ይህ ጥያቄ እጅግ በጣም ተገቢ ጥያቄ ነው።
እዚህ ጋር ሁለት ነገር እናያለን።
መጽሐፉን የሙጥኝ ብሎ በመገኘትና ቤተክርስቲያን በዘመናት መካከል በፈለሰፈቻቸው ነገሮች ላይ እምነት መጣል።
እውነት ለመናገር ሥላሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም። በአራተኛው መቶ ክፍለዘመን በግሪካውያን ፍልስፍና የተማረኩ የቤተክርስቲያን "አባቶች" የመጽሐፍ ቅዱስን ግልጽ አባባሎች ከዚህ ፍልስፍና ጋር አቆራኝተው ሥላሴን ፈጠሩ። በሥላሴ ትምህርት ባልተቃኘ አእምሮና ንጹህ ልብ ሲነበቡ ግልጽ የሚሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሥላሴን ከደሙ ጋር ላዋሃደው ለዚህ ህዝብ ለሥላሴ ማስረጃ ሁነው ክርክር ሲነሳባቸው በጣም ያሳዝናል። እንደውም እንደውም ሰይጣን አዳምንና ሄዋንን አሳስቶ የዘላለም ህይወት ከማሳጣቱ ይልቅ የክርስትናን እምነት ገና ከጨቅላነቱ እንዲህ በፍልስፍና በማጨማለቁ ይበልጥ ተሳክቶለታል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የተናገረው ይህንን ነበር፡
Quote:
ማቴዎስ 13፡ 37 - 41፡ "እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥"
ጳውሎስም ስለዚህ ሲናገር፡
Quote:
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡8 "እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።"
ዛሬ ግን እውነቱን ፍልስፍና፣ ፍልስፍናን እውነት አድርጎ የሚወስድ ትውልድ ላይ ነው የደረስነው። ለሰይጣን ከዚህ በላይ ስኬት ይመጣል ብዬ አላስብም።
ወንድሜ፣ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ነው የሚለውን የሥላሴ ትምህርት ከተቀበልህ "ኢየሱስ ያማልዳል" ብለህ መቀበል አይኖርብህም። ምክንያቱም ካማለደ፣ እግዚአብሔሩም ራሱ ከሆነ፣ ከማን ጋር ነው ሚያማልደን
?
መጽሐፍ ቅዱስ በሚነግረን፦
Quote:
"በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው" (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5)፤
Quote:
"የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" (ሮሜ 8፡34)
Quote:
በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ" (ዕብራውያን 6፡20)
በነዚህና እነዚህን በመሳሰሉ ጥቅሶች ላይ
(ባጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ በሚነግረን እውነት ላይ
) እምነት ካለን ከሰይጣን ተቃራኒ ጎራ በመሰለፍ ሁሉ በሁሉ የሚሆነውን የመጨረሻውን ባለስልጣን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ እናደርጋለን። እርሱ ላስቀመጠው ታላቅ ንጉስም እንገዛለን ታላቅ አክብሮትም እንሰጣለን።
እግዚአብሔርም አለ፦ "እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።"
(መዝሙር 2፡6
) አዎን የተሾመው ንጉስ ሁሉን ይገዛል። "ተግሳጹን ተቀበሉ [ወይም በዕብራይስጥ እንደተጻፈው "ልጁን ሳሙት"] ጌታ እንዳይቆጣ"
(መዝሙር 2፡12
)
እናስ ማንኛው ይሻላል
? ፍልስፍናን ተቀብሎ መጽሐፉን መሻር
? ወይስ መጽሐፉን ተቀብሎ የፍልስፍና ትምህርቶችን መካድ
?