አዎ ያንተ ጥያቄ ትክክል ነው ግን እንደ እኔ አመለካከት፡- እግዚሐብሔር የፈቃድ አምላክ ነው ሁሉን ነገር ሲያደርግ የኛን ፍቃድ እየጠየቀ ነው፡፡ በተለይ ከበሽታ ለማዳን እሱን እንድንከተለው መፍቀድና ያለመፍቀዱን ለኛ ትቶልናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን እኛ በማናውቀው መንገድ ወይንም ከኛ አቅም በላይ በሆነ ነገር ላይ ለሰይጣን ወይም እኛ ላይ ክፉ ሊያደርግ የመጣው ላይ ስልጣን አይሰጠውም፡፡ እኛ ባለማወቃችን ወይንም ከአቅማችን በላይ ሆኖብን እያየ ለሰይጣን ወይንም ለክፉ አሳልፎ አይሰጠንም በዚህን ወቅት ጣልቃ ይገባል፡፡ ጣልቃ የሚገባው በእኛ እና በክፉ አድራጊያችን መካከል ነው፡፡ ደግሞም እኛን ባይጠይቀንም እንኳን የሱን እርዳታ እንደምንፈልግ ያውቃል ምክንያቱም እሱ ከእስትንፋሳችን ይልቅ ቅርብ ነውና፡፡