ውድ ጠያቂ
ብዙ ሰዎች በራዕይ መጽሐፍ ምዕራፍ 13 ላይ የምናገኘውን አንድ ትንቢታዊና ምሳሌያዊ አውሬ የተሰጠውን ቁጥር በሚመለከት ብዙ መላምቶችን ይደረድራሉ። ከዓለም ነባራዊ ሁኔታዎች ጋርም ለማያያዝ ሲሞክሩ እንሰማለን።
እስቲ ግን ስለጉዳዩ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንመርምር።
ስሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
በመጽሐፍ ቅዱስ ስሞች፣ በተለይም በፈጣሪ የተሰጡ ሲሆኑ ትርጉም አዘል ናቸው። ለምሳሌ አብራም የሚለው ስም "የአሕዛብ አባት" ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ግን ወደ "አብርሃም" ለውጦታል። ይህም "የብዙ ህዝቦች አባት" ማለት ነው።
(ዘፍጥረት 17፡5
)
እግዚአብሔር ለማርያምና ዮሴፍ የህጻኑ ስም "ኢየሱስ" እንደሚባል በመልአክ ገልጾላቸዋል። ይህም "
እግዚአብሔር አዳኝ ነው" የሚል ትርጉም አለው። ከስሙ ትርጉም ጋር በተስማማ መልኩ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በልጁ አድኗል።
(ዮሐንስ 3፡16
)
የአውሬውን ስም 666 ብሎ የነገረን የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑም
(እግዚአብሔር ያወጣው ስም እንደመሆኑ
) ትርጉም አዘል ስም መሆን ይኖርበታል። የስሙን ትርጉም ለማወቅ የአውሬውን ማንነት ማወቅ ይኖርብናል።
የአውሬው ማንነት
በዳንኤል 7፡2
-7 ላይ ዳንኤል "አራት ታላላቅ አራዊት" እንደተመለከተ ይገልጽልናል።
ዳንኤል ቀጥሎ እንደጠቀሰው
Quote:
ትንቢተ ዳንኤል 7፡17 "እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው።"
Quote:
ትንቢተ ዳንኤል 7፡23 "እንዲህም አለ፦ አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል።"
በራዕይ ስለታየው አውሬስ ምን ልንል እንችላለን
? የዮሐንስ ራእይ 13፡7 "ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ
ሥልጣን ተሰጠው።" በማለት የዚህ አውሬ ማንነትም በሰዎች ሁሉ ላይ ይገዛ ዘንድ ሥልጣን እንደተሰጠው በመግለጽ ተመሳሳይ ትርጉም እንዳለው ያሳያል።
"የሰው ቁጥር ነው"
ሦስተኛውን ነጥብ የራዕይ መጽሐፍ አውሬው "ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው" በማለት ይገልጸዋል። ሰይጣን በአውሬው ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው ስለተገለጸና "ክፉው" ሰይጣን ዓለምን በሞላ ስለሚቆጣጠር 666 አንድ ግለሰብ አይሆንም።
(ሉቃስ 4፡5
-6፣ 1ኛ ዮሐንስ 5፡19፣ ራዕይ 13፡2፣ 18
) ቁጥሩ "የሰው ቁጥር" መባሉ ከመንፈሳዊው አጋንንታዊ ዓለም ይልቅ ከሚታየው ሰብዓዊ ዓለም ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይጠቁማል። መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ 3፡23 ላይ "ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል" በማለት የሰብዓዊው ህብረተሰብን ጉድለት
(ፍጹም አለመሆን
) ያጎላል። ይህም ነገስታቱ የሰብዓዊው ህብረተሰብ ሃጢአተኝነት የተጠናወታቸው በአለፍጽምና ላይ የቆመ መሆኑን እናስተውላለን።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጥሮች አንዳንዴ በምሳሌያዊ ሁኔታ ትርጉም እንዳላቸው እንረዳለን። ለምሳሌ በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ የፍጥረት ቀናት ሰባት ናቸው። እግዚአብሔርም ስራውን ሁሉ
ፈጽሞ አረፈ ይለናል።
Quote:
መዝሙር 12፡6 "ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።"
Quote:
ምሳሌ 30፡5-6 "የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው። እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።"
Quote:
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 5፡10, 14፡ "ኤልሳዕም። ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ ሥጋህም ይፈወሳል፥ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ። . . . ወረደም፥ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ።"
በነዚህ ጥቅሶች ላይ እንደምናየው ሰባት ቁጥር
ሙሉነትን፣
ፍጹምነትን የሚያሳይ እንደሆነ እንገነዘባለን።
ስድስት ደግሞ ፍጹምነትን ከሚያሳየው በአንድ የጎደለ ነው። ይህም በእግዚአብሔር ዘንድ የተበላሸንና የጎደለን ነገር እንደሚያመለክት መረዳት ይቻላል።
(1ኛ ዜና 20፡5
-6
)
መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ነገር ለማክበድ
(ለማጠንከር
) ሦስት ቁጥርን ይጠቀማል። በመሆኑም 666 የሚለው ቁጥር "ከባድ ጉድለት"፣ "ያዘቀጠ ኃጢአተኝነት"፣ "ከባድ አለፍጽምና" ማለት ሊሆን ይችላል ቢባል ሚዛን የሚደፋ አባባል ይሆናል።
Quote:
መዝሙረ ዳዊት 146፡3 "ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ።"
እናስ ትምክህታችንን በመንግስታት ላይ በመጣል በከባድ አለፍጽምና ላይ የወደቅን የእግዚአብሔር ጠላቶች እንሆናለን
? ወይስ ትምክህታችንን ሁሉ በእግዚአብሔር መንግስት
(በሰማይ ባለችው መንግስተ ሰማያት
) ላይ ጥለን "
መንግስትህ ትምጣ" ብለን እንለምነዋለን
? (ማቴዎስ 6፡10
)
ሰይጣን ትርጉሙን አዛብቶ ሊያታልለን ቢሞክርም እኛ ነቃንብህ ልንለው ያስፈልገናል።
ሰላም