ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ሰላም ለናንተ. ስለ ልሳን ብታብራሩልን፣ በአሁን ግዚስ አለ?

ሰላም ለናንተ. ስለ ልሳን ብታብራሩልን፣ በአሁን ግዚስ አለ?
Mar 28, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
This is definitely right

2 መልሶች

+1 ድምጽ
በቅድሚያ የልሳን ስጦታ በአሁኑም ዘመን እንዳለና አማኖች እንደሚቀበሉት መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እወዳለሁ። እኔም ይህ ስጦታ ከተሰጣቸው ሰዎች አንዱ ነኝና ማንም የለም ቆማዋል በአሁኑ ዘመን አይሠራም ቢል ፈጽሞ ውሸት እንደሆነ ላረጋግጥ እወዳለሁ።

ልሳን ተብሎ በአማርኛ የተተረጎመው የግሪኩ ቃል glossa ነው። ትርጉሙም ምላስ፣ ቋንቋ ወይም ልሳን ማለት ነው።

በልሳን መናገር በአዲስ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታዎች ተበለው ከሚጠሩትና መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች እንደ ወደደ ከሚሰጣቸው ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ነው።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12
4 የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤
5 አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤
6 አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
7 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።
8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥
9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥
10 ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
11 ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።

ከላይ ባለው ክፍል እንደምንመለከተው በልሳን መናገር ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ የጸጋ ስጦታ ነው። የጸጋ ስጦታ ወይም በግሪኩ charisma ማለት ደግሞ አንድ አማኝ ያንን ስጦታ ለማግኘት ምንም አስተዋጽኦ ሳያደርግ እግዚአብሔር እንዲያው በጸጋው በነጻ የሚያድለው ስጦታ ማለት ነው። ስለዚህ ስጦታው የሰጪውን ቸርነት እንጂ የተቀባዩን የተለየ ቅድስና ወይም ማንነት አይገልጽም።

እነዚህ የጸጋ ስጦታዎች አንድ ሰው በተፈጥሮ ሊኖረው ከሚችለው ችሎታ ወይም ተሰጥዎ (talent) ወይም በልልምድ ሊማረውና ሊያገኘው ከሚችለው ችሎታ ውጪ፤ መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች የሚያድላቸው መለኮታዊ ችሎታዎች ናቸው። ስለዚህ እነዚህን ስጦታዎች ለማግኘት አንድ አማኝ ብዙ ዓመታት በክርስትና መቆየት ወዘተ አያስፈልገውም። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙና ጌታው ከተቀበለበትና እርሱን መከተል ከጀመረበት ቀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንዲያው ሊሰጠው የሚችለው ስጦታዎች ናቸው።

ከላይ የተዘረዘሩት የጸጋ ስጦታዎች ሁሉ በብሉይ ኪዳን በነብያት ላይ ሲገለጡ የታዩ ናቸው። ልሳንን መናገርና መተርጎም ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ኪዳን ብቻ የታየ አዲስ የጸጋ ስጦታ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜም በማርቆስ ወንጌል ኢየሱስ ራሱ ነው በእርሱ ባመኑ ሰዎች ላይ ሊታዩ ከሚችሉ ምልክቶች አንዱ እንደሆነ የጠቀሰው፦
Quote:
የማርቆስ ወንጌል 16
17 ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ ...

ለመጀመሪያ ጊዜ አማኞች ልሳን የተናገሩት፤ ኢየሱስ ካረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲወርድና 120 የሚሆኑ የክርስቶስ ሐዋርያትና ደቀመዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሞሉ ወቅት ነው።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 2
1 በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
2 ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር
5 ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤
6 ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።
7 ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?
8 እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?

ከዚያ በኋላ የመጀመሪያው አይሁዳዊ ያልሆነ አሕዛብ ቆርኔሌዎስና ቤተሰቦቹ የጴጥሮስን ስብከት ሲሰሙ መንፈስ ቅዱስ በወረደባቸው ጊዜ በልሳኖች ተናግረዋል።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 10
45 ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤
46 በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና።

በመጨረሻም ሐዋርያው ጳውሎስ የመጥምቁ ዮሐንስን ደቀመዛሙርት አግኝቶ ስለ ክርስቶስ ከሰበከላቸው በኋላ እጁን ጭኖ ሲጸልይላቸውና መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ በልሳን እንደተናገሩ በሐዋርያት ሥራ እናነብባለን።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 19
4 ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው።
5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
6 ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው በልሳኖችም ተናገሩ፥ ትንቢትም ተናገሩ።

1ኛ ቆሮንቶስ ምእራፍ 14 ላይ ብዙ ስለ ልሳን ስጦታና እንዴት በጉባዬ መጠቀም እንደሚገባ ተጽፎአል። በዚሁ ክፍል ሁለት አይነት ልሳኖች እንዳሉ ተጠቅሷል። አንደኛው የሚተረጎምና ጉባዬውን ለማነጽ የሚረዳ ማለትም ተናጋሪውን ሳይሆን ሰሚዎችን የሚያንጽና የሚጠቅም ልሳን ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ተናጋሪውን ብቻ የሚያንጽና የሚጠቅም ልሳን ነው።

በበዓለ ሃምሳ ሃዋሪያቱና ደቀመዛሙርቱ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በፈሰሰ ጊዜ የተናገሩዋቸው ልሳናት ተናጋሪው ምንም ባይገባውም ሰሚዎችን ግን ሊያንጹ የሚችሉ፤ ሰሚዎቹ ሊገባቸው የሚችሉ ቋንቋዎች ነበሩ።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤
3 ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል።
4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።
...
14 በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
...
27 በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤
28 የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር።

ከላይ በተጠቀሱት ክፍሎች እንደምንመለከተው ራስን ለማነጽ የሚሰጠው ልሳን ተናጋሪው የሚናገረውን እርሱን ጨምሮ ማናም አያስተውለውም፤ ለእግዚብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና ይላል። ይህ የራስን መንፈስ ለማነጽ ወይም ለመገንባት የሚሰጥ የጸጋ ስጦታ ነው። ከላይ በቁጥር 14 ላይ "በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው" ይላል። ማለትም በልሳን ስጸልይ የምጸልየውን አዕምሮዬ ስለማይገባው፤ አእምሮዬ አይታነጽበትም ወይም አይጠቀምበትም፤ ነገር ግን መንፈሴ ይታነጻል። ከላይ በቁጥር 2 እንደተጠቀሰው ተናጋሪው "በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል"ና።

በአዲስ ኪዳን የተሰጡት የጸጋ ስጦታዎች በሙሉ ራስን ሳይሆን ሌሎችን ለመጥቀም የተሰጡ ናቸው። በልሳን መናገር ግን የራስን መንፈስ ለማነጽ የተሰጠ ለግል መንፈሳዊ ሕይወት እጅግ ጠቃሚ ስጦታ ነው። በእርግጠኝነት ለመናገር ቢያንስ ቢያንስ 98 በመቶ የሚሆኑ ይህ ስጦታ ያላቸው አማኖች ፈጽሞ ችላ ያሉትና የማይጠቀሙበት ስጦታ የልሳን ስጦታ ነው ብል ማጋነን አይመስለኝም።

ጌታ ይመስገንና ራሴን በዚህ ስጦታ ለማነጽ ጌታ እድሉን ከሰጣቸው ውስጥ ስለሆንኩ፤ ምን ያህል እጅግ እጅግ ጠቃሚ ስጦታ እንደሆነ ከሕይወቴ አውቀዋለሁ። መንፈስን ከሚጎትቱና ከሚያዳክሙ፤ መንፈሳዊ እንቅልፍ ውስጥ ከሚጥሉና የመንፈስን እሳት ከሚያጠፉ ማናቸውም ሁኔታዎች እሳት እንደሚያነድድ መንፈስን በመንፈስ ቅዱስ እሳት የሚያቀጣጥልና ከፍ ወዳለ የምስጋና ስፍራ በመንፈስ የሚያስቀምጥ እጅግ እጅግ ጠቃሚ ስጦታ ነው።

ምንም እንኳን ይህ ስጦታ የተሰጠው ለግል አማኞች ራሳቸውን እንዲያንጹበት ቢሆንም፤ በአብዛኞቹ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው ውጪና ፈጽሞ ላልታሰበበት ዓላማ ማለትም በጉባዬ ብቻ ትንሽ ትንሽ ሲጠቀሙበት ነው የሚታየው። ከላይ በቁጥር 28 እንደምንናብበው የማይተረጎመውና ራስን ለማነጽ የሚሰጠው ልሳን ያለው ሰው፤ በጉባኤ ሌሎችን ስለማያንጽ ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር ነው የሚለው።

እኔ ይህ ስጦታ ያላቸውን አጥብቄ መምከር የምፈልገው፤ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ነው። ቢቻላቸውስ ሰዎች በቀን በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ያህል በዚህ የጸጋ ስጦታ ተጠቅመው ራሳቸውን ቢያንጹ እስከ ዛሬ ካዩትና ከተለማመዱት ክርስትና እጅግ የተለየ በመንፈስ ቅዱስ እለት ዕለት የሚሞላ ሕይወት መለማመድ ይችላሉ።

ከልሳን ስጦታ ጋር አብሮ ልሳንን የመተርጎም ስጦታ አለ። ለጉባኤው መልእክት በልሳን መጥቶ እንደሆነ ተናጋሪው ወይም በጉባኤው ውስጥ ይህ የመተርጎም ስጦታ ያለው እንዲተረጉመው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። የሚተረጎመው ልሳንና የትርጉም ስጦታ በአንድ ላይ ተናጋሪውን ወይም ተርጓሚውን ለመጥቀም የሚሰጡ ሳይሆኑ ጉባኤውን ለማነጽ የሚሰጡ ናቸው።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
5 ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።
...
12 እንዲሁ ደግሞ እናንተ መንፈሳዊ ስጦታን በብርቱ የምትፈልጉ ከሆናችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ እንዲበዛላችሁ ፈልጉ።
13 ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።

በልሳን ለማሕበሩ የሚተላለፍ መልእክት ከተተረጎመ ልክ እንደ ትንቢት አገልግሎት ነው የሚያገለግለው።

ሆኖም ልሳን በአብዛኛው የተሰጠው ራስን ለማነጽና ጌታ ከላይ በማርቆስ ወንጌል እንዳለው ላላመኑ ምልክትነት ነው።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
21 ሌሎችን ልሳኖች በሚናገሩ ሰዎችና በሌላ አንደበት ለዚህ ሕዝብ እነግራቸዋለሁ፥ እንዲህም ቢሆን አይሰሙኝም ይላል ጌታ ተብሎ በሕግ ተጽፎአል።
22 እንግዲያስ በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው እንጂ ለሚያምኑ አይደለም፥ ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ አይደለም።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤

ልሳን ራስን እንጂ ሌሎች አማኞችን ለማነጽ የተሰጠ ስላይደለና ልሳንና ትርጉም ሲደመር ደግሞ ራሱ እንደ ትንቢት ስለሆነ ብዙ ጊዜ በጉባኤ ልሳን አማኞችን ለማነጽ ጥቅም ላይ አይውልም። ልሳን በመሰረቱ ሌሎችን ሳይሆን ራስን ለማነጽና ለማያምኑ ደግሞ እንደ ምልክት ብቻ የሚያገለግል እንጂ በጉባኤ አማኞችን ማገልገያ አይደለም። ስለዚህም ነው ጳውሎስ አንደኛ አማኞች በጉባኤ ሰዎችን ለማነጽ የትንቢትን ስጦታ በብርቱ እንዲፈልጉ የሚመክረውና እርሱም ራሱ ምንም እንኳን በብዙ ልሳኖች ቢናገርም በጉባኤ ግን በልሳን የማይናገረው።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
1 ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ
...
5 ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።
...
14 በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
15 እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።
16 እንዲያማ ካልሆነ፥ አንተ በመንፈስ ብትባርክ ባልተማሩት ስፍራ የተቀመጠው የምትለውን ካላወቀ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ አሜን ይላል?
17 አንተማ መልካም ታመሰግናለህ፥ ሌላው ግን አይታነጽበትም።
18 ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
19 ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።

በማኅበር ወይም በጉባኤ የሚሰራው አንድ አሠራር ብቻ ነው ይሄውም ሌላውን ማነጽ የሚል ነው። ሌሎችን የማያንጽ ምንም ነገር በጉባኤ መደረግ የለበትም። ጉባኤ ራስን ሳይሆን ሌሎች የመጥቀሚያ ማሕበር ነውና።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
26 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ምንድር ነው? በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ ሁሉ ለማነጽ ይሁን
Mar 29, 2011 በቃሉ (2,230 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 29, 2011 በቃሉ ታርሟል
በልሳን መናገር ....................
–1 ድምጽ
ሰላም ይሁንልዎ፡

ልሳን በዚህ ዘመን ካለ ግዴታ የሰዎች የመግባቢያ ቋንቋ መሆን አለበት
ከሃዋሪያት ም. 2 እንመልከት፤ -

"ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ 6 ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። 7 ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?
8 እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?
Oct 28, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ውድ እንያት ልሳን በአሁን ግዜ የሚናገር ሰው የለም። ትክክለኛ ልሳን ተናጋሪ ከሆነ መተርጎም መቻል አለበት እንጂ እራሱም ወይም ሌላው ሰው የማያውቀውን ነገር መንፈስ እያስጮሀቸው ያሉትን ሁሉ ልሳን ማለት አይቻልም ልሳን መናገር የሚችል ሰው የለም ከቻለ መተርጎም አለበት ቀጥሎ ያለውን አንብቢ
(የሐዋሪያት ሥራ 2፤11) የግሪኩ ቃል ልሳኖችን ቃል በቃል የተረጎመው “ቋንቋዎች” በማለት ነው፡፡ ስለዚህ የልሳኖች ሥጦታ አንድ ያንን ቋንቋ የሚናገረው ሌላውን ሰው ለማገልገል በማያውቀው ቋንቋ መናገር ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 እስከ 14 ምዕራፎች ጳውሎስ ድንቅ ስጦታዎችን “አሁን ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?(1ኛ ቆሮንቶስ 14፤6) እያለ ያነሳል፡፡ እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ እና በሐዋሪያት ሥራ ውስጥ ከተገለጸው ከልሳኖች ቋንቋ ጋር በሚስማማ መልኩ በልሳኖች መናገር አንድ በራሱ ወይም በራሷ ቋንቋ የእግዚአብሔርን መልዕክት በመስማት ላይ ላለ/ላለች ጠቃሚ ነው፤ ካልተተረጎመ ግን ለማንኛውም ሰው ጥቅም የለውም፡፡

ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ያለው ሰው (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤30) ምንም እንኳን በመነገር ላይ የነበረውን ቋንቋ ባያውቅም የልሳን ተናጋሪው በመናገር ላይ የነበረውን ነገር መረዳት ይችላል፡፡ ልሳን ተርጓሚው ልሳኖቹን የሚናገረውን ሰው መልዕክት ሁሉ ሰው መረዳት እንዲችል ለእያንዳንዱ ሰው ይናገራል፡፡ “ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።”(1ኛ ቆሮንቶስ 14፤13)፡፡ የማይተረጎመቱን ልሳኖች በተመለከተ የጳውሎስ ማጠቃለያ ጠንካራ ነበር፤ “ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።” (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤19)

በልሣኖች የመናገር ስጦታ ለዚህ ዘመን ነውን? ምንም እንኳን መሻሩ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13፤10 ፍጹም የሆነው ከመምጣቱ ጋር ቢገናኝም 1ኛ ቆሮንቶስ 13፤8 የልሳኖች ስጦታ መሻሩን ይጠቅሳል፡፡ አንዳንዶች የትንቢትን እና የዕውቀትን “መሻር” እና “ፍጹም” የሆነው ከመምጣቱ በፊት “የሚሻሩቱን ልሳኖች” ለልሳኖች መሻር እንደ ማስረጃ በማስመልከት የተወሰኑቱ በግሪኩ ግስ አመጣጥ ላይ ወዳለው ልዩነት ያመለክታሉ፡፡ መሆን ሲቻል እንኳን ይኸ ከምንባቡ በጣም ግልጽ አይደለም፡፡ በተጨማሪም የተወሰኑቱ በልሳኖች መናገር እየመጣ ላለው የእግዚአብሔር ፍርድ ምልክት እንደነበር ትንቢተ ኢሳይያስ 28፤11 እና ትንቢተ እዩኤል 2፤28-29 ወደ መሳሰሉት ምንባቦች እንደ ማስረጃ ያመለክታሉ፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 14፤22 ልሳኖች “ለማያምኑት ምልክት” እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በዚህ ክርክር መሠረት በልሳኖች የመናገር ስጦታ እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስን መስዕነት ባለመቀበላቸው እስራኤላውያንን ሊፈርድባቸው እንዳለ ለአህሁዶች ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ ስለዚህ በእርግጥ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በፈረደበት ጊዜ (በ70 ዓመተ ዓለም የኢየሩሳሌም በሮማውያኖች መውደም) የልሳኖች ስጦታ የታሰበለትን ዓላማ አላገለገለም ነበር፡፡ ይህ አመለካከት የሚቻል ቢሆንም የመጀመሪያው በልሳኖች የመሞላት ዓላማ የግድ መሻሩን ተፈላጊ አያደርገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በልሳኖች የመናገር ስጦታ እንደተሻረ በመደምደም አያውጅም፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ በልሳኖች የመናገር ስጦታ ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚስማማ መልኩ ይደረግ ነበር፡፡ እውነት እና ግልጽ ቋንቋ ይሆናል (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤10)፡፡ ሌላ ቋንቋ (የሐዋሪያት ሥራ 2፤6-12) ከሚናገር ሰው ጋር ለመነጋገር ዓላማ የሚጠቅም ይሆናል:: እግዚአብሔር በሐዋሪያው ጳውሎስ በኩል ከሰጠው ትዕዛዝ ጋር የሚስማማ ይሆናል፤ “በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤ የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር።” (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤27-28) በተጨማሪም በ1ኛ ቆሮንቶስ 14፤33 መሠረት ይሆናል፤ “እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።”

እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ሌላ ቋንቋ ከሚናገር ሰው ጋር መግባባት እንዲያስችለው ወይም እንዲያስችላት ለአንድ ሰው በልሳኖች የመናገርን ስጦታ ሊሰጥ ይችላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በማካፈል ሉዓላዊ ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤11)፡፡ ሚሲዮኖች ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት ካልሄዱ እና ወዲያው በራሳቸው ቋንቋ ለሰዎች መናገር ቢችሉ ምን ያህል የበለጠ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ እስኪ አስብ፡፡ ሆኖም ግን አግዚአብሔር ይህንን የሚያደርግ አይመስልም፡፡ ምንም አብዝቶ ጠቃሚ የሚሆኑ እንኳ ቢሆኑም ልሳኖች በአዲስ ኪዳን በሆነው መልኩ የሚከሰቱ አይመስልም፡፡ በልሳኖች የመናገርን ስጦታ እንተገብራለን የሚሉ ብዙኃኑ የአማኞች ክፍል ከላይ ከተጠቀሱት ከቅዱሳን መጽሐፍት ጋር በሚስማማ መልኩ ያንን አያደርጉም፡፡ እነዚህ እውነታዎች ለዛሬይቱ ቤተክርስቲያን የልሳኖች ስጦታ ተሽረዋል ወይም ቢያንስ በእግዚአብሔር ዕቅድ ብርቅ ነው ወደሚለው ድምዳሜ ይመራል፡፡ስለዚህ በአሁኑ ግዜ ወይንም ወቅት እንደምናየው ትንቢት ተናገር በማለት ያልተገባ ማንም ራሱ ተናጋሪው የማያውቀውን መናገሩ ትልቅ ስህተት ነው
ወንድሜ
በአንድ ጎኑ ያልከው ምንም እንኳን ትክክል ቢሆንም አንተ ያላየኸውና ችላ ያልከው ግን ሌላ ጎን አለው ልሳን።

እስቲ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፦
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል
3 ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል።
4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።
...
14 በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው
15 እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።

እነዚህ ከላይ ስለ ልሳን የተዘረዘሩትን አንድ በአንድ ብትመለከታቸው፤ ስለ ልሳን ሚዛናዊ የሆነ መረዳት እንዲኖርህ ይረዱሃል።

በቅድሚያ ሁለት አይነት ልሳን እንዳለ መረዳት አለብህ። አንዱ ሰውን ለማገልገል ሁለተኛው ደግሞ ራስን ለማነጽ የሚሰጥ ነው። ሰውን ለማገልገል ሰዎቹ በሚሰሙት ቋንቋ የሚነገር ወይም ደግሞ የሚተረጎም ልሳን ነው። ይህ ሌሎችን ለማገልገልና ለመጥቀም የሚሠራ ልሳን ነው። ከላይ በቁጥር 3 እንደተጻፈው ልክ እንደ ትንቢት ሌሎችን ለመምከርና ለማጽናናት የሚያገለግል ነው።

ከላይ ባሉት ክፍሎች ውስጥ ግን ሌላም አይነት ልሳን ተጠቅሷል። ይህም ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር የሚነገርና ሰው የማያስተውለው። "በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና" ይላል ቁጥር 2። ደግሞም በዛው ቁጥር "በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል" ይላል። እናም አእምሮአችን እየተረዳውና እየገባው የሚደረግ ሳይሆን በመንፈስ (እዚህ ጋ ልብ በል በአእምሮ ሳይሆን በመንፈስ) ለእግዚአብሔር ሚስጥርን የምንናገርበትና መንፈሳችን ብቻ የሚታነጽበት፤ ራስን ማነጺያ ልሳን ነው ሁለተኛው አይነት ልሳን። ከላይ ባለው ክፍል ቁጥር 3 እንዲሁም 14 እና 15ም ይሄንኑ ነው የሚያረጋግጡት። በመንፈስ በልሳን ሰው ሲጽልይ መንፈሱን ያንጻል አእምሮው ግን ምንም አይነት ነገር ስለማይገባው አይታነጽም። ሆኖም ቃሉ በመንፈስም በአእምሮም እንድንጸልይ ነው የሚያበረታታን።

ስለዚህ ልሳንን አእምሮቻችን ብቻ እንዲረዳው የሚያስፈልገው አድርገን ማየት የለብንም። አእምሮማ ብቻ የሚረዳው እንዲሆን ከተፈለገ እኮ ልሳን ጨርሶም አያስፈልግም። ትንቢት ይበቃል። ልሳን ግን ተናጋሪው ራሱን በመንፈስ እንዲያንጽ የሚያስችለው ከፍተኛ ሃይል አለው። ይሄንን የምልህ ከራሴም ልምድ ተነስቼ ነው። በልሳን በመንፈስ እንደመጸለይ ያለ እጅግ effective (ውጤታማ) የሆነ ጸሎት እኔ አላውቅም። ሰዎችን በጉባዬ ለማነጽ በአእምሮ መናገር ይጠቅማል፤ የራስን መንፈስ ለማነጽ ግን ከልሳን የሚበልጥ ያለ አይመስለኝም። ብዙዎች ግን ልሳንን የፕሮግራም ማሳመሪያ ብቻ አድርገውት ፈጽሞ ፈጽሞ አይጠቀሙበትም። እንደ እኔ ግምት በጌታ ዘንድ በጣም የሚቆጩበት አንዱ ነገር ቢኖር በየእለቱ በበቂ ሁኔታ በልሳን አለመጸለያቸው ይመስለኛል። ምን ያህል የመንፈስ ቅዱስን ህብረት እያጡ እንደሆነ ብዙዎች አያስተውሉም። ስለዚህ ከልምድ እንደ ወገን ማንንም ክርስቲያን የምመክረው፤ ልሳን ተሰጥቶህ ከሆነ እባክህ እባክህ ቢያንስ በቀን 30 ደቂቃ እንኳን የሚሆን ባይገባህም ዝም ብለህ ጸልይ። እግዚአብሔር ይህንን ሞኝ የሚመስል ነገር ለምን እንደሰጠው ከጥቂት ቀናት በኋላ እስኪገርምህ ታየዋለህ። የሚዳሰስ የመንፈስ ቅዱስ ህብረትን መለማመድ ከፈለግህ እባክህን እለት እለት ቢያንስ ቢያንስ 30 ደቂቃ የሚሆን ጊዜ በልሳን ጸልይ ነው ምክሬ። የእግዚአብሔር ሞኝነት ከሰው ጥበብ ይበልጣልና።
ወገኔ ወይ፦

ተናጋሪውም ሌላውም የሚባለውን ካላወቁ የእግዚአብሔር መንግስት እየርገመ ይሁን እየባረከ በምን እናውቃለን?

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 የዘለልከው ጥቅስ ከቁጥር 10 ላይ የሚያወራው ስለሰው ልጆች ቋንቋ ነው " በዓለም ምናልባት ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል ቋንቋም የሌለው ሕዝብ የለም፤ 11 እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው እንግዳ እሆናለሁ፥ የሚናገረውም ለእኔ እንግዳ ይሆናል። " ፍችውን የማያውቅ ሊያስተውለው አይችልም ለዚ ነው "የሚያስተውለው የለምና" ያለው።

ለምሳሌ በአዲስ አበባ ወስጥ በጉባኤ ላይ አንዱ በፖርቲጋል "ልሳን" ቢናገር ለአገሪው ህዝብ እንግዳ ቋንቋ ስለሚወን እስካልተተረጎመ ድረስ የሚያስተውል አይኖርም፤ እግዚአብሔር ግን ምን እንደሚነገር አስተርጓሚ አያሻውም። ስለወነም እዚህ ምእራፍ ወስጥ የተጠቀሰው ልሳን የሰው ልጆችን መግባቢያ ቋንቋን በተመለከተ ነው።

በነገራችን ላይ ጌታስ እንድንጽልይ ያስተማረን እንዲ ነው.. " እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥...."
ሰላም ወገኔ

የምጸፈውን በጥሞና ያነበብከው አልመስልህ አለኝ። በእርግጥ ከላይ ያልከው በአንድ ጎኑ ትክክል ነው። ይህ ግን አንዱ ጎን ብቻ ነው። ከላይ የጻፍኩትን በደንብ አንብበው። ሁለት አይነት ልሳን አለ ብዬ ጽፌአለሁ። አንዱ ጉባኤን ማለትም ሌሎችን ታዳሚዎች ለማነጽ የሚውል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቃሉ እንደሚለው ሰው የማያስተውለው ለእግዚአብሔር ብቻ የሚነገር ልሳን ነው። ከላይ እኮ የሰጠሁትን ጥቅሶች አለነበብከውም መሰለኝ።

ስለዚህ ነው የማይተረጎም ልሳን በጉባኤ ለሌሎች እንዳይነገር የሚመከረው። ሆኖም ግን ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር ይላል ቃሉ።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
27 በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤
28 የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር

አሁንም ከላይ የሰጠሁትን ጥቅስ ልድገመው እስቲ
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤
..
4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።

ሰዎችን ለማነጽ ለሰው የሚነገር ልሳን አለ፤ ደግሞ ቁጥር 2 ግልጽ እንደሚያደርገው ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ብቻ የሚነገር ልሳን አለ። ሌሎችን በጉባኤ ለማነጽ የሚነገርና የሚተረጎም ልሳን አለ፤ ደግሞ ቁጥር 4 ግልጽ እንደሚያደርገው ራስን ብቻ ለማነጽ የሚነገር ልሳን አለ። ራስን ብቻ ለማነጽ የሚነገረውን ልሳን ሰው ለራሱና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገረው እንጂ በማህበር ጮኾ እንዳይናገረው መጽሃፍ ቅዱስ ይናገራል ቁጥር 28። ምክንያቱም ይሄ ራሱን ብቻ የሚያነጽበት ልሳን ስለሆነ። ለራሱና ለእግዚአብሔር ግን መናገር ይችላል። ስለዚህ ቃሉን ሳንጨምር ሳንቀንስ ሙሉውን ነው መያዝ ያለብን እንጂ፤ ወደ አንድ ጎን ብቻ አጋድለን ሚዛናዊ ያልሆነ መረዳት መያዝ የለብንም።
ውንድሜ ውይ፡
ሁለተኛው አይነት ልሳን ያልከው ያንተ መረዳት ነው።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር የተባለው እኮ የሰው ልጆች ቋንቋ ስላልውነ ሳይሆን በጉባኤ መካከል የሚነገርው ልሳን የሚይስተርጉም ወይም የሚረዳ ከሌለ ነው (የሰዎች ልጆች ቋንቋ ለምሳሌ ፤ ለምሳሌ ነቀምት ወስጥ ያለ ጉባዬ መሃል የቱርክ ልሳን ቢኖር፡ - ተናጋሪው ዝም እንዲል ታዞአል። ምክንያቱም ሕዝቡ አስተርጓሚ ከሌለ መለክቱን ሊሰማ ስለማይችል።

አንድ ልሳን ተነጋሪ የሚለውን ካላወቀው እርሱን እንዴት አድርጎ ነው እርሱን የሚያንጸው ግን?
ወገኔ ሆይ

ቃሉን ሳንቀናንስ በሙሉ እናንብበው እንጂ። "በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል" 1ቆሮ 14፡2 ማለት ምን ማለት ነው? እዚህ ጋ እኮ በቀጥታ የሚናገረው ያለው፤ በልሳን የሚናገር ሰው የሚናገረው ለሰው አይደለም ለእግዚአብሔር ነው እያለ ነው።

1ቆሮ 14፡4 ላይስ ምን ይላል? "በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል"። በልሳን የሚናገር ሌሎችን ሳይሆን ራሱን እያነጸ ነው፤ ራሱን በመንፈስ እየገነባ ነው ይላል። ታዲያ በማያውቃው የሌሎች ሰዎች ቋንቋ ማለትም ለምሳሌ በፈረንሳይኛ ስለተናገረ እንዴት አድርጎ ነው ራሱን የሚያንጸው?
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤
..
4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።

ይህ ብቻ አይደለም እስቲ የአንተን ሎጂክ እንከተል። በጉባዬው ውስጥ በልሳን የሚናገረውን ቋንቋ ማለትም አንተ እንደምትለው የሰው ቋንቋ ከሆነና ተርጓሚም ከሌለ ለምንድነው ታዲያ እግዚአብሔር ይህን እያወቀ፤ ይህንን ልሳን ለሰውዬው የሚሰጠው? ማለትም በአንድ አማርኛ ብቻ በሚናገሩ ጉባዬ ውስጥ፤ ቻይንኛ የሚተረጉምም ይሁን የሚሰማ ሰው እንደሌለ እያወቀ እግዚአብሔር፤ እንዴት በጉባዬ ላለው ለአንዱ ሰው በዚያ ጉባዬ ውስጥ ቻይንኛ እንዲናገር ይሰጠዋል? ይሄ ምንም ትርጉም አይሰጥም። ምክንያቱም በዚያ ጉባዬ ቻይንኛ የሚሰማም ይሁን የሚተረጉም የለምና፤ እግዚአብሔር ይሄን እያወቀ ሰውዬ በዚያ ጉባዬ ቻይንኛ እንዲናገር ማድረጉ ምንም ፋይዳ የለውም። ስለዚህ የአንተን ሎጂክ እንኳን እንከተል ብንል ፈጽሞ የሚያስኬድ አይደለም።

እኔ ከመጽሃፍ ቅዱስ በተጨማሪም በህይወት ልምድም ዕለት ተዕለት ከምለማመደውም ጭምር ነው እየመሰከርኩልህ ያለሁት። እንዲሁ ስለማላውቀው ነገር፤ በስማ በለው ብቻ አይደለም የምናገረው።
እኛ ጋ ከከመጋቢያችን ጭምር አንዳንዶች በጉባአ ላይ በማይታወቅ ቋንቋ (ልሳን) እየጮሁ (እየተናገሩ) መንፈስ ነው የሚያናግረን ይሉናል፡ እንደነሱ የማንወነውን አንዳልዳንን ሊንግሩን ይሞክራሉ።
ወንድም፡
አንድ ልሳን ተነጋሪ በማይታወቅ ቋንቋ እየተናገረ የሚለውን ካላወቀው እርሱን እንዴት አድርጎ ነው የሚያንጸው ? ጉባኤውን በማይታወቅ ቋንቋ እየረገም ቢወንስ፡ ወንድሜ ወይ ያንተ ልምምድ ማስረጃ ሊወን አይችልም። በተጨማሪም ደግሞ 1ቆሮ 14 በሙሉ ጸልየ አንብበው ይበልጥ ትረዳዋለ ከሓዋ 2፡ ጋርም አዛምደው።

ከዚያም ልሳን ማለት የሰዎች ቋንቋ እንደውነ ትረዳዋለ ለዚህም ጌታ ይርዳ።
ወገኔ ስለ ምክርህ አመሰግናለሁ፤ ሆኖም እኔ ማንበብ ብቻ አይደለም ቃል በቃል ምእራፉን አጥንቼዋለሁ። የእኔን ልምምድ እንደ ተጨማሪ ጨመርኩ እንጂ እስከ አሁን ያቀረብኩት ሁሉ ቃሉን ብቻ ነው። ከላይ ላቀረብኩልህ መረጃዎች አንዳችም ያንን የሚያፈርስ ጥቅስ አልሰጠኸኝም። ሌላ አንድ ደግሞ ልጨምርልህ እስቲ።

1ቆሮ 14፡14 ምን ይላል? "በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።" ይላል። ስለዚህ አሁንም አንተ በአእምሮ ስለመረዳት ነው የምታወራው። ቃሉ ግን የሚለው በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል፤ አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው ይላል። ስለዚህ በአእምሮህ ስላልገባህ ብቻ መንፈስህ አይታነጽም ማለት አይደለም። የልሳን ጸሎትም አንዱ ምስጢር መንፈስን እንጂ አእምሮ ላይ አይደለም የሚያተኩረው። አዎ በልሳን የምትጸልየው ስለማይገባህ አእምሮህ ያለፍሬ ነው። ሆኖም ግን መንፈስህ ይታነጻል፤ ይገነባል። ሙሉውን ጥቅሶቹን በሙሉ እናንብብና እናጥና እንጂ አንዲት ቃል ብቻ ወይም አንድ ሃሳብ ብቻ ይዘን በመሄድ መሆን የለበትም። ያለዚያ ሚዛኑን የለቀቀና ወደ አንድ ጎን ብቻ ያጋደለ እምነት ነው የሚኖረን። መጽሃፍ ቅዱስ ያለውን በሙሉ፤ ሙሉ ለሙሉ ሳንጨምር ሳንቀንስ ማጥናትና መቀበል አለብን፤ ቢስማማንም ባይስማማንም። ሌላ አማራጭ የለም።
ወገን ያነበቡት አይመስለም

ምክንያቱም የርሶ ሃሳብ ሚያፈርስ ጥቅስ " ከሓዋ 2፡ ጋርም አዛምደው" ብዬ ነበር። አሁንም ይኽው - የሓዋሪያት ስራ ም. 2 ፤8 "እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? " - በመጀመሪይቱ ቤ/ክ የነበርው ስጦታ እንደዚ ነበር።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 ወረድ ብለው፡ ቁጥር 22 ላይ እንዲ ይላል

"እንግዲያስ በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው እንጂ ለሚያምኑ አይደለም"

ይህንን እውነት ቢቀበሉ ይባረኩበታል።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...