ርስት ማለት አንድን ንብረት የመውረስ መብት ያለው ሰው ወይም ቃል የተገባለት ሰው የሚወስደው ንብረት ወይም ሃብት ወይም ውርስ ማለት ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ እንደመሆኑ መጠን የዳዊትን ዙፋን ወርሷል። (ኢሳይያስ 9፡7፣ ሉቃስ 1፡32) የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑም መጠን እግዚአብሔር በገባለት ቃል ኪዳን መሰረት በሠማይ ንግስናን ተቀብሏል። (መዝሙር 110፡4፣ ሉቃስ 22፡28-30) በዚህም መሰረት ክርስቶስ አሕዛብን ሁሉ ወርሷል፣ ጠላቶቹን ሁሉ ሰባብሮ ለዘላለም ይገዛል። (መዝሙር 2፡6-9)
ኢየሱስ ተከታዮቹ በመንፈስ ተቀብተው የሰማያዊ ውርስ ተካፋዮች እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ከዚህም ባሻገር ከክርስቶስ ጋር ስለሚወርሱት ውርሻ / ርስት / ሲናገር የርሱ "ወንድሞች" እንደሆኑ ይገልጻል። (ኤፌሶን 1፡14፣ ቆላስይስ 1፡12፣ 1 ጴጥሮስ 1፡4,5) ምድርንም ይወርሳሉ ተብሎላቸዋል። (ማቴዎስ 5፡5)
እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ በማውጣቱ /በመቤዠቱ/ እነርሱ የእግዚአብሔር "ርስት" / "ውርሻ" ሆነው ነበር። (ዘዳግም 32፡9፣ መዝሙር 33፡12፣ 74፡2፣ ሚክያስ 7፡14) እስራኤላውያን ጥላ የሆኑለት "ህዝብ" (ማለትም መንፈሳዊ እስራኤል) እግዚአብሔር በአንድያ-ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የገዛቸው በመሆኑም የርሱ "ርስት" ተብለዋል። (1 ጴጥሮስ 2፡9፣ 5፡2,3፣ የሐዋርያት ሥራ 20፡28)
ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ስሙ ሲሉ ያላቸውን የሚተዉና የሚሰደዱ "የዘላለም ህይወት እንደሚወርሱ" ተናግሯል። (ማቴዎስ 19፡29፣ ማርቆስ 10፡29,30)
ሰላም