ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 21 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እየሱሰ ሃዋርያ ነው

እብራውያን 3፡1 የሃይማኖታችንን ሃዋርያና ሊቀካናት ሲል
Apr 22, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
Quote:
ወደ ዕብራውያን
3፡1 ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤

NKJV
Therefore, holy brethren, partakers of the heavenly calling, consider the Apostle and High Priest of our confession, Christ Jesus,

NASB
Therefore, holy brethren, partakers of a heavenly calling, consider Jesus, the Apostle and High Priest of our confession;

በቅድሚያ ግልጽ ለማድረግ ሃይማኖታችን ተብሎ በዚህ ክፍል የተተረጎመው ቃል "our confession" ወይም የእምነታችን ምስክርነት ወይም አምነናል ብለን የምንናገረው የምስክርነት ቃላችን ማለት ነው፤ እንጂ ፕሮቴስታንትነታችን ወይም ኦርቶዶክስነታችን ማለት አይደለም።

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ይህ ምስክርነታችን ወይም የምስክርነታችን ቃል ብለው አማኞች የሚጠሩት ነገር ምን እንደሆነ ሮሜ 10 ላይ ተጽፎአል። ይህም የክርስቶስ ጌትነትና አዳኝነት ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 10
8 ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።
9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና

በዕብራውያን ላይ እንግዲህ ለዚህ የምስክርነት ቃላችን ወይም እምነታችን ኢየሱስ ሃዋርያና ሊቀ ካሕን እንደሆነ ተጽፎአል። በመሠረቱ ሃዋርያ ማለት በላኪው ሙሉ ስልጣን የላኪው ወኪልና አምባሳደር ሆኖ የላኪውን ፈቃድ የሚያስፈጽም ማለት ነው።

ኢየሱስ ደጋግሞ በወንጌላቱ እርሱ በአብ ተልኮ የመጣ እንጂ ከራሱ የመጣ እንዳልሆነ ተናግሮአል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 20
21 ኢየሱስም ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው።

ኢየሱስ ለዚሁ የምስክርነት ቃላችን ወይም እምነታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ አምባሳደር ነው። ማለትም ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ አዳነን እርሱ ጌታና የእግዚአብሔርን ልጅ ነው ብለን እንድንመሰክር ከአብ ዘንድ የተላከ መልክተኛ ወይም ሃዋርያ ነው። ክርስቶስ ከአብ የተላከ አብን ወክሎ የመጣ የአብ መልከተኛና ሐዋርያ ሲሆን፤ እነ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደግሞ በክርስቶስ የተላኩ የክርስቶስ ሐዋርያትና መልእክተኞች ናቸው። ሐዋርያ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ የተላከ ማለት ነውና።
Apr 22, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...