ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 24 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አንድ ክርስቲያን የሆነ ሰው ገና ዳግም ካልተወለደች አህት ጋር ጋብቻ ሊመሰርት ይችላል?

መጽሀፍ ቅዱስ የሚለው ነገር አለ ወይ? ምን ያስትምርናል?
Apr 6, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ካልተወለደች ማለት በእናትዋ ማህጸን ያለች ማለት ነው?
ሰላም
ጠያቂው "ካልተወለደች" ብቻ ሳይሆን ያለው "ዳግም ካልተወለደች" ነው ያለው። ስለዚህ የሚያወራው ስለ ዳግም ልደት ወይም ዳግም መወለድ ነው።

ስለ ዳግም መወለድ ደግሞ የሚከተሉትን ጥቅሶች ከመጽሃፍ ቅዱስ ማንበብ ይበልጥ ግንዛቤ ይሰጣል፦

የዮሐንስ ወንጌል 3:3
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡23
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡35

1 መልስ

+1 ድምጽ
በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 7 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በትዳር ነክ ዙሪያ በተለይ ላላገቡ ወንዶችና ሴቶች ምክር ይሰጣል። ምክሩን የሚጀምረው በቁጥር 1 ላይ "ስለ ጻፋችሁልኝስ ነገር“ በማለት ነው። ይህም የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞች በትዳር ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ልከውለት እንደነበር የሚያሳይ ነው።

ጳውሎስ በዚህ ምዕራፍ ከሚመልሳቸው ጥያቄዎች መካከል "ሴት ባልዋ ከሞተ በኋላ ሌላ ባል ማግባት ትችላለች ወይስ አትችልም?“ የሚል ይገኝበታል። ወንድ ሚስቱ ከሞተች በኋላ ማግባት እንደሚችል ለቆሮንቶስ አማኞች ግልጽ ነበር። ነገር ግን ሴትም ባሉዋ ከሞተ በኋላ ሌላ ባል ማግባት መቻሉዋ ለቆሮንቶስ ሰዎች ጥያቄ የሆነባቸው ይመስላል። ጳውሎስ እንግዲህ ይሄንን ጥያቄ ሲመልስ፤ ሴት ባልዋ ከሞተ በኋላ ነጻ እንደሆነችና የወደደችውን ሰው ለማግባት ነጻነት እንዳላት ይናገራል። ሆኖም የወደደችውን ሰው ሲባል በጌታ ያልሆነ ሰው ማለት እንዳልሆነ ለመግለጽ "በጌታ ይሁን እንጂ" በሚለው ቃል ግድብና አጥር ሰርቶለታል።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች (የድሮው ትርጉም)
7፥39ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
7፥39አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ከእርሱ ጋር የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን፣ የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት

1 Corinthians 7:39 (NIV)
A woman is bound to her husband as long as he lives. But if her husband dies, she is free to marry anyone she wishes, but he must belong to the Lord.

ለዚህ ጥያቄ የጳውሎስ መልስ እንግዲህ ማግባት ትችላለች ነገር ግን የምታገባው ሰው የግድ በጌታ መሆን አለበት ወይም አማኝ መሆን አለበት የሚል ነው።

ሌላው በዚሁ በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 7 ላይ ጳውሎስ የሚመልሰው ጥያቄ ጌታን ከመከተላቸው በፊት በተጋቡ ባልና ሚስት ዙሪያ የተነሳ ጥያቄ ነው። ይህም ወንዱ ወይም ሴቷ ጌታን መከተል ቢጀምሩ፤ ከማያምነው የትዳር ጉዋደኛቸው ጋር መፋታት አለባቸው ወይ? የሚል ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ የማያምን ባል ወይም የማታምን ሚስት ላላቸው ክርስቲያኖች የሚመክረው ምክር፤ የማያምነው የትዳር ጉዋደኛ ከሚያምነው ጋር እምነቱን ተቀብሎ እኖራለሁ እስካለ ድረስና የማያምነው መለየት እስካልፈለገ ድረስ፤ መፋታት እንደሌለባቸው ነው። ነገር ግን የማያምነው የትዳር ጉዋደኛውን እምነት መቀበል ካቃተውና መለያየት ከፈለገ መለየት ይችላል እንጂ ለትዳር ብሎ አማኙ እምነቱን መተው እንደሌለበት ይመክራል።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7
12ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤ 13ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው።
...
15የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል።

ይሄ የማያምን የትዳር ጉዋደኛ ያሉዋቸው ትዳራቸውን ይፍቱ ወይም አይፍቱ የሚለው ጥያቄ በቆሮንቶስ መነሳቱና ጳውሎስም ይሄንን ጥያቄ አንስቶ መልስና ምክር መስጠቱ ራሱ፤ የሚያምን ከማያምን ጋር መጋባት የተለመደ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መደበኛ ጋብቻቸውን የሚፈጽሙት በጌታ ካመኑና እርሱን ከሚከተሉ ጋር እንጂ ካላመኑ ጋር እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው።

ከላይ ካየናቸው ክፍሎች በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 6 ላይ አማኞች በማይመች አካሄድ ከማያምኑ እንዳይጠመዱና እንዳይያዙ ያስተምራል።
Quote:
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6
14 ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? 15 ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? 16 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 17-18 ስለዚህም ጌታ። ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።

በዚህ ክፍል "በማይመች አካሄድ አትጠመዱ" የሚለው ሐረግ የተለያዩና እኩያ ያልሆኑ የከብት ዝርያዎች፤ ለምሳሌ በሬና አህያ፤ አንድ ላይ በአንድ በቀምበር ሲጠመዱ አይነት የሚያሳይ መልእክት ነው ያለው። የእንግሊዝኛውም ትርጉም ይሄንኑ ነው የሚያጎላው "Be ye not unequally yoked together with unbelievers“ ሁለት ወደ ተለያየ አቅጣጫ ለመሄድ የሚፈልጉ በሬዎች ወይም አንድ በሬና አንድ ፈረስ ወዘተ ሁለት የማይመጣጠኑ እንስሶች በአንድ ቀንበር ሥር ሲጠመዱ ያለውን አይነት ሥዕል በመሳል፤ ለሁለቱም የማይመችና በቀላሉም ሊወጡበት የማይችሉት ቀንበርና ወጥመድ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ምንም እንኳን ይህ ክፍል በቀጥታ ስለ ትዳር የተጻፈ ባይሆንም፤ ትዳርንም ይመለከታል። ምክንያቱም አማኞች ከማያምኑ ጋር ሊጠመዱበት ከሚችሉት ከማናቸውም ቀንበር በላይ በጣም ከባዱና በቀላሉም ሊወጡበት የማይችሉት የትዳር ቀንበር ነውና። ከማናቸውም ወዳጅነትና ጉዋደኝነት ይበልጥ ሁለት በደም የማይዛመዱ ሰዎችን ሕይወታቸውን ሁሉ አብረው እንዲኖሩ የሚያስርና የሚያጣብቅ ከትዳር የበለጠ ቀንበር የለም።

በሚያምንና በማያምን በሁለት ፈጽሞ በማይመጣጠኑ ሰዎች አንገት ላይ ትዳርን የሚያክል ሰዎችን እስከ ሞት ድረስ የሚያሥር ኃይለኛ ቀንበር መጫን፤ ትልቅ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ነው ብዬ አምናለሁ። ሳይመጣጠኑ ቀንበር እላያቸው ላይ ስለተጫነ አንዳቸው አንዳቸውን መጎተትና ማወላገዳቸው አይቀሬ ነው። ይህም ለእነርሱ የማጅራት መላላጥ ሲብስ ደግሞ የቀንበሩንም ስብራት ሊያስከትል የሚችል ነው። ለሁለቱም እንደማይመቻቸው ግልጽ ነውና።

እንግዲህ ካላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ በሚያምኑና በማያምኑ ሰዎች መካከል ትዳርን መመሥረት እንደማይገባ አይተናል። ከዚህ በተጨማሪም፤ ከራሴና ከሌሎችም የትዳር ሕይወት ልምድ ተነስቼ ትዳርን የሚያክል ብዙ ውስብስብ ችግርና ፈተና ያለበትን ትልቅ የሕይወት ጉዳይ፤ በቀላሉ እንዳታየው እመክርሃለሁ። እንኳን እምነትን በሚያክል ጉዳይ ሳይስማሙ ይቅርና፤ በአንድ እምነትም ሆነው እግዚአብሔር ካልረዳ የትዳር ኑሮ ትልቅ ፈተናዎች ያሉበት መብሰልና ትዕግስትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ገብቶ በኋላ ከመቆጨት ከአሁኑ በቁምነገር ከልብ ልትጸልይበትና ልታስብበት የሚገባ ነገር ነው። የመጽሐፍ ቅዱስንም ትምህርት ችላ ባትል መልካም ነው። ቃሉ የተፈተነና እውነተኛ ነውና። ለራስህ የወደፊት ሕይወት ስትል ይሄንን እንዳታደርግ አጥብቄ እመክርሃለሁ። ባልተመጣጠነ የትዳር ቀንበር ታሥሮ ደስተኛ መሆን እጅግ ከባድ ነውና።

በመጨረሻም፤ አንዳንዶች ራሳቸውን እንደሚያታልሉት፤ ካገባኋት በኋላ ወደ እምነት አመጣታለሁ ብለህ ራስህን አታታል። በዚህ የጉም ተስፋ አንዳንዶች ተታልለው ፍዳቸውን ያያሉና በዚህ ፈጽሞ ባልተጨበጠ ተስፋ ላይ ግዙፉን ትዳርን እንዳትመሠረት። ላላመኑት ወንጌልን እንድንሰብክ እንጂ ከእነርሱ ጋር ትዳር መሥርተን አንድ ቀን ያምኑ ይሆናል እያልን ተስፋ እንድናደርግ እግዚአብሔር አልላከንምና።
Apr 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...