ስለ ስላሴ
ኦሪት ዘፍጥረት 1
1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1
26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። 27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
በመልካችን እንደ ምሳሌአችን በማለት በብዙ ቁጥር ተገልጸል ስለዚህ እግዚአብሔር ከአንድ በላይ ገጸ እንዳለዉ እንረዳለን ነገር ግን አንድ መሆኑን ለመግለጸ ደግሞ እግዚአብሔርም አለ; አለ አንጂ እግዚአብሔርም አሉ አላለም፤
ትንቢተ ኢሳይያስ 6፥
3 አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
ሶስትነትን የሚያሳይ የመላክት ምስጋና ነዉ፤፤
ማቴዎስ ወንጌል 28
19 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤
24 ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
ከእግዚአብሔር ጋር ማን ነበረ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ሲፈጥር ማንም አልነበረም ብቻዉን ነዉ፤፤
እየሱስ ክርስቶስ ፈጠረን ከባህሪ አባቱ ከአብ ከባህሪ ሀይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
ትንቢተ ኢሳይያስ 45
7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
የዮሐንስ ወንጌል 1
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
ቆላስይስ ሰዎች 1
እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።
ትንቢተ ሚልክያስ 2
10 ሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?
ሁላችን አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው ፤፤አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?አዎ እግዚአብሔር ፈጠረን ፤፤ስለዚህ እግዚአብሔር ስንል አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ነዉ፤፤ ማለት ነዉ
እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነዉ፤፤
ሮሜ ሰዎች 9
5 እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።
ዮሐንስ ወንጌል 20
28 ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት
ትንቢተ ኢሳይያስ 9
6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3
16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
እግዚአብሔርን ማን ይመሰለዋል ከራሱ ከእግዚአብሔርን በቀር የእየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን መምሰል እግዚአብሔርነቱ ብቻ ነዉ፤፤
ዮሐንስ ወንጌል 14
9 ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። 9 ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን?
እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?
በብዙ ቦታዋች የተገለጸው እግዚአብሔር አምላክህ አንድ መሆኑን ሌላ አምላክ አለመኖሩን ብቻ ነዉ፤፤
ኦሪት ዘጸአት 20
2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
ኦሪት ዘዳግም 6
4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 43
10 ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 44
6 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። 7፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።
እየሱስ ክርስቶስም አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው ነዉ፤፤
የዮሐንስ ራእይ 22
13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 3
30 እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8
4እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
የያዕቆብ መልእክት 2
19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
መዝሙረ ዳዊት 136
እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና
እግዚአብሔር እየሱስ ክርስቶስ ጌታ ብቻ አይደለም የጌታዎች ጌታ ነዉ፤፤
እግዚአብሔር እየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ብቻ አይደለም የነገሥታት ንጉሥ ነዉ፤፤
የዮሐንስ ራእይ 19
16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት። የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።
የዮሐንስ ራእይ 17
14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
በብዙ ቦታዎች አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በግሪክ ቋንቋ እንዲህ አይልም ለተባለዉ ብዙዎች ግርኮች ስላሴን የተቀበሉ መሆናቸዉ ግልጸ ነው፤ ቅዱስ መጸሀፉም የሚመሰክረው ይህንኑ ነው፤፤