ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ሰዎች መጽሃፍ ቅዱስን ለምን ያጣምማሉ?

አስባችሁ እንድትመልሱ አደራ እላችሁዋለሁ!
Jan 24, 2014 መንፈሳዊ 1234 (160 ነጥቦች) የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ሰይጣን ውሸት ሲስፋፋ ይከብራል። ይህንንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር መረዳት ይቻላል፡
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 8፡44 "እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።"

በመሆኑም ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ (በአጉል ቅንዓት) የአባታቸውን ምኞት ይፈጽማሉ። በኢየሱስ ዘመን የነበሩት አይሁድም እንዲሁ ነበሩ። "በ[እውነት ]እውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር" ከፍተኛ አጉል ቅንዓት ነበራቸው። (ሮሜ 10፡2)

ሰዎች በሰይጣን ስለተሳሳቱ ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጣምሙት፤ ራሳቸውም ለመጣመም ዝግጁ ስለሆኑ ጭምር እንጂ። ለዚህ አይደል ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ፡
Quote:
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡3 "ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ (መስማት የሚያስደስታቸው) ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።"
ያለው!

በሌላም ቦታ ጳውሎስ ሰዎች እግዚአብሔርን ለማወቅ አልወደዱም ብሎ በግልጽ ጽፏል።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡28 "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤"

ለዚ አይደለም ሰዎች በዚህ ድረገጽ ላይ እንኳ ስንት ውሸት ለማስተላለፍ የሚታገሉት!? ለምሳሌ በ1ኛ ቆሮንቶስ 15፡28 ላይ ላለው ግልጽ ጥቅስ "ሞት" የሚል ቃል ለማስገባት ሲሟሟቱ ሳይ በጣም ይገርመኛል። ሰይጣን አዳምንና ሄዋንን በሀሰት ወሬ ከገነት ለማስወጣት እንደተሳካለት ሁሉ "ሥላሴ" በሚለው የስህተት ትምህርቱ ዓለምን አስቷል። (1ኛ ዮሐንስ 5፡19) በመሆኑም ሥላሴ የዓለም ቋንቋ ሆኗል፣ (ፕሮቴስታንቱ፣ ካቶሊኩ፣ ኦርቶዶክሱ፣ ሂንዱው . . . አረ ማንም አልቀረ!፣ ሁሉም ተይዟል)

በመሆኑም ሰው ያለውን ቢል፣ ዓለም ሁሉ ውሸተኛ ቢሆን፣ "እግዚአብሔር እውነተኛ እንዲሆን" የበኩልህን ትወጣለህ? (ሮሜ 3፡4) ጥያቀው ይህ ነው
Mar 7, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...