ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 7 March 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የወይን ተጅ መተጣታት አጢያት ነው?

የወይን ጠጅ መጠጣት አጢያት ነው?
Jul 26, 2013 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

4 መልሶች

0 ድምጾች
አስቀድሞ የተሰጠው መልስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ የሎጂክ ስህተት አለበት። በዚህ ሎጂክ መሰረት ጾም ሰውነትን ስለሚጎዳ መጾም የለብንም፣ ለአገልግሎቱ ሲባል ረጅም መንገድ በእግር መሄድ እግርን ስለሚጎዳ መኬድ የለበትም፣ ወዘተ ወደሚሉ የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ላይ የሚያደርስ አስተሳሰብ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ላይ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ያደረገበትን የመጀመሪያ ተዓምር ይነግረናል። ኢየሱስ ምን እያደረገ ነበር? አንዳንዶች የርሱ ወይን ጠጅ አያሰክርም ነበር የሚል ስንኩል ምክንያት ያቀርባሉ። ነገር ግን ዮሐንስ 2፡10 እንደሚለው ያሰክራል። ሌሎችም የጌታ እራት የሚዘጋጅበት ወይን እንዲሁ አያሰክርም የሚል አመለካከት አላቸው። 1 ቆሮንቶስ 11፡21 እንደሚለው ግን አብዝቶ ቢጠጣ ያሰክራል

በሌላ በኩል ግን
Quote:
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥23 "ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።"
በማለት የወይን ጠጅ መጠጣት ስህተት የማይሆንበትን አንድ ጉዳይ ይጠቅሳል።

ቢሆንም ግን መጽሐፍ ቅዱስ በ
Quote:
1ኛ ቆሮንቶስ 6፥10 "... ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።"
በማለት ስካርን ያወግዛል።

ሰላም
Jul 30, 2013 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
Jul 30, 2013 ኦፍቲ ታርሟል
0 ድምጾች
መስከር ነው ሓጥያት አንጂ የወይን ጠጅ መጠጣት ኣይደለም፥፥
Jul 31, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
በደንብ የተብራራ መጽሃፍ ቅዱሳዊ መልስ ከፈለግህ እዚህ አንብብ
Aug 1, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
መጠጣት ይቻላል፤ ሓጥያትም አይደለም። ከፈልጉ ደገሞ አለመጠጣት ይችላሉ። መልሱ የተንዛዛና ዙርያ ጥምጥም አይደለም። በዩሓ 2፤ ጌታ በሰርግ ቤት ውስጥ ወይን አትጠጡ አላለም እንዲያሁም ታምር አድርጎ ወይን እንዲጠጡ አድርጎአል።

መጠጣት አይቻልም ሓጥያት ነው የሚሉ ፓስትሮችን አይስማቸው፤ የራሳቸውን ተረት ተረት ወይም የስህተት መንፈስ የሚያስተላልፈወን መልክት እያስተጋቡ ነው።

በዩሓ 2፤ ጌታ በሰርግ ቤት ውስጥ ወይን አትጠጡ አላለም፤ እንዲያሁም ታምር አድርጎ ሰርገኞችና ተጋብዦች ወይን እንዲጠጡ ወኖአል።
Aug 1, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...