ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 8 December 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አዘጋጆች ሙስሊም አቀነባባሪዎች ስለመሆናችሁ ማስረጃ በመጥቀስ ይኮንኑዋችዋል።

አዘጋጆች ሙስሊም አቀነባባሪዎች ስለመሆናችሁ ማስረጃ በመጥቀስ ይኮንኑዋችዋል። አቀራረባችው ድገሞ ይህንኑን ያረጋግጣል። አርፋቸሁ የራሳችውን አምነት ብታስተምሩ አይበጅም?
Dec 2, 2013 ስለ እኛ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ሰላም

ሙስሊሞች ስለመሆናችን ማስረጃውን በዝርዝር ብትነግረንና እኛም ስለዚያ መልስ ብንሰጥበት አይሻልም ብለህ ነው? መጽሃፍ ቅዱስ በሃሰት አትመስክር ይላልና በሃሰት ሰውን ከመክሰስ በፊት ማስረጃና ማረጋገጫ መያዙ ከዚያም አልፎ የተከሰሰው ሰው ስለ ክሱ መልስ እንዲሰጥና ራሱን እንዲከላከል እድል መስጠቱ ተገቢና ትክክለኛ አሰራር ነው። ስለዚህ ማስረጃዎቹን በዝርዝር አቅርብልንና እኛም መልስ እንድንሰጥበት እድል ስጠን። መሰረተ ቢስ የሃሰት ስም ማጥፋት ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ግን አትተባበር።

እስከዚያው ግን እኛ ሙስሊም ስለ አለመሆናችን የሚከተሉትን ማስረጃዎች እንስጥህ፦
) አንድ ሰው ሙስሊም ሊባል የሚችለው ቢያንስ ቢያንስ የሚከተሉትን መሰረታዊ የሙስሊም እምነቶች ሲያምንበት ነው፦ አንደኛ አላህ ብቸኛ አምላክ መሆኑ፣ ሁለተኛ መሃመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነብይ መሆኑና ሶስተኛ ቁራን የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ሲያምን ነው።
እኛ ግን በእነዚህ በሶስቱም አናምን! ልብ በል ከላይ የጠቀስናቸውን የሙሊም እምነቶች ልክ እንደዚህ እንደኛ በሙሉ ልብ "አላምንም" ብሎ የሚናገር ወይም የሚጽፍ ሙስሊም በምድር ላይ የለም። ምክንያቱም ይሄንን ያለ እለት እስልምናን ካደ ማለት ነው። እኛ ግን በመጽሃፍ ቅዱሱ የእስራኤል አምላክ አብ፣ በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና በመጽሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃልነት እንጂ በአላህ ወይም በመሃመድ ወይም በቁራን አናምንም።

) ሌላው እኛ ሙስሊም እንዳልሆንን የሚያረጋግጠው ነገር በዚህ በእኛ ድረገጽ ላይ ሰዎች መጽሃፍ ቅዱስን በኦንላይን እንዲያነብቡና በቀላሉም ቃላቶችን እንዲፈልጉ የሚያደርግ የመጽሃፍ ቅዱስ የቃላት መፈለጊያ አዘጋጅተናል። ከዚህም አልፈን በነጻ ዳውንሎድ የሚደረግ የአማርኛ የመጽሃፍ ቅዱስ ሶፍትዌር በድረገጻችን ላይ አቅርበናል። ይህም ሁሉ መጽሃፍ ቅዱስን ለማስፋፋትና ሰዎች ቃሉን እንዲያጠኑ ለመርዳት ነው። ታዲያ መጽሃፍ ቅዱስን በነጻ የሚያስፋፋ ሙስሊም መቼ ነው ያየኸው? ሙስሊሞች መጽሃፍ ቅዱስን ሊያስፋፉ ይቅርና በእጃቸው ሊነኩትም አይፈልጉም። ደግሞስ ለሙስሊሞች መጽሃፍ ቅዱስን እንዲህ ማስፋፋት ምን ይጠቅማቸውል?

እነዚህ ከላይ የጠቀሰነው ማስረጃዎች በጣም ጥቂቶቹን ብቻ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ትምህርቶቻችንን፣ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናቶችን ወዘተ በማየት ሙስሊሞች እንሁን ወይም አንሁን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። በእርግጥ እውነትን ለሚፈልግ ማለት ነው!

ለማናቸውም ሙስሊም ያስባለንን ማስረጃ በዝርዝር ንገረንና እኛም መልስ እንሰጥበታለን።

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከአንተና ከከሳሾቻችን ሁሉ ጋር ይሁን። አሜን!

iyesus.com
Dec 2, 2013 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...