ክርስትና ከመምጣቱ በፊት በአይሁድ እምነትና ባህል ለእምነት መርጃ የሚሆን የማናቸውም ቅዱስ ሰው ወይም እግዚአብሔር ወዘት ምስል ወይም ቅርጽ መስራትና መጠቀም አጥብቆ የተከለከለ ነው።
Quote:
ኦሪት ዘዳግም 4
15 እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ
16 እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥
17 በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥
18 በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥
ክርስትናም እንዲሁ ከአሁድ የብሉይ ኪዳን የወጣ/የሚቀጥል እምነት እንደመሆኑ በአዲስ ኪዳንም በመጽሃፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ ቅዱሳንንም ይሁን እግዚአብሔርን ወይም ኢየሱስን የመሳል ወይም የመቅረጽ ልምድና ተግባር በፍጹም አልነበረም።
ይህ ለቅዱሳን ስእል መሳልና መቅረጽ ወዘተ የተጀመረው ክርስትና ከተመሰረተ በኋላ ከ100 እስከ 300 ዓመታት ማለትም በ2ኛው እስከ 4ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ነው። ምንም አይነት መጽሃፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የሌለው በፍጹም አይሁዳዊ ወይም የጥንቱ ክርስቲያናዊ ባህል ያልሆነ ፈጽሞ የባእድና የአህዛብ ባህል ነው።
ታሪካዊ አመጣጡን በይበልጥ ለመረዳት
እዚህ አንብብ።