ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Friday, 4 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሄር ነው?

ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሄር ነው?
Apr 1, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

6 መልሶች

0 ድምጾች
ክፍል 1

በቅድሚያ

በቅድሚያ እግዚአብሔርና ኢየሱስ ያላቸውን ግንኙነት በአዕምሮ መረዳት በብዙዎች ዘንድ እንደ ትልቅ የክርስቲያኖች መከፋፈያ የሚታይ ጉዳይ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ብዙዎች ስለ እግዚአብሔርና ኢየሱስ ያላቸውን ልዩነት ከመጽሐፍ ቅዱስ መመርመር ወይም ይሄን ጥያቄ ማንሳት እንደሚያስቀስፍ አድርገው ነው የሚያስቡት። ይሄ ስህተት ነው። አንደኛ የኢየሱስን ደቀመዛሙርት ጨምሮ በመስቀል ላይ ተሰቅሎና በክርስቶስ አምኖ የዳነውም ወንበዴ ጭምር የእግዚአብሔርንና የኢየሱስን ልዩነትና አንድነት አብጠርጥሮና ስለ ስላሴም አውቀው አይደለም የዳኑት። የሚያድነው፤ በኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነትና በመስቀል ላይ በሠራው ሥራ ማመን እንጂ ስለ ስላሴ አብጠርጥሮ ማወቅ የደህነነት መስፈርት አይደለም።

ስለዚህ ስለ ስላሴ ማሰብና መጠየቅ አያስቀስፍም፤ የተለያየ መረዳት በአማኞች መካከል ቢኖርም እንኳን ይህ የሃሰት ትምህርት ነው እያሉ መናቆሪያ መሆን የለበትም። በዚህ ጉዳይ ወንድሞቻቸውን የሚከሱ ብዙዎቹም ራሳቸው ነገሩ በደንብ እንዳልገባቸው የሚናገሩ ናቸው። ሁላችንም ያኔ ለሁላችን ደሙን ባፈሰሰው ጌታ ፊት ስንሆን የእግዚአብሔርና የኢየሱስ ልዩነት ይገባናል። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ከእኛ የተለየ ሃሳብ ያለው ወንድም ብናይ ወደ ብርገጋና ጌታ ደሙን ያፈሰሰለትን ወንድም ወደ መኮነን ቸኩለን እንዳንገባ መጠንቀቅ ያሰፈልገናል። ይልቁኑም በእርጋታ ቃሉን መመርመር ይበጃል፤ ወደ አንድ አሳብ እስክንመጣም መታገስና መማማር ይሻላል።

አሁን ወደ መልሱ ...

በዚህ ጥያቄና ባጠቃላይ የእግዚአብሔርንና የኢየሱስን ማንነት በተመለከተ በተለይ ሁለት የከረሩና ሚዛናቸውን ያልጠበቁ በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አመለካከቶች አሉ።

አንደኛው አመለከካት ኢየሱስ አምላክ ወይም መለኮታዊ አይደለም ሰው ብቻ ነው ወይም እንደ ማናቸውም አንድ ፍጥረት ብቻ ነው የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሆነ ራሱም እግዚአብሔር የሆነ ነው የሚል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ስንመለከት ሁለቱም የተለጠጡና ሚዛን ያልጠበቁ አመለካከቶች እንደሆኑ እንረዳለን። ኢየሱስ ሰው ብቻ ወይም ከፍጥረት አንዱ እንዳልሆነና አምላክም እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎአል። ከፍጥረት በፊት ስለነበረና ያለ እርሱም አንዳች ስላልሆነ፤ ፍጥረት ውስጥ ሊካተት አይችልም።

ኢየሱስ አምላክ ነው ማለት ግን ራሱ ያ አንዱ እግዚአብሔር ነው ማለት ግን አይደለም። ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አንዱ እግዚአብሔር ሲናገር እግዚአብሔርንና ኢየሱስን በአንድነት አብሮ አንድ እግዚአብሔር እያለ አይደለም የሚጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን ስለ አንዱ እግዚአብሔር ወይም ስለ አንዱ አምላክ ሲናገር ብዙዎቻችን እንደሚመስለን ስለ ስላሴ ሳይሆን የሚያወራው ስለ አብ ብቻ ነው።
Quote:
አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው“ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፣5

„መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።“ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፣5-6

„በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።“ ኤፌሶን 4፣4-6

„ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።“ የሉቃስ ወንጌል 18፣19 የማርቆስ ወንጌል 10፣18

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ እንጂ እርሱ ራሱ ያ አንዱ እግዚአብሔር እንደሆነ አይናገርም።

ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ሲናገር ምን ማለቱ ነው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወራው ስለ ኢየሱስ የዘር ክፍል ወይም ምድብ ነው። ማለትም አበቦችና ቅጠሎች በአትክልት የዘር ክፍል፣ አራዊትና አእዋፋት በእንስሳት የዘር ክፍል እንደሚመደቡ፣ ጥቁሮችና ነጮች ደግሞ በሰዎች ወገን እንደሚመደቡ፣ ሱራፌልና ኪሩበልም ከመላእክት ወገን እንደሚመደቡ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ወይም ከአምላክ ክፍል ነው የሚመደበው።

ይሄ ማለት ግን ኢየሱስ ከአንዱ ከእግዚአብሔር ማለትም ከአብ እኩል ነው ወይም እርሱ ራሱ ነው ማለት አይደለም። ኢየሱስ መለኮታዊ ነው፤ አምላካዊም ባሕርይ አለው ለማለት እንጂ።

በዮሐንስ ወንጌል 1፣1 ላይ „ቃልም እግዚአብሔር ነበረ“ ሲል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አብ ነበረ ማለቱ አይደለም:: ነገር ግን የዘር ምድቡን/class ሲነገረን ነው:: ከመላክት ወይም ከሰው ብቻ ወይም ከፍጥረት የሚመደብ እንዳልሆነ ለመግለጽ ነው:: በሌሎችም ክፍሎች እንደዚሁ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መልክ/form እና የባሕርይው ምሳሌ/image እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል::
Quote:
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
2፥6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
(በእግዚአብሔር መልክ/ምንነት/essence/form of God /very nature of God)

NASB
Philippians 2:6
who, although He existed in the form of God, did not regard equality with God a thing to be grasped,

ኢየሱስ ራሱ ያ አንዱ እግዚአብሔር ሳይሆን የዛ የማይታየው የአንዱ እግዚአብሔር የክብሩ መንጸባረቂያና የባሕርይው ምሳሌ ነው።
Quote:
ወደ ዕብራውያን
1፥3 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤

„እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው።“ ቆላስይስ 1፣15

ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ያለ አምላካዊ ባሕርይ ቢኖረውም፤ እግዚአብሔር ከኢየሱስ እንደሚበልጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይሄ ታዲያ አንዳንዶች እንደሚሉት ሰው ሆኖ በተመላለሰበት ጊዜ ብቻ አይደለም።

ለምሳሌ ኢየሱስ ከተነሳና ካረገ በኋላም ዮሐንስ ያየውን ራእይ ብንመለከት፤ አንደኛ ራእይው ራሱ እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ራእይ ነው።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 1
1 ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥

ሁለተኛ በዛው በራእይ መጽሐፍ ላይ ብንመለከት ኢየሱስ ከተነሳና ካረገም በኋላም አሁንም እግዚአብሔርን አምላኩ እንደሆነ ነው የሚናገረው።
Quote:
„ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።“ የዮሐንስ ራእይ 3፣2

„ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።“ የዮሐንስ ራእይ 3፣12

ይሄም ብቻ አይደለም፤ ኢየሱስ በዘመን ፍጻሜ በሁሉ ላይ ስልጣን ካገኘም በኋላ ቢሆን፤ ሁል ጊዜ ከአብ ሥር ሆኖ ከእርሱ በታች የሚገዛ እንደሆነ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚነገረን።
Quote:
„ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።“ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፣27-28

እግዚአብሔር ከኢየሱስ እንደሚበልጥ፤ እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀውና ኢየሱስ ግን የማያውቀው ነገር እንዳለ፤ እግዚአብሔር ሲያደርግ የሚያሳየውን እንጂ ከራሱ ኢየሱስ ምንም ማድረግ እንደማይችል ወዘተ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎአል። ሁሉንም ክፍሎች መዘርዘር እዚህ ባይቻልም አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው።
Quote:
„ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።“ 1ኛ ቆሮንቶስ 11፣3

„ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።“ ዮሐንስ 5፣19

የዮሐንስ ወንጌል
14፥28 እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።

„ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።“ የማቴዎስ ወንጌል 24፣36

የኢየሱስ አንዱ የአምላክነት ባሕርይ የሆነው በውስጡ ሕይወት መኖሩ ወይም self-existent መሆኑ ራሱ ከእግዚአብሔር የተሰጠው እንደሆነ ነው ኢየሱስ የሚናገረው። ይህ self-existent የሆነ ሕይወት ደግሞ የአምላክነት እንጂ የሰው ባሕርይ አይደለም።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና

Amplified Bible
John
5:26 For even as the Father has life in Himself and is self-existent, so He has given to the Son to have life in Himself and be self-existent.

እግዚአብሔር በብሉይም በአዲስ ኪዳንም አንድ ነው። የማይታይ፤ የማይሞት ብቸኛ እግዚአብሔር ነው። ኢየሱስ ደግሞ የዚህ የአንዱ እግዚአብሔር ልጅና የባሕርይው ነጸብራቅና ምሳሌ ነው። ያ አንዱ እግዚአብሔር የኢየሱስም አምላክና አባት ነው። ኢየሱስን ጨምሮ ሁሉ ከእርሱ በታች የሚገዙለትና የሚታዘዙት አንዱ እግዚአብሔር ነው። ሁሉን እንደ ፈቃዱና እንደ እቅዱ የሚያደርግ አንድስ ሰው እንኳን ያላየው አምላክ ነው።
Quote:
ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።“ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፣17

እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።“ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፣16

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ሁሉ እንጂ እንዲያው ወደ ቀኝም ይሁን ወደ ግራ የተለጠጠውንና የተጋነነውን መቀበል የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስ ሚዛናዊ ነው። አንድ እግዚአብሔር አለ ሲል አንድ እግዚአብሔር አለ ማለቱ ነው እንጂ ሶስት አካላት በአንድ ተጠቃልለው ነው ያ አንዱ እግዚአብሔር የሆኑት የሚል አንድም ቦታ የለም።
Quote:
„እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው“ ዘዳግም 6፣4

አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው“ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፣5

„መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።“ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፣5-6

„በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።“ ኤፌሶን 4፣4-6

„ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።“ የሉቃስ ወንጌል 18፣19 የማርቆስ ወንጌል 10፣18

ክፍል 2 ይቀጥላል ...
Apr 1, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Apr 1, 2011 ታርሟል
+1 ድምጽ
ክፍል 2

መጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ ያን አንዱ እግዚአብሔርን ሲናገር፤ እኛ እንደሚመስለን እግዚአብሔር አብ፤ እግዚአብሔር ወልድ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እያለ አይጠራም። ብዙ ጊዜ የሚጠራው እግዚአብሔር አባታችን እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያለ ነው። አንዱን እግዚአብሔርና ኢየሱስን ለያይቶ ነው።
Quote:
„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፣3

„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ 2ኛ ቆሮንቶስ 1፣2

„የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።“ አሜን። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፣14

„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ ገላትያ 1፣3

„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ ኤፌሶን 1፣2

„ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።“ ኤፌሶን 6፣23

„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ ፊልጵስዩስ 1፣2

„በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን።“ ቆላስይስ 1፣2

„ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።“ 1ኛ ተሰሎንቄ 1፣1

„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።“ 2ኛ ተሰሎንቄ 1፣2

„በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።“ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፣2

„ለተወደደው ልጄ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።“ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፣2

„በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።“ ቲቶ 1፣4

„ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ ፊልሞና 1፣3

„የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።“ ያዕቆብ 1፣1

„የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።“ 2ኛ ጴጥሮስ 1፣2-3

„ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ።“ 2ኛ ዮሐንስ 1፣2

„የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤“ ይሁዳ 1፣1
Apr 1, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Apr 1, 2011 ታርሟል
በነገራችን ላይ ኢየሱስ መለኮትነት ያለው ፍጡር ነው የሚለው አስተምህሮ ዛሬ በእርሶ የመፅሃፍ ቅዱስ እውቀት ወይም ከላይ ጌታ አስተማረኝ እንዳሉት አዲስ ግኝት አይደለም።
ስለዚህ ሰው ታሪክ ምን እንደሚናገር ያውቃሉ?
አሪዎሳዊያን
አርዮስ በግብጽ የሚኖር የአለክሳንደርያ ጳጳስ
ነበር።የአሪዎስ ትምህርት ከክርስቶስ ማንነት ይልቅ በብዛት ሚያተኩረው
በእግዚአብሔር ዶክትሪን ቢሆንም አንዱ ከአንዱ ሊለያዩ
አይችሉም።አርዮሳዊያን ሲያስተምሩ ክርስቶስ ከዘለኣለም አልነበረም፣ በእርሱ
ሁሉ ነገሮች የተፈጠሩ ሲሆን ራሱ ግን የተፈጠረ ፍጡር ነው
ይላሉ።በተፈጠረበት ሁኔታ ሎጎስ፣ ወንድ ልጅ፣አንድያ ልጅና የእግዚአብሔር
ፍጥረት መጀመርያ ይባል ነበረ።ወልድ እግዚአብሔር ተብሎ ቢጠራም የቃሉ
ሙሉ ሃሳብ ግን እግዝአብሔር እንዳልነበረ ነገር ግን የተፈጠሩ ፍጥረታት ሁሉ
የበላይ እንደሆነ ያመለክታል ብለው ያስተምራሉ።ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ
ነበር ነገር ግን አምላክ አልነበረም ይላሉ። በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ
ግማሽ አምላክ የሆነ አምላክ ነበር ይላሉ።አርዮሳዊነት በ321-325ዓ.ም አከባቢ
እንዲሁም አሪዮስ በአሌክሳንደርያዊው ጳጳስ በአሌክሳንደር የተወገዘ
ነበር።እንደውም አሪዎስ ከማንኛውም የቤተክርስቲያን ቢሮ፣ሥራ፣ህብረት
ከማድረግ የተከለከለና የተባረረ ሰው ነበር።ይህ ስህተት ትምሕርት የክርስቶስ
ዘለዓለማዊነትና ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል መሆን የሚክድና ክርስቶስ
የተፈጠረ ፍጡር ብቻ አድርጎ የሚያይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ የመጠበቅያ ግንብ
(ራሳቸውን የጆሁቫ ምስክሮች ብለው የሚጠሩ) አማኞች የዚህ ትምህርት
ተከታዩች ናቸው።
ሰላም ወገኔ

ብዙ ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተው ማስረዳትና ማብራራት ሲያቅታቸው ወደ ውግዘት ይሄዳሉ። የፕሮቴስታንት እምነት በኢትዮጵያ ሲጀመር የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቄሶች ሲያደርጉ የነበሩት ይሄንን ነው።

በቅድሚያ እኔ ክርስቶስ ተፈጥሮአል ፍጡር ነው አላልኩም። ስለዚህ አርዮስ ምናምን እያሉ ያላልኩትን ከሌላ ሰው ጋር ለማዛመድ መሞከር ትክክል አይደለም። እስጢፋኖስና ኢየሱስ የተከሰሱትም ባላሉትና ባላደረጉት ነው።

ስለዚህ ወገኔ በቅድሚያ የጻፍኩትን ያንብቡት፤ ከዚያም የማይስማሙበት ሃሳብ ካለ ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተው ሊያርሙኝ ይሞክሩ። ምክንያቱም ክርስቶስ ሰዎችን ሊያድን እንጂ ሊፈርድ አልበጣምና። የተሳሳተም ካለ ለመመለስና ለመምከር ምንም ሙከራ ሳናደርግ እንዲያው አርዮስ ነው ምናምን ነው ብንል ይሄ የክርስቶስን መንፈስ እየተከተልን አይደለም።

በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፈው ደግሞ ለማረምና ሃሳቦትን ለመግለጽ ካልቻሉ አርፎ መቀመጥና ሌላ የሚያስተምር እስኪመጣ መጠበቅ ይሻላል። ዝም ብሎ መራገሙ ወይም ሰው ያላለው ብሏል ብሎ ሐሰተኛ ምስክርነት መስጠቱ አያዋጣም።
ኢየሱስ የአምላክ ባሕርይ ያለው የተፈጠረ አምላክ ነው ላሉ ወዳጄ የተሰጠ ምላሽ እንዲሁም መፅሓፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ አምላክነት ምን ይላል ብለው ለሚጠይቁ ሁሉ በጥቂቱ ግንዛቤ ለመስጠት::ብዬ ርእስ ሰጥቼ የሰጠሁት መልስ እዛላይ ሙሉ ሃሳቤን ያገኙታል:: Toto ነኝ
0 ድምጾች
ከላይ ያለውን ሰው ሃሳብ ለመቃረን ሳይሆን መጽሃፍ ቅዱስ ግን ራሱ አብ ነው ይልለዋል
1ተሰ.3:11:- አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እናንተ መንገዳችንን ያቅና፤
እየሱስ ራሱ እግዚአብሄር ነው ማለትና ኢየሱስ እግዚአብሀር ነው ማለት አማርኛው 1 ይመስለናል
ምናልባትም ከላይ የመለሰው ሰው እየሱስ እግዚአብሀር አይደለም ለማለት የፈለጉ አይመስለኝም

ቢሆንም ባይሆንም እየሱስ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሄር ነው ምክንያቱም ከመጀመሪያ የነበረው እሱ ነው በዮሐ.1:1:- በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

በሰዎች መካከል ያለው እግዚአብሄር ራሱ እየሱስ ነው ማቴ.1:23:- እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፡- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

ነገር ግን እግዚአብሀር እንደት እንደታረቀን redemption ሲናገር በልጁ እያለ ይተርካል ስፈጸም ደግሞ አብ ይለዋል ።
ክርስትና የሚሞቱና የሚቀሰቅሱ አማልክቶች አይውቅም በልዩ ልዩ እምነቶች እንደሚባለው ሳይሆን ክርስቲአኖት 1 አምላክ አምላኪዎች ነበሩ ናቸውም 1 አምላክ እናምናለን እሱም ሁሉን ቻይ ነው
Jun 23, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ሰላም ወገኔ ከላይ የመለስካቸው መልሶች ፈጽመው የማይገቡና ግራ የሚያጋቡ ናቸው። መጽሃፍ ቅዱስ አንዱ አምላክ አብ ነው ካለ፡ ኢየሱስ ምን አይነት የአምላክ ምድብ ውስጥ ነው የሚገባው? እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ ነው፡ እሱም አብ ነው። ኢየሱስም ሆነ መላእክቶች አምላክ (ኤሎሂም) ተብለው መጠራታቸው፡ አምላክን ወክለው መላካቸውን ለማመልከት እንጂ፡ አምላካዊ መደብ ስላላቸው አይደለም። ዩሃ 10፡30-35 ላይ ጌታ ኢየሱስ የእስራኤል ገዦች ሳይቀሩ ኤሎሂም (አማልክት) መባላቸውን ተናግራል። በተጨማሪ ኢየሱስንና አምላክን ጠንቅቆ ማወቅ ለዘላለም ህይወት መሰረት ነው። ዩሃ 17፡3 ይህንን ግልጽ አድርጎ አስቀምጦታል። ወንጌል ማለትም በኢየሱስ የመስቀል ስራ ማመን ብቻ አይደለም። የኢየሱስና የሃዋርያቶች መልእክት ስለ እግዚያብሄር መንግስትም ጭምር ነው። እናም ረጋ ብለህ መጽሃፍ ቅዱስን መመርመሩ ጥሩ ነው ወገኔ።

መልካም ጊዜ!
ስለ ኢየሱስ አምላክነትና ስለ ስላሴ በሌላ የጥያቄ አምድ ብዙ ውይይት ተድርጎበታል እና እዚያ ላይ ያለውን እንደገና መድገሙ አይጠቅምም። ውይይቱን እዚህ በመጫን ማንበብ ይቻላል።
0 ድምጾች
ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ነው ከዚህ በታች ያለውን ሀሳብ በጥንቃቄ ይመልከቱ እርሶ እንዳሉት ከመሬት ተነስቼ ለማውገዝ አይደለም( እንግሊዝኛ የማንበብ ችግር ያለቦት አይመስለኝም)i think you don't have a problem to read English.እባኮ ይሀን ያንብቡ

1In the beginning was the Word, and the Word was with God, and the Word was God.

In the beginning - This expression is used also in Genesis 1:1. John evidently has allusion here to that place, and he means to apply to "the Word" an expression which is there applied "to God." In both places it clearly means before creation, before the world was made, when as yet there was nothing. The meaning is: that the "Word" had an existence before the world was created. This is not spoken of the man Jesus, but of that which "became" a man, or was incarnate, John 1:14. The Hebrews, by expressions like this, commonly denoted eternity. Thus. the eternity of God is described Psalm 90:2; "Before the mountains were brought forth, etc.;" and eternity is commonly expressed by the phrase, before the foundation of the world." Whatever is meant by the term "Word," it is clear that it had an existence before "creation." It is not, then, a "creature" or created being, and must be, therefore, uncreated and eternal. There is only one Being that is uncreated, and Jesus must be therefore divine. Compare the Saviour's own declarations respecting himself in the following places: John 8:58; John 17:5; John 6:62; John 3:13; John 6:46; John 8:14; John 16:28.

Was the Word - Greek, "was the λόγος Logos." This name is given to him who afterward became "flesh," or was incarnate (John 1:14 - that is, to the Messiah. Whatever is meant by it, therefore, is applicable to the Lord Jesus Christ. There have been many opinions about the reason why this name was given to the Son of God. It is unnecessary to repeat those opinions. The opinion which seems most plausible may be expressed as follows:

1. A "word" is that by which we communicate our will; by which we convey our thoughts; or by which we issue commands the medium of communication with others.

2. The Son of God may be called "the Word," because he is the medium by which God promulgates His will and issues His commandments. See Hebrews 1:1-3.

3. This term was in use before the time of John.

(a) It was used in the Aramaic translation of the Old Testament, as, "e. g.," Isaiah 45:12; "I have made the earth, and created man upon it." In the Aramaic it is, "I, 'by my word,' have made," etc. Isaiah 48:13; "mine hand also hath laid the foundation of the earth." In the Aramaic, "'By my word' I have founded the earth." And so in many other places.

(b) This term was used by the Jews as applicable to the Messiah. In their writings he was commonly known by the term "Mimra" - that is, "Word;" and no small part of the interpositions of God in defense of the Jewish nation were declared to be by "the Word of God." Thus, in their Targum on Deuteronomy 26:17-18, it is said, "Ye have appointed the word of God a king over you this day, that he may be your God."

(c) The term was used by the Jews who were scattered among the Gentiles, and especially those who were conversant with the Greek philosophy.

(d) The term was used by the followers of Plato among the Greeks, to denote the Second Person of the Trinity. The Greek term νοῦς nous or "mind," was commonly given to this second person, but it was said that this nous was "the word" or "reason" of the First Person of the Trinity. The term was therefore extensively in use among the Jews and Gentiles before John wrote his Gospel, and it was certain that it would be applied to the Second Person of the Trinity by Christians. whether converted from Judaism or Paganism. It was important, therefore, that the meaning of the term should be settled by an inspired man, and accordingly John, in the commencement of his Gospel, is at much pains to state clearly what is the true doctrine respecting the λόγος Logos, or Word. It is possible, also, that the doctrines of the Gnostics had begun to spread in the time of John. They were an Oriental sect, and held that the λόγος Logos or "Word" was one of the "Aeones" that had been created, and that this one had been united to the man Jesus. If that doctrine had begun then to prevail, it was of the more importance for John to settle the truth in regard to the rank of the Logos or Word. This he has done in such a way that there need be no doubt about its meaning.
Jul 2, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Jul 4, 2011 ታርሟል
+2 ድምጾች
Was with God - This expression denotes friendship or intimacy. Compare Mark 9:19. John affirms that he was "with God" in the beginning - that is, before the world was made. It implies, therefore, that he was partaker of the divine glory; that he was blessed and happy with God. It proves that he was intimately united with the Father, so as to partake of his glory and to be appropriately called by the name God. He has himself explained it. See John 17:5; "And now, O Father, glorify thou we with thine own self, with the glory which I had with thee before the world was." See also John 1:18; "No man hath seen God at any time; the only-begotten Son, which is in the bosom of the Father, he hath declared him." See also John 3:13; "The Son of man, which is in heaven." Compare Philippians 2:6-7.

Was God - In the previous phrase John had said that the Word was "with God." Lest it should be supposed that he was a different and inferior being, here John states that "he was God." There is no more unequivocal declaration in the Bible than this, and there could be no stronger proof that the sacred writer meant to affirm that the Son of God was equal with the Father; because:

1. There is no doubt that by the λόγος Logos is meant Jesus Christ.

2. This is not an "attribute" or quality of God, but is a real subsistence, for it is said that the λόγος Logos was made flesh σάρξ sarx - that is, became a human being.

3. There is no variation here in the manuscripts, and critics have observed that the Greek will bear no other construction than what is expressed in our translation - that the Word "was God."

4. There is no evidence that John intended to use the word "God" in an inferior sense. It is not "the Word was a god," or "the Word was 'like God,'" but the Word "was God." He had just used the word "God" as evidently applicable to Yahweh, the true God; and it is absurd to suppose that he would in the same verse, and without any indication that he was using the word in an inferior sense, employ it to denote a being altogether inferior to the true God.

5. The name "God" is elsewhere given to him, showing that he is the supreme God. See Romans 9:5; Hebrews 1:8, Hebrews 1:10, Hebrews 1:12; 1 John 5:20; John 20:28.

The meaning of this important verse may then be thus summed up:

1. The name λόγος Logos, or Word, is given to Christ in reference to his becoming the Teacher or Instructor of mankind; the medium of communication between God and man.

2. The name was in use at the time of John, and it was his design to state the correct doctrine respecting the λόγος Logos.

3. The "Word," or λόγος Logos, existed "before creation" - of course was not a "creature," and must have been, therefore, from eternity.

4. He was "with God" - that is, he was united to him in a most intimate and close union before the creation; and, as it could not be said that God was "with himself," it follows that the λόγος Logos was in some sense distinct from God, or that there was a distinction between the Father and the Son. When we say that one is "with another," we imply that there is some sort of distinction between them.

5. Yet, lest it should be supposed that he was a "different" and "inferior" being - a creature - he affirms that he was God - that is, was equal with the Father.

This is the foundation of the doctrine of the Trinity:

1. that the second person is in some sense "distinct" from the first.

2. that he is intimately united with the first person in essence, so that there are not two or more Gods.

3. that the second person may be called by the same name; has the same attributes; performs the same works; and is entitled to the same honors with the first, and that therefore he is "the same in substance, and equal in power and glory," with God.

ባጭሩ ኢየሱስ ፍጡር የሆነ አምላክ ሳይሆን የሥላሰ ሁለተኛ አካል ነው (አምላክ ስጋ ለብሶ) ማለት ነው።
ሮሜ 9፡5አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።

ቲቶ 2፡13 ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤

1ጢሞ 3፡16እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው እርሱ(እግዚአብሔርንም) በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
በተለይ ዕብ1፡10-12 ከ መዝሙር102 ፡25-27 እያነፃጻርክ ተመልከት በተጬማሪ የሓዋ ሥራ 20፡28
Jul 2, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
እግዚአብሄር ይባርክህ ትልቅ ማስትዋል ያለበት መልስ ነው ኢየሱስ መጽሃፍቅዱስ እንደሚናገረው "ቅዱስ ቅዱስ የነበረው ያለውና የሚመጣው ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ" ራዕ 4፡8 ብሎ እንደሚናገረው ነው ።
0 ድምጾች
ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ነው!!!!!
ኢየሱስ የአምላክ ባሕርይ ያለው የተፈጠረ አምላክ ነው ላሉ ወዳጄ የተሰጠ ምላሽ እንዲሁም መፅሓፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ አምላክነት ምን ይላል ብለው ለሚጠይቁ ሁሉ በጥቂቱ ግንዛቤ ለመስጠት::
ከዚህ በታች ያለውን ሀሳብ በጥንቃቄ ይመልከቱ እርሶ እንዳሉት ከመሬት ተነስቼ ለማውገዝ አይደለም
በእርሶ አባባል በተጨማሪ የቱ ጋር ኢየሱስ የተፈጠረ ከፍጥረት አንዱ ብዬ ጻፍኩ ነው እያሉ ያሉት እስኪ የራስዎን አባባል በቀጥታ ወስደን እንመልከት እንዲህ ይላል
(ኢየሱስ ሰው ብቻ ወይም ከፍጥረት አንዱ እንዳልሆነና አምላክም እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎአል። ከፍጥረት በፊት ስለነበረና ያለ እርሱም አንዳች ስላልሆነ፤ ፍጥረት ውስጥ ሊካተት አይችልም።)
ፍጥረት ውስጥ ሊካተት አይችልም ካሉን በሁዋላ ደግሞ....
ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ሲናገር ምን ማለቱ ነው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወራው ስለ ኢየሱስ የዘር ክፍል ወይም ምድብ ነው። ማለትም አበቦችና ቅጠሎች በአትክልት የዘር ክፍል፣ አራዊትና አእዋፋት በእንስሳት የዘር ክፍል እንደሚመደቡ፣ ጥቁሮችና ነጮች ደግሞ በሰዎች ወገን እንደሚመደቡ፣ ሱራፌልና ኪሩበልም ከመላእክት ወገን እንደሚመደቡ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ወይም ከአምላክ ክፍል ነው የሚመደበው።

ይሄ ማለት ግን ኢየሱስ ከአንዱ ከእግዚአብሔር ማለትም ከአብ እኩል ነው ወይም እርሱ ራሱ ነው ማለት አይደለም። ኢየሱስ መለኮታዊ ነው፤ አምላካዊም ባሕርይ አለው ለማለት እንጂ።
በነገራችን ላይ የተወሰነ ደረጃ ድረስ አባባሎትን እደግፈዋለሁ (ወልድ አብ አይደለም አብም ወልድ አይደለም ኢየሱስ እግዚአብሄር ነው) የሚለውን ማለቴ ነው ::
ምድቡ ከአምላክ ክፍል ነው ብለውናል መለኮታዊ ነው እግዚአብሔር ግን አይደለም ታድያ እግዚአብሔር ካልሆነ አምላክ ግን ከሆነ አባባሎት ከፍጥረት በፊት የተፈጠረ የፈጣሪነት ባሕሪ ያለው ፍጡር የሆነ አምላክ ለማለት ፈልገው ካልሆነ ምን ማለት ፈልገው ይሆን?
የሚገርሞት ነገር የጄሆቫ ዊትነሶች ያላቸውን አንድ አባባል ትዝአስባሉኝ
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
የሚለውን የኢሳያስ 9:6 ክፍል ሁሉን ቻይ አይደለም ኃያል አምላክ ማለቱ እንጂ ብለው የሚከራከሩትን ትዝ አስባሉኝ (የኢሳያስ 9:6 ዋናው አላማው የመሲሁን አመጣጥ እና አገዛዝ ያበስራል ቁ.7 ነገር ገን መሲሁ የሚያደርገውን ሳይነግረን በፊት ማን እንደሆነ በመንገር ይጀምራል እዚህ ጋር ማተኮር ያለብን አምላክ ሆኖ ስለ ሚመጣው መሲህ የተሰጠው ስያሜ ላይ መሆን አለበት ''El gibbor'' אֵ֣ל גִּבֹּ֔ור
Original Word: אֵל
Transliteration: el
Phonetic Spelling: (ale)
Short Definition: God በሚለው የሂብሩ NAS Exhaustive Concordance of the Bible with Hebrew-Aramaic and Greek Dictionaries የሚለውን ትርጉም እናገኛለን )
እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ በሌላ ስፍራ ኢየሱስን በምን ሁኔታ አምላክነቱን እንዳስቀመጠው በማነጻጸር እንመልከት
“ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንን እና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው እርሱማ ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ህዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለእኛ ሰጥቶአል ።'' ቲቶ 2.13-14
የታላቁ አምላካችንን እና የአዳኛችን በ ሚለው ላይ (የኢየሱስን አምላክነት) እንመልከተው በዚህ በ ቲቶ መልእክት የኢየሱስ ማንነት እንደ “የተባረከ ተስፋችን” ተገልጾአል:: ቁልፍ የሆነው ቃል ስለ ኢየሱስ “የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን” የሚለው አገላለጽ ነው:: እንግዲህ በተለይ ቁጥር 14“ እርሱማ ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ህዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለእኛ ሰጥቶአል።'' ይሄ በተለይ ብሉይ ኪዳንን ለሚያስተውል ሰው “ያህዌ” ሕዝቡን ይታደግ እንደነበረው በአዲስኪ ዳንም ኢየሱስ ሕዝቡን ሲታደግ እንመለከታለን

# በመዝሙር 130: 8 እርሱም እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል ይላል”
# በሕዝቂል 37: 23 “በጣኦቶቻቸው በአስጸያፊ ምስሎቻችው ውይም በማንኛውም ኃጢአት ራሳቸውን አያረክሱም ነገር ግን እኔን በመተው ከሰሩት ኅጢአት ሁሉ አድናቸዋለሁ አነፃቸዋለሁም:: እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ”

# በዚሁ በሕዝቄል ላይም ያህዌ ሕዝቡን አድናቸዋለሁ ያለበትን ቃል ጳውሎስም ሲጠቀምበት በተለይ አነጻቸዋለሁ እና ሕዝቤ የሚለውን ያስተውሉ የጳውሎስን አጠቃቀም ይሄ ድንገት የሆነ ነው ብለው ያስቡ ይሆን? ይህ ብቻ አይደለም ሌላ በተጨማሪ ማየት የምንችለው አለ

# “አሁንም በፍፁም ብትታዘዙኝና ቃልኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአህዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ ምንም አንኩአ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም” ዘፀ 19:5

(የተወደደ ርስቴ) የሚለውን እንግዲህ ያስተውሉ በዘዳ 7:6 እና 14:2 ያህዌ ለህዝቡ እንደተጠቀመበት ሁሉ በቲቶ ውስጥም ጳውሎስ ክርስቶስ ኢየሱስ የእርሱ የሆነውን ሕዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ በሎ ጽፎልናል::

እስኪ ወደእርሶ ሃሳብ ልመለስ
“ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ሲናገር ምን ማለቱ ነው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወራው ስለ ኢየሱስ የዘር ክፍል ወይም ምድብ ነው። ማለትም አበቦችና ቅጠሎች በአትክልት የዘር ክፍል፣ አራዊትና አእዋፋት በእንስሳት የዘር ክፍል እንደሚመደቡ፣ ጥቁሮችና ነጮች ደግሞ በሰዎች ወገን እንደሚመደቡ፣ ሱራፌልና ኪሩበልም ከመላእክት ወገን እንደሚመደቡ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ወይም ከአምላክ ክፍል ነው የሚመደበው።” በማለት ሃሳብዎትን ቀጥለውልናል

ይሄ ማለት ግን ኢየሱስ ከአንዱ ከእግዚአብሔር ማለትም ከአብ እኩል ነው ወይም እርሱ ራሱ ነው ማለት አይደለም። ኢየሱስ መለኮታዊ ነው፤ አምላካዊም ባሕርይ አለው ለማለት እንጂ።
ብለው የተጠቀሙት የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ፊሊ2:6 “ እርሱ በባህርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቆጠረውም::
ያሰመርኩበትን ልብ እንዲሉት እፈልጋለሁ ኢየሱስ በባህርዩ አምላክ ነው(እግዚአብሔር ወልድ)!!!! እርሶ እንዳሉት(ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ወይም ከአምላክ ክፍል) የሚመደብ አምላካዊ ባህርይ ያለው ፍጡር አይደለም ለዘህም ተጨማሪ መረጃ:-

- ጌታ <እኔ ነኝ> ያለባቸው /with predicate/ በዮሐንስ ወንጌል
1. የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ /6፡35/

2. የአለም ብርሃን እኔ ነኝ /8፡12፣ 9፡5/
3. እኔ የበጎች በር ነኝ /10፡7/
4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ /10፡11፣ 10፡14/
5. ትንሳኤ እና ህይወት እኔ ነኝ /11፡25/
6. እኔ መንገዴና እውነት ህይወት ነኝ /14፡6/
7. እውነተኛ የወይን ግንዴ እኔ ነኝ /15፡1/

- ጌታ <እኔ ነኝ> /ego eimi/ ያለባቸው /absolute/
o ዮሐ 8፡58 <Before Abraham was I am>
o ይህ ጌታ ኢየሱስ <እኔ ነኝ> እያለሇያስተማራቸው ትምህርቶች ፍጹም አምላክ መሆኑን የሚያመሇለክቱና በብለይ ኪዲን እግዚአብሔር ራሱን ከለገጸባቸው ሃሳቦች ጋር የሚገናኙ ናቸው /ዘፀ 3፡14 ፣ ኢሳ 41፡4 ፣ ኢሳ 43፡10፣ ኢሳ 46፡4/
ከዚህ በተጨማሪ ቆላሲያስን 1:15 ጠቅሰውልናል የሄን የቆላስያስ ክፍል የትአርገውት ነው? ቆላ 2:9 “የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ኖራልና” (ፍፁም አምላክ) ፊሊ 2: 5-11 (ፍፁም ሰውነቱን) ያሰየናል

ከራእይ 1:1 ንም አስቀምጠውልናል ነገር ግን ፍጡር የሆነ አምላክ “እንደእርሶ አባባል” ማለቴ ነው ከዚህ በሁዋላ ያሉትን ቃላቶች ይናገራል እንዴ?

“ባየሁት ጊዜ እንደሞተ ሰው ሆኜ በእግሩስር ወደኩ እርሱም ቀኝ እጁን በላዬ ላይ ጭኖ እንዲህ አለኝ አትፍራ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ ሞቼ ነበር እነሆ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲኦል መክፈቻ በእጄ ነው::” ራዕ 1:17-18

“አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ኋዋለኛው መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ ” ራዕ 22:13

በዮሐንስ 14:28 እሄዳለሁ ተመልሼም ወደ እናንተ እመጣለሁ ማለቴን ሰምታችኋል ብትወዱኝስ አብ ከእኔ ስለሚበልጥ ወደአብ በመሄዴ ደስባላችሁ ነበር::

ለምን ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ በመሄዱ ደስ መሰኘት አለባቸው? ደስ ሊያሰኛቸው የሚያስችለው ምክንቱ ምንድን ነው? ኢየሱስ እያላቸው ያለው አብ “ስለሚበልጥ”(greater) እንጂ አብ ስለሚሻል (better) አላላቸውም በሌላ አባባል እግዚአብሔር አብ በስፍራ (positionally) “ይበልጣል የሄነው እንግዲህ የስላሴ ሚስጥር” ከላይ ያነሳሁት ሃሳብ ግልጽ የሚሆንልን ዮሓንስ 17:5 እንግዲህ አባት ሆይ አለም ሳይፈጠር ከአንተጋር በነበረኝ ክብር በአንተዘንድ አክብረኝ:: ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ከእነርሱ ጋራ በገሊላ እና ባካባቢው መቆየት እንደሌለበት በአባቱ ቀኝ በሰማያት መሆን እንዳለበት ሲነግራቸው እናያለን አብ ከእኔ ይበልጣል ያለበትም ምክንያት በስላሴ ባለው ትርጉም መሆኑ እዚጋ ልናስተውል ይገባል::
so we see that the term ''greater'' speaks to the position of the Father in heaven over agains the position of the Son on earth.
ምክንያቱም ወልድ ራሱን በፈቃዱ ባዶ አድርጎአል ፊሊ2:6

ባጭሩ ኢየሱስ ፍጡር የሆነ አምላክ ሳይሆን የሥላሴ ሁለተኛ አካል ነው (አምላክ ስጋ ለብሶ) ማለት ነው።
“አባቶችም የእነርሱ ናቸው ክርስቶስማ በስጋ የትውልድ ሐረጉ ሚቆጠረው ከነርሱ ነው እርሱማ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው አሜን ”።
ሮሜ 9፡5
“ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንን እና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው እርሱማ ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ህዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለእኛ ሰጥቶአል ።'' ቲቶ 2፡13

1ጢሞ 3፡16እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው እርሱ (እግዚአብሔርን) በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።

በተለይ ዕብ1፡10-12 ከ መዝሙር102 ፡25-27 በማነፃፅ ይመልከቱ በተጬማሪ የሓዋ ሥራ 20፡28
እስኪ ዕብ 1:12 እንተ ግን ያው እንተ ነህ ዘመንህም ፍጻሜ የውም::
መዝ 102 : 27 አንተግን ያው አንተ ነህ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ::
ታድያ (ያህዌ) እንዲህ ነው ይለናል የእብራውያን ፀሓፊ ማለትም ወለድ የሥላሲ ሁለተኛ አካል ነው::
ስለ ሥላሴ
Within the one Bening that is God, there exists eternally three coequal and coeternal persons, namly, the Father, the Son, the Holy Spirit.

እግዚአብሔር አንድ ሲሆን በሶስት አካልነት በእኩል ማንነት ይኖራል እነዚህ አካላት አቻ ናቸው አንድ ባህርይ አላቸው እሱም እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነው:: እውነተኛ የክርስትና እምነት የሶስት አማልክት እምነት አይደለም:: በሌላ በኩል ሥላሴ እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት ሦስት መንገዶች እንደሆነ ሊታሰብ አይገባም:: ሥላሴ ማለት ስለ እግዚአብሔር ሕላዌ እና ማንነት የሚናገር እንጂ ራሱን የገለጠበት ሦስት መንገዶች የሚያሳይ አይደለም::

ትልቁ ችግር እኛ ውስን የሆነ አእምሮ ያለን ከመሆናችን የተነሳ ይሄ ግዙፉን
እና ታላቁን እግዚአብሔርን ልንረዳው አንችልም ለዚህም ይመስላል እግዚአብሄርን በራሳችን እይታና መጠን ለማድረግ የሚቃጣን ይሄደግሞ የእግዚአብሔርን ዋና አላማ መሳት ነው የአምላክን ልዩ ባህሪ በተመለከተ ለሰብአዊ አይምሮ የሚገባ ተምሳሌት የለም ስለሆነም ምንም እንኩአ ከሰብአዊ ግንዛቤና ቌንቌ በላይ ቢሆን በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ላይ በመመሥረት ጠምህርቱን በእምነት መቀበል የገባል::
ለሚሰሙኝ ሁሉ ይህን እላለሁ በነገራችን ላይ አትክልቶች የዘር ምድብ አላቸው እንስሳቶችም እንደዚሁ ሰውም ነጭ ጥቁር ተብሎ ተመድቧል መላእክትም የዘር ምድብ አላቸው ብለውናል እንዲያውም ኢየሱስ ከአምለክ የሚመደብ ግን እግዚአብሔር አይደለም ብለዋል በእርሶ አባባል የእረሶ የሃየማኖት ዘር ምድቦ ግን የትኛው ይሆን ? :) :-) :) ከቻሉ ስለ ኢየሱስ እግዚአብሔር ወልድነት ከላይ ያስቀመጥኩትን የእንግሊዝኛ ሃሳብ ይመልከቱት ::
ቸር ይግጠመን
Toto
Jul 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
እነዚህንም ጥቅሶች ልጨምርልህ ሉቃስ 10፣22 እና 1ኛቆሮ.12፣3
የጌታ ሰላም ይብዛልህ
የምትጽፈውን እንደማነበው ለመረዳት እኮ የምፅፈው ፁህፍ እራሱ ይናገራል ቢሆብም ግን እንዳሰብከው እንደዛ መስሎ ከሆነ አይ እያነበብኩ ነው ብዬ መልስ ልስጥህ፡፡ ሌላው ደግሞ በዚህ መንፈስ ቅዱስን ተሞልተናል በልሳን እንናገራለን እየተባለ የሰዎቹ ህይወትና አስተሳሰብ ሲታይ ግን ተሞልተናል የሚሉ ወይም ተሞልተዋል የሚባሉ ሰዎች በዚህ ዘመን በግልጽና በድፍረት የእግዚአብሔርን እውነተኛ ቃል እየሸራረፉ ለገዛ ፍላጎታቸውና ሰዎችን ለማሳት እንደፈለጉ የሚሆኑበት ዘመን መሆኑን አንተ እራስህ የሚታውቀው ይመስለኛል ስለዚህ ተሞልቻለው በማለት እና እናገራለው በማለት ለእውነተኛነት ማረጋገጫ እነኝህን ነገሮች መጥቀስ ምና አልባት እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርነቱ ለማያውቁት ለእነሱ መሸወጃ ይሆናል እንጂ ለመንፈሳዊያን ግን እውነትን የሚመረምር መንፈስ ስላላቸው ከመጋለጥ በስተቀር ለመሸወድ መሞከር ላም አለኝ በሰማይ …. አይነት ነው ሚሆነው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለው የሚያወራው እኮ ያው አብ ያለውን ወልድ የተረከውን መንፈስ ቅዱስ ኃይል የሆነውን ያንኑ ነው ሚያስተጋባው እንጂ ሌላ መረዳት በድፍረት አይናገርም ስለዚህ ተሞልተና የሚባለው መንፈሱ ከወዴት እንደሆነ ሊለይ ሊረጋገጥ ይገባዋል
ሌላው ደግሞ የት ህብረት ውስጥ እንደምትካፈል የጠየኩህ ህብረት የምታደርግበት ቦታ ስሩን ማወቅ ፈልጌ እንጂ ስተተኛነት ለማወጅ ስም ለማውገዝ ቢሆን ኖሮ እኮ እስካሁን ምትናገረው ነገር በቂ ነገር ነበር ግን ከዚህ ያለፈ ለማውራት እንዲመችና እንዳልከው በእግዚአብሔር ቃል በእውነት ለመማማር የት ህብረት እንደምትካፈል ከመገመ ማወቅ ይጠቅማል ብዬ ስላሰብኩ ብቻ ነው፡፡
ለማናቸውም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንደቆመ ሚመስለው……. እንዲጠነቀቅ ይናገራልና መቆማችንን ብቻ ሳይሆን መሰረቱ እውነተኛ መሆኑን ማጣራት ይጠቅመናል በእውነተኛው መሠረት ላይ በቃልና በመንፈስ መታገዝ በፊደል ከመሞት እውነተኛ መንፈስንም በመቀበል በህይወት መኖር እንዲሆንልን ማኞቴ ነው
አሁንም ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተ አምላክ ነህ የህያው የግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስም ነህ ስፍራን ልታዘጋጅልን በሄድክ ጊዜ ኃይል የሆነልንንና ወደ እውነት የሚመራንን መንፈስ ቅዱስን አስተዋውቀኽን የሄድክ ታማኝ ጌታ ነህ ቃልህም እውነት ነው ያለህና የነበርክ የምትመጣም ጌታ አንተ ብቻ ነህ የተባረከው ተስፋችን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!!! አሜን ቶሎና
ሰላም ወንድሜ
ስለ ምኞትህም ስለ ምክርህም እግዚአብሔር ይባርክህ።

አንድ ነገር ብቻ ለመጨመር እፈልጋለሁ። የተሰቀለውን ኢየሱስን ከሚመሰክርና እርሱን ብቻ የመዳኛ መንገድና ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚመሰክር የበለጠ ምን እውነተኛ መንፈስ አለ? ከተመሰረተውስ ከአንዱ እውነተኛ መሰረት ከክርስቶስ በስተቀርስ ምን መሰረት አለ? ስለዚህ እውነተኛ መንፈስም ይሁን እውነተኛ መሰረት መጽሃፍ ቅዱሳዊ የሆነ መለያና መመዘኛ አላቸው። እርሱም የሞተው፣ ሞትን ድል አድርጎ ከሙታንም የተነሳው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው እንጂ የሃይማኖት መግለጫችን አይደለም። ስለዚህ መንፈስንም ይሁን የቆምንበትን መሰረት ስንፈትን፤ መመዘኛችን የተሰቀለው ኢየሱስ እንጂ የሃይማኖት መግለጫዎቻችን ሊሆን አይገባም እላለሁ።

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን!
አንተ ከላይ "መጠበቂያ ግንብ ... ክፉ መንፈስ.. አጋንንት" ምናምን ብለህ ያልከው ሰው። በእውነት ነው የምልህ እግዚአብሔር ይህን ሃጢአትህን እንዳይቆጥርብህ ከልቤ እለምነዋለሁ። እባክህን ተጠንቀቅ፣ እኔን እንደፈለግህ መስደብ ትችላለህ ነገር ግን በላዬ ያደረውን ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ላይ ቃል እንዳትናገር በጌታ ፍቅር እማጸንሃለሁ።

በተለይ ይሄ አባባልህ እጅግ ያስደነግጠኛል፦ "ምናልባት ይህ ሰው የተሞላው ክፉ መንፈስ ይሆናል አጋንንትም ልሳን አላቸውና" ብለህ ያለከው ቃል።

ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አጋንንትን ሲያወጣ ተቃዋሚዎቹ ከሃይማኖት ቅንዓትና ከጥላቻ የተነሳ የተናገሩትንና ኢየሱስ ደግሞ የመለሰውን እባክህ በጥሞና አንብብ። ማቴ 12፡24-32 ለእኔ ሳይሆን ለራስህ ለህይወትህ ተጠንቀቅ!

ይሄንን ያንተን ባህርይን ነበር ቅድም የጠቀስኩት። አንደኛ ምን እንዳልኩ በትክክል ሳታነብብ ወደ ውግዘትና ወደ ፍርድ ሄድክ ለዛውም መንፈስ ቅዱስ ላይ ቃል ለመናገር ቸኮልክ።

በቅድሚያ ኢየሱስ ክርስቶስን እስቲ ያላከበርኩበት ቦታ የት ነው? ልታሳየኝ ትችላለህ? ኢየሱስንስ ማክበር ማለት ምን ማለት ነው? ሁለተኛ እኔ መጽሃፍ ቅዱስን የምረዳውና "የመጠበቂያ ግንብ" ያልካቸው ጆቫዎች የሚረዱት መረዳት እጅግ የተለያየ ነው። እነርሱ የኢየሱስን አምላካዊ ባህርይ አይቀበሉም እኔ እቀበለላሁ፣ እነርሱ መንፈስ ቅዱስን መሞላት ወዘተ የሚባል ነገር አያምኑም እኔ አምናለሁ። እነርሱ የእነርሱ ድርጅት ውስጥ የሌለ ሁሉ አይድንም ይላሉ፤ እኔ ደግሞ መዳን በድርጅት ሳይሆን በክርስቶስ ነው እላለሁ። እንዴት አድርገህ ነው እውነትን ሳትይዝ በሃሰት ሰውን የምትከስሰው? ለሃይማኖታቸው ቅንዓት ሲሉ ክርስቶስንና እስጢፋኖስን በሃሰት ከስሰው ካስገደሉት ከአይሁዶች አንተ በምን ትለያለህ? ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ በማለትህ ብቻ?

እንደ እነርሱ በሃሰት ሰውን ትከሳለህ፣ እንደ እነርሱ መንፈስ ቅዱስ ላይ ቃል ትናገራለህ፣ ስልጣን ቢኖርህ ደግሞ በድንጋይ የምታስወግረኝ ይመስለኛል። ወንድሜ በጌታ ፍቅር እለምንሃለሁ፤ ንስሃ ግባ። በሃይማኖትህ ጥላ አትታመን።

ይሄ ሁሉ የምመክርህ ለአንተ ብዬ እንጂ እኔን እንደፈለግህ ብትሰድብ ግድ የለኝም። ስለ ሃስት ክሱም ይሁን ስለ ውግዘቱ ሁሉ ጌታዬን አመሰግነዋለሁ። ብቻ ከሃሰት መስካሪዎች፣ አሳዳጆችና ከወጋሪዎች ወገን ሳይሆን ሁል ጊዜም ከሚሰደዱትና ከሚወገሩት ወገን እንዲያደርገኝ እግዚአብሔርን እለምናለሁ።

እግዚአብሔር ይባርክህ!
ዉድ ውገኖች
ምልልሳችሁን ሳነብዉ መልካምም ደግሞም ምልካም ያልሆነዉንም ኣይቻለሁ
ከመልካሙ ስጀምር
* መጻሃፍ ቅዱስን መሰረት ኣድርጋችሁ መነጋገራችሁ
*በኣብዛኛዉ ኣንዱ ሌላዉን በማመስገንና በመባረክ መወያየታችሁ
* ጠልቅ ባለ እዉቀት መከራከራችሁና.......ሌሎችም
ያልተመቸኝ ደግሞ

* መካሰሱ፣ ኣንዱ ተሰዳጅ ሌላዉ ኣሳዳጅ ለመምሰልና ለማስመሰል መሞከር በተጨማሪም ተሰዳጅን ሁሉ እዉነተኛ ማስመሰሉ

*ግልጥ የሆነ መረጃ ቀርቦ ሳለ ቢቻል ተማምኖ ካልሆነም እንደ ልዩነት ሃሳብ መያዝ ሲቻል ኣሁንም ኣሁንም ያንኑ መፍጨትና ሌሎችም
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...