፥ ከእርሱ (ከኢየሱስ ክርስቶስ) ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤
13 ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።
14 ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ (ምክንያቱም) ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።
15 የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
16 ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ (ክርክር) ራቅ፤ (እንደዚህ ያሉ ሰዎች) ኃጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፥ ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤
17 ከእነርሱም ሄሜኔዎስ እና ፊሊጦስ ናቸው፤
18 እነዚህም... ስለ እውነት ስተው፥ የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።
19 ሆኖም፦ "ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል"፥ ደግሞም፦ "የጌታን (የኢየሱስን) ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ (ከክህደት) ይራቅ" የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል ...
22 በንጹሕም ልብ ጌታን (ኢየሱስን) ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።
23 ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤
24 የጌታም (የኢየሱስ) ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።
25-26 ደግሞም፦ "ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሐን ይሰጣቸዋልና፤ ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው ወደ አእምሮ ይመለሳሉ" ብሎ የሚቃወሙትን (ተቃዋሚዎችን) በየዋህነት ይቅጣ።

ጳውሎስ ስለ አገልግሎቱ ሲመሰክር፦

1ኛ ቆሮንቶስ 1፡
22-23 መቼም አይሁድ ምልክትን (ተአምራትን) ይለምናሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን (ምርምርን) ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡
2 በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና።

ሮሜ 15፡
18-19 አሕዛብ እንዲታዘዙ ክርስቶስ በቃል እና በሥራ፥ በምልክት እና በድንቅ ነገር ኃይል፥ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል በእኔ አድርጎ ከሠራው በቀር ምንም ልናገር አልደፍርም፤ ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ

የሐዋርያት ሥራ 8፡
5 ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው።

እውነተኛ ክርስቲያን (የክርስቶስ ተከታይ) መለያው እዚህ ጋር ነው። በአሮጌው ኪዳን የሚኖር አንድ እውነተኛ አይሁዳዊ ይሰብክ እና ይመሰክርለት የነበረው ያልተሰቀለውን ያህዌን ነበር። በአዲስ ኪዳን የሚኖር አንድ እውነተኛ ክርስቲያን ግን የሚሰብከው ስለ እርሱ የተሰቀለውን እና በገዛ ደሙ የዋጀውን ያህዌን ነው (የሐዋርያት ሥራ 20፡28)። ብዙዎች ግን ነገሩ ስለ ዞረባቸው በአዲስ ኪዳን እንዲኖሩ ታዝዘው ሳሉ፣ አዲስ ኪዳን ተገብቶላቸው ሳለ በአሮጌው ኪዳን ለመኖር ሲታገሉ ከሁለቱም ኪዳኖች ውጭ ሆነዋል። እንደ አሮጌው ኪዳን ለመስበክ ሲደክሙም ውድ ዕድሜያቸውን አባክነዋል።

የተሰቀለውን ጌታ ብቻ እንዲህ ሲሰብክ የኖረው አማኙ ጳውሎስ በሕይወቱ ፍጻሜ በርግጠኝነት እንዲህ ሊል ቻለ፦

ይቀጥላል...
...የቀጠለ

2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡
6 በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና (ስለ አምላኬ ስለ ክርስቶስ ስም መስዋእት ሆኜ ልገደል ነው)(ከክርስቶስ ጋር ለመኖር) የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል (ፊልጵስዩስ 1፡23)
7 መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
8 ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።

አንተስ ወገኔ ሆይ በአገልግሎትህ፣ ስለ አንተ የተሰቀለውን አምላክህን ክርስቶስን ትሰብካለህ? (የሐዋርያት ሥራ 8፡5)። የእርሱ ምስክር ነህ? ወይስ በአንተ ፋንታ እጅግ ዝቅ ዝቅ ባለው በእርሱ ታፍራለህ? (ማቴዎስ 10፡32-33፤ ማርቆስ 8፡34-38፤ ሉቃስ 9፡23-26)። በመስዋእት እንደሚደረግ ስለ አምላክህ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስም (2ኛ ጴጥሮስ 1፡1) ለመሰዋት ትፈቅዳለህን? በሕይወትህስ መጨረሻ ደቂቃ ላይ እንደ ጳውሎስ እና እንደ እኔ እንዲሁም እንደ ሌሎቹ አማኞች ከጌታ እጅ ተሸላሚ እንደምትሆን እርግጠኛ ሆነህ ማወጅ ትችላለህን? የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡7)

ፈጣሪህን እመን እንጂ "ምሁርን" አትመን

"የምሁራንን" ቃል ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንደ ምታምን ከአቀራረብህ እረዳለሁ። ይህ ግን መሆን የለበትም። የትኛውም "ምሁር" ሟች ነው አላፊ ነው ወዳቂ ነው (መዝሙር 118፡8-9)። ትምህርቱም ይሻራል። የፈጣሪያችን ቃል ግን በማይሻር ስልጣኑ ለዘላለም እያበራ ይኖራል እንጂ ከቶ አያልፍም (ማቴዎስ 24፡35)። ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ (ማርቆስ 13፡31)፤ ሰዎች ያልፋሉ (ኢሳይያስ 40፡6-8)። ትውልድም ያልፋል፤ እኔና አንተም ዛሬ ላይ ስንታይ የማናልፍ እንመስላለን እንጂ እናልፋለን። የጌታ ኢየሱስ ቃል ግን እያሸነፈ (ሉቃስ 21፡33፤ ዮሐንስ 5፡24)፣ ጠላቶቹንና ውሸታቸውንም ሁሉ እያደቀቀ (1ኛ ሳሙኤል 2፡10) ከሚመጣው አዲስ ትውልድ ጋር አዲስ ሆኖ ይቀጥላል -ጌታ ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ (ኤርምያስ 31፡31፤ ሰቆቃወ 3፡23፤ ማርቆስ 1፡27፤ ሉቃስ 22፡20፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17)። "ምሁራንም" ያልፋሉ (ኢሳይያስ 40፡30)። "ምሁር" በሞት ፊት ሲቆም (መክብብ 8፡8) ባዶነት፣ ብቸኝነት፣ ረዳት-የለሽነት፣ ጸጸት እና ኃጢአተኝነት የሚሰማው ነው (ሞትን ባሸነፈው ጌታ እስካላመነ ድረስ)

እንኳን ላንተ የእምነትህ መሰረት ሊሆን እና የመከራከርያ ማስረጃ ምንጭ ሊሆን፣ "ምሁር" ራሱንም ማዳን የማይችል ነው። ተወዳጁ ኢትዮጵያዊው ምሁር እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስም ያ ሁሉ እውቀት እና ስልጣን እያለው ራሱን ከሞት ማስጣል አልቻለም ነበር።

በታላቁ አምላክህ (ቲቶ 2፡12-13) ፊት ስትጠየቅ "የምሁርን" ጽሁፍ ወይም ዌብሳይት ጠቅሰህ ራስህን ልትከላከል አትችልም። ይልቅ የታላቁን መምህር የክርስቶስን ቃል መሞላት ብልህነት ነው፤ ከስህተትም ያድንሃል። የትኛውንም "ምሁር" አትታመን፤ የእምነትህም መሰረት አታድርግ። ከ"ምሁራን" ጽሁፍ ይልቅ በእጅህ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ እመን፤ ከእርሱም ብቻ ጠቅሰህ እምነትህን አስረዳ። ከሁሉ በላይ ማስተዋል ያለብህ፣ ዛሬ አንዱ "ምሁር" ያስተማረውን ነገ ሌላው "ምሁር" መጥቶ እንደ ሚሽረው (disprove እንደ ሚያደርገው) ነው። አምላክ ሉዓላዊ ባለ ስልጣን ስለ ሆነ፣ የሚያሸንፈውም ስለ ሌለ በኃላፊነት እና በበላይ ጠባቂነት የራሱን ቃል ጠብቆ ለእኛ አድርሷል። ቃሉ ይበቃናል፤ ቃሉን ትተን ማለቂያ ወደሌለው ወደ ትውልዶች "ምርምር" ዘወር ብንል ይጎዳናል እንጂ አይረባንም።

ራሳቸውን "ምሁር" ብለው የሚጠሩ እንዲሁም ሰዎች "ምሁር" የሚሏቸው ልክ እንደ እኔ እና እንደ አንተ ያሉ ደካማ ሰዎች ናቸው። ሟች እና ተጠያቂ የሆኑ ደካማ ሰዎች ግዙፍ ኢንሳይክሎፒዲያዎችን መጻፍ እና ማሳተም ስለ ቻሉ በጽሁፋቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መተርጎም (መተንተን) እንደ ሚችሉ ያስባሉ። አምላክ ግን ለማንም የመተርጎም ስልጣን አልሰጠም (2ኛ ጴጥሮስ 1፥20)። ይሁንና ሰው አቅሙ እስከ ሚፈቅድለት ድረስ የዚህን አለም ጥበብ ተምሮ የማህበረሰብ ሳይንስ ምሁር (ሊቅ)፣ የታሪክ ዶክተር፣ የኬምስትሪ ፕሮፌሰር (ሊቅ)፣ የምህንድስና ፕሮፌሰር (ምሁር)፣ የፖለቲካ ምሁር (ፕሮፌሰር)... ወዘተ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አቅሙ ስለ ማይደርስለት ማንም የእግዚአብሐር ደቀ መዝሙር (ተማሪ) ነው እንጂ የስነ እግዚአብሐር አስተማሪ/ዶክተር ወይም የስነ መሎኮት (የቲዎሎጂ) ሊቅ/ፕሮፌሰር/ምሁር፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር፣ የአዲስ ኪዳን ሊቅ፣ የብሉይ ኪዳን ፕሮፌሰር... ወዘተ ሊሆን አይችልም። ሰው ራሱን እንዲህ ብሎ ቢሰይምም እንዲህ የሰየመው ራሱ ነው ወይም መሰሎቹ ናቸው እንጂ አምላክ ማንንም እንዲህ አልሰየመም። ስለዚህ ይህ ስያሜ ትክክል አይደለም።

በክርስትና ውስጥ ምሁር (ሊቅ) ብሎ ነገር የለም። ሁሉም ክርስቲያን ሁልጊዜም የአምላክ ተማሪ (ደቀ መዝሙር) ነው (ያዕቆብ 1:5)። እንጂ ማንም የበላይ "ምሁር" የለም።

1ኛ ቆሮንቶስ 3፡
18 ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም "ጥበበኛ" የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።
19-20 የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት (ከንቱ) ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና።
21 ስለዚህም ማንም በሰው ("በምሁር") አይመካ። (ምክንያቱም በክርስቶስ ኢየሱስ) ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤
22 (መሪ አገልጋዮች ለምሳሌ) ጳውሎስ ቢሆን፣ አጵሎስም ቢሆን፣ ኬፋም (ጴጥሮስ) ቢሆን፥ ዓለምም ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ ሞትም ቢሆን፣ (አሁን) ያለውም ቢሆን፣ (ወደ ፊት) የሚመጣውም ቢሆን፥
23 ሁሉ የእናንተ ነው (ይህ ማለት ግን "ሁሉ ከእናንተ የበታች ነው" ማለት አይደለም፤ የበላይ ነው ማለትም አይደለም -1ኛ ቆሮንቶስ 4፡10፤ ማቴዎስ 23፡8፤ ገላትያ 3፡28፤ ሮሜ 12፡16)፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ (ይህ ቃል በራሱ የበታችነትን ወይም የበላይነትን አያመለክትም)፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው (ይህም የበታችነትን ወይም የበላይነትን አያመለክትም)

ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ደቀ መዝሙር (ተማሪ) ማለት ነው። ክርስቲያን ከሆንህ ሁልጊዜ የክርስቶስ ተማሪ፣ ተከታይ ነህ። እስከ መጨረሻውም በክርስትና ላይ ምሁር፣ ሊቅ ወይም ፕሮፌሰር ልትሆን አትችልም። ራሱን "የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር" ብሎ የሚጠራ ሰው ደቀ መዝሙር (ተማሪ) መሆኑን ያቆመ ወይም የረሳ ሰው ነው። ስለዚህ ራሳቸውን "ምሁር" (ጠቢብ) ብለው የሚጠሩ፣ ወይም ሰዎች "ምሁር" የሚሏቸው ሁሉ "ምሁር" አለመሆናቸውን አስተውል፤ ምክንያቱም አምላክ "ምሁር" (ጠቢብ) አላላቸውም።

1ኛ ቆሮንቶስ 1፡
17 ...የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም።
18 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
19 የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ፤ ተብሎ ተጽፎአልና።
20 ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ (ምሁር) የት አለ? የዚች ዓለም መርማሪስ (ፕሮፌሰር) የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?
21 በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።
22 መቼም አይሁድ ምልክትን (ተአምራትን) ይለምናሉ፤ የግሪክ ሰዎችም (አህዛብ) ጥበብን (ምርምርን) ይሻሉ፥
23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ (አንተስ የተሰቀለውን ወይስ ያልተሰቀለውን በመስበክ እድሜህን ትጨርሳለህ?)
24 ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይል እና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
25 ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር (የኢየሱስ) ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም (የኢየሱስ) ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።
26 ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ "እንደ ሰው ጥበብ" ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።
27 ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር (እኛን) መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር (እኛን) መረጠ፤
28 እግዚአብሔርም (ኢየሱስ) የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ (ዮሐንስ 6፡70)
29 ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ፤
30-31 ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር (በክርስቶስ)) ይመካ (ፊልጵስዩስ 3፡3) ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ፣ ቅድስናም፣ ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ (የተነሳ) ነው።

ሰዎች ራሳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር (ሊቅ)፣ የአዲስ ኪዳን ሊቅ፣ የብሉይ ኪዳን ሊቅ (ምሁር) ...ወዘተ እያሉ ቢጠሩም ክርስቶስ አያውቃቸውም። እንዲህ የሾማቸውም ክርስቶስ ሳይሆን ራሳቸው ወይም ሌሎች ሰዎች ናቸው ። ክርስቶስ እንዲህ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቶን ነበር፦ "እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ (መንፈስ ቅዱስ) ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ (አብ) ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ (ወልድ) ነውና "ሊቃውንት" (ነጠላ- ሊቅ) ተብላችሁ አትጠሩ" (ማቴዎስ 23፡8-10)

ሁላችንም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት (ክርስቲያኖች) ነን። በክርስትና ላይ ክርስቶስ ብቻ ብቻውን ሊቅ፣ ምሁር፣ ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ መምህር፣ አዋቂ ነው። "የእምነታችንን ራስ እና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ" (ዕብራውያን 12፡1-2)

ማንንም ምሁር (ሊቅ) ብለን እንዳንጠራ፣ ራሳችንም ሊቅ ተብለን እንዳንጠራ፣ እርሱን ብቻ ሊቅ (ምሁር) ብለን እንድንጠራው ክርስቶስ አዝዞናል። ክርስቶስ ብቸኛው ሊቃችን (ምሁራችን) ነው። ከእርሱ እንማራለን። ከእርሱ የሰማኸውን ታስተምረኛለህ፤ እኔም ከእርሱ የተማርሁትን እነግርሃለሁ። በዚህ መልክ እንማማራለን “ (ቆላስይስ 3:16) እንጂ ማንም ሁልጊዜ ያንተ ምሁር ወይም መምህር (ፕሮፌሰር) ሆኖ ክርስቶስን ሊያስተምርህ አይችልም።

ማቴዎስ 23፡
1 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡ እና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው...
6 በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥
7 በገበያም ሰላምታና፦ "መምህር ሆይ፣ መምህር ሆይ" ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።
8 እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ (መንፈስ ቅዱስ) ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ (አብ) ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።
10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ (ወልድ) ነውና "ሊቃውንት" (ነጠላ- ሊቅ) ተብላችሁ አትጠሩ።
11 ከእናንተም የሚበልጠው (በምን? በእድሜ፣ በእውቀት ወዘተ) አገልጋያችሁ ይሆናል።
12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።
13 እናንተ ግብዞች (አስመሳዮች) ጻፎች እና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።

ዛሬ "የጳውሎስን መጻሕፍት" ያጠኑ ሰዎች ራሳቸውን "የአዲስ ኪዳን ፕሮፌሰር"፣ "የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ" እያሉ ሲጠሩ ይታያሉ። ዳሩ ግን በርግጥም በአገልግሎቱ የተሳካለት ጳውሎስ፣ ሁልጊዜም ክርስቲያን (የክርስቶስ ደቀ መዝሙር) ስለሆነ እንዲህ ራሱን አልሾመም ነበር። ጳውሎስ ሁልጊዜም ክርስቲያን (የክርስቶስ ተማሪ) መሆኑን አጥብቆ ስለ ተረዳ በአገልግሎቱ መገባደጃ ላይ "ወንድሞች ሆይ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ" ብሎ ነበር፦

ይቀጥላል...
...የቀጠለ

ፊልጵስዩስ 3፡ (ጳውሎስ ሲናገር)
1 በቀረውስ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ስለ አንድ ነገር መልሼ ልጽፍላችሁ እኔን አይታክተኝም፤ ለእናንተ ግን ደኅና (ጠቃሚ) ነው።
2 ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ።
3 እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ (1ኛ ቆሮንቶስ 1፡30-31) በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና (እውነተኛ መገረዝ ይኼ ነው)
4 እኔ ግን በሥጋ ደግሞ የምታመንበት አለኝ። ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ የሚታመንበት እንዳለው ቢመስለው፥ እኔ እበልጠዋለሁ።
5 በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤
6 ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ ያለ ነቀፋ ነበርሁ።
7 ነገር ግን ለእኔ ረብ (ስም፣ ዝና፣ ሹመት፣ ማእረግ፣ ጥቅም...) የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ።
8-9 አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ። ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ። ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ።
10-11 እርሱን እና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ፥ ቢሆንልኝ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።

12 አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።
13 ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ (ለመማር) እዘረጋለሁ፥ (ፍጹማን እንዲህ ያስባሉ)
14 በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።
15 እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን (እንዲህ) እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤
16 ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ።
17 ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ።
18 ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።
20 እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
21 እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።

ወዴት ያመራል?

የክርስቶስ ተከታይ ከሆንህ ከእርሱ ጋር ሞትን ተሻግረህ ወደ ዘላለም ክብር ትደርሳለህ። የ"ምሁር" ተከታይ ከሆንህም እርሱ በወደቀበት ጉድጓድ ወድቀህ ትቀራለህ። ለመሆኑ በአለማችን የክህደት ተምሳሌት ተደርገው የሚወሰዱ ብዙ ሰዎች እነማን ናቸው? አዎን ራሳቸውን "የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮፌሰር፣ የአዲስ ኪዳን ሊቅ፣ የብሉይ ኪዳን ዶክተር"... ወዘተ ሲሉ የኖሩ እና በመጨረሻም ተሸፍኖ የኖረውን ክህደታቸውን ይፋ ያደረጉ ናቸው። "ቲዎሎጂ" ተምረው በተለያዩ ዲግሪዎች "የተመረቁ" እነዚህ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ "ምሁር" ናቸው ተብሎ ስለ ሚታሰብ የተለያየ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ከሰዎች ይቀርብላቸዋል። ነገር ግን ጥያቄዎቹን ለመመለስ ብቃት የላቸውም። በዚህ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር አለመሆናቸውን እና ደቀ መዝሙር (ተማሪ) መሆናቸውን ተረድተው በንስሐ መመለስ ሲገባቸው እነርሱ ግን ይህን መልካም ዕድል ከመጠቀም ይልቅ "እግዚአብሔር የለም" ወይም ደግሞ "መጽሐፍ ቅዱስ ጎዶሎ ነው" ወዘተ ወደ ሚል ሌላ ቀውስ ያመራሉ።

ቻርለስ ዳርዊን "የመጽሐፍ ቅዱስ ምሩቅ" ወይም "የስነ መሎኮት ምሁር" እንደሆነ ራሱን የሚቆጥር ሰው ነበር። በኋላ ግን ተከድኖ የኖረ ክህደቱን ይፋ ሲያደርግ የእርሱ "ተከታይ" የነበሩት ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደቁ። የስጋ ዘመዶቹ ክርስቶስን አምነው የዘላለም ክብር ወራሾች ሲሆኑ እርሱ ግን በክህደት ኖረ (ሮሜ 8፡18፤ 15፡7፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡18፤ 4፡17-18፤ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡14) ። በህይወቱ መጨረሻ እስትንፋስ ላይም እጅግ ተጸጽቷል፤ እንዲያውም ወደ ክርስትና ተመልሷል እየተባለ ቢነገርም ይህ ትክክል ስለ መሆኑ በቂ መረጃዎች አልተገኙም። ቻርለስ "የቲዎሎጂ ምሁር" ነኝ ሲል የኖረበትን ዘመን እንኳ ሲያስታውስ "ያመንኩትን አላውቀውም ነበር" (I believed in what I could not understand) ብሏል።

በእድሜ ዘመኑ ሁሉ ክርስቲያን (የክርስቶስ ተማሪ/ደቀ መዝሙር) ሆኖ የኖረው ጳውሎስ ግን ሲናገር፦ "ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፥ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፥ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል (እንደሚችል) ተረድቼአለሁ" ብሏል (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፥12)

የመጽሐፍ ቅዱስ "ፕሮፌሰር" የተባለው ሄክተር አቮሎስ ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በ3ኛ (የዶክትሬት) ዲግሪ የተመረቀ ሰው ነበር። ከዚያም "የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ" እየተባለ "ቲዎሎጂ" ሲያስተምር ቆይቷል። ባሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ኤሊኖስ ዩኒቨርስቲ "የሐይማኖት ጥናት ፕሮፌሰር" ሆኖ እየስተማረ ይገኛል። በቅርቡ ባሳተመው መጽሐፉ (The End of Biblical Studies, Hector Avalos) ተሸፍኖ የቆየውን ክህደቱን ይፋ አድርጓል፤ እንዲህ ሲል፦ "መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ጊዜ ያለፈበት መጽሐፍ ስለሆነ መነበብ የለበትም።"

ፈጣሪ አምላካችን ግን በህያው ቃሉ እንዲህ ይለናል፦ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙት እና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው (ራእይ 1፡3)። የቱን ማመን እንዳለብህ ምርጫው ያንተ ነው።

ከስሙ ይልቅ የአሜሪካ የአዲስ ኪዳን "ምሁር (ሊቅ)" በሚለው ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ "ምሁር (ዶክተር)" ደግሞ ባርት ሄርሜን ነው። በዊተን ኮሌጅ 1ኛ ዲግሪውን፣ በፕሪንሴን ሴምናሪ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪዎችን "በቲዎሎጂ" ተመርቋል። ባሁኑ ጊዜ በሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርስቲ "የሐይማኖት ጥናት ፕሮፌሰር" ሆኖ እየስተማረ ይገኛል። ከሃያ በላይ መጻሕፍትን ያሳተመ ሲሆን በቅርቡ ባሳተመው መጽሐፉ ተሸፍኖ የኖረ ክህደቱን ይፋ አድርጓል። "የአምላክ ችግር፡ ከሁሉ ይበልጥ ወሳኝ የሆነውን -ለምን መከራ ይደርስብናል? የሚለውን ጥያቄያችንን መጽሐፍ ቅዱስ ሊመልስልን አልቻለም" (God's Problem: How the Bible Fails to Answer Our Most Important Question- Why We Suffer, Bart D. Ehrman) በተሰኘው በዚህ መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፦ "በአለም ላይ ያለው መከራ ለምን እንደበዛ መጽሐፍ ቅዱስ ሊመልስልኝ ስላልቻለ በመጨረሻ በክርስቶስ ላይ የነበረኝን እምነቴን ክጃለሁ" (ፀጋአብ በቀለ፣ ባለ ራእይነት፣ ክፍል ሁለት፣ ኢትዮጵያ ግን ለምን? ገጽ 227-228)

ልብ በል እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ "ፕሮፌሰሮች" እስካሁንም ድረስ ባሉበት ቦታ ተደማጭ፣ ተወዳጅ እና ተከባሪ "የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን" ናቸው። ብዙዎችንም "ስነ መሎኮት" እያስተማሩ፣ "በመጽሐፍ ቅዱስ ማስትሬት" እና "ዶክትሬት" ዲግሪ እያስመረቁ "ምሁር" እያደረጓቸው ይገኛሉ። ታዲያ የእነዚያን "ምሁራን" ጽሑፎች እና ዌብሳይቶች የእምነታችን መሰረት እና የትክክለኛ መንፈሳዊ መረጃ ምንጮች አድርገን ልንጠቅሳቸውና ልንታመንባቸው ይገባናልን? ከቶ አይገባንም። የእምነታችን መሰረት እና የእውነተኛ መንፈሳዊ መረጃ ምንጭ፣ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ሊሆን ቃል የገባው (ማቴዎስ 28፡20)፣ እንደ ቃሉም አሁን የቅርባችን ሆኖ ከእኛ ጋር ያለው ፈጣሪ እግዚአብሔር እና ቃሉ (መጽሐፍ ቅዱስ) ብቻ ናቸው። እርሱ "በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ" እንዳለው (ዮሐንስ 10፡27)። አዎን በጎቹ የሆኑት መልካሙን እረኛቸውን እርሱን እግዚአብሔርን (መዝሙር 23፡1፤ ዮሐንስ 10፡11፣ 14-15) በደንብ አድርገው ያውቁታል፤ ድምጹንም ይሰሙታል (ራእይ 3፡20፤ ዮሐንስ 10፡16፣ 27፤ 18፡37) ይከተሉታል፤ ይታዘዙታል።

ዳሩ ግን አንተ ከበጎቹ ውጭ (የማታምን) ሆነህ እንዳትገኝ ለራስህ ተጠንቀቅ። ምክንያቱም ይኼ አምላክ ራሱ "እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም" ሲል የማያምኑ ሰዎች እንደ ሚኖሩ ገልጾአል (ዮሐንስ 10፡26)። ስለዚህ ወዳጄ ሆይ "ያመንህ ሁን እንጂ ያላመንህ አትሁን" (ዮሐንስ 20፡27)። መልካሙ አባታችን በቅዱስ ቃሉ እንደሚመክረን "እንግዲህ ፦ እናንተ የምትንቁ እዩ፤ ተደነቁም፤ ጥፉም፤ አንድ ስንኳ ቢተርክላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እኔ እሠራለሁና ተብሎ በነቢያት የተነገረው እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ" (የሐዋርያት ሥራ 13፡40-41፤ ዕንባቆም 1፡5)

የአለም መድኃኒት የሆነውን ክርስቶስን እኛ እናምነዋለን (ዮሐንስ 4፡42፤ 1ኛ ዮሐንስ 4፡14)። እርሱ ፈጣሪያችን፣ አምላካችን፣ አባታችን፣ ጌታችን፣ ንጉሳችን (ይሁዳ 1፡4)፣ ደግሞም ከኃጢአት በቀር በሁሉ ነገር እኛን መስሎ ያዳነን ውዱ ወንድማችን፣ ሁሉ ነገራችንም ነው። ከእርሱ ተለይተን መኖር አንችልምና አይኖቻችንን ቀና አድርገን የፍቅር አይኖቹን እያየን እንዲህ እንለዋለን፦ "ጌታ ሆይ፥ (ከአንተ) ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ" (ዮሐንስ 6፡68)። እርግጠኛ ሁን "እርሱን የሚያምን አያፍርም" (ሮሜ 9፡32-33፤ 10፡11፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡6፤ ኢሳይያስ 28፡16)። ለምን? ምክንያቱም እርሱ ሊታመኑበት የሚችሉት አስተማማኝ እና ጠንካራ ዓለት ስለሆነ፣ የታመኑበትን ሁሉ የሚያድን ኃያሉ አምላክ (እግዚአብሔር) God ስለሆነ ነው። ራሱ እግዚአብሔር "በገዛ ደሙ የዋጃትን፣ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ፣ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ" (የሐዋርያት ሥራ 20፡28)

"ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት (ከሙታን የተነሳውን) ሕያው እግዚአብሔርን (ሉቃስ 24፡5) የሚያስክዳችሁ ክፉ እና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ" (ዕብራውያን 3፡12)። "የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር (ክህደት) ወደ ላይ በቅሎ (አድጎ) እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ ... ተጠንቀቁ" (ዕብራውያን 12፡15)። "ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ (በአሮጌው ኪዳን ዘመን) በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው (ከጌታ) ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን?" (ዕብራውያን 12፡25)። ወዳጄ ሆይ፣ "ከሚመጣው ቍጣ" እንድታመልጥ በአዳኝህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያመንህ ሁን እንጂ ያላመንህ አትሁን (ማቴዎስ 3፡7፤ ሉቃስ 3፡7፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡9-10)

የሐዋርያት ሥራ 28፡
24 እኵሌቶቹም (ክርስቲያኑ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ) የተናገረውን አመኑ፥ እኵሌቶቹ ግን አላመኑም፤
25 እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ። እንዲህም አለ፦ "(ጌታ) መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ፣ ለአባቶቻችን (ሲናገር)
26 ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፦ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤
27 በዓይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ (እንዳያምኑ)(ወደ እኔ) ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ደንቁሮአል፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል በላቸው
28 ሲል (ጌታ መንፈስ ቅዱስ) መልካም ተናገረ። እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ደኅንነት (እናንተን አልፎ) ለአሕዛብ (ለሌሎች ሕዝቦች) እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ እነርሱ (ሌሎች ሕዝቦች) ደግሞ ይሰሙታል።"

አስተውል፤ ብዙውን ጊዜ በነቢያት በእነ ኢሳይያስ ሆኖ ለአባቶቻችን ይናገር የነበረው ጌታ እግዚአብሔር፣ አብ ሳይሆን ወልድም ሳይሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ ለምሳሌ በኢሳይያስ 6፡8-10 ላይ ነቢዩን በድምጽ የሚያናግረው ጌታ እግዚአብሔር፣ መንፈስ ቅዱስ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 28፡25)

ባርት ሄርሜን ያነሣውን ጥያቄ በተመለከተ ግን ስለሚደርስብን መከራ ፈጣሪ አምላካችን መንፈስ ቅዱስ (ኢዮብ 33፥4) ጳውሎስን ተጠቅሞ በጻፈው ህያው ቃሉ እንዲህ ሲል ይመክረናል፦

ይቀጥላል...
...የቀጠለ

ሮሜ 8፡
9 እናንተ ግን የእግዚአብሔር (የክርስቶስ) መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ (የእግዚአብሔር) መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም...

16 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ (መንፈስ ቅዱስ) ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
17 (የእግዚአብሔር) ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
18 ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
19 የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
20 ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤
21 ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።
22 ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
23 እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
24 በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?
25 የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን።
26 እንዲሁም ደግሞ መንፈስ (ቅዱስ) ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል...
28 እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን...
35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?

36 ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
37 በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
38 ሞት ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፥ (ቅዱሳን) መላእክትም ቢሆኑ (ገላትያ 1፡8)፣ ግዛትም ቢሆን፥ (አሁን) ያለውም ቢሆን፣ (ወደ ፊት) የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም (ባለ ስልጣናትም፣ አጋንንትም ወዘተ) ቢሆኑ፥
39 ከፍታም (ስኬት) ቢሆን፣ ዝቅታም (መከራ) ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ። (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16-18)

2ኛ ተሰሎንቄ 1፡
1 ጳውሎስና ስልዋኖስ፣ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤
2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።
3 ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፣ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፣ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤
4 ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁ እና በመከራችሁ ሁሉ፣ ከመጽናታችሁ እና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን።
5 ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው።
6-7 ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
8 እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤
9-10 በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር፥ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊገረም ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።
11-12 ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር፣ እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፣ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፣ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።

እንግዲህ የቱን ማመን እንዳለብህ ምርጫው የግልህ ነው። ለመሆኑ ስለ እነዚህ ሰዎች ክህደት የአምላካችን ቃል ምን ይላል?

1ኛ ዮሐንስ 2፡
18 ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
19 ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን (ጥንትም) ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።
20 እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።
21 እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም።

"ምሁር" በምሁርነቱ የክርስቶስን ማንነት ሊያውቅ እና ሊያሳውቀን አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስን ሊረዳ እና ሊያስረዳን አይችልም። የክርስቶስን ማንነት የሚያውቅ እና ሊያሳውቀንም የሚችለው አብ ብቻ ሲሆን እርሱም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ያስተምረናል።

ማቴዎስ 11፡
25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ የሰማይ እና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞች እና ከአስተዋዮች ("ከምሁራን") ሰውረህ ለሕፃናት (ለእነ ጴጥሮስ) ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤
26 አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
27 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር፣ ወልድም ሊገለጥለት (ራሱን ሊገልጥለት) ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
28 እናንተ ደካሞች ("ምሁራንም" ጭምር) ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
30 ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀሊል ነውና።

ሉቃስ 10፡
21 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይ እና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞች እና ከአስተዋዮች ("ከምሁራን") ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
22 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር፣ ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ።
23 ወደ ደቀ መዛሙርቱም ዘወር ብሎ ለብቻቸው፦ የምታዩትን የሚያዩ ዓይኖች ብፁዓን ናቸው።
24 እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን (መሲሁን) ብዙዎች ነቢያት እና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ፤ አላዩምም፥ የምትሰሙትንም (የመሲሁን ድምጽ) ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ።

እንዲሁም እውነተኛ አማኞች በክርስቶስ ላይ በአመጽ የሚነሳውን የትኛውንም "ምሁራዊ" አስተሳሰብ በአምላካቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያፈርሳሉ። (2ኛ ቆሮንቶስ 10፡4-7፤ መዝሙር 118፡ 8-12)። "በምሁራን" እና በሌሎች ሰዎችም አእምሮ (ዕውቀት) ውስጥ የመሸገውን ተቃዋሚውን ዲያብሎስን ይመታሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን ሊያስረዳን የሚችለው ትናንት በሰዎች ኮሌጅ "የተመረቀ ምሁር" ሳይሆን መጽሐፉን ራሱን ያጻፈው እና የጠበቀው ጌታ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ከእኛ ሚጠበቀው አንድ ነገር ብቻ ነው- በቅን እና ለመማር በሚፈልግ ልብ መጽሐፉን ይዘን ወደ እርሱ ፊት በጸሎት መቅረብ ብቻ ነው።

1ኛ ዮሐንስ 2፡
22 ክርስቶስ (እግዚአብሔር) አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብን እና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
23 ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።
24 እናንተስ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ቢኖር፥ እናንተ ደግሞ በወልድ እና በአብ ትኖራላችሁ።
25 እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።
26 ስለሚያስቱአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።
27 እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት (መንፈስ ቅዱስ) በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት (መንፈስ ቅዱስ) ስለ ሁሉ እንደ ሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
28 አሁንም ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን፣ በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።

በሌላ በኩል እንመልከት

እስቲ አሁን ደግሞ በዚህ አለም ጥበብ (ሳይንስ) ጠቢባን የነበሩትን እና በኋላ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር (ክርስቲያን) ወደ መሆን የመጡትን በጥቂቱ እንመልከት።

()
ገጣሚ፣ የህግ ምሁር እና የክርስትና ተቃዋሚ የነበረው ጊልቤርት ዌስት "የክርስቶስ ትንሳኤ ተረት እንደ ሆነ" በመረጃ አስደግፎ ለማሳየት ቆርጦ ተነስቶ ነበር። ይሁን እንጂ በጥናቱ እያለ በትንሳኤ ከሙታን ከተነሣው ህያው አምላክ ጋር ፊት ለፊት ስለተገናኘ አቋሙን ለውጦ ለጌታ ራሱን የሰጠ ክርስቲያን እና የትንሳኤው ምስክር (የሐዋርያት ሥራ 4፥33) ሊሆን በቅቷል። አስቦ እና አቅዶ ከተነሣበት በተቃራኒው የክርስቶስ ትንሳኤ ታሪካዊ እውነት መሆኑን በመረጃ የሚያስረዳ መጽሐፍ (Observations on the Resurrection of Jesus Christ, Gilbert West) አሳተመ።

ዶክተር ሳሙኤል ጆንሰን "የገጣሚዎች ሕይወት" በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፉ ስለ ገጣሚ ጊልቤርት ዌስት እንዲህ ብሏል፦
...when West's book was published, it was bought by some who did not know his change of opinion, in expectation of new objections against Christianity.
(Johnson's Lives of the PoetsVolume 2 by Samuel Johnson)

()
በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕግ ፕሮፌሰር እና የክርስትና ተቃዋሚ የነበረው ዶክተር ሳይመን ግሪንሊፍ "የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ አፈታሪክ እንደ ሆነ" ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በጥናት ሊያረጋግጥ ቆርጦ ተነስቶ ነበር። ውጤቱ ግን ፍጹም ተቃራኒ ሆኖበታል። የትንሳኤው ጌታ ህያው አምላክ ተገለጠለት። በመሆኑም ወደ ጌታ የመጣ፣ ለጌታ ኢየሱስ ራሱን ሙሉ በሙሉ የሰጠ ክርስቲያን እና የተለወጠ ሰው ሆነ።

Dr. Greenleaf, the Royal Professor of Law at Harvard University, was one of the greatest legal minds that ever lived. He wrote the famous legal volume entitled, "A Treatise on the Law of Evidence", considered by many the greatest legal volume ever written. Dr. Simon Greenleaf believed the Resurrection of Jesus Christ was a hoax. And he determined, once and for all, to expose the "myth" of the Resurrection. After thoroughly examining the evidence for the resurrectionDr. Greenleaf came to the exact opposite conclusion! He wrote a book entitled, An Examination of the Testimony of the Four Evangelists by the Rules of Evidence Administered in the Courts of Justice, Simon Greenleaf. Greenleaf concluded that according to the jurisdiction of legal evidence the resurrection of Jesus Christ was the best supported event in all of history! And not only that, Dr. Greenleaf was so convinced by the overwhelming evidence, he committed his life to Jesus Christ! (The Resurrection of Jesus Christ: Fact or Fiction? Dial-the -Truth Ministries)

ይቀጥላል...
... የቀጠለ

()
እንዲሁም ሌላው ገጣሚ፣ ደራሲ እና የሕግ ምሁር የነበረው ሎርድ ጆርጅ ላይተልተን "የጳውሎስ መለወጥ እና ጌታ ኢየሱስን ማመን አፈታሪክ እንደ ሆነ" በመረጃ ለማሳየት ታጥቆ ተነስቶ ነበር። ሲያጠና ያገኘው ግን ፍጹም ተቃራኒ ሆኖበታል። ከዚያም ለክርስቶስ ሕይወቱን የሰጠ ሲሆን የጳውሎስ መለወጥ ተጨባጭ እውነት መሆኑን የሚያስረዳ መጽሐፍም (Observations on the Conversion of St. Paul, George Lyttleton) አሳትሟል።

ዶክተር ሳሙኤል ጆንሰን "የገጣሚዎች ሕይወት" በሚል መጽሐፉ ስለ ጆርጅ ላይተልተን እንዲህ ብሏል፦

He had, in the pride of juvenile confidence, with the help of corrupt conversation, entertained doubts of the truth of Christianity; but he thought the time now came when it was no longer fit to doubt or believe by chance, and applied himself seriously to the great question. His studies, being honest,ended in conviction. He found that religion was true, and what he had learned he endeavoured to teach; by "Observations on the Conversion of St. Paul."
(Johnson's Lives of the PoetsVolume 2 by Samuel Johnson)

One of the most notable cases is that of Gilbert West and Lord Lyttelton, two eminent lawyers in 18th century England. Lyttelton set out to write a book disproving the conversion of Paul, while (Gilbert) West sought to disprove the resurrection of Christ. Both were convinced by the evidence and became Christians as a result. They wrote their books supporting the gospel stories. ("Exploring faith today" booklets by Rev Dick Tripp)


()
ወደ ክርስቶስ የመጣው ፍራንክ ሞራይዘን
ፍራንክ ሞራይዘን "ኢየሱስ በችሎት ፊት" የሚል መጽሐፍ ለመጻፍ አቅዶ እና በጅቶ የተነሣ ቢሆንም በጥናቱ መሐል እግዚአብሔር የገለጠለት እውነት አቋሙን የሚያስለውጥ ሆኖበታል። በመሆኑም ያን ርዕስ ትቶ "ድንጋዩን ማን አንከባለለው?" የሚል ምርጥ ጽሁፍ አሳተመ። ብዙዎች ወደ አዳኛቸው እና ወደ ፈጣሪያቸው እንዲመለሱ ምክንያትም ሆኗል። ያን የቀድሞውን ርዕሱንም "አልፃፍ ያለው መጽሐፌ" ሲል ገልጾታል፦


A more up-to-date example is that of Frank Morison, who originally planned to write a monograph on the trial of Jesus. Confronted by the fact of the resurrection, he was convinced by the evidence, became a Christian and wrote instead "Who Moved the Stone?" In the book's first chapter, which is called "The book that refused to be written", he describes how, as he came to examine the material, so far from writing the book that he had intended, he found himself.
("Exploring faith today" booklets by Rev Dick Tripp)

ከዚህ ምን እንማራለን? አዎን፤ በእኛ የቲዎሎጂ ዲግሪዎች ብዛት ክርስቶስን (እግዚአብሔርን) ልናውቀው አንችልም (ዮሐንስ 17፡3)። ክርስቶስን (እግዚአብሔርን) ልናውቀው የምንችለው ራሱ ሲገልጥልን፤ በቃሉ (በመጽሐፍ ቅዱስ) ራሱ ሲያስረዳን ነው።

እንጂ ማንም በሰዎች ኮሌጅ ተምሮ ስለ ተመረቀ "የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር (ሊቅ)" ነኝ እያለ ክርስቶስን ሊያውቀውና ሊረዳው ወይም ሊያሳውቀንና ሊያስረዳን አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስንም ሊያውቀውና ሊረዳው፣ ሊያሳውቀንና ሊያስረዳን አይችልም።

"የቲዎሎጂ" ጥናት አእምሮህን በቃላት እና በቁጥሮች ይሞላልሃል፤ ልብህን በእምነት ሊሞላ ግን አይችልም። ብዙ መጻሕፍትን መመርመር ስለ አምላክ ብዙ ነገር ሊያሳውቅህ ይችላል፤ ከአምላክ ከራሱ ጋር ሊያገናኝህ ግን አይችልም። ይህን ማድረግ የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው (ዮሐንስ 16፡9-10)። መጻሕፍትን መመርመር በክርስቶስ ከማመን የሚያግደን ከሆነ ዋጋ የለውም። መጻሕፍትን ሁሉ የሞላው፣ ለ2000 አመታትም ትልቁ ርዕስ ሆኖ የዘለቀው አምላካችን ክርስቶስ ነው። ስለዚህ መጻሕፍትን መመርመር ብቻ ሳይሆን ክርስቶስን በፍጹም ልባችን ማመን እና ከእርሱ ጋር መጣበቅ ነው የሚያዋጣን።

ዮሐንስ 5፡
39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
40 ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።
41-42 ከሰው ክብርን አልቀበልም (ላገለግል መጣሁ እንጂ ልገለገል አልመጣሁም)፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በራሳችሁ እንደ ሌላችሁ አውቃችኋለሁ።
43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ፤ አልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ።
44 እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር (ክርስቶስን) የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?

"የቲዎሎጂ" ትምህርት ስለ እምነት ብዙ ይነግርሃል፤ እንጂ ትምህርቱ በራሱ አማኝ ሊያደርግህ አቅም የለውም። ታድያ ትምህርቱን አጥንቶ የተመረቀ ሰውስ፣ ትክክለኛ አማኝ ሊያደርግህ ምን አቅም አለው? ራሱስ ለመሆኑ አማኝ መሆኑን አይተሃልን? በቲዎሎጂ ተመረቀና "የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር" ስለ ተባለ፣ ወይም ራሱ "የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር" ነኝ ስላለ፣ ክርስቲያን መሆኑን እርግጠኛ ነህን? ልብ በል የክርስትና አባት የሆነው ክርስቶስ እንዲህ ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶን ነበር፦

ማቴዎስ 7፡
15 የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት (ከአስመሳዮች) ተጠንቀቁ።
16 ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
17 እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
18 መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት (መልካም ትምህርት ማስተማር) አይቻለውም።
19 መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል።
20 ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።

እንዲሁም ሐዋርያው ወንድማችን ከጌታ ተቀብሎ እንዲህ ሲል አስጠንቅቆናል፦

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡
13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች (አስመሳዮች) ናቸውና።
14 ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።
15 እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።

በመቀጠልም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ሁሉ፣ ሙሉ በሙሉ ማመን አለብህ እንጂ የምትፈልገውን መርጠህ ማመን፣ የማትፈልገውን መርጠህ ማስተባበል (አለማመን) የለብህም። በግልጽ የተጻፈውን ቃል ዮሐንስ 1፡1ን መካድ እንጂ ማመን ስለ ማትፈልግ ሌላ ጥቅስ (ማርቆስ 8፡33) ጠቅሰህ ልታስተባብለው ጥረሃል።

ዮሐንስ 1፡
1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ (እኔም፣ አንተም፣ ሌላውም) በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

ማርቆስ 8፡
33 እርሱ ግን ዘወር አለ፤ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና አለው።

እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች የሚናገሩት ስለ ተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ከመሆኑም በተጨማሪ እርስ በርስ ሊስተያዩ የማይገባቸው ናቸው። አንደኛው ጥቅስ፣ የትኛውም ፍጡር ሳይፈጠር በፊት ከሁሉ በፊት "በመጀመሪያው ቃል ነበረ" ይላል። ሁለተኛው ጥቅስ ግን 'ከሁሉ በፊት በመጀመሪያው ጴጥሮስ ነበረ' አይልም። አንደኛው በግልጽ "ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ" ይላል። ሁለተኛው ግን 'ጴጥሮስ በሰይጣን ዘንድ ነበረ' አይልም። አንደኛው በግልጽ "ቃልም እግዚአብሔር ነበር" ይላል። ሁለተኛው ግን 'ጴጥሮስ ሰይጣን ነበር' አይልም። በርግጥ እንደዚያ ቢል ኖሮ ልናስተያያቸው ምናልባት እንችል ነበር። አሁን ግን በምንም መንገድ አንዱ ከሌላው ሊስተያይ፣ አልፎም ደግሞ አንዱ ሌላውን ሊያስተባብለው ወይም ሊያከሽፈው አይችልም። በመሰረቱ ጥቅሶችን መጠቀም ያለብን የተጻፈውን ቃል በሙሉ ለማመን እና ለመታዘዝ (1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6)፣ እንዲሁም ሌሎች ጥቅሶችን ለማጠናከር ነው። እንጂ እንደ ሰይጣን ሌሎች ጥቅሶችን ለማስተባበል ወይም ለማፍረስ መሆን የለበትም (ማቴዎስ 4፡5-7)

"አምላክ ብርሃን ነው!"

ዋው! አምላክ ብርሃን መሆኑን ታውቃለህን? እንዲህ አይነቱን ጣፋጭ እና ሕያው ቃል ካንተ መስማት እንዴት የሚያስደስት ነው? አንተም ተናገረው ማንም ይናገረው፤ መቼም ይናገረው እንዴትም ይናገረው፤ ቃሉ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እጅግ ጣፋጭ፣ አስደሳች እና አጽናኝ ቃል ነው። አዎን ፈጣሪ ብርሃን ነው። ጨለማ በሆነው በዚህ አለም (ኤፌሶን 6፡12)፣ ሊነጋጋ በቀረበው (ፍጻሜው በተቃረበለት) በዚህ ሌሊት ዘመን እግዚአብሔር ብርሃናችን ነው። እውነተኛው ብርሃን አማናዊው የጽድቅ ጸሐይ የንጋት ኮከብ ፈጣሪ አምላካችን እርሱ ሲመጣ አዎን ይህ ሌሊት ወገግ ብሎ ይነጋል። "ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል" (1ኛ ዮሐንስ 2፡8)

1ኛ ቆሮንቶስ 13፡
12 ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን። በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ። በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ (ያህል) አውቃለሁ።

መዝሙር 36፡
9 የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።

በርግጥ ከአቀራረብህ በግልጽ እንደሚታየው ያንተ ዋና አላማ አምላክ ብርሃን መሆኑን ለማስረዳት ሳይሆን ለራስህ "የሰዋሰው ሕግ" ምሳሌ እንዲሆንልህ እግረ መንገድህን አንድ ሐተታዊ ዓረፍተ ነገር ለመሥራት ነው። ቢሆንም አምላክ ብርሃን መሆኑን የሚገልጽ ዓረፍተ ነገር በራሱ አስከፊ አይደለም። ታድያ የሚያሳዝነው ምን መሰለህ? ብዙዎች 'አምላክ ብርሃን ነው' በማለት እውነታውን ቢናገሩም፣ ካሉበት ድቅድቅ የሕይወት ጨለማ ወጥተው ወደዚህ ፈንጣቂ ብርሃን (ወደ አምላክ) ለመምጣት ፈቃደኛ አይደሉም።

ዮሐንስ 3፡
19 ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤
21 እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።

ወደ እርሱ መምጣት ከባድ ውርደት ወይም ሞት የሚመስላቸውም ጥቂት አይደሉም። እርሱን ማን እንደሆነ ገና ያላወቁትም ብዙ ናቸው።

ኢሳይያስ 1፡
2 እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፣ ምድርም አድምጪ፣ ልጆችን ወለድሁ፣ አሳደግሁም፣ እነርሱም አመጹብኝ።
3 በሬ የገዢውን፣ አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም አላስተዋለም።

ኤፈሶን 5፡
7 እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤
8 ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤
9-10 የብርሃኑ ፍሬ በበጎነት እና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤
11 ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥
12 እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤
13 ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና።
14 ስለዚህ፦ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም (እግዚአብሔርም) ያበራልሃል ይላል።

ራእይ 21፡
22 ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ (ክርስቶስ) መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።
23 ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ (ክርስቶስ) ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።
24 አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤
25 በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥
26 የአሕዛብንም ግርማ እና ክብር ወደ እርስዋ ያመጣሉ።
27 ለበጉም (ለክርስቶስ) በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰት እና ውሸትንም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።

ራእይ 22፡
3 ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
4 ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
5 ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃን እና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
6 እርሱም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ (ክርስቶስ) በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ (ራእይ 22፡16)

ይቀጥላል...
...የቀጠለ

ይህ ብርሃን የሆነው ፈጣሪ ማን መሆኑን ፊት ለፊት ልትተዋወቀው ትፈቅዳለህን? ወይስ ምርጫህ ከእርሱ እየሸሸህ፣ ራስህን ባሳመንከው "ኃይማኖትህ" ውስጥ አሊያም በተለያዩ ሰብአዊ ትምህርቶች ውስጥ ተደብቀህ ቀሪ እድሜህን መጨረስ ነው? ለመሆኑ ብርሃን የሆነው ይህ እግዚአብሔር ማን ነው? ከላይ የሚጎበኘን ይህ ሕያው ብርሃን ማን ነው? (ሉቃስ 1፡78፤ የሐዋርያት ሥራ 26፡13)። አሳዳጆቻችን እና ተቃዋሚዎቻችን ቀና ብለው ሊመለከቱት የማይችሉት ይህ አብረቅራቂ ብርሃን (የሐዋርያት ሥራ 9፡3-5) እጅግ ቅዱስ የሆነው የምንመካበት ውዱ አባታችን ነው (ኢሳይያስ 9፡6፤ ዕብራውያን 2፡14-15፤ ፊልጵስዩስ 3፡3፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡30-31፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡17-18)። አዎን "ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን (በቅርቡ) ይበራል" (1ኛ ዮሐንስ 2፡8)። ለመሆኑ ይህ እውነተኛው ብርሃን ማን እንደ ሆነ አውቀኸዋል ወይስ ገና አላወቅኸውም?

እውነተኛው ብርሃን

ዮሐንስ 1፡
9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
10 በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።
11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

አዎን መላው መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሚያስረዳን፣ እውነተኛው ብርሃን ፈጣሪ አምላካችን እግዚአብሔር ወልድ (ክርስቶስ ኢየሱስ) ነው። እውነተኛው ብርሃን እውነተኛው አምላክ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (1ኛ ዮሐንስ 5፡20)። እርሱ በአለም ነበረ። አለሙም በእርሱ ተፈጠረ። ከተፈጠረውም ሁሉ አንዳች እንኳ ያለ እርሱ አልተፈጠረም (ዮሐንስ 1፡3)። ይሁን እንጂ እርሱ የፈጠረው አለም እርሱን አላወቀውም።

ዮሐንስ 1፡
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
4 በእርሱ (በክርስቶስ) ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
6 ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
7 ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን (ስለ ክርስቶስ) ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።
8 ስለ ብርሃን (ስለ ክርስቶስ) ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ (መጥምቁ ዮሐንስ) ብርሃን አልነበረም።
9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
10 በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ (ተፈጠረ)፥ ዓለሙም አላወቀውም።
11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።

ታላቅ ብርሃን

በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን (ክርስቶስን) አየ።

ማቴዎስ 4፡
12 ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ።
13 ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎን እና በንፍታሌም አገር፣ በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።
14-16 በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድር እና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን (እግዚአብሔርን) አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።

መዝሙር 4፡
6 በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።
7 በልቤ ደስታን ጨመርህ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።

መዝሙር 18፡
27 አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።
28 አንተ መብራቴን ታበራለህና እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።
29 በአንተ ከጥፋት እድናለሁና በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።
30 የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።
31 ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?

መዝሙር 27፡
1 እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ብርሃኔ እና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

ይህ እውነተኛው ብርሃን በልብህ ውስጥ እንዲበራ ትፈልጋለህን? ጠላት ቀና ብሎ ሊመለከተው የማይችለው ይህ ደማቅ ፀዳል በሕይወትህ ውስጥ እንዲበራ ትፈቅዳለህን? ይህ ታላቅ ፀዳል ልጁ እንዲያደርግህ እና አንተንም የአለም ብርሃን እንዲያደርግህ ትፈልጋለህን? ወይስ "በኃይማኖትህ" እና "በእውቀትህ" ጨለማ ውስጥ መተኛት ይበልጥብሃል? ምርጫው በእጅህ ነው። በርግጥ ይህ አንጸባራቂ ብርሃን በሰዎች ልብ ውስጥ እንዲበራ ተቃዋሚው ሠይጣን ዲያብሎስ አይፈልግም (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4-6)። ለምን? ምክንያቱም ብርሃን (አምላክ) ሲበራ ጨለማው (ዲያብሎስ) ይወገዳል፤ ስፍራውንም ይለቃል።

የሚደነቅ ብርሃን

1ኛ ጴጥሮስ 2፡
9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
10 እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

ጨለማ ማለት ከእግዚአብሔር (ከክርስቶስ) ተለይቶ መኖር ወይም ያለ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) መኖር ማለት ነው (ኤፌሶን 2፡12)። ያለ እርሱ ሕይወት ጨለማ፣ መራራ ነው። ትርጉመ ቢስ፣ ጣዕም የሌለው፣ ድግግሞሽ እና አሰልቺ፣ ተስፋ አስቆራጭ፣ ዘላቂ ደስታ የራቀው ነው። የሕይወት ጣዕም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐንስ 8፡12)

አዎን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ (በግዕዙ -እግዚእ) ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመንና የሕይወትህን ጣዕም አጣጥም! (የሐዋርያት ሥራ 16፡31)። እርሱ የአለም አዳኝ ነው (ዮሐንስ 4፡42፤ 1ኛ ዮሐንስ 4፡14)። ከሞት፣ ከሲዖል፣ ከሕይወት ከንቱነት ኢየሱስ ያድናል። ከሥጋ ደዌ፣ ከነፍስ በሽታ (ከኃጢአት)፣ ከመከራ፣ ከጭንቀት፣ ራስን ከመጥላት፣ ከምሬት፣ የሕይወት ትርጉም ከማጣት፣ ከነፍስ ክሳት ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል። እውነተኛ ሰላም የሚሰጥህ የሰላም አምላክ እርሱ ነው (ኢሳይያስ 9፡6፤ ዘኍልቍ 25፡12፤ ዮሐንስ 14፡27፤ ኤርምያስ 29፡11፤ ሮሜ 15፡33፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡22፤ ሮሜ 16፡20፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡23)። ለአማኞቹ እና ለማያምኑት ሰላምን የሚሰጥ እና የሚከለክል እግዚአብሔር እርሱ ነው (ኤርምያስ 16፡5፤ መዝሙር 38፡3፤ ኢሳይያስ 48፡22፤ 57፡21፤ ኢዮብ 22፡21፤ ዮሐንስ 14፡27)


እርሱ ለእኛ ለልጆቹ ሰላምን የሚሰጠን ብቻ ሳይሆን ራሱ ሰላማችን ነው (ኤፌሶን 2፡14-15)። ለተጨነቀች ነፍስ እፎይታ፣ እረፍት (ማቴዎስ 11፡28-29)፣ ለተጠማች ነፍስ ውስጣዊ ጥምን የሚቆርጥ እውነተኛው እርካታ (ዮሐንስ 4፡14፤ 6፡35)፣ ክብር የሞላበት ዘላቂ ደስታ (1ኛ ጴጥሮስ 1፡8-9) ሌላ ሳይሆን ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር ወልድ) ነው (ኢሳይያስ 55፡1፤ ዮሐንስ 7፡37፤ ራእይ 22፡17)። ተንኮል የሌለበት ክፋት የሌለበት እውነተኛው ፍጹም ፍቅር እርሱ ነው (ዮሐንስ 15፡13)። መኖር የሚያስወድድ የሕይወት ጣዕም እርሱ ነው። ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሰላም እንዲኖርህ (ዕብራውያን 12፡29፤ ሮሜ 5፡1፤ ዕብራውያን 10፡19-20፤ 13፡6)፣ ከራስህም ጋር ሰላም እንዲኖርህ (ፊልጵስዩስ 4፡7)፣ ከሰዎችም ጋር ሰላም እና ፍቅር እንዲኖርህ የሚያስችል የሰላማችን ምክንያት እርሱ ነው (ሮሜ 5፡10-11፤ ሉቃስ 24፡36፤ ዮሐንስ 20፡19፤ ዮሐንስ 16፡33)

"በመጀመሪያ ቃል (ክርስቶስ) ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር (አብ) ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር (ወልድ) ነበረ፤ እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር (መንፈስ ቅዱስ) ጋር ነበረ። ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም" (ዮሐንስ 1፡1-3 አ.መ.ት)። "ሁሉ በእርሱ ተጋጥሞ" ተይዞአል (ቆላስይስ 1፡17)። "ሁሉንም በስልጣኑ ቃል እየደገፈ" በሰላም የሚያኖር ፈጣሪ አስተዳዳሪ እርሱ ነው (ዕብራውያን 1፡3)። "በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፤ እንኖርማለን" (የሐዋርያት ሥራ 17፡28፤ ዮሐንስ 14፡19፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡22፤ ዮሐንስ 6፡57፤ 11፡25)

እርሱ ያዳናቸው ብዙዎች ይመሰክራሉ። በአስጨናቂው ሰዓት የደረሰላቸው ብዙዎች ይናገሩለታል። ለመሆኑ አንተ አመልከዋለሁ የምትለው "አምላክ" በመጨረሻው አስጨናቂ ደቂቃ ደርሶልህ ያውቃል? ወይስ ገና አንተንም አያውቅህም? የነፍሳቸውን ወዳጅ ክርስቶስን ያገኙ (መኃልይ 1፡7፤ ሉቃስ 24፡27፤ ዮሐንስ 5፡39)፣ ፍቅሩን የጠጡ ብዙዎች (ዮሐንስ 13፡1፤ 15፡9፣ 13) እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቹ ሆነዋል (የሐዋርያት ሥራ 1፡8፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14፤ የሐዋርያት ሥራ 13፡31፤ የሐዋርያት ሥራ 5፡32፤ ሮሜ 15፡18-19)። እኔም ምስክሩ ነኝ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል፤ እርሱ ብቻ (1ኛ ዮሐንስ 4፡14፤ የሐዋርያት ሥራ 4፡12)

ጨለማ ወዴት እንደምትሄድ ለምን እንደተፈጠርህ ወይም ለምን እንደምትኖር አለማወቅ እና ልክ እንደ እንስሣት በደመ ነፍስ መመራት ነው። እውነተኛው የሕይወት ጣዕም ያለው ግን የፈጠረህን፣ ያዳነህን እና ያኖረህን አምላክ ክርስቶስን በግልህ ስታውቀው ነው።

የዓለም ብርሃን

ጌታ ሆይ እኔ አምንሃለሁ ምስክርነትህ እውነት ነው

ዮሐንስ 8፡
12 ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።
13 ፈሪሳውያንም፦ አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህ፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም አሉት።
14 ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፤- እኔ ስለ ራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደ መጣሁ ወዴትም እንድሄድ አታውቁም።
15 እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ስንኳ አልፈርድም።
16 የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው።
17 የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል።
18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።
(1ኛ ዮሐንስ 5፡8-13፤ ዮሐንስ 9፡5)

የብርሃናት አባት

እኛ የክርስቶስ ልጆች (ዕብራውያን 2፡14-15) እንደ ጨረቃ የጸሐዩን የክርስቶስን ደማቅ ብርሃን (የሐዋርያት ሥራ 9፡3-4) በሰው ፊት ስለምናበራ፣ እንደ መስተዋትም የጌታን ታላቅ ብርሃን ጨለማ በሆነው በዚህ ዓለም ላይ ስለ ምናንጸባርቅ (2ኛ ቆሮንቶስ 3፡18) ከክርስቶስ የተነሳ የዚህ አለም ብርሃናት ነን (ፊልጵስዩስ 2፡16፤ ማቴዎስ 5፡16)። እንግዲህ ብጹዕ እና ቅዱስ አባታችን ክርስቶስ (እግዚአብሔር) (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥15፤ ማቴዎስ 23፡9) የብርሃናት አባት የተባለው ከዚህ የተነሳ ነው (ያዕቆብ 1፡17)

ጨለማ ኃጢአት ነው። ኃጢአት ምንድር ነው? አመጽ ነው (1ኛ ዮሐንስ 3፡4፤ 1ኛ ዮሐንስ 5፡17)። አመጽ ምንድር ነው? ሕግን መተላለፍ ነው። ይኸውም አድርግ የተባለውን አለማድረግ፣ ወይም አታድርግ የተባለውን ማድረግ ነው (ያዕቆብ 4፡17)። ሕግን የፈጸመ በሕይወት ይኖራል (ሕዝቅኤል 20፡11)። ነገር ግን ከሰው ወገን ማንም ሕግን በሙሉ ሊፈጽም የቻለ የለም (ዕብራውያን 7፡23፤ ያዕቆብ 2፡9-12)። በመሆኑም ሰው ከኃጢአቱ መዳን አልቻለም። ስለዚህ እግዚአብሔር ራሱ መድኃኒት ሆነልን (መዝሙር 118፡14፣ 21፣ 28)። እንዴት? አዎን ራሱ ከሰማይ መጥቶ በእኛ ምትክ ሕግን ሁሉ ያለ እንከን ፈጸመ፤ የእኛን ቅጣት በመቀበል ከሕጉ እርግማን ዋጀን (ገላትያ 3፥13)። አሁን ሰው ከኃጢአቱ መዳን ይችላል። በምን? ዕዳውን በከፈለለት በእግዚአብሔር ወልድ በማመን። (ሮሜ 3፡20-24)

ፍጹም ሰው ፍጹም እግዚአብሔር በሆነው በዚህ ብርሃን እመን። ስለ እርሱ ለመመስከርም አትፈር።

ዮሐንስ 12፡
35 ኢየሱስም፦ ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።
36 የብርሃን (የክርስቶስ) ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ አላቸው። ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደና ተሰወረባቸው።
37-38 ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት (ተአምራት) በፊታቸው ምንም ቢያደርግ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ በእርሱ አላመኑም።
39-40 ኢሳይያስ ደግሞ፦ በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው።
41 (የክርስቶስን) ክብሩን ስለ አየ ኢሳይያስ ይህን አለ፥ ስለ እርሱም (ስለ ክርስቶስ) ተናገረ።
42 ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ ነገር ግን ከምኵራብ (ከስልጣን) እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤
43 ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።
44 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤
45 እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።
46 በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

የሐዋርያት ሥራ 13፡
38-39 እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ (በክርስቶስ) በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ (በክርስቶስ) እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
40-41 እንግዲህ፦ እናንተ የምትንቁ፥ እዩ ተደነቁም ጥፉም አንድ ስንኳ ቢተርክላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እኔ እሠራለሁና ተብሎ በነቢያት የተነገረው እንዳይደርስባችሁ (አለማመን እንዳያጠቃችሁ) ተጠንቀቁ።

ይቀጥላል ...
... የቀጠለ

የሐዋርያት ሥራ 10፡
43 በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።

ሮሜ 13፡
11 ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
12 ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
13 በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈን እና በስካር አይሁን፥ በዝሙት እና በመዳራት አይሁን፥ በክርክር እና በቅናት አይሁን፤
14 ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።

ታላቅ ብርሃን (እግዚአብሔር) በራልን

መዝሙር 118፡
27 እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ የበዓሉን መሥዋዕት በገመድ እሰሩት።
28 አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
29 እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘላለም ናትና።

ማቴዎስ 17፡
1 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
2 በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።

2ኛ ቆሮንቶስ 4፡
3 ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።
4 ለእነርሱም (ለሚጠፉ) የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።
5 ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።
6 በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።

ራእይ 1፡
16 በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ (የእግዚአብሔር ቃል) ወጣ (ዕብራውያን 4፡12)ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ ።
17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ


ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ ኢየሱስ (እግዚአብሔር)

ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ፣ ከልጅነታችንም ጀምሮ እስከ እለተ እረፍታችን ድረስ ስለ ታላቁ አምላካችን እና አዳኛችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ መንግስቱም እንስበክ። እርሱ አድኖናልና።

የሐዋርያት ሥራ 28፡
23 ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ (ጳውሎስ) መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት (ከብሉይ ኪዳን) ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር።
24 እኵሌቶቹም የተናገረውን አመኑ፥ እኵሌቶቹ ግን አላመኑም፤
25 እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ (እግዚአብሔር) በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን፦ (ኢሳይያስ 6፡8-10 ላይ ለነብዩ የተናገረው ጌታ እግዚአብሔር፣ አብ ወይም ወልድ ሳይሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ እርሱም ፦)
26 ወደዚህ ሕዝብ ሂድና ፦ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤
27 በዓይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ደንቁሮአል፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል በላቸው
28 ሲል መልካም ተናገረ። እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ደኅንነት ለአሕዛብ (ለሌሎች) እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ እነርሱ ደግሞ ይሰሙታል።
29 ይህንም በተናገረ ጊዜ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ሄዱ።
30 ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፥ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤
31 ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር።

2ኛ ቆሮንቶስ 4፡
5 ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን (ሃይማኖታችንን፣ ባህላችንን፣ ዕውቀታችንን፣ መላምታችንን፣ ምኞታችንን ወይም ፍላጐታችንን) አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።

ማጠቃለያ

ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነውን የኢየሱስን ስም መቃወም ያደቅቀናል (1ኛ ሳሙኤል 2፡10፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡8-15)። አሁን ይብቃን። ከእንግዲህ የእርሱ ባሪያዎች ሆነን እርሱን ማምለክ (ለእርሱ መስገድ) ይሻለናል። እርሱም ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነን (1ኛ ተሰሎንቄ 1፡9-10) ብቸኛው አዳኛችን እና አምላካችን ነው (ፊልጵስዩስ 3፡20፤ ቲቶ 2፡12-13)። አብ ራሱ ለኢየሱስ ስገዱለት ካለ እኛ ታድያ አንሰግድለትም ለማለት ማን ነን?

ዕብራውያን 1፡
6 (አብ) ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ (ለኢየሱስ) ይስገዱ (ያምልኩ) ይላል።

ሕዝቅኤል 46፡
1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦...
3 የአገሩም ሕዝብ በዚያ በር መግቢያ በእግዚአብሔር ፊት በሰንበታት እና በመባቻ ይስገዱ (ያምልኩ)

የሐዋርያት ሥራ 26፡ (ጳውሎስ /ሳውል/ ሲመሰክር)
9 እኔም ራሴ የናዝሬቱን የኢየሱስን ስም የሚቃወም እጅግ ነገር አደርግ ዘንድ እንዲገባኝ ይመስለኝ ነበር።
10 ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፥ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ።
11 በምኵራብም ሁሉ ብዙ ጊዜ እየቀጣሁ (ስሙን) ይሰድቡት ዘንድ ግድ አልኋቸው፤ ያለ ልክ ስቈጣባቸውም እስከ ውጭ አገር ከተማዎች ድረስ እንኳ አሳድድ ነበር።
12 ስለዚህም ነገር ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ስሄድ፥
13 ንጉሥ (አግሪጳ) ሆይ፥ በመንገድ ሳለሁ እኩል ቀን ሲሆን በዙሪያዬና ከእኔ ጋር በሄዱት ዙሪያ ከፀሐይ ብሩህነት የበለጠ ብርሃን ከሰማይ ሲበራ አየሁ፤
14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።
15 እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አልሁ። እርሱም አለኝ፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
16 ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።
17-18 የኃጢአትንም ስርየት (ያገኙ ዘንድ) በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።
19 ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ስለዚህ ከሰማይ የታየኝን ራእይ እምቢ አላልሁም።
20 ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት፣ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ፣ ለአሕዛብም ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ዘወር ይሉ ዘንድ ተናገርሁ።
21 ስለዚህ አይሁድ በመቅደስ ያዙኝ፤ ሊገድሉኝም ሞከሩ።
22-23 ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ።

ይሁን እንጂ ሁሉ ሰው እንደ ማያምን እና ሁሉ ሰው እንደ ማይድን እናውቃለን (2ኛ ተሰሎንቄ 3፡1-2)። እኛ ግን ክርስቶስን ማመን፣ ማፍቀር እና ማምለክ እንቀጥላለን። ከእርሱ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማንም ምንም አይኖርም።

በመጨረሻም፣ ክርስቶስን በማመን መዳን፣ በማወቅ ማደግ ይሁንልን፤ አሜን።

ኤፌሶን 4፡
12-13 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደ ሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን (አማኞች) አገልግሎትን ለመሥራት እና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
14 እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፣ በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያ እና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
15 ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን፣ በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደ ሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
16 ከእርሱም (ከክርስቶስ) የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመ እና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
17 እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው (በእውቀታቸው) ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፤ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ (እግዚአብሔር) ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል። አሜን።
0 ድምጾች
በመጀመሪያ "አንቱ" ማለት በኢትዮጵያውያን ባህል መሰረት የማናውቀውን ሰው ወይም በእድሜ እጅግ የሚበልጠንን የምንጠራበት መሆኑን መንገር አስፈላጊ አይመስለኝም። የመንፈሳዊ እውቀት መለኪያም አይመስለኝም። ቢሆንም አይገባኝም ስላልክ በአንተ እቀጥላለሁ።

አላማችን መማማር ከሆነ፣ ጌታ የሞተለትን ሰው ማዳን ከሆነ ያን በፍርሃት ልናደርገው ይገባል።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡16 "ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።" ተገቢም ነው።

ወደ ተሰጠው መልስ ስሄድ፣ ለዮሐንስ 1፡1 የሰጠሁትን ምላሽ በማስተባበል እኔን ከአንድ ቡድን ጋር ለማዛመድ (አባል ለማድረግ) ሞክረሃል። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። የይሖዋ ምስክሮች እንዲህ ዓይነት እምነት እንዳላቸው አውቃለሁ፤ ነገር ግን እነርሱ ብቻ ናቸው ስለዚህ ጥቅስ የተናገሩት? በጉግል መፈለጊያህ ላይ ዮሐንስ 1፡1 (John 1:1) ብለህ እስቲ ፈልግ። ከምታገኛቸው ገጾች መካከል እነዚህን ታገኛለህ።

http://www.greeklatinaudio.com/john11.htm
http://en.wikipedia.org/wiki/John_1:1
http://vintage.aomin.org/JOHN1_1.html
http://www.scribd.com/doc/34916458/The-correct-translation-of-John-1-1

አንዳንዶቹም የሥላሴን ጽንሰ ሐሳብ አስቀድመው የያዙ በመሆናቸው፣ የጉዳዩን አወዛጋቢነት ቢገልጹም፣ "ቃልም እግዚአብሔር ነበር" ብሎ መተርጎም እንደሚቀላቸው ተናግረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሆነ የሚናገርበት ቦታ ባለመኖሩ፣ እደግመዋለሁ ባለመኖሩ፣ የዚህ ጥቅስ አወዛጋቢነት በራሱ መልሱን ይነግረናል።

አንተም 'ዮሐንስ 1፡1 ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደነበረ ባይናገር ... እንኳ ሌሎች ብዙ ጥቅሶች ይህን እንደሚያሳዩ' ጽፈሃል። ለዚህ አባባልህ ያቀረብኸውን ማስረጃ እንመልከት።

በመጀመሪያ ደረጃ ጥቅሶችን ለማዛመድ የምትጠቀምበት ዘዴ (analogy) በራሱ አያስኬድም። እግዚአብሔር አንድ ነው (አዎን አንድ ብቻ እንጂ ሦስት አይደለም) የሁሉ ጌታ ነው (አዎን) ይህን ሃቅ ማንም አይክድም። ኢየሱስም ጌታ ነው፣ ስለዚህ እግዚአብሔር ማለት ኢየሱስ ነው ማለት ግን አያስኬድም። ለምን? እግዚአብሔር የፈለገውን የመምረጥ፣ የፈለገውን የወደደውን የማድረግ ሥልጣን አለው። በዚህም ኢየሱስን "ጌታም ክርስቶስም አድርጎታል"። (የሐዋርያት ሥራ 2፥36፣ 17፥31) የኢየሱስን ጌትነት አለመቀበል ለኢየሱስ ጌትነትን የሰጠውን እግዚአብሔርን መናቅ ነው፣ የኢየሱስን ጌትነት መቀበል ግን እግዚአብሔርን ማክበር ነው። (ፊልጵስዩስ 2፡5-11)

በግልጽ ካየነውም የማቴዎስ ወንጌል 6፡24 ሁለት ጌቶች (እግዚአብሔርና ገንዘብ) የሚለውን ለመረዳት ማሰብ እንኳ አያስፈልገንም። በመሆኑም analogy በራሱ አያስኬድም። እንዲህ ዓይነቱ አመለካከት ኢየሱስም ናቡከደነጾርም "የነገሥታት ንጉስ" ስለተባሉ ናቡከደነጾር ኢየሱስ ነበር ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል። (ሕዝቅኤል 26፡7፣ ዳንኤል 2፡37፣ ራእይ 19፡16) በኢሳይያስ 43 ላይ እግዚአብሔር ብቸኛ አዳኝ ስለተባለ "አዳኝ" የተባለ ባገኘን ቁጥር እግዚአብሔር ነው ብሎ መደምደም የእስራኤል መሳፍንት የነበሩት ጎቶንያልና ናኦድ (መሳፍንት 3፡9 እና 15) እግዚአብሔር ነበሩ ወደሚል መደምደሚያ ያደርሰናል። በመሆኑም analogy በራሱ አያስኬድም።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ለአምላክ አገልጋዮች የተገለጡት መላእክት እግዚአብሔርን ወክለው ስለሚገለጡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እስከማለት ደርሰዋል። (ለምሳሌ አብርሃም ይስሃቅን ሊሰዋ ሲል የተገለጠለት መልአክ ምን እንዳለው አንብብ፡ ዘፍጥረት 22፡11-12) እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር መልአክ ሆነ ወይስ ጸሐፊው (ሙሴ) አሳስቶን ይሆን፣ ወይስ ምን?

የተጠቀሰውን ሁሉ ለማንሳት አልሞክርም፤ ምክንያቱም አንባቢው በቀላሉ ማስተዋል ይችላልና።

በተረፈ ለመማማር ይመቻልና ጽሑፍህን አጠር ብታደርገው መልካም ነው።


ሰላም
Nov 6, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ወዳጄ ሆይ፣
እነዚህ ዌብ ሳይቶች እኮ የማይለወጥ እና የማይሻር የእግዚአብሔር ቃል (መጽሐፍ ቅዱስ) አይደሉም። ነገር ግን አማኞች ያልሆኑ የዚህ አለም ሰዎች የጻፏቸው ናቸው። እነዚህን ዌብ ሳይቶች የጻፏቸው ሰዎች፣ ራሳቸውን "ምሁራን" ብለው የሚጠሩ ወይም ደግሞ (የዚህን አለም ፊደል ስለ ተማሩ) ሌሎች ሰዎች "ምሁራን" ብለው የሰየሟቸው የዚህ አለም "ጥበበኞች" ናቸው። ደካማ እና ተጠያቂ የሆኑ ከሃዲ ሰዎች ስለ ጻፏቸው ስለ እያንዳንዱ ነገር ይፈረድባቸዋል (ማቴዎስ 12፡36፤ 1ኛ ጴጥሮስ 4፡5)። ልብ በል እነዚህ ጽሑፎች በዌብ ሳይቶች ላይ ለመገኘት ስለ በቁ ትክክል ናቸው ማለት አትችልም። እምነትህን ለማስረዳት እነርሱን ዋቢ መጥቀስም አያዋጣህም። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ቃል ተመዝነው ሲታዩ ባዶ የሰው ምኞት ወይም ከንቱ የሰው ትምህርት ብቻ ናቸው።

ታዲያ የእምነትህን መሰረት በአዳኝህ በኢየሱስ ክርስቶስ (ቲቶ 2፡12-14፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1፡1፣ 11፤ 2፡20) እና በእርሱ ቃል ላይ ማድረግ ትተህ፣ ከእነዚህ ዌብ ሳይቶች በምታገኘው ሰብአዊ መረጃ ላይ ብታደርግ እጅግ አደገኛ ነው። እምነትህን ለማስረዳት ዋቢ መጥቀስ ያለብህ የአምላክ ዘላለማዊ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። እንጂ ካንተ ጋር ተመሳሳይ ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች የጻፉት ዌብ ሳይት ዘላለማዊ እውነት ወይም የእምነትህ መሰረት ሊሆን አይችልም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ ዌብ ሳይት ሊያግባባንም አይችልም። እነዚያን ዌብ ሳይቶች የፈጠርኸው አንተ ራስህ ብትሆንስ በምን አውቃለሁ? ወይስ እኔ ራሴ አለመሆኔን ወይስ ትክክለኛ አማኞች መሆናቸውን እንዴት እርግጠኛ ልትሆን ቻልህ? አዎን፤ ማንም ይሁን ማን፤ ሰው የጻፈው ሁሉ ትክክል ወይም ስህተት መሆኑ በየጊዜው በመጽሐፍ ቅዱስ እየተመዘነ መታየት አለበት፤ እንጂ የእምነቴ መመሪያ ሊሆን ከቶ አይችልም።

በአምላክ ዙፋን (በክርስቶስ የፍርድ ወንበር) ፊት ብትቆም (ሮሜ 14፡10፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡10) እና እምነትህን እንድታስረዳ አምላክ (ክርስቶስ) ቢጠይቅህ፣ እናም እነዚያን ዌብ ሳይቶች ዋቢ ብትጠቅስለት፣ እርግጠኛ ሁን ከቁጣው አታመልጥም (ራእይ 6፡15-17)። ምክንያቱም አምላክ የሚያውቀው እና ላንተም የሰጠህ ትክክለኛ የእምነት መረጃ ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። "የምሁራንን ቃል" እንደ እግዚአብሔር ቃል አትመን። የነፍስህንም እምነት በእነርሱ ላይ አትመሥርት።

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይበቃናል፦

2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡
15 ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) አውቀሃል።

መዝሙር 87፡
6 እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።

ኢሳይያስ 34፡
16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ፤ አንብቡም፤ አፌ አዝዞአልና፥ መንፈሱም ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም።

ኤርምያስ 30፡
2 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ።

ክርስቶስ የማይናወጥ መሰረታችን ነው፦

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡
19 ሆኖም፦ ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።

1ኛ ቆሮንቶስ 3፡
11 ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፦ "ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል" (ማቴዎስ 7፡24)። ለምን? ምክንያቱም "ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም" (ማርቆስ 13፡31)

ኢሳይያስ 40፡
6 ሥጋ ለባሽ ሁሉ (እነዚያን "ምሁራንንም" ጨምሮ) ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።
7 የእግዚአብሔር (የክርስቶስ) እስትንፋስ (2ኛ ተሰሎንቄ 2፡8) ይነፍስበታልና ሣሩ (ሥጋ ለባሽ ሁሉ) ይደርቃል፤ አበባውም (ክብራቸው) ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ (እነዚያን "ምሁራንንም" ጨምሮ) ሣር ነው።
8 ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን (የክርስቶስ) ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች (ማርቆስ 13፡31)

በሚለወጡት እና በሚያልፉት ሰዎች ላይ አትደገፍ። እምነትህን በማይለወጠው በክርስቶስ ላይ ብቻ መሥርት።

እግዚአብሔር አብ ስለ ልጁ ስለ ክርስቶስ ሲመሰክር፦

ዕብራውያን 1፡
10 ጌታ (ክርስቶስ) ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ (አንተ ፈጣሪ አምላክ ነህ)
11 እነርሱም ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ (ፍጥረት) ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።

ዕብራውያን 13፡
8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት እና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው (አይለወጥም)(አሜን።)

ሚልክያስ 3፡ (ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ሲናገር እንዲህ አለ፦)
6 እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ፣ "ልባም ሰው" (ማቴዎስ 7፡24) ከሆንህ በማይለወጠው እና ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው በክርስቶስ እና በእርሱ ቃል ላይ እምነትህን መሥርት። እንጂ አላፊ የሆኑ ሰዎችን አትደገፍ። እንኳን አንተን ሊረዱ፣ ራሳቸውንም ሊያተርፉ የማይችሉ ናቸውና። ለበለጠ ሃሳብ ከላይ <<ፈጣሪህን እመን እንጂ "ምሁርን" አትመን>> የሚለውን ርዕስ ተመልከት። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ (ራእይ 22፡21) አሜን።
Feb 10, 2014 child of Jesus (440 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 17, 2014 child of Jesus ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...