ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በማቴዎስ 13፡24-30 ያለው የኢየሱስ ምሳሌ ትርጉም ምንድነው?

ጥቅሱ እንዲህ ይነበባል፡
Quote:
24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።

25 ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።

26 ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።

27 የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት።

28 እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት።

29 እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።

30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።


ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው ስለየትኛው እንክርዳድ ነው? መቼ የሚዘራ፣ መቼስ የሚታጨድ?

አመሰግናለሁ
Aug 13, 2013 መንፈሳዊ ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
 
ምርጥ መልስ
ጌታ ኢየሱስ ሰለስንዴውና እንክርዳዱ ምሳሌ ትርጉሙን ሰለሰጠ ሌላ የሚያብራራልዎት ሰው አያስፈልግዎትም።
ማቴ 13፡36-43 እንዲህ ይላል

በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
37 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
38 መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
39 እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
40 እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
42 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

ጌታ ይባርክዎት።
Sep 29, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
ስለ ግልጽ መልስዎ አመሰግናለሁ።

አዎን ልክ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ራሱ የምሳሌውን ትርጉም ነግሮናል።

ነገር ግን እኔ፣ ለኛ (በዚህ ዘመን ለምንኖረው ሰዎች) ያለው ትርጉም ምን እንደሆነ ማሰብ ፈለግሁ።

እንክርዳድ ሲያድግ ቁመቱ ከስንዴው እንደሚበልጥ ከአንድ ምንጭ ሰምቼ ነበር። እናም በክርስትና ዘመን ሁሉ ታላላቅ የተባሉ ሰዎች የእውነትን ደብዛ ለማጥፋት ከፍተኛ ትግል በማድረግ በክርስትና አስተምህሮ ላይ አይነተኛ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ሳስብ ከእንክርዳዱ አስተዳደግና ይዞታ ጋር ተመሳስሎ አገኘዋለሁ። ከኢየሱስ ማንነት ጀምሮ፣ ማርያም በአምልኮ ውስጥ ስለሚኖራት ቦታ፣ ስለ ምልጃ፣ በምስል (በሥዕል) ተደግፎ ስለማምለክ፣ እና ስለሌሎችም የተነሱት አጨቃጫቂ ትምህርቶችን ማንሳት ይቻላል።

እናም ለዚህ ሁሉ ትምህርተ-ምስቅልቅል ዋነኛው መንስኤ፣ ጌታ ኢየሱስ እንዳለው፣ እንክርዳዱን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው። ስለዚህ ጉዳይም ሲናገር ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡1 እና 2 ላይ "መንፈስ ግን በግልጥ። በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን(እምነትን) ይክዳሉ ይላል"።

እናም ትምህርቶቻችን የሰይጣን ዲያብሎስ እንክርዳድ ውጤት፣ ወይም የአጋንንት ትምህርት እንዳይሆኑ የቀደመውንና ጥርት ያለውን ትምህርት ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ብርቱ ጥረት ያስፈልገናል እላለሁ። ምክንያቱም ኢየሱስ እንዳለው እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር አብሮ እስከ መከር ዘመን (እስከ መጨረሻው ዘመን = እስካለንበት ዘመን) እንደዘለቀ፣ እውነትና ሐሰቱ እንዲሁ ተቀላቅሎ ነው የደረሰን። እንክርዳዶች ተቆርጠው ወደ እሳት ሲጣሉ እኛም አብረን እንዳንጠፋ የእንክርዳድ መሰሎቹን የሐሰት ትምህርት ልንጸየፈው፣ ልንዋጋው፣ ልንቃወመው ያስፈልገናል።

"ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን መናገር" ያስፈልገናል። - ቲቶ 2፡1


ሰላም
0 ድምጾች
ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ የሚከተለው ነው፦ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር ከዘራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ነገር ግን ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው ላይ እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ። ቡቃያው አድጎ ፍሬ ባፈራ ጊዜ እንክርዳዱም አብሮ ታየ። ስለሆነም የባለቤቱ ባሪያዎች ወደ እሱ ቀርበው ‘ጌታ ሆይ፣ በእርሻህ ላይ የዘራኸው ጥሩ ዘር አልነበረም እንዴ? ታዲያ እንክርዳዱ ከየት መጣ?’ አሉት። እሱም ‘ይህን ያደረገው አንድ ጠላት የሆነ ሰው ነው’ አላቸው። እነሱም ‘ታዲያ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህ?’ አሉት። እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ‘አይ፣ አይሆንም፤ ምክንያቱም እንክርዳዱን ስትነቅሉ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉ ትችላላችሁ። ተዉት፣ እስከ መከር ጊዜ ድረስ አብሮ ይደግ፤ የመከር ወቅት ሲደርስ አጫጆቹን፣ በመጀመሪያ እንክርዳዱን ሰብስቡና እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ከዚያም ስንዴውን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡ እላቸዋለሁ።’”—ማቴ. 13:24-30


በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር የዘራው ሰው ማነው? ኢየሱስ ቆየት ብሎ የምሳሌውን ትርጉም ለደቀ መዛሙርቱ ባብራራላቸው ጊዜ “ጥሩውን ዘር የዘራው የሰው ገጽ 20ልጅ ነው” በማለት መልሱን ተናግሯል። (ማቴ. 13:37) “የሰው ልጅ” ተብሎ የተጠራው ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነባቸው ሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እርሻውን አለስልሶ ለዘር አዘጋጅቷል። (ማቴ. 8:20፤ 25:31፤ 26:64) ከዚያም በ33 ዓ.ም. ከተከበረው የጴንጤቆስጤ ዕለት አንስቶ ጥሩ ዘር የሆኑትን ‘የመንግሥቱን ልጆች’ መዝራት ጀመረ። ይህ የመዝራት ሥራ የተከናወነው ኢየሱስ የይሖዋ ወኪል ሆኖ በደቀ መዛሙርቱ ላይ መንፈስ ቅዱስን ማፍሰስ በጀመረበትና የአምላክ ልጆች አድርጎ በቀባቸው ጊዜ እንደነበረ ግልጽ ነው።* (ሥራ 2:33) ከጊዜ በኋላ ጥሩው ዘር ማለትም ስንዴው አድጎ ጎመራ። ስለዚህ ጥሩ ዘር የሚዘራበት ዓላማ ከኢየሱስ ጋር በመንግሥቱ ተባባሪ ወራሾችና ገዥዎች የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር እስኪሟላ ድረስ እነሱን በጊዜ ሂደት ለመሰብሰብ ነው።


ጠላት የተባለው ማን ነው? እንክርዳድ የተባሉትስ እነማን ናቸው? ኢየሱስ ጠላት የተባለው “ዲያብሎስ ነው” በማለት ተናግሯል። እንክርዳዶቹ ደግሞ “የክፉው ልጆች” እንደሆኑ ተገልጿል። (ማቴ. 13:25, 38, 39) እንክርዳድ መርዛማ እህል ሲሆን በቡቃያነት ደረጃ ከስንዴ ጋር በጣም ይመሳሰላል። የመንግሥቱ ልጆች እንደሆኑ ቢናገሩም እውነተኛ ፍሬ የማያፈሩ አስመሳይ ክርስቲያኖች በእንክርዳድ መመሰላቸው ምንኛ የተገባ ነው! እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የክርስቶስ ተከታይ እንደሆኑ የሚናገሩት እነዚህ ግብዝ ክርስቲያኖች የሰይጣን ዲያብሎስ ‘ዘር’ ክፍል ናቸው።—ዘፍ. 3:15


በእንክርዳድ የተመሰሉት እነዚህ ክርስቲያኖች መታየት የጀመሩት መቼ ነው? በእንክርዳድ የተመሰሉት እነዚህ ክርስቲያኖች መታየት የጀመሩት “ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ” እንደሆነ ኢየሱስ ተናግሯል። (ማቴ. 13:25) ይህ የሆነው መቼ ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሽማግሌዎች እንደሚከተለው ብሎ በተናገረው ሐሳብ ላይ መልሱን እናገኛለን፦ “እኔ ከሄድኩ በኋላ ጨካኝ ተኩላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡና መንጋውን በርኅራኄ እንደማይዙ አውቃለሁ፤ ከእናንተ ከራሳችሁ መካከል እንኳ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ጠማማ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ይነሳሉ።” (ሥራ 20:29, 30) ቀጥሎም እነዚህን ሽማግሌዎች ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁ እንዲሆኑ አሳስቧቸዋል። ክህደት እንዳይገባ ‘አግደው’ የነበሩት ሐዋርያት በሞት ካንቀላፉ በኋላ በርካታ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ አንቀላፍተው ነበር። (2 ተሰሎንቄ 2:3, 6-8ን አንብብ።) ታላቁ ክህደት የተጀመረው በዚህ ጊዜ ነው።


ኢየሱስ እዚህ ምሳሌ ላይ ስንዴው ተቀይሮ እንክርዳድ ይሆናል አላለም፤ ከዚህ ይልቅ እሱ የተናገረው በስንዴው መካከል እንክርዳድ እንደተዘራ ነው። በመሆኑም ይህ ምሳሌ ከእውነት የወጡትን እውነተኛ ክርስቲያኖች የሚያመለክት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ሰይጣን ክፉ ሰዎች ወደ ክርስቲያን ጉባኤ ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ ሆን ብሎ ጉባኤውን ለመበከል የሚያደርገውን ጥረት ያመለክታል። የመጨረሻ ሐዋርያ የነበረው ዮሐንስ ዕድሜው በገፋበት ወቅት ክህደቱ በግልጽ መታየት ጀምሮ ነበር።—2 ጴጥ. 2:1-3፤ 1 ዮሐ. 2:18
Sep 24, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
Sep 24, 2013 ተመልካች ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...