ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ሰይጣን በልባችን ያለ እና ወደ ፊት የሚሆነው ነገር ሊያውቅ ይችላልን?

Mar 28, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
የመዸመርያው በጣም የምያሳዝን መልስ ነው
ሰላም ወንድሜ/እህቴ

አሳዝኜ ከሆነ በጌታ ይቅርታ እጠይቃለሁ። እኔ ላሳዝን አልነበረም፤ ሰይጣንን እንዳንፈራው ላበረታታ እንጂ። በመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኛቸው ደቀመዛሙርት ስለ ሰይጣን እየተጨነቁ፤ ይሄን ያውቅ ይሆን? ያንን ሳስብ ያየኝ ይሆን እያሉ ስላልኖሩ፤ እኛም እንዲህ መጨነቅ የለብንም ለማለት ነው።

ካጠፋሁ ይቅርታ።

የጌታ ጸጋ ይብዛልህ/ሽ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
ወንድሜ ወይም እህቴ ሰይጣን በልባችን ያለውን ወይም ወደፊት የሚሆነውን ቢያውቅ ባያውቅ ምን የሚያመጣው ነገር አለ? ለእኛስ ይህን ማወቃችን ምን ይጨምርልናል?

መጽሐፍ ቅዱስ ከ97 በመቶ በላይ የሚያወራውና የሚተርከው ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሕዝቡ ነው እንጂ ስለ ሰይጣን አይደለም። እኛም አዕምሮአችንና ሃሳባችን በእግዚአብሔር ላይ ነው መሆን ያለበት እንጂ በሰይጣን ላይ አይደለም።

አዲስ ኪዳንም ብዙ ሰለ ሰይጣን አያስተምርም፤ ሰይጣን ይሄን ያውቃል፣ ያንን ይችላል እያለ ስለ ዲያቢሎስ አያስተምርም። ብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንቶች በተሳሳተ መንገድ የሚረዱት "ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል" (ያዕቆብ 4፡7 ) ተብሎ በአማርኛው የተተረጎመው ክፍል እንኳን ጸንቶ ሰለ መቋቋም ወይም resist ስለማደረግ እንጂ በጸሎት ስለ መገሰጽ አይደለም የሚያወራው።
Quote:
የያዕቆብ መልእክት 4
6 ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።
7 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤

ከላይ እንደምናየው ክፍሉ የሚያወራው ስለ ትህትናና ስለ ትዕቢት ነው። እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ስለዚህ ዲያቢሎስን እምቢ በሉት ወይም ተቋቋሙት ከእናንተም ይሸሻል ነው የሚለው። ማለትም ዲያቢሎስ እንዳያስታብያችሁ ተጠንቀቁ፤ የትዕቢት ፈተናም ሲመጣ ጸንታችሁ ተቋቋሙት ወይም resist አድርጉት ነው የሚለው እንጂ፤ እንደው እንደበረገገ በግ ስትደንግጡና እንዲያው በጸሎት ስትገስጹ ኑሮ ማለቱ አይደለም። የትዕቢትን ፈተና ሳንቋቋም ስንገስጽ ብንውል የሚያመጣው ነገር የለም።

የትም ቦታ በአዲስ ኪዳን በጸሎታችን ሰይጣንን እንድናነሳ ወይም ከእርሱ ጋር አተካራ እንድንፈጥር አልተጻፈም። ይህ ሁሉ የሚመጣው ሃሳባችንና ትኩረታችንን ከታላቁ ከእግዚአብሔር ላይ ስናነሳና ወደ ሰይጣን ስናዞር ትልቅ ሆኖ ስለሚታየን ከፍርሃትና ከመበርገግ ነው።

ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ የሰይጣንን ፈተናና ተንኮል እንድንቋቋመው ተጽፎአል። ይህም በኃጢአት እንድንወድቅና እንድንጠላለፍ፤ በዚህም ምድር የባለጠግነት መታለል እንድንያዝ የሚያደርገውን ፈተና ማሸነፍ ማለት ነው። እነዚህን ደግሞ ጸንተን እንድንቋቋም ማለትም እምቢ ብለን ኃጢአትንም ዓለምንም እንድናሸንፍ ተጠርተናል እንጂ፤ ቀንና ለሌሊት ስለ ሰይጣን እያሰብን፤ ይሄን ያውቅ ይሆን? ዛሬ ሳልገስጸው ዋልኩ ወዘተ እያልን የብርገጋ ኑሮ እንድኖር አልተጠራንም።

የዲያቢሎስን ፈተና እንድንቋቋምና አጋንንትን ከሰዎች እንድናስወጣ ተጠርተናል። በተረፈ ግን ስለ ዲያቢሎስ እንድንጨነቅ አልተጠራንም።

በራእይ መጽሐፍ ላይ ስለ እግዚአብሔር ሲናገር፤ አዕላፋት መላእክት እንደሚያመልኩት ተጽፎአል፤ ሰይጣንን ግን አንድ መልአክ ነው ይዞ ለአንድ ሺህ አመት ያሰረው። ራእይ 20፡1-2

በእኛ ላይ የሚሆን ነገር ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን የለም። ከጸጉራችን አንዲት ጸጉር እንኳን ያለ አባታችን ፈቃድ አትወድቅም። የህይወታችንም እጣ ፈንታ የሚወሰነው በሰይጣን ሳይሆን በአባታችን በእግዚአብሔር ነው። ብቻ ራሳችን ከክፋትና ከኃጢአት፤ ከዚህም ዓለም ጊዜያዊ መጎመዠት እንጠብቅ።

ጻድቅ በፍርሃትና በመበርገግ ይኖራል ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው "ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል" ነው የሚለው። ትንቢተ ዕንባቆም 2፡4
Mar 29, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የጌታ ሠላም ይህን ለሚያነቡ ይሁን አሜን ይሁን።

ብዙ ቁንቃዎች ጾታን ይለያሉ ከነሱ አንዱ የአማርኛ ቁንቃ ነው። የማይለዩትን የሚጠቀሙ እንደልባቸው መግለጽ ይችላሉ እኛ ግን ሰዋስው ያግደናል። ይህን ህሉ ያልኩት ለምን እንደ ሆነ ስለተረዳችሁኝ ጌታ ይባርካችሁ። ስለዚህ በምናቀርበው ጥያቄ መጨረሻ ስም መጥቀስ ባንፈልግም ወንድም... ወይም እህት... ብለን ፍንጭ ብንሰጥ ለመልስ ሰጪዎች ሸክም ይቀላል እላለሁ።

የቀረበው ጥያቄ ጥሩ ነው ምክንያቱም ጠላታችንን ድካሙንም ጉልበቱንም ማወቁ የምንዋጋበት ስትራተጂውን ለማመቻቸት ይበጀናል ብዬ አምናለሁ። "ሰይጣን በልባችን ያለ እና ወደ ፊት የሚሆነው ነገር ሊያውቅ ይችላልን?" የሚል ጥያቄ ለማቅረብ ግድ የሆነብት ምክንያት እንዳለ አልጠራተርም። እስቲ ስለ ቀረበው ጥያቄ ባጭሩ ለመነጋግር የእ/ር ቃልን እንይ፦

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች ሲጽፍ በምዕራፍ 10፡8-10 "በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። እየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔር ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናልህና ሰው በልቡ አምኖ በአፉም መስክሮ ይዽናኣልና" እንዲሁም በምሳሌ 18፡21 "ሞትና ሕይወት በምላስ ደጅ ናቸው ይላል። ምንድ ነው የምታወራው ጥያቄዬኮ "ሰይጣን በልባችን ያለ እና ወደ ፊት የሚሆነው ነገር ሊያውቅ ይችላልን? ነው እባል ይሆናል። እርግጥ ነው ገብቶኛል ግን ትንሽ ልቀጥል ይፈቀደልኝና በአፋችን ያለውን ሃይል ስልጣን ማስተዋሉ በጣም ይጠቅመናል። ቅጩን ላንገር! ጠላት ምንም አያቅም ቢያውቅ ኑሮ ፈሪሳዊያንንና ተከታዮቻቸውን ገፋፍቶ ሽብር ማስነሳቱ ቢሰቀል ቢሞት አበቃለት ድል አደረጉት ብሎ በአጉል ምኞት ስካር ነው እንጂ የሚጣልበት መሆኑን ቢያውቅ ኑሮ ጌታን አይሰቅለውም ነብር። ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ነጥብ ነው በኔው አባባል ያልኩት።

ችኮላ ጥድፍያ ያለበት ነገርና ሁኔታ ሁሉ የጠላት ጥንሥስ መሆኑን እናስተውል። እነ ማርታና ማርያም ያ የምትወደ አልዓዛር ሞቶዋልና ቶሎ ድረስ ብለው ሲልኩበት ጌታ ግን ወቅታዊ የሆነውን ስራወን ሲያከናውን እንጂ ወደ ቢታንያ ሲጣደፍ አናየውም። ጠላት የተሸነፈ እየሱስ እግር ስር የረገጠው ድል የሆነ ጠላት ነው ግን እኛ ፊት ስለ ምንሰጠው ነው አንሰራርቶ ሊጥለን ፈልጎ ሁሌ የሚዋጋን። ክብር ምስጋና ውዳሴ ለጌታችን ለእ/ር ልጅ በነፃ እንድንኖር ነፃ ያወጣን ለእየሱስ ክርስቶስ ይድረሰው። አሜን ይድረሰው!!!

ጌታ ይባርካችሁ
Mar 30, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Apr 4, 2011 ተመልካች ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...