ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እየሱስ አያማልድም ወይ?

Jun 16, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

7 መልሶች

0 ድምጾች
ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ነው። ስለዚህም በአብ ቀኝ ሆኖ ዘወትር ይማልድልናል። ኢየሱስ ማማለድ ብቻ ሳይሆን በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቅ የሚችል ብቸኛ መካከለኛ ነው።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 8
33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
Quote:
ወደ ዕብራውያን 7
24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
Quote:
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
2፥5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
Quote:
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2
1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
2 እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።
Jun 16, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ያልገባኝ ነገር ጌታን የተቀበለ ይድናል ካላቹ እንድት ነው ክርስቶስ ሚያማልደው አንዴ ከዳናቹ እንደት ያማልዳል?
ጌታ ስለ ዳኑት የሚማልደው እንዲድኑ ሳይሆን በሰይጣን ተጠልፈው እንዳይወድቁና እንዳይጠፉ ነው።

የሉቃስ ወንጌል 22
31 ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ
32 እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።
ጌታይመስገን እሱኮ ሰው አያታም ደስ የምል ማብራሪያ ነው።ተጋው ይብዛላችሁህ
እየሱስ ክርስቶስ እኮ እግዚአብሂር ነው ። እርሱ ያደረግው ነገር ሁሉ የትህትና ስለሆነ ነው እንጂ እርሱ ሁሉን ማድረግ ይችላል።ማማለድ እኮ መለመን እኮ የሰው ስራ ነው እንጂ የአምላክ ስራ አይደለም ስንት አምላክ አለን አብ አምላክ ነው ወልድ አምላክ ነው መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው ስለዚህ አንድ አምላክ አልን እርሱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው።ናቸው አይባልም መለኮት አንድ ስለሆነ
–2 ድምጾች
ሰላም ለርሶ ይሁን።

ጌታ የማስታረቅ አገልግሎቱን በመስቀል ላይ ተፈጸመ ብላል። አሁን ከአባቱ በተስተካከለ ክብሩ ነው ያለው። እናም እሁንም እንደስጋው ወራት ክብሩን ትቶ አይለምንም።

መጽሃፍ ቅዱስ እንዲ ይላል

"እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤[/size] ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
Oct 28, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ወንድሜ በሎጂክ እኮ ብቻ መሄድ በመጽሃፍ ቅዱስ አያዋጣም። መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ ያማልዳል እያለ አንተ አይ አያማልድም ትላለህ። ይህን የምትለው ከአንተ ሎጂክ ጋር ስላልሄደልህ ነው።

እስቲ ከላይ የተጠቀሰውን ሮሜ 8፡34ን አንብብ:-
"የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" ያላል።
በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ኢየሱስ ስለ እኛ ይማልዳል ይላል። አንተ ታዲያ እንዴት ብለህ ነው አያማልድም የምትለው?

ከላይ የተጠቀሰውንም ዕብራውያን 7፡25ንም አንብብ፦
"ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል"
ስለዚህ ከትንሳኤ በኋላ ስላለው የኢየሱስ ህይወት ሲናገር፤ ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በህይወት ይኖራል ነው የሚለው። ታዲያ መጽሃፍ ቅዱስ ኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ በአብ ቀኝም ሆኖ ይማልዳል ብሎ በግልጽ ከጻፈ አንተ ለምን ለመቀበል ይከብድሃል?

አንተ የጠቀስከው ጥቅስ እኮ ፈጽሞ ስለምልጃ የሚናገር ጥቅስ አይደለም። የሚያወራው ስለ መስዋእት ነው። መስዋእትማ ኢየሱስ አንዴ ነው የተሰዋው ሌላ መስዋእት ሊያቀርብ አያስፈልገውም። ጥያቄው ስለ መስዋእት ሳይሆን ስለ ምልጃና ልመና ነው። ምልጃ ደግሞ ኢየሱስ አሁንም ያደርጋል ይህን መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽና በማያሻማ ቃላት የሚናገረው ነገር ነው።

ከእኛ ሎጂክ ጋር ሄደ አልሄደ፤ መጽሃፍ ቅዱስ ያለውን ሳንጨምር ሳንቀንስ መቀበል አለብን። ከሌሎች ጥቅሶች ጋር የሚጋጭም ቢመስለን እንኳን፡ ከተጻፈው ለመቀነስ ወይም የተጻፈውን ለመለወጥ መሞከር የለብንም። ለቃሉ ታማኝ መሆን የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት መሰረትና ሀሁ ነውና።
ሰላም ወዳጆቼ! አንዳንዴ በደፈናው ሳይሆን የቃላት አገባብን/ተትርጉም ማየት ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ፡ "ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።" ከአብ ቀኝ የተቀመጠ ከጌታ በቀር ማንም የለም፡፡ አዎ ኢየሱስ በስጋ የመጋለጥ ወራቱን በጨረሰ ጊዜ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ በአብ ቀኝ መቀመጥ ማለት ምን ማለት ነው?እግዚአብሄር አብ ቀኝና ግራ አለውን? አይደለም! በመፅሀፍ ቅዱስ መቀመጥ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ምሳሌ እናንሳ፡፡ የአለም ፍርድ ቤት ስንሄድ ዳኞቹ ዛሬ ‹‹ለፍርድ ይቀመጣሉ›› ነው ወይም ‹‹ይቆማሉ›› ነው የሚባለው? ዳኞቹ ‹‹ለፍርድ ይቀመጣሉ›› ነው የሚባለው በተቃራኒው ደግሞ ዛሬ ጠበቃዬ ስለእኔ ‹‹ይቆምልኛል›› ነው ወይስ ‹‹ይቀመጥልኛል›› ነው የሚባለው፡፡ ‹‹ይቆምልኛል››፡፡ ስለዚህ ከዚች አለማዊ ምሳሌ የምረዳው የዳኛ ስራ መቀመጥ/ መፍረድ / ነው፡፡ ነገር ግን የጠበቃ ስራ መቆም (መከራከር፣ መለመን ) ነው፡፡
•በዕብ1÷3-4 ‹‹ በስልጣኑ ቃል እየደገፈ ሃጢያታችንን በራሱ ካነፃ በኋላ በሰማያት በግርማው ተቀመጠ›› ይላል፡፡ መቀመጥ መፍረድ ማለት ነው፡፡
•ዩሐ 5÷23 ‹‹… ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው…›› መፍረድን ማፅደቅን መኮነንን ሁሉ ለወልድ (ክርስቶስ) ተሰጥቷል፡፡ የሚፈርድ የሚያፀድቅ የሚኮንን ኢየሱስ ነው ማለት ነው፡፡
•ሀዋ 10÷42 ‹‹ ለአህዛብ እንድንሰብክና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደሆነ እንድንሰብክ አዘዘን›› ሀጢያትን በሠሩ ሙታን ላይ የመፍረድ ስልጣን የጌታ ክርስቶስ ነው፡፡
•«ከእንግዲህ ወዲህ የሰውን ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመና ታዩታላችሁ፤» ማቴ 26፥83
•ኤፌ 2÷10 ‹‹….. መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ›› ይላል የመፍጠር የመግደል ስልጣንም የእርሱ የክርስቶስ ነው፡
ይህንን ለመግለጽ ነው ተቀመጠ የተባለው፡፡ የሰውን ለልጅ ከመላዕክት ጋር በክብር ለፍርድ እንደሚመጣ መጽሃፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ለመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳልን....? ኢየሱስ ክርስቶስ ከመገለጡ በፊት ሰማይና ምድርን በውስጧ ያለውን መላ ፍጥረታቷን ከመፍጠሩ በፊትና ከፈጠረ በኋላ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ብንፈልግ፡-
•ዘፍ1÷26 ‹‹ እግዚአብሔርም አለ፡ ሠውን በመልካችን እንደ አምሳሌያችን እንፍጠር ….› እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱን በመልካችን እንደአምሳላችን (በኛ መልክና አምሳል) ሲል ሶስቱን ያመላክተናል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ አለም ነበር፡፡
•ዘፍ3÷22 ‹‹ እግዚአብሔርም አምላክም አለ፡- እነሆ አዳም መልካሙንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ›› እግዚአብሔር አምላክም አለ ሲል አንድነቱን ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ሲል ደግሞ ሶስትነቱን ያመላክተናል፡፡
•ዘፍ2÷18-19 ‹‹ እግዚአብሔር አምላክም አለ፡- ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት›› እግዚአብሔር አምላክም አለ (ነጠላ ቁጥር) አንድነቱን የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት (ብዙ ቁጥር) ሶስትነቱን ያሳየናል፡፡
ብዙዎች ኢየሱስ አማላጅ ነው ሲሉ አንዳንዶች ኢየሱስ ፍጡር ነው በማለት ያልተገባ ይናገራሉ፡፡ ጌታ ክርስቶስ ይቅርታውን ያደረጋቸው ከላይ ያየናቸው የማስረጃ ጥቅሶች ሁሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ከአብ አባቱና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል እንደሆነ እንጂ እንደሚያንስ አይናገሩም ፡፡ በኢሳ9÷6 ላይ ‹‹ ህፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፣ ስሙም ድንቅ መከር፣ ሃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል…›› ነው ያለው፡፡ ኢሳይያስ በትንቢት መነፅር ጌታ ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ሰለመወለዱ እልፍ አመታት በፊት የፃፈው ነው፡፡ ስሙም "ድንቅ መካር ሃያል አምላክ" አለው እንጂ ፍጡር ወይም አማላጅ አላለውም፡፡ በራሱ በቃሉ ሁሉን ማድረግ የሚችል መሆኑን ሲያሳየን ነው፡፡ አንዳንድ የእምነት ድርጅቶች ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው ይላሉ ሮሜ 8፡31-34 ተመልከተው ‹‹ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን ….. ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው…..››፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በፃፈው መልዕክቱ ምዕራፍ 8 ከቁጥር 1 ጀምሮ ብናነብ የሚያወራው ስለመፍረድ፣ መኮነን ማፅደቅ ነው፡፡ ዕብራውያን 7፡25ንም እንዲሁ፡፡ አንዴ ሊቀካህን ሆኖ ሰለእኛ ሰለበደልነው ዘወትር መስዋዐት የእንሰሳት ደም አያሻንም አንዴ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ስለእኛ ሞቶዋልና ሌላ ደም አያሻንም፡፡
ብዙዎች በስጋ ዘመኑ እንደኛ ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋን ለብሶ ሰው ሆኖ በዚህች አለም በተመላለሰ ጊዜና ስራውን ከፈፀመ በኋላ ያለውን መለየት አልቻሉም፡፡ በዕብ 5፣7 ‹‹እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ፀሎትና ምልጃን አቀረበ›› ይለናል፡፡ ሁሉን በስጋው ወራት ፈጸመ፡፡ ኢየሱስ አንዴ እኛን ከራሱ ከአባቱ እንዲሁም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን፡፡ ሰለዚህ በእኛ በሃጢያተኞቹና በአብ መካከል ሆኖ ለማስታረቅ የወረደ ጌታ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፥5) ፡፡ የሚገርመው በሮሜ8÷26 ‹‹ ነገር ግን መንፈስ (መንፈስ ቅዱስ) ራሱ በማይናገር መቃተት ይማልድልናል….›› ይላል፡፡ ሮሜ 8÷34ን የሚተረጉሙ ሠዎች ሮሜ 8÷26 አላዩትም ይሆን? የኤር 7÷25 ላይም ‹‹ አባቶቻችሁ ከግብፅ ….. በዕየለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼንና ……›› ይህ ቃል የተነገረው ለአብ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ወልድ በድንግል ማሪያም ስጋን ለብሶ አልተገለጸም ነበርና መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል አልወረደም ነበርና፡፡ ታዲያ ወልድ (ሮሜ 8÷34) መንፈስ ቅዱስ (በሮሜ 8÷26) ና አብ (ኤር 7÷25) አማልዱ ማለት አይደለምን? አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም አማላጅ ከሆኑ በዙፋኑ ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈርድ ማን ነው? ቅዱሱ መፅሐፉ ግን እንዲህ ይላል ነገር ግን በዩሃ 16÷25-28 ‹‹ …. በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ እኔም ስለእናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለም››፡፡ እራሱ ክርስቶስ ስለእናንተ አልለምንም እያለ በግልፅ ይነግረናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ናቸው ይላል እንጂ አማላጅ ተማላጅ ብሎ አልከፈለም፡፡
•ዩሃ 10÷30 ‹‹ እኔና አብ አንድ ነን››
•ዩሀ 17÷9-10 ‹‹ የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተም የእኔ ነው››
•1ኛ ቆሮ 3÷23 ‹‹ ክርስቶስም እግዚአብሔር ነው››
•ዩሀ 14÷7 ‹‹ ከእኔስ ብውቀኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፡፡ ከአሁን ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው››
ሎጂክ ነው ላሉኝ ስም-አልባ

ወገኔ ወይ፡ ኸረ ወዴት ወዴት? ምን ሎጂክ እያሉ መሸሽ ነው። ወደ ዕብራውያን 7፡27 ያለውን ያንብቡ ፤ እኔስ ከቅዱስ መጽሃፍ ነው የጠቀስኩሎዎ ፤እርስዎ ሎጂክ ብለው ከተረዱት ይህ የእርሶ መረዳት ነው።

ዕብ7፡27 "ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤" እያለ ፤ እርስዎ ኖት አሁንም ሊያቀርብ ይስፈልገዋል እያሉ ያሉት። ኸረ ለመሆኑ ምልጃና ልመና ያቀርባል ካሉ ፤ ዋናው ለሃጥያት የሚቀርብ ካልወነ ለምን ሊቀርብ ኖራል ፤ ለልብስና ለምግብ እንደማይሉኝ ተስፋ አደርጋለው። ምልጃና ልመና ከመሥዋዕት የተለየው ደግሞ መቼ ነው? የምስጋን መሥዋዕት እንዳለ አልሰሙም ይዎን?

የክርስቶስ ሰላም በሁላችን ላይ ይሁን
ሁለታችሁ ከላይ የጻፋችሁት ወገኖቼ

እኔ እኮ ብዙ መሽከርከር ሳያስፈልገኝ፣ ብዙ የማብራሪያ ብዛት ሳያስፈልገኝ ከመጽሃፍ ቅዱስ በቀጥታ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ኢየሱስ ይማልድልናል የሚለውን ነው ያሰቀመጥኩላችሁ። መጽሃፍ ቅዱስ ያማልድልናል ካለ ሌላ ቲዎሎጂና ሎጂክ አያስፈልግም። ያማልድልናል ማለት ያማልድልናል ማለት ነው በቃ አለቀ! የፈለጋችሁትን ያህል የቃላት ድርደራ ብታደርጉ ቃሉን ልትቀየሩ አትችሉምና አትልፉ።
Quote:
ሮሜ 8፡34
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

ዕብራውያን 7፡25
ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል

የጻፍኩትን ደግሞ የማታነብቡ ከሆነ ባንወያይ መልካም ነው። ምንም ጥቅም የለውም። በተለይ ስለ መስዋእት ደጋግመው የሚጽፉ ሰውዬ፤ ከላይ ቢያነብቡት እኮ ኢየሱስ አንድ ጊዜ መስዋእት እንዳደረገ ቃሉ ስለሚል ይህ ለማንም ችግር አይደለም። ስለዚህ መጀመሪያ በመስዋእትና በምልጃ መካከል ያለውን ልዩነት ትንሽ ያንብቡ። ልዩነታቸውን እስካልተረዱ ድረስ ውይይት ማድረጉ ማንም አይጠቅምም። ዋናው ጥያቄው የተነሳው ስለ ምልጃ ነው። አይ እኔ በግድ ስለ መስዋእት ነው መነጋገር የምፈልገው ካሉ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ቢከፍቱ መልካም ነው። ስለ መስዋእት የተወያየ ማንም የለም እዚህ።

ኢየሱስ አንዴ ብቻ ነው ምልጃ ያደረገው፤ አሁን ምልጃ አይደርግም የሚል ቃል እኮ ከመጽሃፍ ቅዱስ ሊያሳዩኝ አልቻሉም። መልሰው መልሰው ስለ መስዋእት ነው የሚያወሩት። ይሄ ቅንነት ሳይሆን አውቆ የተኛን እንደሚባለው አይነት ነው።

እርሶ ደግሞ ስለ ኢየሱስና አብ አንድ ነን ወዘተ ብለው የጻፉ ሰውዬ፤ ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ ውይይት ስለተደረገ አሁን መድገም አያስፈልግም። የሚከተሉትን ውይይቶች ያንብቡ። አንድ ነን ማለተ እኩል ነን ማለት አይደለም። ይሄንኑ አንድ የሚለውን የግሪክ ቃል ኢየሱስ በዚያው በዮሃንስ ወንጌል ስለ አማኞችም ሲጸልይ "አንድ እንዲሆኑ" ይላል። ልክ ባልና ሚስት አንድ ናቸው እንደሚባለው ስለ ህብረት እንጂ ስለ የስልጣን ተዋረድ አይደለም የሚያወራው። የሚከተሉትን ውይይቶች ያንብቡ፦

እግዚአብሔር ይባርካችሁ
"አንድ ነን ማለተ እኩል ነን ማለት አይደለም። " ይህ የእርስዎ ሎጂክ ነው እንጂ የመጽሃፍ ቅዱስ እውነት አይደለም።

ፊል 2፡6 "እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።" ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እኛ በስጋ ጠገልጦ ከመምጣቱ በፊት ከእግዚአብሔር አብ ጋር እኩል ነበር።

ዮሐ 17፡5 "አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።" ጌታ እንዳለው በአሁን ወቅት ወደሰማይ ካረገ በዋላ ከአብ ጋር የተካከለ ክብር አለው። ከአብ ጋር እኩል ነው።
"...እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። ...በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤"

"...እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።..."

ኽረ የምናመልከው ኢየሱስ እንደ አብ ሕይወትን መስጠት ከቻለ፤ ከአብ ፊት በአሁኑ ወቅት ምልጃን ማቅረብ ለምን አስፈለገው?
አንደኛ ምልጃ ማቅረብ ምን አስፈለገው ሳይሆን፤ ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን እንደሆነ ጨርሶ የዘነጉት ይመስላል። አንዱ የሊቀካህን ሥራ ደግሞ ስለ ህዝቡ መማለድ ነው። ሃጢአታቸውን ማሰረይ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ ኢየሱስ አልፎ በሚሰጠብት ወቅት ምን አለ፤ "እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ" ይላል። ሉቃ 22፡31-32

ስለዚህ ምልጃ ሲባል ስለ ሃጢአት ወይም የምንፈልገውን ነገር እግዚአብሔር እንዲሰጠን ብቻ አይደለም። መንፈሳዊ ውጊያንና አደጋንም ያካተተ ነው። በአባታችን ሆይ ጸሎት ላይ "ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን" የምንለው አይነት ጸሎት ማለት ነው። ስለዚህ ምልጃን በጣም አጥብበን ማየት የለብንም።

ዮሃንስ 14፡13-16 ምን ይላል? ኢየሱስ ወደ አብ እንደሚሄድና አብን እንደሚለምን ይናገራል። "እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል"። ያላል።

በአንድ ጎን ብቻ ጥቅሶችን ይዞ መሄድ ችግር ያመጣል። ከላይ በዘረዘሩት ጥቅሶች ሌሎችን ጥቅሶች መሻር ትክክለኛ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጓሜ ላይ ሊያደርሰን አይችልም። ምንም እንኳን የሚጋጩ ቢመስሉንም ሁሉንም ጥቅሶች መቀበል እንጂ ያለብን አንዱን በአንዱ ለመሻር መሞከር የለብንም።

እግዚአብሔር ከኢየሱስ እንደሚበልጥ የሚያሳዩትን እና ያለምንም መዟዟር በቀጥታ ኢየሱስ እንደሚማልድ የሚናገሩትን ጥቅሶች ምን ሊያደርጓቸው ነው? ሊሽሯቸው ነው? እንዲህ አይነት አተረጓጎም አይሰራም። እስቲ የሚከተሉትን ጥቅሶች ምን ውስጥ ሊከቷቸው ነው?
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
11፥3 ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።

የዮሐንስ ራእይ 1
1 ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥

ሮሜ 8፡34
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

ዕብራውያን 7፡25
ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል
ሰላም ለናንተ
ኢየሱስ ያማልዳል (በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ) ሚለው ቃል እራሱ የማማለድ ስልጣንነቱን ሚገልጥ ነው:: እግዚአብሔር ቀኝ ወይም ግራ የለዉም መንፈስ ነው ::

ጴንጤ ደሞ ክርስቶስን ስንቀበል ድነናል ቃሉ እንዴት ነው አዉን ያማልዳል ሚሉት?
0 ድምጾች
መጽሃፍ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ክርስቲያኖች እንዲህ ይላል።

2ኛ ቆሮ 5፤ 14-20
" ... አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ...ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ...በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 20 እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን

+ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም!

+በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ!

+ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን! ይህ መጽሃፍ ቅዱስ እውነት ነው ።

ሰላም ሁኑ
Oct 29, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
እኔ እኮ አንዳንድ ጊዜ በቃ መወያየት ይከብዳል ልበል።
ጥያቄው ክርስቶስ ያማልዳል ወይም አያማልድም የሚል ነው። ከላይ እንደሚያማልድ ቁልጭ ባለ ጥቅስ ተገልጿል ታዲያ ሰዎች አንዴ ስለ መስዋእት አንዴ ስለማስታረቅ አገልግሎት ወዘተ ዘልለው ሌላ ያልተባለ ርዕስ ውስጥ እንደሚገቡ ሊገባኝ አልቻለም። ስለ እኛ ይማልዳል ወይም አይማልድም የሚል ጥቅስ ከመጽሃፍ ቅዱስ በቀጥታ ማውጣት እየተቻለ። ወደ ሌላ መሽከርከርና ድርቅ ማለት ምን ይባላል። ይሄ የቅንነትም እውነትንም የሚፈልግ ሰው ባህርይም አይደለም። ያልተጠየቀ ጥያቄ ባንመልስና በተጠየቀው ላይ ብናተኩር መልካም ነው። ሮሜ 8፡34 በእግዚአብሔር ቀኝ ሆኖ ይማልድልናል ይላል በቃ ያንን መቀበል ነው። የምን መጋጋጥ ነው።
በእውኑ መማለድ ማለት ምን ማለት እንደወነ ያውቃሉን? ካልወነ ሰውን insult ከማድረግ ወደ መጋቢዎ ቀረብ ብለው ይጠቁ።

2ኛ ቆሮ 5፡20 አንብበውታል??? ስለ ሌላው ቅንነት ከመፍርድዎ በፊት እባክዎትን ያብቡት እንዲህ ይላል " እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማል(?)ድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን"። ይህ ጥቅስ ለርስዎ ሰለመማለድ ካልመሰልዎ እባክዎትን እርስዎን ይመርምሩ፤ ሌላውን ቅንነት የሌለው ብለው ከመሳድብ።
+1 ድምጽ
ሰላም በክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ላይ በተሰራው ስራና በጌታ ብቸኛ አዳኝነት ለሚያምኑ ሁሉ ይሁን
በክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነትና አዳኝነት የምናምን ስለምን በማይሆንና ባልተጻፈ ነገር እየተከራከርን ልዩነታችንን እናሰፋለን? በሐዋርያትም ሆነ በጥንት አባቶቻችን (ከ14ኛ ክ.ዘ በፊት) ያልነበረ ትምህርት እናንጸባርቃለን?? መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለምልጃ በግልጽ ተጽፎልናል:: አስቀድሞ በሌሎች ወገኖች እንደተገለጸው;
Quote:
በሮሜ 3: 11,23-34 ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥... ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። ይላል መ.ቅ ስለምልጃ በግልጽ የተቀመጠልን ክፍል አለ
Quote:
ሮሜ 8:34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ይላል ደግሞም በተደጋጋሚ እንደተገለጸው
ዕብራውያን 7:25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። እስኪ አስተውሉት ይህንን ክፍል (ሊያማልድ ሲል ስለኃላፊ ጊዜ አይደለም የሚናገረው በዚህ ላይ ደግሞ ዘወትር ነው የሚለው)
Quote:
ከዮሐንስ 14:6 ጋር አገናኙት "ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም"። በተለይ አንደኛው ወንድሜ የኢየሱስን አማላጅነት መ.ቅ በግልጽ ያስቀመጠውን ሐሳብ ለመከላከል ያቀረብከው ምሳሌ (ስለ መቀመጥ/መፍረድ እና ስለ መቆም/ጠበቃ) ከመ.ቅ ጋር ይጋጫል ብተለይ
Quote:
ከ1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንግዲህ አየህ ወንድም አነተ ያየኽውና በራስህ የተረጎምከው መቀመጥ የሚለውን ከመፍረድ ጋር ያያዝከው ታዲያ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን የሚለውን ካቀረብከው ምሳሌ ጋር እንዴት እንደሚሔድልሕ ብታስተውለው ይበጃል እላልሁ; ይህ ብቻ አይደለም የእብራውያን ጸሓፊ የሰው እጅ ባልሰራት ቤተ መቅደስ አገልጋይ ነው ይለናል
Quote:
ዕብራውያን 8:1-2 ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት። በተጨማሪም በአሁን ሰዓት በአብ ፊት ስለእኛ የሚታይልን ኢየሱስ ነው
Quote:
ዕብራውያን 9:24 ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ። ለምን ቢባል በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለ መካከለኛ እርሱ ስለሆነ ነው
Quote:
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ስለዚህ ያማልዱናል ብለን ያስቀመጥናቸው ሰዎችም ይሁኑ ቅ.መላዕክት አያድኑንም እነሱ እራሳቸው ለእግዚአብሔር በመታዘዛቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ, ሕዝቅኤል 14:20 ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ስለዚህ የሚዳነው በመስቀል ላይ እርቃኑን ዋጋ የከፈለልን በእርሱ መሰቀል ለኛ ፈውስና መዳን የሆነልን ብቸኛ አዳናችን ጌታ ኢየሱስ ነው!!!!!! የስጋችንም ሆነ የነፍሳችን መዳኛ እርሱ ብቻ ነው መ.ቅ እንደሚል
Quote:
ሐዋ 4:12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። በብዙዎቻችን ዘንድ ኢየሱስን አማላጅ ነው ብሎ መቀበል ክብሩን እንደመንካትና ዝቅ እንደማድረግ ስለሚታይ ነው ነገር ግን ይህ አመለካክት ኢመ.ቅዊ ነው ሐዋርያት አባቶቻችን ያላስተማሩት ነው ለምን ቢባል እነ ጳውሎስና ዮሐንስ አምላክ መሆኑን እያወቁ ነገር ግን ከሞት በድል ከተነሳም ብኋላ እንኳን በአብ ቀኝ ተቀምጦ ለኛ ሊቀ ካህን;አገልጋይ;አማላጅ;መካከላኛ;ጠበቃ;አሁን ስለእኛ የሚታይልን እያሉ ነው የጻፉልን ታዲያ እኛ ለምን ከበደን? ለምንስ ስርዋጽ(ሾልኮ የገባ) ትምሕርትን እንቀበላልን??
ተጨማሪ መ.ቅ ውስጥ የትም ቦታ ላይ ባይጻፍም መ.ዚቅ ግን እንዲሕ ይላል ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አአርግ ሰማየ ሐበ አቡዬ በእንተ ዕሥዕል ምሕረተ ለዕሊአዬ ትርጉም ኢየሱስም አለ ወደ አባቴ ወደ ሰማይ እሄዳለሁ በዚያም ምህረትን እለምናለሁ ይላል መቼም ይህንን እንደ ማስርጃ ባንወስደውም እውነትነት ግን አለው:: ምክንያቱም ኢየሱስ ስሌኛ ያማልዳልና;
እንግዲህ ከዚህ በታች ካለው ሀሳብ ጋር ነው እየተጋጨን ያለነው እናስተውል
1, ሮሜ 8:34....በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
2,ዕብራውያን 7:25....ሊያማልድዘወትር በሕይወት ይኖራልና
3,ከዮሐንስ 14:6....በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም"።
4,ዕብራውያን 8:1-2....እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥
5,1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:1.... ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
6,ዕብራውያን 9:24....በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ
7,1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5.... በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Nov 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Nov 3, 2011 ታርሟል
–1 ድምጽ
የክርስቶስ ሰላም ለሁሉም ይሁን።

የተጠቀሰው እግዚአብሔር ቃል እየውነ እንዶት ሾልከው የገቡ ብለው የንጉሱ ቃል ያቃልላሉ

የ2ኛ ቆሮ 5፤ 14-20
" ... አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ...ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ...በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 20 እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።

+ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም!

+በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ!

+ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን! ይህ መጽሃፍ ቅዱስ እውነት ነው እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት ሾልኮ የገባ ቓል አይደለም።
Nov 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ሰላም ወገኔ

ምን ለማለት እንደፈለግህ ሊገባኝ አልቻለም። ጥያቄው እኮ ኢየሱስ አሁን ይማልዳል ወይስ አያማልድም የሚል ነው እንጂ ስለ እኛ አይደለም። መልሱም ሊሆን የሚገባው ይማልዳል ወይም አይማልድልም የሚል በግልጽ ከመጽሃፍ ቅዱስ አውጥቶ ማስየት ብቻ ነው።

ይህ ሳይሆን ግን ያልተጠየቀ ጥያቄ ውስጥ ገብተን እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ እንደሚያስታርቅ የሚል ጥቅስ መጻፉ ጥያቄውን የሚመልሰው አይመስለኝም። እግዚአብሔርማ በእኛ ሆኖ በወንጌል ሰዎችን ከራሱ ጋር እንደሚያስታርቅ ግልጽ ነው። ጥያቄው ግን ስለ እኛ ሳይሆን በሰማይ ኢየሱስ አሁን ይማልዳል ወይስ አይማልድም የሚል ነው። እና ያልተጠየቀ ጥያቄ ባንመልስ መልካም ነው እላለሁ። አማኞች ለሌሎች ሰዎች እንደሚማልዱማ መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጽፎአል። የሞቱ ሰዎች አያማልዱም ተባለ እንጂ፤ በህይወት ያሉማ አማኞች መማለድ አንዱ አገልግሎታቸው ነው። እናም ነገሮችን እያዘበራረቅን ሰዎችን ግራ ባናጋባ መልካም ነው። በተጠየቀው ጥያቄ ላይ እናተኩር። ጥያቄው ስለ ኢየሱስ ነው እንጂ ስለ እኛ አይደለም።

ሮሜ 8:34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
ወንድሜ ከላይ እኔም ሆንኩኝ ሌሎች ወገኖቼ የሰጡትን መልሰ ማየት ትተህ ስርዋጽ(ሾልኮ የገባ) ትምሕርትን ለምን እንቀበላልን?? ብዬ የጻፍኩትን ትኩረት ሰጠኽው??? ሾልኮ የገባ ያልኩት ሐዋርያት ያላስተማሩት ትምህርት ስለምታንጸባርቁ ነው አሁን ኢየሱስ ሳይሆን ቅዱሳን ሰዎች ናቸው የሚያማልዱት የሚል ሐዋርያት ያላስተማሩትን ስለምታንጸባርቁ ነው;; ደጋግመህ የጠቀስከው
2ኛቆሮንቶስ 5;18-20 ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።
እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።

ይህ ሃሳብ እኮ ከላይ አንድ ወንድም እንደገለጸው የሞቱ ሰዎችን አይመለከትም በህይወት ላለነው ለኛ ነው የሚመለከተው እርሱም በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖ እንደተባለው አስታራቂ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል የተከፈለለትን ዋጋ ሳያውቅና ሳያምን በጥፋት መንገድ እየሔደ ያለውን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ስለዚህ ወዳጄ መ.ቅ ያማልዳል ካለ እሱን መስማትና መቀበል ነው እንጂ አያማልድም የሚል ጥቅስ ፍለጋ መዞር እያዋጣም ለዛውም ላይገኝ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የክርስቶስ ሰላም በሁሉም ላይ ይሁን፡

ወንድሜ ወይ፡

አስተያየትሁን ሳነበው በጣም ገርመኝ፤ ከርስዎ በፊት የጻፉት ወንድም የ2ኛ ቆሮ 5፤ 14-20 ያለው ቅል ስለምልጃ አይደለም አሉ እርስዎ ደግሞ የሞቱ ሰዎችን አይመለከትም በህይወት ላለነው ለኛ ነው አሉ። በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ስለሞቱ ስዎች እዚጋ የጠቀስኩት ፈጽሞ የለም። እኔ እንደጻፍኩ ማስመሰል በሃሰት መክሰስ አይሆንምን?

ሁለተኛ ከርስዎ በፊት ያጻፉት ጥቅሱ ስለማስታረቅ ነው እንጁ ስል መማለድ አይደለም ይሉና፤ ጥቅሱን እኛ መማለድ እደምንችል ይህንን ቃል መስረት አድርገዋል። ይህ በቃሉ ላይ አውቆ/ሳያውእቁ ሁለት የተለያየ ሃሳብ ማንሰባረቅ አይሆንምን?

በተጨማሪም ደግሞ እኔ በክርስቶስ እየሱስ ያላምኑ ስዎች ያማልዳሉ ብዪ ፈሞ አልጻፍኩም። እንዲያሁም እኔ አንደናንተ ለቃሉ ማብራሪያ አልስጠውም። የ2ኛ ቆሮ 5፤ 14-20 ላይ ያለሁን ቃልን ነው የተቀስኩት። ይህ ቃል የምናምነውን የሚፈትን ከወነ እራሳችንን ልንመረምር ይገባል እንጂ፤ እኔ በእየሱስ ያላምኑ ስዎች ፤ የሞቱ ሰዎችን እንደጻፍኩ ማሰመሰል ያሁም እንድ አንካን እኔ ማብራሪያ ሳልሰጥ ይህ ሁሉ ትግል ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ምን የሚሉት ነው።

እናም እንደኣይሁድ በሃሰት ወንድማችንን ባከስ መልካም ነው። ከእግዚአብሔር ቃል እንዲ ይላል "ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።" ከዚ ቃል ጋር መታገል የወደደ ይታገል።

ኢየሱስ ጌታም እውንተኛም አምላክ መድሃኒትም ነው።
0 ድምጾች
የዮሐንስ ወንጌል 16፤26

"በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ [እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም... ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።"

ጌታ አብን የምለምንላቹ አይደለሁም አለኮ ኸረ በቃን።
Nov 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ይቅርታ አድርግልኝና አይበቃም። አንተ እያደረግህ ያለኸው በጣም የታወቀ የመጽሃፍ ቅዱስ አተረጓጎም ችግር ነው። ይሄውም አንዱን ጥቅስና አንዱን ጎን ብቻ ይዞ መሄድና ሌላውን ከዚያ የሚቃረን የሚመስለውን ለመሻር ወይም ለማፈን መፈለግ ነው። እንዲህ ያለው የመጽሃፍ ቅዱስ አተረጓጎም ወደ ስህተት ያመራል። የስህተት ትምህርት ማለት ብዙ ጊዜ አንድ እውነት ብቻ ይዞ ሌላውን ሁሉ አፍኖ መሄድ ማለት ነው እንጂ ሙሉ ለሙሉ መሳት ማለት አይደለምና።

እስቲ የአንተን ጥቅስ እንመልከተው።

የዮሐንስ ወንጌል 16
"26 በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤
27 እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና።"

ይህ ክፍል የሚጀምረው "በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ" ብሎ ነው። ከዚያው ደግሞ ሁለት ጥቅሶችን ከፍ ብለን ስናነብብ በቁጥር 24 ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ ስለ ደቀመዛሙርቱ ልመና ወይም ጸሎት ነው የሚናገረው፦

24 እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ

ስለዚህ አንተ የጠቀስከው ክፍል ሁሉ የሚያወራው ደቀመዛሙርቱ ስለሚያደርጉት ልመና ነው። ኢየሱስ ምን እያላቸው ነው ታዲያ? እስከ አሁን በስሜ አልለመናችሁምና ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን በስሜ ለምኑ (ቁጥር 24)። ይህ ማለት ግን እኔ ጸሎታችሁ እንዲሰማ እለምንላችኋለሁ ማለት አይደለም (ቁጥር 26)። አብ ራሱ ስለወደዳችሁ ጸሎታችሁን ይሰማል (ቁጥር 27)

ይህ እንግዲህ ደቀመዛሙርቱ የሚፈልጉትን ነገር በኢየሱስ ስም አብን እንዲለምኑ የሚያበረታታ ክፍል ነው።

ይህ ማለት ኢየሱስ ስለ ደቀመዛሙርቱ መንፈሳዊ ህይወት፤ እነርሱ ስለማያውቁትም መንፈሳዊ አደጋ ወዘተ ጨርሶ አልማልድም ብሎ ተናገረ ማለት ነው? በፍጹም አይደለም። ምክንያቱም በሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ኢየሱስ ራሱ እንደሚማልድ በግልጽ ተጽፏልና። እና እነዚያን ጥቅሶች እናፍናቸው? እንሻራቸው? አይገባም። ሁሉንም ከአውደምንባቡ ጋር በጥንቃቄ አጥንተን መልእክታቸውን መያዝ ነው ያለብን።

እነዚህ ከዚህ በታች ያሉት ጥቅሶች ለምሳሌ በግልጽ ስለምልጃ የሚናገሩ ናቸው። ታዲያ እነዚህን እናፍናቸው? እንሻራቸው? አይሆንም።

ሮሜ 8፡34
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደውክርስቶስ ኢየሱስ ነው

ዕብራውያን 7፡25
ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል

ምልጃ ሲባል እኛ ስለምንፈልገው ነገር ብቻ ማለት አይደለም። ምልጃ ሰፋ ያለ ነገር ነው። እኛ የማናውቀውና የማንለምነው ብዙ የሚያስፈልገን መንፈሳዊ ነገሮች አሉ።

ለምሳሌ ኢየሱስ አልፎ በሚሰጠብት ወቅት ምን አለ፤ "እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ" ይላል። ሉቃ 22፡31-32

ስለዚህ ምልጃ ሲባል ስለ ሃጢአት ወይም የምንፈልገውን ነገር እግዚአብሔር እንዲሰጠን ብቻ አይደለም። መንፈሳዊ ውጊያንና አደጋንም ያካተተ ነው። በአባታችን ሆይ ጸሎት ላይ "ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን" የምንለው አይነት ጸሎት ማለት ነው። ስለዚህ ምልጃን በጣም አጥብበን ማየት የለብንም።

ዮሃንስ 14፡13-16 ምን ይላል? ኢየሱስ ወደ አብ እንደሚሄድና አብን እንደሚለምን ይናገራል። "እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል"። ያላል።

በአንድ ጎን ብቻ ጥቅሶችን ይዞ መሄድ ችግር ያመጣል። ከላይ በዘረዘሩት ጥቅሶች ሌሎችን ጥቅሶች መሻር ትክክለኛ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጓሜ ላይ ሊያደርሰን አይችልም። ምንም እንኳን የሚጋጩ ቢመስሉንም ሁሉንም ጥቅሶች መቀበል እንጂ ያለብን አንዱን በአንዱ ለመሻር መሞከር የለብንም።

ሁሉንም ስለ ምልጃና ጸሎት የሚናገሩ ክፍሎችን በጥንቃቄ ካየንና ካጠናን በኋላ ነው በቃ የሚባለው እንጂ አንድ ጥቅስ ነጥለን ይዘን በመሄድ አይደለም።
ሰላም ወንድሜ ፡

ጥቅሱ የኔ ሳይሆን የጌታ ቃል ነው! እኔ ምንም የተረጎምኩት ነገር የለም፤ ቃል ቃል ነው ያሰፈርኩት። ዝርዝር ትንተና ትርጉም የሚይስፈልገው ቃል አይደልም። ወንድሜ ሆይ፡ አንተን ልስማ ወይስ ጌታ ኢየሱስ ራሱ ያለሁን፤ ይቅርታ አድርግልኝና እኔ ጌታን መስማት እመርጣለው። እርሱም እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም በስሜ ለምኑ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
እንዲያሁም ይበልጥ ደስ የሚለው ነገር በስሙ ማንኛውም ነገር ስንለምን ጌታ ኢየሱስ እራሱ ያደርገዋል። በጌታ የሚያምን ሁሉ ደስ ሊለው የሚገባው፤ በስሙ የምንለምነው ሁሉ እርሱ ያደርገዋል ይኽም ጌታ አሁን በክብሩ እንዳለ ማስረገጫ ነው። ዮሐ 14፡13 ኢየሱስ በአሁኑ ወቅት ያማልዳል ማለት አሁን ያለሁን ክብሩን አለማየት ነው።

ወንድሜ ሆይ፦ እኔ የሚቃረን ጥቅስ አለ ብዬ ያፈንኩትም የሻርኩትም አንዳች ጥቅስ የለም። ብልስ እኔ ማን ነኝ? እንኳን የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ይቅርና ያንዲት ከተማ ህግ እንኳን የሻረ የሚደርስብትን የሚያውቁ ይመስለኛል።

እስቲ እርስዎ እንዳሉት እርስሆ ታፍነዋል ያልዋቸውን ጥቅሶች ከፍ እና ዝቅ ብለን እንያቸው፡
ሮሜ 8፡ 28-35
28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤30 አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።31 እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?32 ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?36 ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።37 በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።

ይህ የመጻህፍ ቅዱስ ክፍል እርስሆ እንዳሉት በፍጹም ስለምልጃ የሚናገር አይደለም። ይህ ክፍል የሚናገርው እግዚአብሔር የጠራው ፤ ያጸደቀው፤ያከበርው የልጁንም መልክ እንዲመስሉ የወሰናቸውን ማንም ሊከሳቸው እንደማይችል ምክንያቱም ሊያጸድቅም ሊኮንንም የሚችል እግዚአብሔር ይልቁንም ሞቶ ተንሰቶ አሁን ግን በክብር ያለው ኢየሱስ ነው። (ማስረገጫ -ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል። 23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው ዮሐ 5፡21)
ዕብ 7፡24-27
24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ 25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። 26 ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤
የጌታ ኢየሱስ ሊቀ ካህንነት ዘላለማዊ ነው ዕብ 7፡27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ዕብ 7 ፡ 25 ታእስከ 27 ውርድ ብለው ያንብቡት የሚለው እኮ ጌታ እርሱን ስለ ሕዝቡ በመስቀል ላይ ባቀረበ ጊዜ ፈጽሞአል ነው የሚለው። የሚገርመኝ ነገር ቁጥር 25 ለምልጃ የሚጠቅሱ ወንድሞች/እህቶች ቁጥር 27 ከነሰኡ ሓሳብ ጋር ስለማይሄድ ስለመስዋእት ነው የበጽሃፍ ቅዱሱን ሃሳብ ብራሳቸው ሎጂክ ሊለያዩ ይጥራሉ። እንዚህ ወገኖች እኮ ይህ የመጽሃፍ ቅዱስ መልእክት ሲጻፍ ምእራፍም ቁጥርም እንዳልነበርው ስለማያውቁ ፤ መጽሃፍ ቅዱስን በጎጥ ሊከፋፍሉት ሲጥሩ ስታይ ያሳዝናል። ወንድሜ ወይ ለዘመናት ያስተማርከው ወይም የተማርከው ስልወነ ሳይወን ምእራፍ 7 አጠካላይ መልእክት ልትረዳ ይገባል ይኽውም የሚያስረዳው ኢየሱስ ዘላለማዊ(ለዘላለም በህይወት የሚኖር) ሊቀ ካህን እንደወነ እለት እለት መሥዋዕትን (የህይወት፤ የጸሎት፤የምልጃ) ሊያቀርብ እንደማያሰፈልገው። በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞኢየሱስ እርሱ ሊያድናቸው ይችላል።

ዮሃንስ 14፡14-19 14ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።19 ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።

የተቀሱት ምእራፍ ላይ በወደ አብ ሄዶ እንደሚለምን በጹም አይልም። ጌታ በምድር ላይ በሚያስተምርበት ወቅት ብዙጊዜ ይጸልይ እንደነበር የታወቀ ነው። ኢየሱስ የሄደው ቦታ ሊያዘጋጅልንንና አጽናኙን ሊልክ ነው፡ ሊለምን አይደለም። ኢየሱስ ምድር ላይ እያለ (ከመክበሩ በፊት) አብን ይልምን እንደነበር ለምረዳት ዮሐ 17 ጸልየው ያንብቡት።

ሁሉን ቻዩ ጌታ በስሙ የምንለምነውን እራሱ ያደርገዋል። አሜን
እንግዲያውስ ይሄንንም ጥቅስ ያለ ማብራሪያ ቃል በቃል ይቀበሉዋ! ወይስ የሚስማማዎትን ብቻ እየመረጡ ነው የሚቀበሉት?
Quote:
ሮሜ 8፡34
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

እርሶ ባነሱት ጥቅስ ላይ ምልጃ ወይም መማለድ ወዘተ የሚል ቃል እንኳን የለውም። ይሄ እኔ የጠቀስኩት ሮሜ 8፡34 ግን በግልጽ ስለ ምልጃ ነው የሚያወራው። እንግዲያውስ ያለ ማብራሪያ ይቀበሉታ!

ይቅርታ ያድርጉልኛ ውይይታችን ለመማማር ሳይሆን "አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም" አይነት ሆነብኝ። እግዚአብሔርና ኢየሱስ እኩል ናቸው አይበላለጡም የሚል አስተሳሰብ ስለያዙ ብቻ፤ ቃሉን በግልጽ እንዳያዩ ትልቅ መጋረጃ የሆነብዎት ይመስላል። በግልጽ "ይማልድልናል" ብሎ መጽሃፍ ቅዱስ የሚናገረውን እንኳን አይ "አይማልድልንም" ማለት ነው ብለው እንዲተረጉሙት ተገደዋል። ይህ ጤናማ አይደለም።
ወንድሜ ወይ

ከዚህ በፊት በሰጡት አስተያየት ላይ አንዱን ጥቅስና አንዱን ጎን ብቻ ይዞ ከመሄድ ከጥቅሶቹ ከፍ ብለን እናንብበው ባሉት ሃስብ መሰረት፡

ሮሜ 8፡ 28-35 ያለውን ቃል ስናነበው የመረጣቸውን፤ ያጸደቃቸውን፤ ያከበራቸውን እነዚህን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? እያለ ይጠይቅና ቃሉ ለዚህ ጥያቄ እዚያው እንዲህ እያለ መልስ ይሰጣል ፦ መኰነንም ማጽደቅም የሚችለው ኢየሱስ እንደወነ ከሳሾች ግን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ሲናገር ቁጥር 37 እንዲህ ይላል "በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።" ስለወነም ለዘመናት ሰዎች የራሳቸውን ሎጂክ ጥቅሱን እየተራሱ ያስትላለፉትን ለጊዜው ተውት አድረገን ምእራፉን በሙሉ ቢያነቡት እውነቱ ይበልጥ ይታይዎታል።

ሃሳቦ በየጊዜው እየቀያየሩ አንዴ ጥቅሱ ብቻ እንይ ከጥቅሱ በላይ ያሉትን እና ሌሎች የመጸሃፍ ቅዱሱ ክፍሎች ለማፈን ከፈለጉ ቃሉ እንኳን አሁን እየማለደ ነው ብሉ አይገልጸውም ምክንያቱም የቃላቱ ዝይቤ እንካን ስናይ፡
የሞተው፥ ያለፈን ነገር
ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ ... አሁንም እንደተነሳ ነው ያለው
በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ... አሁንም በቀኝ ያለው
ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ... ከላይ "የሞተው" የሚለው ቃል አሁንም ጌታ ሞቶ እንዳለ እንዳማያሳይ ሁሉ የሚማልደው የሚለውም አሁን በሰማይ እይደርገው እንዳለ አይሳይም። (who also maketh intercession for us; which is done, not by vocal prayer, as in the days of his flesh on earth; or as supplicating an angry judge; or as controverting: a point in the court of heaven; but by the appearance of his person for us, by the presentation of his sacrifice, by offering up the prayers and praises of his people, by declaring it as his will, that such and such blessings be bestowed upon them, and by seeing to it, that the benefits of his death are applied to those, for whom they were designed; which intercession of Christ proceeds upon the foot of a satisfaction made; it always continues, and is ever prevalent, and so has a considerable influence to secure from condemnation.)


ወንድሜ ሆይ - "አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም" አይነት ሆነብኝ ምነው ይላሉ። እርሶዎ አይደሉምን ጌታ ያለውን "እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም" ቃል አልስማም ያሉት።
የቃላት መሰንጠቅ ከመጣማ እንግዲያውስ እውነቱን በትክክል እንሰንጥቀው።

Romans 8:34 (NIV)
Who is he that condemns? Christ Jesus, who diedmore than that, who was raised to lifeis at the right hand of God and is also interceding for us.

በዚህ ክፍል ስለ ክርስቶስ የተነገሩትን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገሮች እንያቸው እስቲ፦
  • Christ Jesus, who died (ኃላፊ ጊዜ / past tense)
  • more than that, who was raised to life (ኃላፊ ጊዜ / past tense)
  • is at the right hand of God (የአሁን ጊዜ / present tense)
  • and is also interceding for us (የአሁን ጊዜ - አሁን በመደረግ ላይ ያለ / Present Continuous)
I rest my case!
ምን መጽሃፍ እየተቀሙ እንደውነ አስተውለሁታልን? The New International Version,(NIV), which was first published in 1978. It has many omissions and errors.

እኔ በበኩሌ ቃላት አልሰነጠኩም እርስዎ እንደዚያ ካሉት መብቶ ነው። እስቲ እንደ NIV ስህተት የሌለበትን King James Bible (Cambridge Ed.)1611 Edition እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገሮች እንያቸው እስቲ
Romans 8:34
Who is he that condemneth?
It iS Christ that died,
yea rather, that is risen again, "IS" not was
who is even at the right hand of God,
who also maketh intercession for us.

እርስዎ ከጠቀሱት (NIV)King James ዓረፍተ ነገሮቹ ምን ያህል እንደሚለዩ አስተዋልን? King James Bible የእርሶን ትንተና እንደአማርኛው ዜሮ ያደርገዋል።
ኢየሱስ ጌታ ነው።
እረ ወንድሞች አንድ ስለሚያደርገን ስለሚያስማማን ሃሳብ ብንለዋወጥ አይሻል ይሆን? ካልተሳሳትኩ ይቅርታ አርጉልንኝና ፍቅራችን የሚያደላው ለአምላካችን ሳይሆን ላለንበት የ እምነት ድርጅት ይመስላል። ሁላችንንም የሚያስማማን በዝቶ ሳለ ነገር ግን ስለማንግባባበት መባክን ለምን ይሆን? ከሁላችሁም መረዳት እንደቻልኩት አጠር ባለ መልኩ በጌታችን በመደሃኒታችን እና በአምላካችን በ እየሱስ ክርስቶስ ማን/ምን እነት ላይ ያተኮረ ጉዳይ ነው። ለኔ እስከሚገባኝ እና እስክምረዳው ግዜ ከሆነ አሁንም በአጭሩ አምላክ ነው ወይስ አማላጅ? የሚለው ነው። እናንተ ያላችሁት እንዳለ ሆኖ እኔን የሚገባኝን እንካችሁ። ከነበራችሁም መማማር የተረዳሁት ይህ ነው። ወንድሜ "ሎጂክ" እያሉ አመላሴን ሊያጣጥሉት እንደሚችሉ ቢገለጥልኝም እንደ መረዳቴ ከላይም እንደ አገላለጼ "አምላካችን" ብየ ነው። አዎ እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው። የአማላጅነት ስራው በመስቀል ሞት ተጠናቅዋል። ቀጥተኛ መልስ የሚያስፍልገው ጥያቄ እየሱስ አማላጅ ወይስ አምላክ? ነው ከላይ እንደተመለከተው አማላጅ መካከለኛ ሊቀ ካህን ተብልዋል። ያንን ካልን አምላክ አደለም ማለታችን አይሆንብንምን? ለግንዛቤዬ ማነስ ይቅርታ ይደረግልኝ እና እኛን በ እግዝያብሄር ፈቃድ ወላጆቻችን ወለዱን ክ እነሱም ባገኝነው ስብእና የሰው ልጆች ወይንም ሰውች ተባልን። ሌላውም ፍጡር እንዲሁ አንበሳውም አንበሳ ሌላውም ሌላ...። የአምላካችን የ እግዚያሄር ልጅ አምላክ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። አምላክ እና አማላጅ ልዩነታቸው ይታወቃልና። ይገባኛል አምላክን ከፍጡሮቹ ጋር አነጻጸርክ ወዘተ ...በሚል መልስ እንደሚሰጥበት ይሁን እንጂ ፍላጎቴ እና እምነቴ በ እኔ ደካማው ሊገለጽ ቀርቶ ሊታውቅም የማይችለውን መለኮታዊ ባህሪ አቃለሁ የማለት ድፍረትም አድሮብኝ አደለም ነገር ግን በሚገባኝ አገላለጽ ለመጠቀም እንጂ። መደሃንያልም ክርስቶስ የ አምላካችን የእግዝያብሄር አብ አንድዬ ልጅ ከ አምላክነቱ ሌላ ምንም መገለጫ የለውም። ሮሜ 8፡36 ላይ "ስለኛ የሚማደው" በሚለው መሰረት ወንድማችን ቃሉን እያያችሁ ለመቀበል አትፍቅዱም ይላሉ። ቀደም ብሎ ግን ሮሜ 8፡26 "እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤" ይላል። ስለዚህ መንፈስ/ቅም ይማልዳል ልንል ይሆን? የተጻፈውን መማልድ የሚለውን ቃል አይተን?
እኔ ግን የምረዳውን የ እግዚያብሄር አብ አንድዬ ልጅ ስለሆነው ስለጌታችን መደሃኒታችን እና አምላካችን አምላክነት ብቻ ነው። ጌታችን መደሃንያልም ክርስቶስ እኮ ሊያማልድ ሳይሆን ሊፈርድ ነው የሚመጣው። ፈራጅ እና አማላጅ ያላቸውን ልዩነት ይታውቃል እና።

ዮሃንስ ወንጌል 5፡26 "አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።
27 የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።" (ይፈርድ ዘንድ እንጂ ያማልድ ዘንድ አይልምና)

ዮሃንስ 5፤ 22 "ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።" (የኔ ግንዛቤ እብን እና እየሱስ ክርስቶስን እኩል እንድናከብር እና ወልድ መፍረድን እንጂ ማማለድን አይደለም ከአብ እንደተሰጠው)

ሮሜ 9፡5 "አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።"

አሜን!! አዎ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው!! ክርስቶስ አምላክ ነው!!!
በዚህ ርዕስ ላይ ከላይ በቂ ማብራሪያዎች የተሰጡበት ቢሆንም ሰዎች ያንን ለመቀበል አይፈልጉም። እኔም መቀበል ለማይፈልጉ ሰዎች ጥቅስ በመደጋገም ማሰልቸት አልሻም። አንዳንድ ነጥቦችን መግለጽ እፈልጋለሁ።
1/ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው ነው። በአምላክነቱ ሞት የማያውቀው፤ድካም የማያሸንፈው ከሦስቱ አካላት አንድ አካል ነው።
2/ በሰውነቱ ከኃጢአት ብቻ በቀር እንደእኛ የኖረ፤ የአዳምንና የልጆቹን ኃጢአት የተሸከመ፤ የሕግ እርግማንን በመስቀል ላይ ጠርቆ በማስወገድ ያጣነውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ጸጋ እንዲያው የሰጠን መድኃኒታችን ነው።
3/ ኢየሱስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሰው ነበረ፤ በመስቀልም ላይ በሥጋው ሞተ፤ በሥጋው ሞትና መቃብርን ሽሮ ትንሣዔውን አሳየን፤በአብ ቀኝም በሥጋው በክብር ተቀመጠ።
4/ በሥጋ የመገለጹ ዋና ምክንያት ማስታረቅ፤ ማማለድ ነበር። ማስታረቁንና ማማለዱን በመስቀል ላይ ፈጸመ። አንዴ በፈጸመው ማስታረቅ አገልግሎቱ ከኃጢአትና ከክህደት በንስሐ ለሚመጡት ሁሉ ዛሬም የእርቅ አገልግሎቱን ከአብ ዘንድ ያገኛሉ። በአብ ቀኝ መቀመጡና ስለእኛ በሥጋው መታየቱ የአባቱን ፈቃድ በመፈጸሙ፤ በስሙ ለለመኑ ሁሉ ዘንድ እንዲሰጣቸው ነው።እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ ዮሐ 14፤13
ኢየሱስ ይማልዳል ማለት ዛሬም እንደሥጋው ወራት ስለእኛ ይለምናል ማለት አይደለም። ይህንንማ አንዴ አድርጎታል። አንዴ ያደረገው መስዋዕት እስከ በሌለው ፍጻሜ ወደአብ የሚመጡ ሁሉ በሞቱ የተሰጠውን ይቅርታ ያገኛሉ ማለት ነው። ስለዚህ የኢየሱስን አምላክነት እንደመሻር ወይም እንደማሳነስ አድርጎ ማሰብ የዋህነት ሲሆን ይህንን አለመቀበል ደግሞ ከመስቀሉ በኋላ በሥጋው እንዳላረገ አድርጎ ማሰብን ያስከትላል።
ወንድም ብርሃን

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክህ።

ከ15 አመታት በላይ ኢየሱስ በአሁኑ ወቅት አባቱን ስለእኛ ይለምናልን? የሚለውን ለራሴ ለመመለስ የመጽሃፍ ቅዱስ እና የተለያዩ ቤተክርስቲያናትን አስተምሮት ለመመርመር ሞክሬአለው። የደረስኩበት መደምደሚያ ከአንተ መደምደሚያ ጋር ከጥቃቅን ጉዳዪች በስተቀር ፍጹም ተመሳሳይ ነው።

ጌታ በስጋው ወራት ያደርገው የማስታረቅ አገልግሎት ለዘለአለም (እስከ አለም ፍጻሜ) ህያው ወኖ ይሰራል (ዕብ 7: 27)። ጌታ በምድር ያደርገው እንደነበረው አሁንም በአባቱ ቀኝ ወኖ አባቱን ይለምናል፤ ይጸልያል ማለት፦ ኢየሱስን አሁን ባለው ፍጹም አምላዊ ክብር አለማየት ወይም አለመርዳት ነው። ይህም አለመረዳት መነሻው መስሎ የሚታየኝ፦

1)ብዙዎች ከኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር ስለሚመሳሰልባቸውእና
2) እንደ የሃይማኖት መሰረት የሚል በመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከጥቂት አስርተ አመታት በፊት በተጻፈ መጽሃፍ ኢየሱስ አሁንም በሰማይ በአባቱ ቀኝ ሆኖ አሁንም ይለምናል፤ ይጸልያል ተብሎ ስለተጻፈ፤ እንዲሁም በአማኙ ዘንድ ይህ አስተምሮ እንዲሰርጽ ስለተደረገ ነው።

ኢየሱስ እንደስጋው ወራት አሁን በሰማይ ወኖ ስለእኛ እንደማይለምን ወይም እንደማይጸልይ ለመቀበል ብዙ ሰዎች ለጊዚው ድፍረቱ የላቸውም። እናም ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ አስተምሮት ጋር ስለተመሳሰለ እውነታን ላለመቀበል ማመንታት መልካም አይደለም።
እርግጥ ብለሃል ወንድሜ፡ ማለትም
"...እናም ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ አስተምሮት ጋር ስለተመሳሰለ እውነታን ላለመቀበል ማመንታት መልካም አይደለም።" ባልክው አባባል ላይ ማለቴ ነው። የህም ምክነያቱ የ አማኞች ፍቅር ከሚመለከው ከእግዚያብሄር ይልቅ ወደ እምነት ድርጅታቸው ስልሚያደላ ይመስላል።
0 ድምጾች
አያማልድም ይፈርዳል ።
Apr 3, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...