ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 8 May 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ታሀድሶ ማለት ምን ማለት ነዉ

Jun 20, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ተሐድሶ ማለት በፊት ከነበረ ነገር በበጐ መልኩ መቀየር ወይንም መለወጥ ማለት ነው፡፡
Aug 10, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
+1 ድምጽ
ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው?
ተሃድሶ ማለት አንድን ነገር ወደነበረበት የበፊት ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡ ተሃድሶ ማለት አዲስ ነገር ማምጣት ወይም መፍጠር ማለት አይደለም፡፡ በዙ ሰዎች ዋናውን ወይም ኦሪጂናሉን ነገር ሳያዩት ይቀሩና ጭራሽኑ የነሱ ወይም የአባቶቻቸው ንብረት ወይም እሴት እንዳልነበረ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ይሁን እንጂ የድሮውን ዋናውን ነገር የሚያውቁ ሰዎች ወደ ድሮው እውነት እንመለስ ብለው የድሮውን ለለመለስ ማለትም ተሃድሶ ለማምጣት ጥረት ሲያደርጉ እንድ መጤ ወይም አዲስ ነገር እንዳመጡ ይቆጠራሉ፡፡
ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስን ተመልከቱ፡፡ ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ያልነበረ አዲስ ነገር ወይም ትምህርት ይዞ አልመጣም፡፡ ይሁን እንጂ ሰው ከውድቀት የተነሳና ህግን በመካከለኛ እጅ ከመቀበሉ የተነሳ ህግን ለምዶ ለዘመናት ኖረ፡፡ ነገር ግን የዘመን ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን በላከ ጊዜ " እኔ ከአባቴ ወጥቻለሁ/መጥቻለሁ " ቢላቸው እንኳነ ሊቀበሉት አልቻሉም፡፡ ሊቀበሉት ያልቻሉት ግን የእግዚአብሔርን ነገር ይቃወማል ብለው እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር ሆን ብለው ለመቃወም አልነበረም፡፡ እንግዲህ ጌታ ተሃድሶን ይዞላቸው መጥቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ዋናውን ወይም የመጀመሪያውን የእግዚአብሔርን እቅድ ይዞ መጣ ማለት ነው፡፡ ልብ በሉልኝ! ታዲያ ይህን ስል ጌታ ያመጣው ነገር አዲስ ኪዳን ተብሎ እንደተጠራ ዘንግቼው አየደለም፡፡ የእግዚአብሔር እቅድ ግን ሰውን በህግ ፈትኖ ማሳለፍና ከዚያ አዲስ ኪዳን መስጠት አልነበረም ለማለት እንጂ!

ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፦
ማርቲን ሉተር ጀርመን ውስጥ የሰራው ስራ የተሃድሶ ስራ ነው፡፡ ማርቲን ሉተር አዲስ ወንጌል ይዞ አልመጣም፡፡ ሉተር ይዞ የመጣው ጌታ ያስተማረውን ሐዋሪያትም ተቀብለው የሰበኩትን ለሰዎች ደህንንነት የሚሆነውን ወንጌል ነው የዞ ብቅ ያለው፡፡ ነገር ግን ይህ የወንጌል እውነት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተበርዞና ሰው ሰራሽ ስርዓትና ህግ ተጨምሮበት ሊታይ እስከማይችል ድረስ ደብዝዞ ነበር፡፡ ሉተር አንድ ነገር አደረገ፡፡ ይኸውም የወንጌልን እውነት የረሳችውን ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችበትን እውነት ከመጣል ይልቅ መልሳ እንድታነሳውና እንድትሰብከው፡ እንድትኖርበትም ወደ መሰረቷ ሊመለሳት ተነሳ፡፡ በዚህን ጊዜ መሰረቷን ረስታ የነበረችው የወቅቱ ቤተክርስቲያን ተብየዋ ድርጅት አዲስ ነገር የመጣባት ያህል ተናወጠች፡፡ ያልነበረ ትምህርት መጣ አለች፡፡ ወንጌል ግን ያልነበረ ትምህርት ሳይሆን የነበረ የቀድሞ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓይነቱን የሉተር እንቅስቃሴ የተሃድሶ እንቅስቃሴ እንለዋለን፡፡
ዛሬም ይህን የሚመስሉ በዙ የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች በተለያየ መጠን ቢሆንም እንኳን አሉ፡፡
ነገር ግን ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ነገር አለ፡፡ በተሃድሶ ስም ጥቅስን ያለአግባብ በመተርጎም " የድሮ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንዲህ ነበር" ማለት የተሃድሶ ስራ አይደለም፡፡ ያ ሌላ ወንጌል ወይም ሌላ ትምህርት ነው ሊሆን የሚችለው፡፡
ለምሳሌ አንድ ታሪካዊ ህንፃ ወይም ስእል ሊፈራርስ ካለ የነበረውን ዲዛይን እንደያዘ መጠገን ቤቱን ማደስ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አፍርሶ እዛው ቦታ ላይ ሌላ ህንፃ መስራት ሌላ ህንፃ ያስብለዋል እንጂ ቦታው እዛ በመሆኑ ብቻ የእድሳት ስራ አይባልም፡፡ ይህ ከላይኛው መሳሌ ጋር ሊሄድ ይችላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚል ስያሜ ስለተሰጠው ብቻ ሌላ ትምህርት በመጣ ቁጥር እንደ ተሃድሶ መቁጠር ስህተት ነው፡፡
እንግዲህ ያቅሚቲ ይቺን ካልኩ በዚህ ቢበቃኝስ?
(ማናቸውም ዓይነት እርማት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ)፡፡
Aug 26, 2011 SSA (240 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...