አስቀድሞ የተሰጠው መልስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ የሎጂክ ስህተት አለበት። በዚህ ሎጂክ መሰረት ጾም ሰውነትን ስለሚጎዳ መጾም የለብንም፣ ለአገልግሎቱ ሲባል ረጅም መንገድ በእግር መሄድ እግርን ስለሚጎዳ መኬድ የለበትም፣ ወዘተ ወደሚሉ የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ላይ የሚያደርስ አስተሳሰብ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ላይ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ያደረገበትን የመጀመሪያ ተዓምር ይነግረናል። ኢየሱስ ምን እያደረገ ነበር
? አንዳንዶች የርሱ ወይን ጠጅ አያሰክርም ነበር የሚል ስንኩል ምክንያት ያቀርባሉ። ነገር ግን ዮሐንስ 2፡10 እንደሚለው
ያሰክራል። ሌሎችም የጌታ እራት የሚዘጋጅበት ወይን እንዲሁ አያሰክርም የሚል አመለካከት አላቸው። 1 ቆሮንቶስ 11፡21 እንደሚለው ግን አብዝቶ ቢጠጣ
ያሰክራል።
በሌላ በኩል ግን
Quote:
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥23 "ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።"
በማለት የወይን ጠጅ መጠጣት ስህተት የማይሆንበትን አንድ ጉዳይ ይጠቅሳል።
ቢሆንም ግን መጽሐፍ ቅዱስ በ
Quote:
1ኛ ቆሮንቶስ 6፥10 "... ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።"
በማለት ስካርን ያወግዛል።
ሰላም