ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 14 June 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የክርስቶስ ኢየሱስ ልደቱ (ገና)ታህሳስ 29 እንደሆነ መጻፍ ቅዱስ ሚነግረን ነገር አለ ወይ?

Feb 21, 2014 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ሰው መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ መልስ እንዲሰጥህ አትጠብቅ ራስህ አንብብና ተረዳው።
አንተም ማንበብ ስለምትችል ማለት ነው።
Mar 3, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
እስቲ የሚከተሉትን ገጾች አንብብ።

http://www.gty.org/resources/questions/QA68/why-do-we-celebrate-christmas-on-december-25

http://www.biblicalarchaeology.org/daily/biblical-topics/new-testament/how-december-25-became-christmas/

http://en.wikipedia.org/wiki/Christmas

http://www.whychristmas.com/customs/25th.shtml

እነዚህ ድረገጾች እንደሚያወሱት የአራተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን "ክርስቲያኖች" የገና በዓል (የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት) በዲሴምበር 25፣ ወይም በታህሳስ 29 እንዲከበር ያደረጉት በተጨበጠ መረጃ ላይ ተመርኩዘው አልነበረም። ይልቁንም የአረማዊውን ዓለም ሰዎች ሰደ ክርስትና ለማማለልና እነርሱ ከለመዱት በዓልና ባህል ሳይወጡ ክርስትናን መቀበል እንዲችሉ ለማድረግ ነበር። ይህ የጥላቻ ትችት አይደለም። አብዛኞቹ ሰዎች "የትም ፊጪው ዱቄቱን አምጪው" እንደሚባለው የአገራችን አባባል (http://www.whychristmas.com/customs/25th.shtml) የተባለው ድረገጽ እንደደመደመው በምናገባኝ ስሜት መጓዝን ይመርጣሉ።

ኢየሱስ ክርስቶስ "ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት" በማለት ስለሞቱ ተናገረ እንጂ ልደቴን ታስባላችሁ አለማለቱ ለኔ ትልቅ ትርጉም አለው። (የሉቃስ ወንጌል 22፡19 "እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።") ከዚያ በፊት እግዚአብሔር የእስራኤል ህዝብ እንዲያከብር የሚፈልገውን በዓል ትክክለኛ ቀን እንደጠቀሰ እናነባለን። (ዘጸዓት 12፡18፤ ዘሌዋውያን 23፡6፤ ኢያሱ 5፡10፤ ዘዳግም 16፡16፣ ዘሌዋውያን 23፡34)

ሦስቱ የእስራኤላውያን በዓላት፡ (1) የቂጣ /የፋሲካ በዓል (አቢብ ወር 14ኛ ቀን)(2) የሰባቱ ሱባኤ / በዓለ-ሃምሳ (ከአቢብ 14 ሃምሳ ቀን አልፎ የሚከበር)(3) የዳስ በዓል (በሰባተኛው ወር ከ15ኛው ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀን የሚከበር)

ታዲያ የልጁን ልደት እንድናከብር ቢፈልግ አይነግረንም ብለህ ታስባለህ?

ከዚህም በተጨማሪ "አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአል" (ሮሜ 15፡4) ብለው ለሚያምኑ ክርስቲያኖች በዘፍጥረት 40 እና በማቴዎስ 14 ላይ የተጠቀሱት ልደቶችና አብረዋቸው የተደረጉት ነገሮች ምን ያስተምሩናል ብለው ያስባሉ? መልሱን ለአንባቢው መተው ነው የሚሻለው።
Mar 7, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...