ኢየሱስ ብዙ ጊዜ መልስ ሲመልስ ወይም ደግሞ ጳውሎስ በደብዳቤው ሲጽፍ "
ተብሎ ተጽፎአል" እያሉ ከመጽሃፍ ቅዱስ የተጻፈውን እየጠቀሱ ነው እንጂ "ተብሎ ተወርቶአል" ወይም ሰዎች "እንዲ አሉ" እያሉ አልነበረም። ስለዚህ በመጽሃፍ ቅዱስ ባልተጻፈና ሰዎች ፈጥረው በሚያወሩት የአሉ ወሬ ብዙ ጊዜህን ባታጠፋና ወደ ተረት ፈቀቅ እንዳትል ብትጠነቀቅ መልካም ነው።
Quote:
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4
3 ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።
4 እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።