ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 8 December 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጳውሎስ ስናገር ሃይማኖትን ጠብቃለሁ ካላ እኛም ክርስቶስን በመከተል ሃይማኖትን መጠበቅ የለብንም ዎይ?

ባሁን ባለንበት ሰኣት ብዙ ሰዎች የአለም ፍጻሜ እንደ ደረሳ ይናገራሉ፣ ይህ ነገር ከመጽሃፍ ቅዱስ እውነታ ጋር ምን ያህል ዬሚዛመድ ነው? ዬአለም ፍጻሜ ቀንስ ማን ያውቃል?
Apr 8, 2011 ስለ እኛ ወንድሙ (130 ነጥቦች) የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
ሰላም ወንድሙ

በጌታ ስም ሰላም እንላሃለን።

ስለ ዓለም ፍጻሜ አንድ ወንድማችን የመለሰውን መልስ እዚህ ተመልከት።

ልክ ነህ ክርስቶስን በመከተል ሃይማኖትም ባይሆን እምነትን መጠበቅ አለብን። ቁም ነገሩም ያለው በክርስቶስ ማመኑና እርሱን መከተሉ ላይ እንጂ፤ ኦርቶዶክስን ወይም ፕሮቴስታንትነትን ወይም ጆቫነትን መጠበቁ ላይ አይደለም።

ባለፈው መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት ሃይማኖት ብሎ የሚናገረው የትኛዋን ነው? ለሚለው ጥያቄ በሰጠነው መልስ ለመግለጽ እንደሞከርነው፤ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ቋንቋ ማለትም በግሪኩ እንዲሁም በብዙ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች እነዚህ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በልብ ስላለ እምነት እንጂ ስለምንከተለው ሃይማኖት አይደለም የሚናገሩት።

ካለ አማርኛው ትርጉም በሰተቀር ኦርጂናሉ የግሪኩም ይሁን እንግሊዝኛው የሚያወራው ስለ ልብ እርግጠኝነት ወይም በልብ ስላለ እምነት ነው እንጂ፤ ዛሬ እደምናስበው የኦርቶዶክስን ወይም የካቶሊክን ወይም የፕሮቴስታንትን ወዘተ ሃይማኖት ስለመጠበቅ አይደለም። ስለ አንዲት ሃይማኖት የመለስነውን መልስ እንደገና በጥሞና እዚህ እንድታነብበው በጌታ ፍቅር እንጠይቅሃለን።

አሁን አንተ ያነሳኸው ክፍል የሚገኘው በጢሞቴዎስ መልእክት ላይ ነው። ለማነጻጸር እንዲቻልህ የተለያዩ የእንግሊዝኛ ትርጉሞችን ከታች ተቀምጠዋል። አንዳቸውም ስለ ሃይማኖት (religion) አያወሩም፤ ነገር ግን ስለ እምነት (faith) ነው የሚናገሩት። የግሪኩም ቃል pistis እንዲሁ በልብ ስላለ እርግጠኝነት (conviction) ወይም እምነት (faith) ነው የሚያወራው።
Quote:
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
4፥7 መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤

NIV ©
I have fought the good fight, I have finished the race, I have kept the faith.

NASB ©
I have fought the good fight, I have finished the course, I have kept the faith;

NKJV ©
I have fought the good fight, I have finished the race, I have kept the faith.

መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት ሃይማኖት ብሎ የሚናገረው የትኛዋን ነው? ለሚለው ጥያቄ በሰጠነው መልስ ለመግለጽ እንደሞከርነው፤ አዲስ ኪዳን ላይ በአማርኛው ብቻ ሃይማኖት ተብለው የተተረጎሙት ክፍሎች ሁሉ የሚያወሩት ስለ ኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት ወዘተ ሃይማኖቶች ሳይሆን፤ ሰው በልቡ አምኖ ስለሚድንበት በክርስቶስ አዳኝነትና ጌትነት ስለማመን ነው። ስለዚህ የሚያወሩት በልብ ውስጥ ስላለ በክርስቶስ ላይ የተመሰረተ እምነት እንጂ፤ ዛሬ እንደምንረዳው የአንድ ሃይማኖት ተከታይነትን ስለመጠበቅ አይደለም።

በአዲስ ኪዳን ያለው አንዲት እምነት ብቻ ናት። ያቺም እምነት በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነትና ጌትነት ማመን የምትባል ናት።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 10
8 ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።
9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና
10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።

አንተ በጠቀስከውም የጢሞቴዎስ መልእክት ላይ ጳውሎስ "ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ" ሲል እንግዲህ ኦርቶዶክስነቴን ወይም ፕሮቴስታንትነቴን ወዘተ ጠብቄአለሁ ማለቱ ሳይሆን፤ በክርስቶስ ላይ ያለኝ የዳንኩበትን ያቺን እምነት አሁንም በልቤ ጠብቄአለሁ፤ ከዚያች እምነት ፈቀቅ አላልኩም። አሁንም ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ አምናለሁ ማለቱ ነው።

የጌታ ጸጋ ይብዛልህ!
Apr 8, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
Apr 8, 2011 iyesus ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...