ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 18 January 2022
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት ሃይማኖት ብሎ የሚናገረው የትኛዋን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት ሃይማኖት ብቻ እንዳለች ይናገራል። በዓለም ላይ ደግሞ ብዙ ሃማኖቶች አሉ። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ የትኛዋ ሃይማኖት ነው?
Feb 26, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

+5 ድምጾች
ሐዋርያው ጳውሎስ "አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት" ብሎ የጻፈበት ጥቅስ የሚገኘው በኤፌሶን መልዕክት ላይ ሲሆን፤ ሙሉ ጥቅሱም እንደሚከተለው ነው፦
Quote:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4
4 በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤
5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።

ብዙዎች ይህንን ጥቅስ የራሳቸው ሃይማኖት ብቸኛውና ትክክለኛው የመዳኛ መንገድ እንደሆነ ለማሳመን የሚጠቀሙበት ጥቅስ ነው። ችግሩ ግን ከአማርኛው ትርጉም በስተቀር በመጀመሪያ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በግሪኩም ይሁን በእንግሊዝኛው ትርጉም በዚህ ጥቅስ ላይ "ሃይማኖት" የሚል ቃል የለም። በአዲስ ኪዳን በአማርኛው "ሃይማኖት" ተብለው የተተረጎሙት ቃላት በአብዛኛው በግሪኩ "እምነት" የሚለው ቃል ነው። በዚህ ክፍልም "ሃይማኖት" ተብሎ በአማርኛው የተተረጎመው ቃል በግሪኩ pistis የሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም እምነት ወይም faith, believe, assurance ማለት እንጂ ሃይማኖት ማለት አይደለም። ስለዚህ ይህ ክፍል የሚያወራው ኦርቶዶክስ ወይም ፕሮቴስታንት ወይም ካቶሊክ ወዘተ ስለሚባሉ ሃይማኖቶች ሳይሆን፤ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ በልባቸው ስለሚያምኑት አንዲት እምነት ነው። ይህም ለሃጢአታችን ደሙን ባፈሰሰው በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ማመን ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 10
8 ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።
9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።

የዮሐንስ ወንጌል 3
14-15 ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
17 ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

ስለዚህ አንዲት እምነት ብሎ ጳውሎስ የሚናገረው ሰው በልቡ አምኖ ስለሚድንበት እምነት ነው። ይህም በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው።

ይሄ በግሪኩ pistis (እምነት) የተሰኘው ቃል በአማርኛው "ሃይማኖት" ተብሎ የተተረጎመባቸው አንዳንድ ጥቅሶች የሚከተሉት ናቸው፦
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
16፥13 ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች
4፥5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤

ወደ ቆላስይስ ሰዎች
2፥7 ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
Feb 27, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
Feb 27, 2011 iyesus ታርሟል
+1 ድምጽ
መልሱ በትክክል የተመለሰ ይመስለኛል እና አንድ ሐይማኖት የሚለው ሰው የፈጠራቸው የድርጅቶች እና የሐይማኖት ስሞች ሳይሆን በአንድ አምላክና ፈጣሪ በሆነው በእየሱስ ክርስቶስ ማመንን ነው፡፡ ምክንያቱም እና ሁላችንም በክርስቶስ የምናምን አንድ ነንና፡፡
Apr 16, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2022 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...