ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 22 October 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

Why do I feel hopeless all the time?

ሁል ግዜ ተስፋ እንደሌለኝ ይሰማኛል በጣም ብዙ ግዜ ራሴን ስለማጥፋት ኣስባለሁ ምን ይሻለኛል ? Why do I feel hopeless all the time?
Jun 7, 2011 ሌሎች ስም-አልባ የተጠየቀ
ሰላም ወንድሜ

ጥያቄህን ለመመለስ እንዲህ ሊሰማህ የቻለበትን የችግሩን ምንጭና ሥሩን ማወቅ ያስፈልጋል። ስለዚህ ካልከበደህ ስለ ራስህ ትንሽ ብትነግረን። የክርስቶስ ተከታይ ነህ? ከሆንክስ ምን ያህል ሆነህ አማኝ ከሆንክ? የክርስትና ሕይወትህስ ምን ይመስላል? የቤተሰብና የጓደኞች እንዲሁም የምትኖርበት የኑሮ ሁኔታስ? ከመቼ ጀምሮ ነው እንዲህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚሰማህ? እንዲህ ተስፋ እንድትቆርጥ ያደርገህ አንት የምታውቀው አንድ በሕይወትህ የተከሰተ ነገር አለ? ካለስ ምንድነው?

በመጨረሻም አንድ በእርግጠኝነት ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር፤ የዚህች ምድር ሕይወት ቻሌንጅ መሆኗን ነው። እናም ተስፋ እንድንቆርጥባት ሳይሆን እንድናሸንፋት ነው የተጠራነው። ራስን በማጥፋት የሚፈታ ጥያቄ ወይም የሚመጣ መፍትሔና እፎይታ የለም። የባሰ መውጫ ወደሌለው የዘላለም ጸጸት ያመራሃል እንጂ። ስለዚህ ራስን ማጥፋት እንደ አማራጭ እንኳን የሚታይ አይደለም፤ በሃሳብህም ለደቂቃ እንኳን ልታስተናግደው የሚገባ ጉዳይ አይደለም።

ስሜት ጊዜአዊ ነው፤ የደስታም ይሁን የሃዘን፣ የፈንጠዝያም ይሁን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ጊዜያዊና ተለዋዋጭ ነገር ነው። ስለዚህ የሕይወትህን ምሰሶና አቅጣጫ የደስታም ይሁን የሐዘን ወይም የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዳይመራው ተጠንቀቅ። ስሜት ሃላፊና ተለዋዋጭ ነገር ነውና።

ነገር ግን በድን የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሬሳ ሕያው ያደረገው የክርስቶስ መንፈስ የአንተንም ሕይወት ማለምለምና የሕይወት ተሳፋ መዝራት ይችላልና፤ የትንሳኤው ጌታ ኢየሱስ የሞትን ጥላ ከላይህ እንደሚሠብርልህ እመን።

መቃብርን ከፍቶ ሙታንን የሚያስነሳ፤ የሞቱ አጥንቶችንም የሚያለመልም አምላክ ይጠብቅህ። መልስህ እስኪመጣ ድረስ ትንቢተ ሕዝቅኤል 37ን እንድታነብብ እጋብዝሃለሁ።

ጌታ ይጠብቅህ!
በቅድሚያ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ
ለጥያቄዎችህ መልስ 1ኛ - አዎን የክርስቶስ ተከታይ ነኝ 2ኛ -ጌታን ከተቀበልኩ 5ዓመት ሆኖኛል 3ኛ - የምኖረው ብቻዬን ሲሆን የክርስትና ሕይወቴ ጥሩ ነው ምንም አገልግሎት ባልጀምርም 4ኛ - እንዲህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የጀመረኝ ጌታን ለመቀበል ከወሰንኩበት ጊዜ ጀምሮ ነው like 6ዓመት አካባቢ ማለትም ጌታን ከመቀበሌ 1ዓመት በፊት ማለት ነው በዛ ወቅት ምንም ሳልሆን even ትምህርቴን withdraw አድርጌ ነበር ነገር ግን ይሄ ነው የምለው ምንም ምክንያት የለኝም እናም ይኸው ለ6ዓመት ከራሴ ጋር እየተጣላሁ አለሁ
ሰላም ወንድሜ

ከጻፍከው ጥቂት ነገሮች የአንተን ሁኔታ ስለመረዳት አንዳንድ ፍንጭ ሰጥተውኛል። ሆኖም ገና ሙሉ በሙሉ መረዳት በጣም ይከብዳል እናም ካልከበደህ እንደገና አንዳንድ ጥያቄዎች ላቅርብልህ?

እስቲ በእውነት ግልጽ ሆነህ honest የሆነ መልስ ስጠኝ። ትምህርትህን withdraw ስታደርግ ለራስህ የሰጠኸው ምክንያት ምንድን ነበር? ጌታን ተቀብለህ አገልጋይ ለመሆን ፈልገህ ነው? Please ጊዜ ውሰድና እውነቱን ብቻ ንገረኝ። ለራስህ አንድ ምክንያት ሳትሰጥ ትምህርትን withdraw እንደማታደርግ ግልጽ ነው። ያ ምክንያት በእውነት ምንድን ነበር?

ቢሆንልህ ሙሉ ጊዜህን ማገልገል ትፈልጋለህ? እናም ይሄ እስካሁን አልሆነልህም? የእግዚአብሔር ቃል እውቀትህንስ በተመለከተ ራስህን እንዴት ትገምተዋለህ። ቃሉን በግልህ የመመርመርና የማጥናት ልምድ አለህ ወይስ በቤተክርስቲያን በሳምንት አንድ ጊዜ በሚሰበከውን ስብከት ብቻ ነው የምትኖረው?

ብቻዬን ነው የምኖረው ስትል፤ ከወገኖች ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋርስ ትገናኛለህ?

ጥያቄ እንዳበዛው አውቃለሁ ነገር ግን ችግሩን በደንብ ሳልረዳ አስተያየት መስጠት ስላልፈለኩ ነው።
ሰላም ወንድሜ
From what I read. It sounds like you have not seen your self yet as God see you. The mint you know who really are in Christ, things will change. in 1996 one day I heard a voice that voice was telling me i was a loser all of my family and friend will live without me. I have nothing to live for. so I drove to a church to find out someone to tell me who I was. I didn't even know really what I am all about at that time. That day no one could be found. So I got back to my car and just cried out and ask God, isn't true what i hear why should i live for? And it was clear within me; I knew without a shadow of a doubt some thing is ready to destroy me before my time. God gave me a reason to live. My reason was to worship HIM. So my dear see your self as God sees you, remember the cross of Christ is for you. *( you know this) but don't lose focus. keep your eyes on HIM. STAY ALIVE AND SEE HIS GLORY HE HAS A PLAN FOR YOU THAT IS GOOD NOT EVIL. JER29:11 " ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።"
YOU ARE LOVED BY GOD. NO OTHER THING GREATER THAN THAT SO DELIGHT YOURSELF IN HIM.
Blessing
in HIM
Emy.
ሁላችሁንም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ !!!
The Devil always fights against you and all other Jesus children.This is a number one fact.He doesn't sleep for us.he fights you in ideas, illusional false thoughts,he falsely accuses you for all things that you think "I am wrong" here.
So This is also one fight that you faced now,but don't worry the devil is defeated ,if you really believe in Jesus I believe Jesus is an eternal savior of you and all of us.What i rather think is Jesus wants you to learn something for your future Christianity services whether in church or any where you are going to work.So you have to pray and ask what is that? that Jesus is going to teach you?...the other thing I want to remind you is if the devil is not sleeping for you and all of us why do we sleep for him? and how can we defeat him and crush is false accusation? the answer is pray and Rebuck him in the almighty name Jesus Christie the lord and the savior,rebuck him in his powerful word,,read bible like you eat food...because that's our weapon....If you make sin ..you shouldn't quite these things because no one is righious in front of God,we only live by his mercy..i don't mean that here you make sin and so on but one tactic of devil is to let you fail in temporary sin and detract or break you from your trends of praying and reading bible.
So all these things will grow your faith in Jesus..if your faith grows your hope grows and you will understand everything and be a counsler for those who will pass in your situation now. The bible says the lord is my Shepherd and I lack nothing(psalms 23),the lord is your Shepherd just now,look it says "IS" not "will be" not "was" it just says "IS" read the whole psalm 23.So the lord is your Shepherd don't worry.Jesus loves you and we all love you in Christie and there are lot of good times in front of you so just don't let yourself down and make devil happy.make your God happy by holding his hand and rely on him...you are not here by yourself and we all are not here by ourselves.He who brought us here and above all who protects us from all evil with his begotten son's blood take cares of us.AMEN!!!
I pray in the name of Jesus that your history will be changed drastically.May God be with you and carry all you burdens, brother/sister.AMEN

2 መልሶች

0 ድምጾች
ይህን ለሚያነቡ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜእን!!!

ይህን ጥያቄ በእንግሊዝኛ ለማቅረብ ለምን ግደታ ሆነ ብዬ መጀመሬ ይገርማችሁ ይሆን? ጥያቄው ድፈን የሆነ መልስ ለመስተት የማያመች ስለሆነ አንዱ ወንድም የሚከተለውን

"ጥያቄህን ለመመለስ እንዲህ ሊሰማህ የቻለበትን የችግሩን ምንጭና ሥሩን ማወቅ ያስፈልጋል። ስለዚህ ካልከበደህ ስለ ራስህ ትንሽ ብትነግረን። የክርስቶስ ተከታይ ነህ? ከሆንክስ ምን ያህል ሆነህ አማኝ ከሆንክ? የክርስትና ሕይወትህስ ምን ይመስላል? የቤተሰብና የጓደኞች እንዲሁም የምትኖርበት የኑሮ ሁኔታስ? ከመቼ ጀምሮ ነው እንዲህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚሰማህ? እንዲህ ተስፋ እንድትቆርጥ ያደርገህ አንት የምታውቀው አንድ በሕይወትህ የተከሰተ ነገር አለ? ካለስ ምንድነው?" የሚል ጥያቄ አቅርቦ እስካሁን መልስ አልተሰበጥም።

ውንድማችን ጌታ ይባርከውና ይህን ድህረገጽ ልንደጋገፍበት በሩን ከፍቶልን ሲያበቃ ለምን እኛ ፈላጊዎችና ክሩዎች እንሆናለን? ወንድም ትሆን ወይም እህት አላውቅም ግን ትንሽ ማብራሪያ ቢጨመርልን እርዳታ ማግኘት ይቻላልና እባካችሁ እንቀባበል ማንም ማንን ሊፈርድ የሚፈልግ ያለ የሚኖር አይመስለኝምና በነፃነት መብራሪያ ይሰጠን።

የጌታ ስም ይባረክ
Jun 16, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜን!!!

Why do I feel hopeless all the time? በሚለው ጥያቄ ላይ ተጨማሪ ልባዊና የግል ሁኔታን የሚገልጽ ማብራሪያ ከተለገሰልን ውስጥ ከዚህ በታች አጠር አድርጌ በመያዝ ትንሽ ሃሳቤን ለመግለጽ ይፍቀደልኝ። ጥያቄው ከባድ ጥያቄ ነው። ለምን ጌታ ልጆቹን በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ለምን እንደሚያሳልፈን አናውቅም ጌታችን ግን ሁሉን የሚያውቅ ሁሉን የሚሰማ ሁሉን የሚያይ ዘላለማዊ የፍቅር አባትና ጌታ ነው።

ከተሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ ባጭሩ የወሰድኩት ይህ ነው። አሁን የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ጌታን ከተቀበልኩ 5ዓመት ሆኖኛል። የምኖረው ብቻዬን ሲሆን የክርስትና ሕይወቴ ጥሩ ነው ምንም አገልግሎት ባልጀምርም። እንዲህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት የጀመረኝ ጌታን ለመቀበል ከወሰንኩበት ጊዜ ጀምሮ ነው like 6ዓመት አካባቢ ማለትም ጌታን ከመቀበሌ 1ዓመት በፊት ማለት ነው። በዛ ወቅት ምንም ሳልሆን even ትምህርቴን withdraw አድርጌ ነበር ነገር ግን ይሄ ነው የምለው ምንም ምክንያት የለኝም እናም ይኸው ለ6ዓመት ከራሴ ጋር እየተጣላሁ አለሁ።

ማብራሪያው ውስጥ "ይህ ስሜት የጀመረኝ ጌታን ለመቀበል ከወሰንኩበት ጊዜ ጀምሮ ነው like 6ዓመት አካባቢ ማለትም ጌታን ከመቀበሌ 1ዓመት በፊት ማለት ነው" የሚል ሃሳብ ተመልክቻለሁ። እንዴት እንድሆነ አልገባኝም ግን አንድ ነገር ሁለት ጅማሬ ሊኖረው እንደማይችል ነው የማውቀው። የዚህ አለሁበት የምትለው/ይው ሁኔታ አጀማመሩን ማረጋገጡ በጣም አጅግ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም መፍትሔውን ለመፈለግና ለማዘገጀት ይበጃልና በጣም ጊዜ መሰጠት ያለበት ትልቅ ጉዳይ ነው። ከዚህ ቀጥዬ ያለኝን አጭር መልስ ይሆናል ያልኩትን አስቀምጣለሁ።

ተስፋ ምንድ ነው? ተስፋ ይሆንልናል ብለን በልባችን የምንመኘው መልካም ክፉም ሊሆን ይችላል ሁኔታ ነው። ደቀ መዛሙርት ደስ የሚሉ መልካም ሶስት ዓመት ተኩል ከጌታ ጋር ካሳለፉ በኋላ የመጨረሻው የራት ምሽት ልባቸው ምን ያህል እንዳዘና እና መንፈሳቸው እንደታወከ እስቲ እንይ። ምንም እንኳ ጌታ ደጋግሞ ቢነግራቸውና ቢአስጠነቅቃቸውም ቀኑ ግን እንደ ጨለመባቸው ግራም እንደ ተጋቡ እናያለን። ቤተ ሰቦቻቸውና የዕለት ኑሮዋቸውን የሚያሸንፉበት ሥራቸውን ጥለው ሲከተሉት ያልተጨበጠ ግን ይሆናል ብለው ያደረጉት ተስፋ ጌታ ተይዞ ሲወሰድ ምን ሁኔታ ውስጥ እንደነበሩ መገመቱ አያስቸግርም ምክንያቱም በተለያዬ ሁኔታ እኛንም ያጋጠመን ጥቂት ላይሆን ይችላልና።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሁለት ቤት የገነቡ ሰዎች ሲያስተምረን አንዱ ሞኝ ሁለተኛው ጥበበኛ እንደ ነበሩና ቤታቸው የሰሩበት መሰረት ትልቅ ሚና እንደ ተጫወተና መጨረሻቸው ሁለት የተለያዩ እንደ ነበረ ይነግረናል። ወገኖቸ አሁን የምንኖረው ነሮ ከዓመታት በፊት የወሰድነው እርምጃ ውጤት ነው። ጌታን ለመቀበል ስንወስን ምክንያታችን ምን ነበር? እምነት ተስፋ ስለ ምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማይነውጥንም ነገር የሚያስረዳ ነው ይላል (ዕብ 11፡1)

ስለዚህ ተስፋ አሰቃቂ አደጋ ያጋጥመን የፈለገው ይሁን ያበጠው ይፈንዳ ከባድ ችግር ይድረስብን ነገ ጸሐይ ይወጣል ይህም ያልፋል እስኪያልፍ ግን ከኢየሱስ ጋር መጣበቁ ያሻል። ጌታ ኢየሱስ ከሁኔታዎች በላይ የሆነ ጌታ ነው በምትሄድበትም መንገድ እመርሃለሁ ይለናል። ስለዚህ ጸልይና ከፓስተርህ/ሽ ጋር ጊዜ ወስደህ/ሽ ምክር እሻ/ሺ አገልግሎት እንዴት እንደ ምትጀምር/ሪም ጠይቅ/ቂ ከዚህ በፊት ግን ስለ ጌታ ያለህ/ሽ መረዳት ከጌታ ጋር ያለህ/ሽ ግንኙነት አጥርተህ/ሽ ተረዳው/ጂውና ያለ ምንም ወልም ዘለም ከልብ ጨክነህ/ሽ ወስን/ኚ ጌታም አያሳፍርህም/ሽ የድል አምላክ ሲናገርም የምፈውስህ አምላክህ እኔ ንኝ ያለ ነውና።

ጌታ ይባርካችሁ
ወንድማችሁ
Jun 22, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Jun 22, 2011 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...