ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 20 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እባካችሁን የጆቫ እምነት እና የኦንሊይ ጂሰስ እምነት ምን እንድሆነ እብራራሉኝ

Apr 5, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
በነገራችን ላይ ኦንሊ ጀሱስ የሚባል ሃይማኖት የለም ለምሳሌ ጰንጤ የሚባል ሃይማኖት የለም ሰዎች ሲሳደቡ ነው ጰንጠ የሚሉት ወይም ወይም በመንፈስ ቅዱስ በዝህ ዘመን መውረድ ያምናሉ ለማለትም ይሆናል ጴንጤ የሚለውን ስያሜ የሰጡት ፡ ኦንልይ ጀሱስ ማለትም ኢንደዚያው ነው ኢንጂ ኦንልይ ጀሱስ የሚባል ሃይማኖት የለም፡ ምናልባትም በኢየሱስ ስም ነው የሚጠመቁት ለማለት ይሆናል ኢንደሱ ለማለት ከሆነ በኢየሱስ ስም የሚተመቁ የስላሴ አማኞችም አሉ መጽሃፍ ቅዱስ ላይም የእየሱስ ስም ጥምቀት ብዙ ቦታ ተጠቅሶአል በአጭሩ ግን ኢትዮጲያ ውስት ሃዋርያዊት በተክርስቲአን ሲባሉ በኢየሱስ ስም ያጠምቃሉ አብ ወልድ መነፈስ ቅዱስ 1 አማልክ ነው ብለው ያምናሉ
ይህዋ ምስክሮ ደግሞ ኢግዚአብሄር አብ ሁሉን የሚችል አልላክ ሲሆን ኢየሱስ ደሞ አምላክ ነው ግን ሁሉን አይችልም ይላሉ( Mighty ,Almighty)
ተባረኩ
በእኔ መረዳት ትክክለኛ ትምህርትና የሐሰት ትምህርት የተመሠረተው በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ላይ ነው፡፡
ስለዚህ አንደኛው ቡድን በራሳቸው መ/ቅ ላይ ስለ ኢየሱስ In the beginning was the word, the word was with God and the word was a god.small g(John 1:1)---Watch Tower
ሥላሴን ስለሚክዱ ደግሞ መ/ቅ እንዲህ ይላል Who is a lair but he who denies that Jesus is the Christ.He is antichrist who denies the Father AND the Son.(1John 2:22)

3 መልሶች

0 ድምጾች
እኔ እንደሚገባኝ አንድ ትልቅ ልዮነት አላቸው ጆቫ ገነት ምድር ላይ ናት ሲሉ ኦንሊ ጂሰሶች ግን በዚህ አያምኑም ሌላውን ከኔ የተሻለ እውቀት ያለው ሰው ቢያስረዳዎት ደስ ይለኛል፡፡
Apr 5, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
+1 ድምጽ
ኦንሊ ጂሰስ

ኦንሊ ጂሰስ ከሌሎች ክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ ከፕሮቴስታቶች ጋር ካለ አንድ ጉዳይ በስተቀር ብዙ ተመሳሳይነት አለው። ሰው በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ በጸጋው ብቻ እንደሚድን ያምናሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ያምናሉ ወዘተ። ዋናው ከሌሎች ክርስቲያኖች የሚለያቸው ጉዳይ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሶስቱም ኢየሱስ ናቸው በሚለው ትምህርታቸው ነው። እንደ እነርሱ መረዳት ከሆነ አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም አንድ ነው እርሱም ኢየሱስ ነው የሚል ነው። ስለዚህ ባልተከፋፈለ በአንድ እግዚአብሔር ያምናሉ፤ ሆኖም ያ እንድ እግዚአብሔር ለእነርሱ ኢየሱስ ብቻ ነው። እንደ አብ ሆኖ ራሱን የገለጠውም ኢየሱስ ነው፤ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በሥጋ ተመላልሶ የሞተውም ኢየሱስ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ኢየሱስ ነው።

እንደ እኔ አመለካከት ይሄ አብም ኢየሱስ ነው፤ ወልድም ኢየሱስ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ኢየሱስ ነው የሚለው አመለከካከት፤ የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቦ ከማየት የመጣ እንጂ እንዲህ ያለ ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት አይቻልም። "እኔና አብ አንድ ነን"ዮሐ 10፡30 የሚለውን ጥቅስ እንኳን ብንወስድ፤ በዚህ ክፍል በግሪኩ "አንድ" ብሎ የተጠቀመበትን ቃል ጌታ ለደቀመዛሙርቱ አንድነትም ያንኑ ቃል ሲጠቀምበት እናያለን።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 17
11 ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።

ይሄ ማለት ታዲያ ደቀመዛሙርቱም ሁሉ አንድ ሰው ናቸው ማለት አይደለም። በተጨማሪም በብዙ ቁጥር "እኔና አብ አንድ ነ" እንጂ በነጠላ "እኔና አብ አንድ ነ" አላለም። አብም ወልድም ራሱ ኢየሱስ ቢሆን "እኔና አብ አንድ ነ" እንጂ "ነን" ማለትም ባላስፈለገው።

ይሄ የአንድነትን አስተምህሮት (The oneness doctrine) የሚቃረን በጣም በጣም ብዙ ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማውጣት ይቻላል። ሆኖም እኔ ኦንሊጂሰሶች ስለ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የተምታታ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ አይድኑም ለማለት አልችልም። ምክንያቱም በመስቀሉ የጸጋ ማዳን የሚያምኑና የመንፈስ ቅዱስንም ሙላት የሚቀበሉ ናቸውና።

የጆቫ እምነት

ትንሽም ቢሆን ከጆቫ አማኞችና እምነት ጋር ንክኪ ነበረኝ፡፡ በአንድ ቃል ለማለት የምፈልገው፤ የጆቫ እምነት እጅግ የተምታታ፤ ቃሉን የሚያጣምም በፍጹም ከመንፈስ ቅዱስ ሊሆን የማይችል እምነት ነው። ጆቫ ከእምነት ይልቅ አንድ በሃይለኛ ቁጥጥር ስር የሚተዳደር ድርጅት ነው። በክርስቶስ ማዳን እናማናለን ይላሉ፤ ነገር ግን ከጸጋው ይልቅ እጅግ በሥራ የሚያምኑ፤ ሰዓት እያስመዘገቡና እየወጡ የድርጅቱን መጽሔት እንዲያድሉና ድርጅቱ በሚሰጣቸው ሥራ እጅግ የሚያምኑ ናቸው። ብዙዎቹ በጣም ያሳዝኑኛል። ክርስቶስንና የጸጋውን መንፈስ ጨርሶ የማያውቁ ነገር ግን በአንድ ድርጅት ኃይለኛ ቁጥጥር ውስጥ ወድቀው ያሉ ናቸው።

ከሁሉም በላይ ለክርክር ጥቅሶችን በዝርዝር ከመያዝ በስተቀር ቃሉን ጨርሰው የማያውቁ ናቸው። ብዙዎቹ የድርጅቱን "የመጠበቂያ ግንብ" መጽሔቶች እንጂ የወንጌሉን ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስን ራሳቸው በግል በሙሉ አንብበው አያውቁም። ስለዚህ በጣም ለተምታታው የድርጅቱ አስተምህሮት የተጋለጡ ናቸው።

መንፈስ ቅዱስን እንኳን ሊሞሉ ይቅርና፤ የሆነ ኃይል ነው ስብዕና የለውም የሚሉ ናቸው። የጸጋ ስጦታዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ በኋላ ቀርቷል ወዘተ የሚሉ እጅግ የተሳሳቱ እምነቶችን የሚከተሉ ናቸው። ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ክርስቶስን በመንፈስ ቅዱስ አልተለማመዱትም። ሁሉ ነገር በሥጋዊ አዕምሮ፣ በመጽሔታቸውና በህግ ነው።

ማንንም በእውነት በክርስቶስ የዘላለም ሕይወትንና ድነትም ማግኘት የሚፈልግን ሁሉ የምመክረው፤ ከጆቫ ድርጅት እንዲርቁ ነው። ይሄ ሰው በነጻነትና በእግዚአብሔር ጸጋ እግዚአብሔርን እየወደደ በመንፈስ ቅዱስ ደስታ የሚኖረው የእምነት ሕይወት ሳይሆን፤ እድሜ ልክ ድርጅቱ የሚጭነውን ሸክም ተሸክሞና መፈናፈኛ አጥቶ በባርነት የመኖር ኑሮ ነውና።

ስለዚህ እንደው አትሞክሩት እላለሁ። ፈጽሞ የክርስቶስ መንፈስ አይደለም እዛ የሚሠራው። ክርስቶስን አንዳንዴ ከማንሳት በስተቀር ክርስቶስን የሚያከብርና የእምነቱ ማዕከላዊ የሚያደርግ ነገር የላቸውም። ስለዚህ ሰዎች ከዚህ ድርጅት እንዲርቁ በጌታ ፍቅር አጥብቄ አሳስባለሁ!
Apr 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ጌታ ይባርክህ "ሆኖም እኔ ኦንሊጂሰሶች ስለ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የተምታታ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ አይድኑም ለማለት አልችልም" የተማታታ አሰተሳሰብ ብቻ አይደለም ለምሳሌ የጆቫ እምነት ተከታዩች ገነት በምደር ነች ይላሉ ይህ የተማታታ አሰተሳሰብ በቻ እይደለም እምነታቸሁም ጭምር ነዉ የኦንሊጂሰሶችም እምነታቸሁም ጭምር ነዉ ሰለዚህ ስላሴን ሳያምኑ መዳን አለ እንዴ? 2 ሚሊዩን ህዝብ በዚህ የስህተት ትምህርት ዉስጥ ተዘፍቆ ይገኛል መዳን የሚገኝሁ ክርስቶስ እየሱስን በማመን እንደህነ ምንም ጥርጥሮ የለኝም የአማኞች ትልቁ እስተምህሮት ድግሞ ሰላሴ ነወ የኦንሊ ጂሰስ አስተማሪ የነበር "ከ20በላይ"
አሁን ወደ ጌታ መተቶል ሲናገር ለንዚህ ሰወች ልንደርስላቸሁ ይገባል በዙቹ በሴይጣን መንፍስ ታሰረዉ ነወ የሚገኙት ነዉ ያለሁ በመንፍስ ቅዱሰ እናምናለን ቡሉም በዳቢይሉስ መንፍስ ተይዘሁ ነዉ የሚገኙት እንዲድኑ ልንፀልይላቸሁ ይግባል
ኦንሊ ጂሰስ ከሌሎች ክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ ከፕሮቴስታቶች ጋር ካለ አንድ ጉዳይ በስተቀር ብዙ ተመሳሳይነት አለው።

በመጀመሪያ ኦንልይ ጀሱስ ራሱ ፕሮትእስታንት ነው ሁለተኛ ፕሮተስታንት ወይም ኦንልይ ጀሱስ የሚባል ሃይማኖት የለም ኦንልይ ጀሱስ ከስላሴ አምኞች ጋር ብትለው ጥሩ ይሆን ነበር

አብ ወልድ መነፈስ ቅዱስ 3ቱም እየሱስ ናችው ብለው ያምናሉ ያለህ ማን ነው ? ጠያቂዋ ትክክለኛ መረጃ ትፈልጋልች ያናበብክበትን መጽሃፍ ርእስና ገጽ ወይም ወብ ሊንክ መለጠፍ ጥሩ ነው። እውነቱ ግን አብ ወልድ መነፈስ ቅዱስ ሶስቱም እየሱስ ነው ብለው ሳይሆን የሚያምኑት አብ ወልድ መነፈስ ቅዱስ 1 አምላክ ነው ብለው ነው። ያ 1ዱ አምላክ ደግሞ በስጋ የተገለጠ ነው ብለው ያምናሉ ።

ዮሃ.17.11 አብና ወልድ ቸርች ውስጥ እንዳሉ ሁለት ሰዎች ናችው ብሎ እንዲረዳ ከሆነ ያቀረብከው አንተም ራስህ ከስላሴ ትምህርት ጋር ትቃረናለህ ዮሃስ 17 11 ስለ ማን ይናገራል የሚል ርእስ ቢኖርህ መልስ መስጠት ይቻላል ጠያቂያችንን ላለማሰልቸት

ሌላው ግን እግዚአብሀር ይባርክ ድነዋልም አልዳኑምም ለማለት ሁላችንም ስልጣን የለንም

ተባረኩ
'ስላሴን ሳያምኑ መዳን አለ እንዴ?' መዳን ብስላሴ ያደረገው ማን ነው ?መጽሃፍ ቅዱስ ኢንደውም አማራች አይሰጥም መዳን በእየሱስ ብቻ ነው ሐዋ.4:12:- መዳንም በሌላ በማንም የለም፤

የአማኞች ትልቁ እስተምህሮት ድግሞ ሰላሴ "" ኢንደውም ካል ስላሴ ትምህርት የለውም ዝም ብሎ ማመን ነው የጉባኤ ውሳኔዎችን በመቀበልና በመስማማት ነው ስላሴ የሚታመነው ኢንጂ ትምህርት የለውም

ነገር ግን የሚታመነው የምንማረውም መጽሃፍት ሁሉ የሚመሰክሩት ስለ እየሱስ ነው """"ዮሐ.5:39:- እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤

አንተ ስለ 20 ሰዎች ነው የምታወራው እንሱ ደግሞ 2 ሚሊዮኑም ከስላሴ እምነት ነው የመጣነው የሚሉት

ሰይጣን አለበት ... ከማለት ግን መጸለዩ ትሩ ነው አለም በልጁ ኢንዲድን ነው ኢንጂ በአለም ሊፈርድ አልመጣም

ተባረኩ
ኦንሊ ጂሰስ እምነት አደገኛ እና ስውን ወደ ዘላልም ጥፋት የሚሰድ ነው። ስለዚህ የስህተት ትምህርት ነው። >>የመዳን ባለቤት አብ ነው። አብ ሰለ ወደደ ወልድን ላከ፤ ወልድ ታዞ መጣ። ወልድ ዋጋ ሰለኛ ከፍሎ ወደ አብ ሲሄድ፤ መንፈስ ቅዱስ ላከልን። ይህ ሊአደናገር አይገባም መዳን በ ጌታ ነው አዎ። የምንድነው ከሰኦል በቻ ሳይሆን የጥል ግድዳም ፈርሶአል በዚህ በምድር አሁን በጌታ ከ ሆንን በአብ ፊት መቅረብ ችለናል ይህን ነው አዳም ያሳታን አንዱ ከአብ ጋር ህብረት ማድረግ ጭምር ነው።
የመዳን ባለበት አብ ነው ??? ምን ማለትህ ነው የስላሴ ኣማኝ ትመስላልህ ... ያንተ ደግሞ ለየት ያለ ነው ወልድ ማዳን ኣይችልም ለማለት ነው???? ኦንልይ ጀሰስን ለመቃወም ብልህ ከእየሱስ ጋር እንዳትጣላ >> ኣሁን እየሱስ ክርስቶስ የለም እንዴ ? እነሆ እስከ አለም ፍጽሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ አለልም እንዴ [? አብ ወልድ መነፈስ ቅዱስ 1 አምላክ ነው ብለህ ብታምን ኖሮ አንደኛው ሲሄድ አንደኛው መጣ እያልክ የእምነት ድርጅቱን አትሳደብም ነበር አሁንም ለጠያቂያችንም ሆነ ላንተ የሃዋርያት ቤተክርስቲያን አብ ወልድ መነፈስ ቅዱስ 1 አምላክ ነው ብላ በማመኑዋ ነው ኦንልይ ጀሱስ የተባለችው ወይም በኢየሱስ ስም ስለምታጠምቅ ነው ኦንልይ ጀሱስ የተባለቸው
ጌታ አብዝቶ የባርክዎ ስም-አልባ እኔ በእግዚአብሄር አንድ እና ሶስት እነት አምናለሁ ትንሽ ላብራራ፡-
ዮሓ3፡16
"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"
ላኪ ማነው ብንል የልጅ አባት " አብ" ነው በዚህ ረገድ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር መታረቅ ሃሳቡ የመታው ከአብ መሆኑ ያሳያል። ጌታ በዙ ግዜ አብ የላከኝ የላል ሰለዚ እዳችንን የከፋላ እርሱ ነው መዳን በክርስቶስ እየሱስ በማመን ብቻ ነው ።ሌላው ደግሞ ዮሐ16፡7-15 ቢመለከቱ ስለ መ/ቅ ጌታ የሚናገረውን ሃሳቤ ይገባዎታል ብይ አምናለሁ። እ/ዚ አብ አምላክ ነው. እ/ዚ ወልድ አምላክ ነው. እ/ዚ መ/ቅ አምልክ ነው፤ አብ ወልድ አይደለም ወልድም አብ አይደለም ይህን አሳስቶ ወልድ አብ ነው ወልድ መ/ቅ ነው ማለት ስህተት ነው። የኦንሊ ጂሰስ ስህተቱ ( what makes it cult is this) ይህን መካዱ ነው ። ከተሳሳትሁ ያርሙግኝ አመስግን አለሁ።
ከሁሉ አስቀድሜ ሁላችሁንም ኤግዚአብሔር ይባርካችሁ እያልኩ፥ በመጀመርያ የስላሴ አማኞች ነን የምንል ማወቅ አለብን ብዬ የማስበው እግዚአብሔር አምላክ እንጂ በፍጹም ፐርሰን አይደለም፥ በፐርሰናሊቲም አይገለጽም። ሁለተኛው ደግሞ እግዚአብሔር አምላክ መንፈስ ነው እንጂ አካል የለውም። መንፈስ አካል የለውምና። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ራሱ የእግዚአብሔር ጣት፥ የእግዚአብሔር ክንድ ፥ የእግዚአብሔር ሙላት፥ ማንነቱ ነው። ወልድም በመጀመርያ ቃል የነበረ፥ በእግዚአብሄር ዘንድ የነበረ ብቻ ሳይሆን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የነበረ፥ በሁዋላ ግን በስጋ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው። በርሱ ዉስጥ አብ አለ፥ በአብ ውስጥም ወልድ አለ። በአባቱም ቀኝ ተቀምጦ አሁን የሚማልድልን እርሱ ነው። አብም ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶለታል። እርሱም ለአብ ይገዛል። መንፈስ ቅዱስ የአብ መንፈስ እንደሆነ ሁሉ የኢየሱስም መንፈስ ነው። ይህን ነገር ስንመረምር እንግዲህ መጽሓፍ ቅዱስን ለሚያምን ሁሉ ግልጽ የሚሆነው ነገር እግዚአብሄር አንድ መሆኑ ነው። አሐዱ አምላክ። አሜን።
ነገር ግን ሰው ሁሉ በተረዳበት በዚያ አንዲመላለስ፥ አምላኩንም በፍጹም ልቡ እንዲወድና እንዲያገለግል ፥ ሌላውን አማኝ አልዳነም ብሎ ከመፍረድ እንዲቆጠብ፥ በተለይም በርኩስ መንፈስ ነው የሚሞሉት ብለን ምናልባት የእግዚአብሔርን መንፈስ ሰድበን ስርየት ወደሌሌው ሃጢአት እንዳንገባ እመክራለሁ። ጌተችን እንዳለው ጠላት የዘራው እንክርዳድ እንኳን ቢኖር እኛ ልንነቅለው አንሌዬውምና ስንዴ ስናጠፋ እንዳንግኝ ለጌታ እንተወው።
እግዚአብሔር አምላክ ነው ፥ ለኛም በራልን። አሜን።
0 ድምጾች
ኦንሊ ጂሰስ እንደሃይማኖታዊ ተቋም አለ። በካናዳዊ ኢቫንጀሊስት በ1913 ዓም በካሊፎርኒያ ስቴት ተመሰረተ። እግዚአብሔር አንድ ገጽ፣ አንድ አካል እንጂ አብ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በሚል የስም፤ የግብር እንዲሁም የአካል ሶስትነት የለውም የሚል አስተምህሮ የዶክትሪኑ መሰረት ነው። አንዱ ኢየሱስ ራሱ ነው በሶስት ገጽ የተገለጠው ነው የሚል ትምህርት ያስፋፋል።
«እኔና አብ አንድ ነን» ዮሐ10፣30 የሚለውን እኔና እኔ አንድ ነን ማለቱ ነው የሚሉ ይመስላሉ። «እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ አይላክላችሁም የሚለውም እኔ ራሴ አጽናኙን ሆኜ ልመጣላችሁ ነው ማለቱ ነው የሚሉም ናቸው። ከእስልምና ዶክትሪን የሚለየው መሐመድን ባለመቀበል ብቻ ነው። ይህ አስተምህሮ የ3ኛ ው ክ/ዘመን መናፍቅ አግናጢዮስ አስተምህሮ ነው። ይህንን ይጫኑት ከዚያ ባሻገር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን እውነታ ካልፋቀ በስተቀር ኢየሱስን ውሸታም አድርጎ «አባቴ» የሚለውን ሁሉ ራሱን ለመግለጽ በሽወዳ የተጠቀመበት ቃል ነው ማለት የጤንነት ሊሆን አይችልም።
ጄሆቫ የሚባሉት ደግሞ የ3ኛው ክ/ዘመን ግብጻዊ መናፍቅ የአርዮስን አስተምህሮ የሚያንጸባርቁ ናቸው። እግዚአብሔር ወልድን ፈጠረ፤ ፍጥረትን ሁሉ ደግሞ በእሱ ፈጠረ በማለት ኢየሱስን ትንሹ እግዚአብሔር አድርጎ የሚስል አስተምህሮ አላቸው።
ስለጄሆቫ ማንነት ተስፋዬ ሮበሌ ጥሩ አድርጎ የጻፈውን ከዚህ በፊት የሰጠሁትን የፒዲኤፍ ሊንክ ልደግም እገደዳለሁ። ይህንን ይጫኑ ቁጥር 1...ይህንን ይጫኑ ቁጥር 2.
ሁለቱም ድርጅቶች ዞሮ ዞሮ ቀደምት መናፈቃን የመሰረቷቸው ናቸው።
Apr 9, 2012 ብርሃን (1,840 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...