በአማርኛው አቢግያ በእንግሊዝኛው ደግሞ Abigail የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን የሚገኝ የዕብራይስጥ ስም ሲሆን ቃሉ ሁለት የእብራይስጥ ቃላትን የያዘ ነው። Abi ማለት አባት ማለት ሲሆን gail ማለት ደግሞ ደስታ ማለት ነው። ሆኖም አንድ ላይ Abigail የሚለው በትክክል ትርጉሙ ምን እንደሆነ የተለያዩ ሌክሲኮኖች በተለያየ ሁኔታ ነው የሚተረጉሙት።
STRONG እንደሚከተለው ይተረጉመዋል፦
father (i.e. source) of joy "የደስታ ምንጭ"
HALOT (THE HEBREW AND ARAMAIC LEXICON OF THE OLD TESTAMENT) እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል፦
(my) father was delighted "አባቴ ተደሰተ"
Brown-Driver-Briggs Hebrew and English Lexicon ደግሞ እንዲህ ይለዋል፦
my father is joy "አባቴ ደስታ ነው"
Wikipedia ደግሞ እንደሚከተለው ይተረጉመዋል፦
her Father's joy "የአባቷ ደስታ" ወይም fountain of joy "የደስታ ፏፏቴ"