ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በጣም ከባድ ሓጥያት ሰሪሑኝ እና ገታ ጋሪ ለገናኛት አቅም አጥሁኝ ምን ይሽላል>

ጊታ ጋሪ ከምታሓሁኝ 2009 ነው፡ ኣና ከቢለቢቲ ሰላም የልኝም እሱ አማኝ አደልም አደባል አና ሚስት ፍቅር የለንም ለ10 ኣመት ሙሉ ፍቅር መስራት የለም፤ ደንገት ከሊላ ሰው ፍቅር ያዘኝ አና ሓጥያት ሰራሑኝ ምንደን ልደርግ?
May 11, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
ሰው ሁሉ ሐጢያትን ሰርቷል የእግዚሐብሔርም ክብር ጐድሎታል ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ በምድር ላይ ስንኖር መፈተናችን ሆነ መውደቃችን ያለ ነው ዋናው ቁምነገሩ ዳግመኛ ያንን ስሕተት ላለመድገም በእግዚሐብሔር ፊት ንሰሐ መግባት ነው እንጂ ከእግዚሐብሔር በራቅን ቁጥር ሐጢያት ልምምድ ውስጥ እንገባለን ያ ደግሞ ለዚህኛውም ምድር ለሚመጣውም ክብር አይጠቅመንም፡፡ እኔ የምመክርሽ/ህ በእግዚሐብሔር ፊት ንሰሐ ግቢ/ባ ይቅር ባይ አምላክ ነው ያለን እንኳን የኛ ድንቅ አምላክ ቀርቶ ደካማው ሰው እንኳን ይቅርታ ማድረግን ያውቃል፡፡ እግዚሐብሔር ሁላችንንም ይርዳን አሜን!
May 11, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
ቤተክርስቲያን የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪዎች አሉ እነርሱ ጋር ሂጂ የበለጠ ሊረዱሽ ይችላሉ፡፡
–1 ድምጽ
ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይብዛላቹህ። አሜን!!!

"በጣም ከባድ ሓጥያት ሰሪሑኝ እና ገታ ጋሪ ለገናኛት አቅም አጥሁኝ ምን ይሽላል"። ይህን ጥያቄ ሁሉም ራሱን ጠይቆ ትክክለኛውን መልስ መስጠት መቻል አለበት ያለበልዚያ የጠላት መጫወቻ መሆን አለ። ስለዚህ ጥሩ ጥያቄ ነው እላለሁ።

ሰው መንፈስ ነው ነፍስ አለው በስጋ ውስጥ ይኖራል። ነፍስ መሃከለኛ ሁና በሁለት መከፈል የማትችል እዚህ እዚያ ማለቱ የማያዋጣት እንደሆነ ተገንዝባ አንዱን መያዝ መምረጥ አለባ፡፡ ይህ ውሳኔ ግን በጣም ከባድ ነው መልካም ከተመኘን መስዋዕት መከፈል አለብን። ፍላጎታችን ከሆነ እ/ር ሥጋችንን ገዝተን የምንኖርበት መንፈስ ሊሰጠን ደጅ እየጠናን ነው እርሱ ፍቃደኛ ነው። አንቺ አንት እኔስ እንፈልጋለንን? ምክንያት መደርደሩ አያዋጣንም ግን ከፓስተር ከወገኖች ጋር ችግራችንን መወያየት እንችላለን የምንነግረውን ሰው ግን መምረጥ አለብን።

"የያዘውን የወረወረ አይባልም ፈሪ" የሚለውን አንድ የአባቶች ተረት ትዝ አለኝ። ስለዚህ ያለብንን ችግር መግለጽ የምናውቀውን መፍትሔ ይሆናል የምንለውን ማካፈሉ መልካም ነው። ወደ ጥያቄው አንኩዋር እንምጣና "...ከጌታ ጋር ለመገናኘት አቅም አጣሁኝ ምን ይሻላል" ብሎ መጠየቁ እርስ በራሳችን ልንማማር ይህን ደህረ ግጽ በወንድማችን ያሬድ በኩል ስላዘጋጀልን የጌታ ስም ይባረክ ወንድማችንና ቤተሰቡን ከክፉ ሁሉ ይጠብቃቸው።

ጌታ እየሱስ በማቴ 12፡31-32ና በማር 3፡28 የሚለን አንድ ትልቅ ማስጠንቀቂያ አለ፡፡
"ስለዚህ እላቹኅዋለሁ ሃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም ይላል። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ እስካልሰደብን ደረስ ሃጢአት ሰረተን ንስሐ እንግባ ማለት አይደልም። ለያንዳናዱ ሃጢአት መተላለፍ በደል በዚህ ምድር እንቀጣለን በመጨረሻም ነፍሱ በጭንቅ ትድናለች ይላል መጽሐፍ ቅዱስ እንጠንቀቅ። ጌታ መልካም አባት ነው ልጆቹን ስለ ሚወድ ይቀጣል እኛ ዲቃላዎች ስላልሆን ማለት ነው የኛን መልካም ስለ ሚያስብልን ነው።


ጌታ ይባርካቹህ

ወንድማችሁ
May 11, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
May 12, 2011 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...