ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው? ስፋ ባለ መልኩ ብታብራሩት..

ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው? ነጻ ስጦታ ከሚለው የተለየ ማለት ነው?
May 31, 2011 መንፈሳዊ BINIYAM (120 ነጥቦች) የተጠየቀ

3 መልሶች

0 ድምጾች
ሮሜ 3 ፡23-24 ቲቶ 2፡11
- ፀጋ በጣም እጂግ ብዙ ትርጉም ያለው ሲሆን በጥቅሉ ግን ፍፁም የሆነ የእግዚያብሄር ስጦጣ ሲሆን የሰጪውን እንጂ የተቀባዩን ማንነት የማያሳይ የማይገባውን ሰው እንደሚገባው አድርጎ የሚቆጥር ሃጢያጠኛን በእምነት ምክንያት ጻድቅ ይሚያደርግ አንድን አማኝ በመንፈስ ብቁ የሚያደርግ ብቃትን የሚሰጥ የእግዚያብሄር የፍፁም ደግነቱ መገለጫ የሆነ ሙሉ ምህረት ስጪ መነሻው መስቀል የሆነ ለክርስቶስ መምጣት የሚያዘጋጅ… መገለጫውና ስራው ብዙ ቢሆንም ማንነቱ ግን አንድና አንድ ብቻ የሆነ እርሱም ኢይሱስ ክርስቶስ መልካሙ አዳኛችን ነው።
Jun 19, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜን!!!

ጸጋ ማለት ምን ማለት ነው? ማንም አማኝ ነኝ የሚል መለስ ለመስጠት የሚያስገድድው ጥያቄ ነው። ጌታ ይባርከውና ወንድም ቢንያም ይህን ጥያቄ ስላቀረበልን እኔ ለራሴ ሰፋ ያለ ትምህርት አገኛለሁ ብዬ አምናለሁ።

ስለ ጸጋ ከዘፍጥረት የሚጀምር ይመስለኛል። ምን ነካው ይህ ሰውዬ! ጥያቄው የአዲስ ኪዳን ጉዳይ ሲጠየቅ ወደ ቡልይ የሚወሰድን አትበሉኝና ትንሽ ላውጋችሁ።

በእግዚአብሔር መልክና በምስላቸው ስላሴ ስለ ፈጠሩን ትልቅ ክብር እና ትልቅ እድል ነው። ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር በምስራቅ በኤደን ገነትን ተከሎ አዳም ይጠብቃትም ዘንድ ያበጃትም ጭምር ከአንድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር ሰጠው ይኸውም መልካሙንና ክፉን ከሚያስተውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና የሚል ነበር። እንዲህ ያለ ጠቃሚ ምክር አዘል ጉዳይ የፍቅር አባታቸው ነገረው እሱ ግን በወረት ከውሸት አባት ጋር የማይጠቅም ጓደኝነት አበጀ። የተከለከለው ፍሬ በመብላት አዳም ወደቀ። ፈጣርም ከገነት አባረራቸው በሞት ፈንታ ግረው ጥርው እንዲበሉ አዘዛቸው። ይህ በሰዎች ተስፋ የማይቆርጥ እግዚአብሔር በዘፍ 3፡15 እኛ ዛሬ ወንጌል የምንለውን "ቃል" ገባላቸው። ጸጋ እዚህ ላይ የጀመረ ይመስለኛል።

ይህ ብቻ አይደለም ትውልድ በትውልድ እየተተካ በዘላለማዊ ዙፋኑ ላይ ያለውን ፈጣሪ ኩሉ ዓለምን ሰው በመፍጠሩ እስኪጸጸትና በኖህና ቤተሰቡ ጊዜ በውሃ እስኪያጠፋት ድረስ እጅግ አሳዝነውታል። እውነቱን እንናገርና እኛስ እንዴት እንሆን? ወገኖቼ የጌታ ምጻት ብቻ ሳይሆን ምንም ምልክት ያልተሰጠን ምን ጊዜ ሊሆን የሚችል የቤተ ክርስቲያን መነጠቅም አለና እንደ ሌባ እንደሚመጣ አንርሳ። እግዚአብሔር ቃሉን የማያጥፈው ተስፋውን ለመፈጸም ጊዜው ሲደርስ አንዲት ድንግል ብጽእት መረጠና መልአኩን ልኮ አስታወቃት ድንግልም በተዓምር መንፍስ ስለ ጸለላት ወንድ ሳታውቅ አረገዘች የእግዚአብሔርም ልጅ ኢየሱስ የስሙ ትርጉም ሕዝቡን ከሃጢአታቸው ያድናቸዋል የሚባለው ጌታ ተወለደ (ዮሐ 3፡16)

አባዬ! ይህች ጽዋ ከኔ ትለፍ እያለ በገቴሰማኒ ላቡ እንድ ደም እስኪንጠባጠብ ድርስ ጨንቆት ነበር ግን ያባቱን ፈቃድ እንዲሆን የተቀበለ የእግዚአብሔር ልጅ ይባረክ። ሳይበድል በደልኛ ሆኖ ባላደረገው ወንጀል በውሸት ተከሶ በኛ ፈንታ በኛ ቦታ በጎልጎታ መሰቀል ክቡር ደሙን አፈስሶ ለያይቶን የነበረው የጥል ግድግዳ አፍርሶ ከአብ ጋር ለዘላለም አስታርቆናል። ጳውሎስ በእርሱ ሁነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት የማያውቀው አንድያ ልጁን ኃጢአት አደረገው ይላል (2 ቆሮ 5፡21)። አሁን አባቶች እንድ ሚሉት እንሆ ፈረስ እንሆ ሜዳ ሆኖልናል የቀረው የሰው ፈንታ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲሁ በነጻ የሰጠን አንድያ ልጁ ነው ጸጋ ምክንያቱ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እሱን በማመን በሱ በኩል ብቻ ነው ሁሉን ያለ ምንም ዋጋ ሳንከፈል የተሰጠን ያገኘነው። ሳይመሽ አሁኑኑ እንወስንና እጅ ለእጅ በፍቀር ተያይዘን በጨለማ ላሉት እንድርስላቸው። ለዚህ ነው የተጠራነው።

ጌታ ይባርካችሁ
ወንድማችሁ
Jun 19, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Jun 19, 2011 ታርሟል
በጥሩ መረዳት ከመጣህ በሆላ ከአብ ጋር ለዘላለም አስታርቆናል የሚለው ከአባቱ ከአብ ከራሱ ጋር እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን በማለት መስተካከል አለበት ምክንያቱም መጀመሪያ የተጣላነዉ ከእግዚአብህር ጋር ነው መታረቅ ያለብን ከእነሱ ጋር ነው
0 ድምጾች
ሰፊ ማብራሪያ መስጠት ባልቸልም "ጸጋ ማለት ለማይገባው ሰው የተሰጠ ነጻ ስጦታ ማለት ነው(ለማይገባው ሰው)
Sep 5, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ድንግልም በተዓምር መንፍስ ስለ ጸለላት.... ስለ ጸለላት ምን ማለት ነው? ይቅርታ ቃሉ አልገባኝም
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...