የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ የፕሪፓራቶሬ ውጤት አምጥቼ ሂሳብ መምህር መሆን ስለምፈልግ ተፈጥሮ ሳይንስ ገባሁ፡፡ እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ውጤት አምጥቼ ዩንቭርስቲ ገባሁና የመጀመሪያ ምርጫዬ ሂሳብ ስለሆነ ተሰጠኝ፡፡ ሂሳብ የመረጥኩበት ምክንያት ህልሜ በጥሩ ውጤት ተመርቄ የዩኒቨርስቲ መምህር መሆን ነው፡፡ እግዚአብሄር ረድቶኝ አምስት ሰሚስተር 4፡00 አምጥቼ በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቁ፡፡ ይሁን እንጂ በ2005 ዓ.ም እንደበፊቱ ለሌክቸርነት(ዩኒቨርስቲ መምህር) ውድድር ቀርቶ ሁሉም ተመራቂ ተመርቆ ወደየመጣበት ሄዶ ስራ መፈለግ ሆነ፡፡ ሶስት አይነት አገርአቀፍ ፈተናዎችን ተፈትኜ አልተሳካልኝም፡፡ በጣም ተስፋ ቆርጬ የክልላችን አብዛኛው ስራ አጥ ስራ ሚያገኝበት ወደ አሶሳ ሄድኩ፡፡ ለ3 ወር ተቀምጬ በኛ ዲፓርትመንት ምንም አይነት ማስታወቂያ አልወጣም፡፡ ቀጥታ አቅራቢያ በሚገኘው ወደ አጎቴ ቤት ሄድኩ ተስፋ በቆረጠ መልኩ፡፡ አጎቴ ክርስቲያን ነው እ/ርን በጣም ያገለግላል፣ እኔንም በጣም ይመክረኝ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አጎቴ ሊያፀልይልኝ ወደሚግባባው የጌታ አገልጋይ( በጣም የሚወራለት የተናገረው ሁሉ የሚሆን) የሆነው ሰው ይወስደኛል፡፡ በእለቱ ከ2 ወር በፊት የተፈተንኩትን ፈተና ውጤቱን በስልክ እየተጠባበቁ ነው፡፡ ፀሎቱ እንደተጀመረ እግዚአብሄር ብዙ ነገር ተናገረ ልቤን በጣም ነካኝ ስልክ በቅርቡ ተደውሎ ያሰብኩት ህልሜ እንደሚሳካልኝም እግዚአብሄር በባሪያው በኩል ተናገረ እኔም በእግዚአብሄር ተማምኜ እንደሚደወልልኝ ተማመንኩ ነገርግን አንድ ቀን ካደረ በኋላ ውጤቱን ሰማሁ፡፡ አላለፍኩም፡፡ መልዕክቱ የተነገረኝ እለት ግን ሴጣን ገፋፍቶኝ ትልቅ ኃጢያት ሰርቻለሁ፡፡
ወገኖቼ!!! እግዚአብሄር እኮ ለአብርሃም የተናገረውን ራዕይ ባለበት ጊዜ ባይሆንም ቆይቶ ፈፅሞለታል፡፡ መልዕክቱ ከእግዚአብሄር እንደሆነ ያመንኩት ይህ አገልጋይ ስልክ እየጠበቁ እንደሆነ አያውቅም፡፡ የኔ ህልም የነበረው የዩኒቨርስቲ መምህር መሆን ፈተናውም ያው ነበር አሁን ግን ቢሮ ውስጥ እየሰራሁ ነው፡፡ የተናገረው እውነት እ/ር ከሆነ ሳይፈፅም ይቀራል?? እባካችሁን ትከክለኛ እና መንፈሳዊ የሆነ ምክር እፈልጋለሁ፡፡