ከጥያቄህ ለመረዳት እንደቻልኩት ወንድሜ እንደቀድሞ የነበረህ ደስታ አሁን እንደሌለህ ለእግዚአብሔር ያነበረህ ቅናት ደግሞ እንደቀነሰ ተረድተሃል፡፡ በቅድሚያ ወደዚህ መረዳት መምጣትህ ትልቁ ነገር ነው፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ዛሬም እንዳልተወህ የምህረት እጁ ላንተ እንደተዘረጋች ልብ ልትል ይገባል፡፡ ወንድሜ እግዚአብሔር ባለ ብዙ ምህረት አምላክ ነው፡፡ አሰቀድሞም በራስ አልቆምክም ሁላችንም በእግዚአብሔር ምህረትና ፀጋ ነው የቆምነው፡፡ በመሆኑም ፈጥነህ እውነተኛ ንሰሀ ገብተህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ በፀጋውም እንዲያበረታህና እንዲያፀናህ ለምን፡፡ የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ከአንተ ጋር ይሁን አሜን፡፡