ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 20 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ሰይጣን እንዴት መንግስተ ሰማይ ይገባል????? ገድለ ተክለ ህይማኖት ምእራፍ 48

በገድለ ተክለ ህይማኖት ምእራፍ 48 ክቁ 1 ጀምሮ ተክለ ህይማኖት ሰይጣንን በማማተብ እንደያዘውና ምርጫ ሰጥቶት፤አስተምሮት፤ገርዞት፤ ልብሰ ምንኩስና እልብሶት ወደ በአቱ እንዳስገባውና ሰይጣኑም ሞቶ መንግስተ ሰማይ እስኪገባ ድረስ በቅንነት ሲያገልግል ኖረ ይላል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?????? በክርስቶስ ሰምራ በኩል እምቢ አሻፈረኝ አልታረቅም ያለው ሰይጣን እንዴት ሆኖ ነው በተክልዬ በኩል ፈቃደኛ የሆነው???
አልገባኝምና ብታስረዱኝ
May 5, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ሰላም ወንድሜ ወይም እህቴ

ይህ ድረገጽ እኮ እኛ ከእግዚአብሔር ቃል ማለትም ከመጽሐፍ ቅዱስ ልንማማርበት እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ያልሆኑ መጻሕፍትንና ገድሎችን እየጠቀስን ፋይዳ በሌለው ክርክር ጊዜአችንን እንድናባክንበት የተዘጋጀ አይመስለኝም።

የገድል መጽሐፍትማ በስህተት ትምህርቶች የተሞሉ እንደሆኑና ብዙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረኑ ነገሮችን እንደያዙ በኦሮቶዶክስ ሊቃውንት ጭምር የታወቀ ነው። ስለዚህ የእነርሱን ስህተት እንቁጠር ከተባለ ብዙ ወራት ሊያስፈልጉን ነው።

ይልቁን ትኩረታችንን ወደ እግዚአብሔር ቃል ማለትም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ብናደርግ ይሻላል።
ልክ ነህ ወንድሜ የነሱን ስህተት እናውራ ብንል ብዙ ጊዜ ማባከን ነው፤ ነገር ግን በጣም ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ እያለቁ ስለሆነ ነው

ጌታ ይባርክህ
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብንነጋገር መልካም ነው ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ ብዙዎችን ስለማያስማማ እኔንም ጨምሮ፡፡
ድሮ በአሜሪካን ባንኮች ውስጥ የሚሠሩና እውነተኛውን ከውሸተኛው ዶላር የሚለዩ ሠራተኞች ያደርጉት የነበረው፤ እውነተኛውን ዶላር በጥንቃቄ ማጥናት ነበር ይባላል። ምክንያቱም ውሸተኞቹ ብዙ ስለሆኑ እነርሱን ሁሉ ማጥናት ስለማይችሉ ነው። እናም እውነተኛውን ዶላር፤ ጥቃቅኗን ምልክት ሳይቀር በጥንቃቄ ስለሚያውቁ ከእውነተኛው ትንሽ የተለየ የውሸት ዶላር ሲያዩ ወዲያው መለየት ይችሉ ነበር ይባላል።

እናም ውሸተኞች ገድሎችና መጻሕፍት ቁጥራቸው ብዙ ስለሆኑ እነርሱንና ስህታቸውን ሁሉ ማጥናት አንችልም። ይልቁኑ እውነተኛውንና ኦርጂናሉን የእግዚአብሔር ቃል ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ሰዎች በሚገባ ካወቁ ማናቸውም አይነት የተሳሳተ ትምህርትና መጽሐፍን በቀላሉ መለየት ይችላሉ።
ኸመጽሃፍ ክዱስ ዉጭ በሆኑ መጽሃፍት ላይ መወያየት አልወድም።የሰይጣን ስፍራ ሲኦል ነው። በዘፍጥረት 3፤15እንደተጻፈው ሁዋላም መዲሃኢታችሂን ኢየሱስ ኪርስቶስ በሞቱ ዲል እንደነሳው እኛም በዳንንበት እና በተዋጀንበት በክቡር እየሱስ ስም እና ስልጣን ሰይጣንን ከነሰራዊቶቹ በየሱስ ክርስቶስ ስምና ስልጣን እያሰርን ወደሲኦል እንሰዳለን!ላመኑት የግዚአብሔር ልጅ ይባሉ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው ዮሓንስ ወንጌል 1፡12 ጌታ የሱስ ይባርካችሁ!አሜን!!

1 መልስ

0 ድምጾች
ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ወደኛ እንደደረሰና የአዋልድ መጽሐፍት ምነነትን የሚገልጥ አጭር ጽሁፍ በአማርኛ በሚከተለው ሊንክ ይመልከቱ፦ በነጻም ዳውን ሎድ ማድረግ ይቻላል።
http://www.scribd.com/fullscreen/55221381?access_key=key-2c6modi89v70yw67ffjf
May 26, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
የተሰጠው ሊንክ የሚናገረው ስለ ራዕይ እንጂ ስለ አዋልድ መጻሕፍት ስላልሆነ ሊንኩ ቢስተካከል።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...