ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 29 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እየሱስ ክርስቶስ ጊታ፣አምላክ፣ፈጣሪ፣እግዚአብህር ነው አማላጅ ግን አይደለም።

Mar 25, 2014 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

12 መልሶች

0 ድምጾች
ስለ ስላሴ
ኦሪት ዘፍጥረት 1
1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1
26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። 27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
በመልካችን እንደ ምሳሌአችን በማለት በብዙ ቁጥር ተገልጸል ስለዚህ እግዚአብሔር ከአንድ በላይ ገጸ እንዳለዉ እንረዳለን ነገር ግን አንድ መሆኑን ለመግለጸ ደግሞ እግዚአብሔርም አለ; አለ አንጂ እግዚአብሔርም አሉ አላለም፤
ትንቢተ ኢሳይያስ 6፥
3 አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
ሶስትነትን የሚያሳይ የመላክት ምስጋና ነዉ፤፤
ማቴዎስ ወንጌል 28
19 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤
24 ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
ከእግዚአብሔር ጋር ማን ነበረ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ሲፈጥር ማንም አልነበረም ብቻዉን ነዉ፤፤
እየሱስ ክርስቶስ ፈጠረን ከባህሪ አባቱ ከአብ ከባህሪ ሀይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
ትንቢተ ኢሳይያስ 45
7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
የዮሐንስ ወንጌል 1
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

ቆላስይስ ሰዎች 1
እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።
ትንቢተ ሚልክያስ 2
10 ሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?

ሁላችን አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው ፤፤አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?አዎ እግዚአብሔር ፈጠረን ፤፤ስለዚህ እግዚአብሔር ስንል አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ነዉ፤፤ ማለት ነዉእየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነዉ፤፤
ሮሜ ሰዎች 9
5 እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።
ዮሐንስ ወንጌል 20
28 ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት
ትንቢተ ኢሳይያስ 9
6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።


1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3
16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
እግዚአብሔርን ማን ይመሰለዋል ከራሱ ከእግዚአብሔርን በቀር የእየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን መምሰል እግዚአብሔርነቱ ብቻ ነዉ፤፤
ዮሐንስ ወንጌል 14
9 ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። 9 ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን?
እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?

በብዙ ቦታዋች የተገለጸው እግዚአብሔር አምላክህ አንድ መሆኑን ሌላ አምላክ አለመኖሩን ብቻ ነዉ፤፤
ኦሪት ዘጸአት 20
2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
ኦሪት ዘዳግም 6
4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 43
10 ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 44
6 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። 7፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።
እየሱስ ክርስቶስም አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው ነዉ፤፤
የዮሐንስ ራእይ 22
13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 3
30 እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8
4እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
የያዕቆብ መልእክት 2
19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
መዝሙረ ዳዊት 136
እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና

እግዚአብሔር እየሱስ ክርስቶስ ጌታ ብቻ አይደለም የጌታዎች ጌታ ነዉ፤፤
እግዚአብሔር እየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ብቻ አይደለም የነገሥታት ንጉሥ ነዉ፤፤
የዮሐንስ ራእይ 19
16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት። የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።
የዮሐንስ ራእይ 17
14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።

በብዙ ቦታዎች አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በግሪክ ቋንቋ እንዲህ አይልም ለተባለዉ ብዙዎች ግርኮች ስላሴን የተቀበሉ መሆናቸዉ ግልጸ ነው፤ ቅዱስ መጸሀፉም የሚመሰክረው ይህንኑ ነው፤፤
May 8, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
ወዳጄ

እኔ የምልህ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የግሪክኛ ቋንቋ የተባለውን ነው። የማወራልህ ስለ ግሪኮች ወይም ስለ ግሪክ ፍልስፍና አይደለም። የክርስትና ሥላሴ ሳይመሰረት ከ800 ዓመታት በፊት የኖረው ፕላቶ ስለ ግሪክ አማልክት የባህርይ ሥላሴነት ሲያስተምር የነበረ ሰው ነበር።

ከክርስትና በፊት የነበረው የግብጽ እምነትም "ኦሲሪስ"፣ "አይሲስ" እና "ሆረስ" በሚባሉ የሶስት አማልክት ጥምረት ላይ የተመሰረተ ነበር።

እንደውም የግሪክ ፍልስፍና የክህደቱ ምንጭ ነው። አንተም እንዳልከው የሥላሴ አማኞች ናቸው። እኔ ይህ አይገደኝም!።

ስላነሳሃቸው ጥቅሶች እንነጋገር ይልቅ።

ዘፍጥረት 1፡26፡ "በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ"
- እንዴት እንደተገናኘልህ አይገባኝም። "አበበ እንሂድና ምሳ እንብላ አለ" ለሚለው ምን መልስ ትሰጣለህ? አበበ "እንሂድ" ስላለ ብዙ ነው "አለ" ስለተባለ አንድ ነው፣ ስለዚህ አንድም ሦስትም ነው! ስታስበው ያስኬዳል?

ኢሳይያስ 6፡3 ላይ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ" ይሉ ነበር ኪሩቤል። ይህን ጥቅስ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ "አባቶች" ሲጠቀሙበት እንደነበር ይታወቃል። ቅዱስ የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ ስለተጠቀሰ ሥላሴን ነው የሚያመለክተው ካልን፣

በሕዝቅኤል 21፡27 ላይ "ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደርጋታለሁ" የሚለውን የትኛውን ሥላሴ ያመለክት ይሆን?

በኢሳይያስ 21፡9 ላይ "ባቢሎን ወደቀች ወደቀች" የሚለውስ ባቢሎን በሁለት የተጣመረች አማልክት ነገር ትሆን? (ራእይ 14፡8 እና 18፡2ን ጨምርበት)

እንደው ባጠቃላይ የባቢሎንን አወዳደቅ ለማጉላት አይመስልህም? የእግዚአብሔር አምላካችንን እጅግ የከበረ ቅድስና ለማጉላት "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ" ቢባል ይበዛበት ይሆን? አየህ ለእኔ በሥላሴ ትምህርት ባልተቃኘ ጭንቅላት ሳነበው የሚሰጠኝ መልእክት እንዲህ ግልጽ ያለ ከየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ጋር የማይጋጭ ነው።

ኢሳይያስ 45፡7 ላይ ". . . እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ" ይላል።
ዮሐንስ 1፡3፡ "ሁሉ በእርሱ [በክርስቶስ] ሆነ" ይላል። በመሆኑም ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ብለህ የደመደምኸው አያስኬድም። ምክንያቱም እነዚህ ጥቅሶች ላይ አንድ ሌላ ብንጨምር ነገሩ ግልጽ ይሆናል።

ዕብራውያን 1፡1-3 ላይ ጳውሎስ "እግዚአብሔር . . . ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ" በማለት በፍጥረት ወቅት እግዚአብሔር ዓለማትን ለመፍጠር በልጁ እንደተጠቀመ ነግሮናል።

ዮሐንስም በወንጌሉ ም. 1፡3 ላይ (እንደ ግሪክኛው ትክክለኛ አገላለጽ) "ሁሉ በእርሱ በኩል ሆነ" ይለናል። ዮሐንስ ሲጽፍ እዚህ ላይ "ዲያ" የሚል የግሪክኛ ቃል ተጠቅሟል። ቀጥተኛ ትርጉሙም "በኩል" [በእንግሊዝኛ THROUGH] ማለት ነው። ይህንኑ ቃል ተጠቅሞ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 8፡5-6 ላይ እኛ ሁላችን "በክርስቶስ በኩል" መገኘታችንን ገልጿል።

ስለዚህ ሁሉን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፣ የፈጠረው ግን በልጁ በኩል ነው ብንል የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ሁሉ አሜን ብለው ይቀበሉናል።

(ሮሜ 9፡5፤ ዮሐንስ 20፡28፤ ኢሳይያስ 9፡6) ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ይናገራሉ፣ አዎን ኢየሱስ አምላክ ነው፣ ጥያቄ የለውም። እግዚአብሔርም አምላክ ስለተባለ እንግዲያው ሁለት አምላክ ሊኖር ነው፤ ነገር ግን ያለው አንድ አምላክ ነው ብለህ ላነሳኸው ነጥብ ግልጽ እንዲሆንልን አንድ ጥቅስ እንጨምርበት፡

ቆላስይስ 1፡15 "እርሱ [ክርስቶስ] የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው" (የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅ ነው - ዕብራውያን 1፡3) እንግዲህ ምን እንላለን?

አዎን እውነተኛው አምላክ አንድ ነው፤ አማልክት የሚባሉ ምንም ቢኖሩ፣ ወይ የሐሰት አማልክት ናቸው፣ አሊያም የእውነተኛው አምላክ ነጸብራቅ ናቸው። (1ቆሮንቶስ 8፡4-6) ሙሴ "አምላክ" / "በእግዚአብሔር ፋንታ" ሆነ ተብሏል። (ዘጸአት 4፡16 እና 7፡1) መላእክትም "አማልክት" እንደሆኑ ተጠቅሷል። (መዝሙር 8፡5 በዕብራይስጥ "ከአማልክት ይልቅ" ይላል)

ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አባቱን "ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ" በማለት ነገሩን ይበልጥ ግልጽ አድርጎልናል።


ሌላው 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 ላይ ያለውን "እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር" የሚለውን ጠቅሰሃል። መምሰልና መሆን ይለያያል ወዳጄ። አይደለም ክርስቶስ ኢየሱስ እኛም እግዚአብሔርን እንድንመስል ታዘናል። (እዛው 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1-2፤ 5፡4፤ 6፡4-6፤ 6፡11 እና 2ኛ ጴጥሮስ 1፡6 ላይ ማየት ይቻላል)። እግዚአብሔርን መምሰል ማለት ለአምላክ ያደሩ መሆን ማለት ነው፣ ለእርሱ መሰ'ጠት ማለት ነው።


ሌላው ዮሐንስ 14፡9 ላይ ያለውን "እኔን ያየ አብን አይቶአል" እንደ ማስረጃ ጠቅሰሃል። ምን እያለን ነው ኢየሱስ? እኔ አብ ነኝ እያለን ነው? ወይስ ቁጥር 11 ላይ "እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ" እንዳለው እርሱ የሰራው አብ "ሥራ" ብሎ የላከውን ተግባር ማከናወኑን አይተው ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ? ነጥቡ ግልጽ ነው።

ለዛሬ እዚህ ላይ ይብቃን


አመሰግናለሁ።
0 ድምጾች
ስለ ስላሴ ከተረዱ ሌላው ቁልፉ ነገር

ክርስቶስ ሰዉ መሆን ሚስጥር ነው

ኦሪት ዘፍጥረት 2
7እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
15 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።
17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።
18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።
20 እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት ወደ አዳምም አመጣት።
ኦሪት ዘፍጥረት 3
6ከፍሬውም ወሰደችና በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እና ሰዉ ተጣሎ እግዚአብሔርም ቸር ስለሆነ በዳይን አዳምን
ይቅር ለማለት ወሰነ ለዚሀ ደግሞ መታረቂያ ንጸህ መስዋአት አስፈለገ በደሎም ግዙፍ ስለሆነ የፍጠራን ሰውና እንስሳ ደም በቂ አልነበረም እግዚአብሔር መሀረ ስለሆነ ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በአንድ ልጁ ስጋ ለብሶ እንዲሰዋ ወሰነ፤፤
ኦሪት ዘፍጥረት 3
15በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።
ባለው መሰረት በዳይም ተበዳይም ልጅ ልጃቸውን አዋጥተው የአምላክም ልጅ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤እግዚአብሔር ወልድ፤አማኑአል በመባል ስጋ ለበሰ፤፤ስጋና መለኮት ተዋሀደ ሰው ሆነ፤የሰው ልጅ ጠላትን ሰይጠንን ድል ነስቶ ከዳቢሎስ ባርነት ነጻ አወጠን ከሶስቱ አካላት አንዱ በተለይ አካሉ እግዚአብሔር ወልድ ስጋ ለብሶ ፤ተሰቃይቶ ፤ተገርፎ፤ተሰቅሎ፤ አለምን አዳነ፤፤በመስቀል ላይ ከአባቱ ከአብ ከራሱ ጋርና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን፤፤
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5
18ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ 19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በመለከቱ የአብ ልጅ በስጋው የማርም ልጅ ይባላል፤፤
ኢየሱስ ክርስቶስ በመለከቱ አምላክ፤ አምላከ አምላክት ነው፤፤
ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው ንጉሰ ነገስት፤ሊቀ ካህናት፤ነው፤፤

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በመሆኑ በትንሽ ትንሹ አድጎል፤ እንደ እጻን አድጎል፤ተርቦል፤ተጠምቶል፤ምራቅ ደም ወቶታል ሙቶል----
ኢየሱስ ክርስቶስ በመለከቱ በድንግልና ተወልዶል፤በተዘጋ ቤት ገብቶል፤በባህር ላይ ሄዶል፤ሙታንን አስነስቶል፤ከሞት ተነስቶል፤፤ወዘተ
ስለዚህ ሰውም አምላክም የሆነ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በተለይ በአዲስ ኪዳን የተነገሩትን ቃላት ፤ምንባብ ፤አርፍተ ነገር ስናነብ የመራብን፤መጠማትን፤መየጠቅን፤መድከምን፤መጸምን፤መጸለይን፤ማማለድን፤የመሳሰሉትን የኢየሱስ ክርስቶስ የስጋ የማርያም ልጅ ባህሪ ናቸው፤፤
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮት ባህረ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን፤ቃልነቱ፤ከአብ ጋር አንድ መሆን፤መንፈስ ቅዱስን መላኩ፤የጌታዎች ጊታ መሆኑ፤የሚሰገድለት መሆኑ፤ጸሎት ተቀባይ መሆኑ፤ሀጥአትን ይቅር ባይ መሆኑ ወዘተ ናቸው፤፤ታዲያ በሁለት ባህሪ በተዋህዶ አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንላለዋለን፤፤
ዮሐንስ ወንጌል 9
6ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና። 7 ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።
ስለዚህ መጸሀፍ ቅዱስ አንባቢ ክርስቲይን ማስተዋል ይህንን ነው እንጂ አንድ ጥቅስ ይዞ ፍጠር ነው፤አማላጅ ነው፤የተቀባ፤አንድ ገጸ፤ነብይ፤አብ ይበልጣል ወዘተ ትክክል አይደለም፤፤በማቲ 7 የተገለጸውን ማስተዋል ነው፤፤
20በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። 22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። 23 የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
ስለዚህ ይሁዳ መልእክት 1
3 ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
ይቆየን
May 10, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...