ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 21 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አንድን አማኝ አጋንንት ሊይይዘው ይቻላል?

አንድ ግራ የገባኝ ቢኖር አንድ ሰው በጌታ አምኖ ከዳነ በኋላ ጌታን እያመለከ ሳለ እንዴት አጋንንት ሊይዘው ይችላል?
May 12, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
በዚህ ጉዳይ ይህ ሊሆን አይችልም በሚሉና ሊሆን ይችላል በሚሉ መካከል ብዙ የሃሳብ ልዩነቶች አሉ።

ሆኖም እኔ ለዚህ ጥያቄ ይሆናል ወይም አይሆንም ብሎ መልስ መስጠቱ የሚለውጠው ነገር ያለ አይመስለኝም። ቁም ነገሩ ያለው አጋንንት ያለበት ሰው ከዚያ መላቀቁ ላይ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ አጋንንቱ ያንን ሰው የያዘው በእርግጥ ጌታን ከተቀበለ በኋላ ነው ወይስ "ተቀብያለሁ" ከማለቱ በፊት ተደብቆ የነበረ ጉዳይ ነው? ጌታን ከተቀበለ በኋላስ በሐዋርያት ዘመን ይደረግ እንደነበረው በዚያው ጊዜ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶአል ወይስ አልተሞላም ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች ሁሉ መመለስ አለባቸው የሐዋ 19፡2 ።

Quote:
የሐዋርያት ሥራ
19፥2 አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ። ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን? አላቸው። እርሱም፦ አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት።

ሆኖም አንድ ግን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ነገር ቢኖር መንፈስ ቅዱስን በተሞላ ሰው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከዚያ ሰው እስካልተለየ ድረስ አጋንንት ሊይይዘው በፍጹም አይችልም። መንፈስ ቅዱስንና አጋንንት በአንድ ቤት ሊኖሩ አይችሉምና። ሆኖም ሰው መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ኃጢአት ሊሠራ እንደሚችል ሁሉ፤ ቀስ በቀስ በኃጢአት ብዛትና እምነትን ከመጣል ሰው ከጌታ ሊለይና መንፈስ ቅዱስንም ሊያጣ ይችላል። በዚህ ሁኔታ እንደ ሳኦል ለአጋንንት ሕይወቱን ሊከፍት ይችላል።

ጌታ ይባርክህ
May 12, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
በትክክል ስለመዳኑ እርግጠኛ ነን እንበልና እንጀመር አይደል? ስለዚህ በትክክል በዳነ ሰው ውስጥ አጋንንት ገባበት ወይም አለበት ብሎ መናገር መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይሆንም፡፡ በዘመናችን ግን አጋንንት አሳዳጅ የፈውስ አገልጋዮች በትክክል የዳነ ነው በሚሉት ሰው ውስጥም አጋንንት አወጣን ሲሉ ይደመጣል-የማይሆን ነገር! ባይሆን ሳይኮሎጂካል አሰራራቸውን ጭምር ቢመረምሩት ይበጃል፡፡ ማለቴ ሰዎች አጋንንት ሊኖርብህ ይችላል ከተባሉ አጋንንት ያለበት ሰው ያህል ሊጮሁ እንደሚችሉ ማስታወስ! ሁለተኛ ደግሞ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የሚጮኸውን ሰው መለየት መቻል ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እንደዘመናችን ቤተክርስቲያን ከአማኞች አጋንንት የወጣበት ዘመን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ አንድ ወዳጄ ስለ ሳኦል ያነሳኸው አግባብነት ያለው ቢሆንም በአዲስ ኪዳን ግን ከዚህ የተለየ ሁኔታ መኖሩንም መዘንጋት የለብንም፡፡
የጌታ የኢየሱስ ሰላም ይብዛላችሁ!!!
ይሁዳ እኮ በጌታ ኢየሱስ ተጠሪነት ሐዋርያ ለመሆን የተመረጠ ሰው ነበረ ማለትም “አማኝ” ነበረ ማለት ነው ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን “ሰይጣንም ከአስራሁለቱ ቁጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ” ይለናል ስለዚህ አውነቱን ከተነጋገርን ህይወታችንን እለት እለት ካልጠበቅን ካልቀደስን ክፉ መንፈስ ሊገባብን ብቻ ሳይሆን በፊት ከነበረው ክፉ መንፈስ በባሰና በከፋ ሁኔታ ክፉ መንፈሶች ሊገቡበት ይችላል ማለት ነው፡፡
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...