ዶክትሪን ማለት በቀጥታ የአማርኛ ትርጉሙ አስተምህሮት ማለት ሲሆን ዊኪፔዲያ እንደሚከተለው ያብራራዋል፦
Quote:
Doctrine (Latin: doctrina) is a codification of beliefs or a body of teachings or instructions, taught principles or positions, as the body of teachings in a branch of knowledge or belief system
የላቲኑ ቃል
doctrina ትምህርት ማለት ሲሆን፤ እምነትን በተመለከተ ዶክትሪን ማለት በቀላል አማርኛ የተለያዩ አመለካከቶችን ያካተተ የእምነት ትምህርት ወይም እምነተ አስተምህሮት ማለት ነው።
በዘመናችን እያንዳንዱ የክርስትና ሃይማኖት ከሌላው የሚለይበት ወይም የሚመሳሰልበት ዶክትሪን ወይም እምነተ አስተምህሮት አለው። ለምሳሌ፦ እንዴት ነው መዳን የሚቻለው በሚለው ጥያቄ ላይ ወይም ማርያምን በተመለከተ ወይም ጥምቀትን በተመለከተ ወዘተ የተለያዩ ዶክትሪኖች ወይም አስተምህሮቶች አሉ። አንድን ሃይማኖት መከተል የሚፈልግ ሰው እንግዲህ የዚያችን ሃይማኖት ዶክትሪኖች ወይም አስተምህሮቶች
(መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሆኑም አልሆኑም
) መቀበል አለበት ማለት ነው።
ብዙ ጊዜ ሃይማኖቶች የራስቸውን ዶክትሪኖች ወይም አስተምህሮቶች፤ ከመጽሐፍ ቅዱስም አስተምህሮት በላይ ስለሚያዩት፤ ከዶክትሪናቸው አንዱን ያልተቀበለ ሰው በብዙ ሃማኖቶች ዘንድ እንደ አሳችና የተረገመ ተደርጎ ስለሚታይ ስደትና ጥቃት ሊደርስበት ይችላል። ብዙ ጊዜም በሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ እነዚህ የሃይማኖቱ ዶክትሪኖች ሊደራደሩባቸው የማይችሉ ተደርገው ነው የሚታዩት። ስለዚህም አንዴ የተሳሳተ ዶክትሪን አንድ ሃይማኖት ከተቀበለች፤ ያንን ለማረም ፈጽሞ የማይቻል ነው የሚሆነው።
ሆኖም ግን ዶክትሪን ለእምነት ብቻ ሳይሆን ለሌላም የአስተሳብ ወይም የአመለካከት ዝንባሌ የሚያገልግል ቃል ነው። ለምሳሌ ሳትቀደም ቅደም ጦርነት
(preventive war) ወይም በማን አለበኝነት የዓለምን ህብረተሰብ እሺታ ሳትጠብቅ ለብቻህ መንቀሳቀስ
(Unilateralism) ወዘተ ያሉት አመለካከቶች የፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ዶክትሪን
(The Bush Doctrine) በመባል ይታወቃሉ።